mandag 20. mai 2013

ዲያስፓራው ለወያኔውች አልተመቻችም!


ዲያስፓራው ለወያኔውች አልተመቻችም!
ከአልንበረከክም
የዛሬ ሰባት አመት ኣካባቢ ወያኔ ሁለት መሰሪ ጽህፎችን አዝጋጅቶ ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ ከመልቀቁ በፊት በአገር ወዳጆች
ተጠልፎ ነበር፡፡ ቅድመ ጥንቃቄ እንድናደርግ ለሃቀኛ ኢትዮጵያውያን እነዚህ ጽሁፎች ተብትኖ ካነበብኩት አንዱ ነኝ፡፡
አንደኛው ጸያፍ ጽሁፍ በውጭ ኗሪ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ዘር በተመለከተ ብዛቱን ይጠቁማል፡፡ ስንት አማራ ጉራጌ
ትግሬ ኦሮሞ አደሬ .... በምንኖርበት አካባቢ እንዳለ ዘርዝሮ ያስቀምጣል፡፡ በዘር ለመከፋፈል እንዲያመች ተደርጎ የተዘጋጀ
ነው፡፡ ሌላኛው በርካታ ገጾች ያሉት ደግሞ ዲያስፖራውን ሰርስሮ ለመግባት ምን መላ መጠቀም እንደሚገባቸው መመሪያ
ሰጭ ነው፡፡ በተቻለ መጠን ሰርስሮ መግባትን ሲያበረታታ ካልተቻላቸው ግን ዲያስፖራውን እርስ በርሱ ማበጣበጥ እንዴት
አንደሚቻል ሴራ ይቀርጻላ፡፡ ዲያስፖራውም እንዲቀበለው የተለያዩ ጥቅሞችን እንደሚሰጥ ያባብላል፡፡
የተለመው ሴራ ተግባራዊ የሚሆንባቸውም በኮሚኒቲዎች በእምነት ቤቶች በስፓርት ክለቦች በእድሮችና እቁቦችም ሳይቀሩ
ትኩረት እንዲደረግባቸው ቀንና ማታ እየሰራበት ይገኛል፡፡ ሴራው አልያዘላቸውም፡፡ ግን ተስፋ አልቆረጡም፡፡ በየጊዜው
ዘዴያቸውን እየቀየሩ ይመጡብናል፡፡ ዛሬ ይሳካልናል ብለው የያዙት መንገድ “የአባይን ግድብ ማሰራት”የባሚለው ቀቢጸ
ተስፋ ነው፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ አባይ ለልማት መገንባቱን ባይቃወምም ግን በወያኔ ተግባራዊ ይሆናል ብሎ አያምንም፡፡
ይህ አዲስ የወያኔ መክበሪያ ዘዴና የሕዝብን ጥላቻ መጠን ለመቀየር የታቀደ እንደሆነ ዲያስፓራው አልጠፋውም፡፡
በመሆኑም ዲያስፓራው በየሚኖርበት ሁሉ ሴራውን በማንኮታኮት ላይ ይገኛል፡፡ ስለ እውነተኝነቱ በቅርቡ በካናዳ ሳንዲያጎ
ኒውዮርክ ዳላስ ኣሮፓ ሴንት ሉዊስ ዲሲ አትላንታ . . . የተከናወነውን ያስተውሉ፡፡ ኢትዮጵያ በሃቀኛ ልጆችዋ ትኮራለች፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወያኔ ካድሬዎቹን በየዲያስፖራው ብር በብር አሸክሞ አስማርቷል፡፡ የሚገርመው ትናንት በስደተኝነት
ወደ ዲያስፖራው ተሰደው ወራት ሳይሞሉ መንግስት በደለኝ ሊገለኝ ሲል አመለጥኩ በማለት እንዳልኮነኑ ወደ ወያኔ
መንግስት መሰስ ብለው ሲገቡ ኣስተውለናል፡፡ ይህን ጽሁፍ የሚያነብ ሁሉ ይህ የማወራው ጉዳይ ሃሰት አለመሆኑን
ከነማስረጃው አንደሚሰጥ የቅንጣት ያህል አልጠራጠርም፡፡ ጸሃፊው በሚኖርበት አካባቢ ካንድ በላይ የወያኔ ባንዳዎችን
ስለሚያውቅ ለሚመለከተው መንግስታዊ ድርጅት መረጃውን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቁኣል፡፡
በየዲያስፓራው የሚኖረው ኢትዮጵያውያን የተለያየ ሐይማኖት የሚከተልና የየራሱ የሆነ የፓለቲካ ድርጅት ያለው ወይም
የሌለው ቢሆንም በሃዘንና በደስታ ጊዜ ከብረት የጠነከረ ትብብር አለው፡፡ ካልተተናኮሱት አይነሳም፡፡ የሆነ ሆኖ ይህን
ሁኔታ በሞኝነት መድበው በጭንቅላታችን ላይ ቁጢጥ ሊሉ የከጀሉ ወያኔዎችን ኣይተን ግን ኣልተነጠፍንላቸውም፡፡
እንዲያውም እያሳፈርናችው ኣለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ ሁላችንም ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ቢኖር አንዱ የዚህ ርኩስ ቡድን ሴራ የወዳጅ ክፍሉን ለመበታተን
የሚጠቀመው ዘዴ ሃሜትንና ውሸትን በማናፈ ነው፡፡ ‘አንተ ወዳጄ ነው ትላለህ እንጅ እርሱ ሊያጠፋህ ሌት ተቀን
ያሴርብሃል . . . የአባይን ግድብ ላማ ይቃወም መስሎሃል። በጠራነው ስብሰባ ላይ በድብቅ ተገኝቶ ድጋፍ ከመስጠቱ በላይ
ገንዘብም ሰጥቷል’ እያሉ ያስወራሉ፡፡ ዲያስፓራው ይህን አይነቱን ሴራ በንቃት በመከታተል የወያኔዎቹን ቅስም መስበር
አለበት፡፡
በቅርቡ ከየዲያስፓራው የተጠናከሩ መርጃዎችን ያካተተ ጽሁፍ ማለትመ ማንኛአው ወያኔ በየትኛው አካባቢ
ኢትዮጵያዊውን ለመቆጣጠር ካልሆነም አንድነቱን ለመበተን አንደሚሰራ ይቀርባል፡፡ አስከዚያው ግን ሁሉም ሃቀኛ
ኢትዮጵያዊ ለኮሚኒቱው ለእምነት ቤቱ ለስፓርት ክለቡ ለእድሩ ... በተጠንቀቅከወያኔ የመከፋፈል ሴራው ዘብ ይቁም፡፡
ወያኔንና ሆድ አደር ጭፍራዎቹን በማሳፈር ከሕብረተሰቡ መነጠሉና ማጋለጋለጡ ይቀጥላል!!!!!!!!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar