mandag 20. mai 2013

ባለፈው ሰሞን የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች የኢንዱስትር ሰላም አሳጥተውኛል ያለው የጉዞ ወኪሎችና አስጉብኚዎች ማኅበር፣ የፌደራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዴስክ ከፍቶ ጉዳዩን እንዲመረምር ጥያቄ ሊያቀርብ ነው፡፡


የአስጐብኚዎች ማኅበር የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዴስክ እንዲያቋቁም ጥያቄ ሊያቀርብ ነው


ባለፈው ሰሞን የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች የኢንዱስትር ሰላም አሳጥተውኛል ያለው የጉዞ ወኪሎችና አስጉብኚዎች ማኅበር፣ የፌደራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዴስክ ከፍቶ ጉዳዩን እንዲመረምር ጥያቄ ሊያቀርብ ነው፡፡ 
በተካሄደው የማኅበሩ ጉባዔ ላይ የፀረ ሙስና ኮሚሽንና ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት መረብ ሰሞኑን እየወሰዱ ያሉትን ዕርምጃ ካደነቀ በኋላ፣ አባላቱ በባለሥልጣኑ ኃላፊዎች የደረሱባቸውን በደሎች የሚያጣራና የሚመረምር ዴስክ እንዲቋቋምላቸው ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ 
በዚህ ውሳኔ መሠረት ማኅበሩ በዚህ ሳምንት ጥያቄውን በደብዳቤ ለኮሚሽኑ እንደሚያቀርብ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ፍፁም ገዛኸኝ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 
የአስጐብኚዎች ማኅበር 181 አባላት ሲኖሩት፣ ማኅበሩ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ለዓመታት ሲያጨቃጭቁት የቆዩት ችግሮች በርካታ ቢሆኑም፣ በዋናነት ሁለት ችግሮች ጎልተው ይወጣሉ፡፡ የመጀመርያው የተጨማሪ እሴት ታክስ አከፋፈል ሲሆን፣ ሁለተኛው ከቀረጥ ነፃ በገቡ ተሽከርካሪዎች ዙርያ ነው፡፡ አስጐብኚዎቹ ተጨማሪ እሴት በማይከፈልባቸው መስኮች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፍሉ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን ባለፉት ሦስት ዓመታት ሞግተዋል፡፡ 
ማኅበሩ በተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ያለውን ቅሬታ በተደጋጋሚ ለባለሥልጣኑ ቢያቀርብም አጥጋቢ ምላሽ እንዳልተሰጠው ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ተሽከርካሪዎች ሁኔታ ነው፡፡ የማኅበሩ አባላት በተሰጣቸው ከቀረጥ ነፃ የማስገባት መብት አማካይነት ተሽከርካሪዎችን አስገብተው መሥራት ጀምረው ነበር፡፡ ነገር ግን ግልጽና ተዓማኒ ማስረጃ ሳይኖር ባለሥልጣኑ ተሽከርካሪዎቹን ላልተገባ ሥራ አውላችኋል በሚል በየመንገዱ ላይ በማገድ አስሯል ይላሉ፡፡ 
በዚህ ምክንያት ድንጋጤና ሥጋት ያደረባቸው የኢንዱስትሪው ተዋናዮች 400 የሚጠጉ ተሽከርካሪዎችን በየቤታቸው ለማቆም መገደዳቸው ተገልጿል፡፡ ከ150 የማያንሱ ተሽከርካሪዎች በባለሥልጣኑ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ላለፉት ዓመታት ፀሐይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው እንደሚገኙ ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ዘርፉ ክፉኛ እየተጎዳ መምጣቱን በመግለጽ፣ ባለሥልጣኑ አንዳች መፍትሔ እንዲሰጣቸው አጥብቀው ሲጠይቁ ከርመዋል፡፡ 
ነገር ግን ምላሽ ባለማግኘታቸውና በጉዳዩ ዙርያ ሆነ ብሎ የሚሠራ የጥቅማ ጥቅም ሻጥር አለ በሚል የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጊዜ ሰጥቶ እንዲያዳምጣቸው አባላቱ በጉባዔያቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar