የዘረኝነትን ሰደድ እሳት እናጥፋ
ብዙውን ጊዜ የነገሮች መነሻ መድረሻውን ሊያመለክት ይችላል ። በአገራችን በሕዝብ ላይ የተጫነው በዘር ላይ የተመሰረተ
የፖለቲካ ሥርዓት ከመነሻው የተሳሳተና ያለሕዝብም ይሁንታ የተቋቋመ በመሆኑ ቅቡልነት አልነበረውም፤ አሁንም የለውም።
ተቀባይነት የማጣቱ ዋነኛ ምክንያት ጎሣዎችን እንደፖለቲካ ማዋቀሪያነት መጠቀም በአገራችን የረዥም ጊዜ ታሪክ ቀርቶ
በሌላውም የዓለም ዳርቻ/ክፍል ታይቶም ተሰምቶም አለመታወቁ ነው።
ፖለቲካው በቋንቋና በዘር ሲዋቀር ሳንክ እንዳለበት የሚያሳይ ወጥነት የሌለው አካሄድ ከጅምሩ ተሰተውሏል። የትግራይ ፣
የአማራ፣ የኦሮሞ ፣ የአፋር፣ የሱማሌ ፣የሀድያ፣ የወላይታ ወዘተ ተብለው ክልሎችና ዞኖች ሲፈጠሩ እንደ ወያኔ/ አህአዴግ
የፖለቲካ ዓላማ መሰራት ካለበት በአገሪቱ በመላ ከ82 በላይ ጎሣዎች ስላሉ በዚያው ልክ የመንደር መንግሥታት መቋቋም
ግድ ሊል ሆነበት። በዚህ ግራ የተጋባው ወያኔ በርካታ ጎሣዎች የሚገኙበትን ደቡብና ደቡባዊ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል
ጨፍልቆ ደቡብ ሕዝቦች የሚል መጠሪያ አወጣላቸው ። በነገራችን ላይ ደቡብ የአቅጣጫ መጠሪያ እንጂ ሲዳማውን ፣
ወላይታውን፣ ጋሞውን፣ ኮንሶዉን ፣ ሀዲያውን፣ ከምባታውን፣ የሙን፣ ጋምቤላውን፣ ጉራጌውን፣----------ሊገልጽ አይችልም።
የወያኔ የአገዛዝ ክልል ሕዝብን ለማስተባበርና አገርን በልማት ጎዳና ለማራመድ የታቀደ ሳይሆን ሕብረተሰቡ በትንሽ በትልቁ
የሚናቆርበት ክስተት እንዲፈጠር ለማድረግ በመሆኑ ከሃያ ዓመታት በላይ በአገሪቱ የትርምስ ትርኢት እየታየ ነው።
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመዘርጋትና የሕዝብ ውክልና የተሰጠው መንግሥት ለማቋቋም በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተካተቱት
መርሆዎች “ ዘርን” ወይም “ ጎሣን” መነሻ ያደረጉ ሳይሆን ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ሆነው ነው የተቀረጹት። ጎሣ ፣ ነገድ ፣
የቆዳቀለም ፣ ዕምነት ፣ ባሕልና የኑሮ ዘይቤ አንድን ግለሰብ ወይም ማህበረሰብ ለጥቃት እንዲጋለጥ የሚያበቃ ምክንያት
የለም። አምባገነኖችና ዘረኞች ግን ከሞራልም ከሕግም በላይ ሆነው የከፋ ወንጀል በሕዝብና በአገር ላይ ይፈጽማሉ።
በአገራችንም እየታየ ያለው ይኸው ነው። አንዳንድ አእምሮቸውን ለጥፋት የሚያውሉ ግለሰቦች የጭካኔ መንፈስ አድሮባቸው
ኢሰብአዊ ድርጊት ሊፈጽሙ ቢነሳሱና በተግባር ቢገልጹት በማህበረሰብ የሚወገዝ ሲሆን በቡድን ተሰባስቦ ለጭካኔ ተግባርና
ጥፋት መስማማት ግን ከወንጀሎች ሁሉ የበለጠ ወንጀል ነው የሚሆነው። ለዚህም ነው የዓለም መንግሥታት ( UNITED
NATIONS) እንደነዚህ ያሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች እንዲዳኙ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ሸንጎ የሰየመው።
በአገራችን በጎሣ ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሥርዓት ጥንስሱ የሰብአዊ መብቶች ከግለሰብ ጀምሮ የሚከበርበት ሳይሆን
ሰዎች በጎሣቸው ተያይዘው ከዚያ ውጪ ላለ ግለሰብ ወይም ጎሣ ደንታ እንዳይኖራቸውና ልዩነታቸውን እንዲያሰፉ የሚያደርግ
ነው። ሰው ነኝ ማለት ከሁሉም የሰው ዘር ጋር ያስተሳስራል። የዚህ አገር ዜጋ ነኝ ማለት ደግሞ ሌላ ትስስርና የማንነት
መገለጫ ነው። ኦሮሞ ነኝ ፣ አማራ ነኝ ፣ ትግሬ ነኝ ፣ --------ወዘተ ማለቱ ወያኔ በሚጠቀምበት መልክ ለፖለቲካ ዓላማ
የሚውል ከሆነና ኢትዮዮጵያዊነትን በማደብዘዝ የበላይነትና የበታችነት፣ የአናሳና የብዙኃን ---------እያለ ለልዩነት በር
የሚከፍት ነው። የወቅቱ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግሥታዊ ቡድን ይህን የመለያየት አጥር ለማጠር የፈለገው ሆን ብሎ ነው።
በልዩነታችን እርስ በርስ ስንራኮት ይኸውና ከሃያ ዓመታት በላይ በሥልጣን መንበሩ ላይ ጉብ ብሎ ሕዝብን እየበደለ
ተጠቃሚ ሆኗል። በዚህ የተነሳም በተለይ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማያወላውል አቋምና ቀናኢም ናቸው ብሎ በፈረጃቸው
የሕብረተሰብ ክፍሎች ፣ ድርጅቶች፣ የሙያ ማህበራትና ግለሰቦች ላይ ጫናውና የጥፋቱ ዘመቻ እጅግ እየክፋ መጥቷል።
በወያኔ/ኢህአዴግ የክህደት ቁልቁለት አካሄድ በሺህ ዓመታት የሚቆጠር ታሪክ ፣ በማህበራዊ ፣ ባሕላዊና ኃይማኖታዊ
መስተጋብር የተጋመደና በሂደትም የተዋሃደ ሕዝብ የሚኖርባት ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም የሚል ነው። ስለኢትዮጵያ
አኩሪ ታሪክ፣ ስለሕዝቧ አንድነትና ውህደት አቀንቃኝ አማራ የሚባል ዘር እስካለ የማራምደው አገርን የማጥፋት አጀንዳ ግብ
አይመታም በሚል ገና በጫካ ማኒፌስቶው የጥፋት ዕቅድ መንደፉን ከወያኔ ድርጅት መስራች አባላት እየተነገረ ከመሆኑም ባሻገር ሰነዱም ምስጢር ሆኖ አልቀረም።
በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሥርዓት የላይ ሽፋኑ ሁሉንም ጎሣዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መስሎ ቢታይም መነሻ
ሰበቡ አማራ የሚባል ዘር ፣ የአማራ የገዢ መደብ የሚባል ሥርዓት በሌሎች ላይ ግፍ እንደፈጸመ ሰፊ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት
ይህን የህብረተሰብ ክፍል ከሥልጣን ማራቅ ፣ ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማገድ ፣ ሥነ-ተወልዶው እንዲመናመን መሥራት ፣
የሰፈረበት መሬት እየተቆረሳ ወደሌሎች ክልሎች እንዲጠቃለል ማድረግ ፣ ከጎንደር ጫፍ እስከ ጋምቤላ ድረስ ያለውን መሬት
ለሱዳን ሰጥቶ መሬቴን አለቅም ያለውን ሕዝብ የወያኔና የሱዳን ሠራዊት በትብብር እንዲያጠቁትና ለሌሎችም ሰቆቃዎች
ተጋላጭ እንዲሆን ስልት መቀየስ እንደፖሊሲ ተወስዷል።
በአርባጉጉ ፣ በወተር ፣ በአሶሳ ፣ በጂማ ፣ ------በአብዛኛው አማራዎች ላይ እንዲሁም በተወሰኑ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ 2
በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሥርዓት የላይ ሽፋኑ ሁሉንም ጎሣዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መስሎ ቢታይም መነሻ
ሰበቡ አማራ የሚባል ዘር ፣ የአማራ የገዢ መደብ የሚባል ሥርዓት በሌሎች ላይ ግፍ እንደፈጸመ ሰፊ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት
ይህን የህብረተሰብ ክፍል ከሥልጣን ማራቅ ፣ ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማገድ ፣ ሥነ-ተወልዶው እንዲመናመን መሥራት ፣
የሰፈረበት መሬት እየተቆረሰ ወደሌሎች ክልሎች እንዲጠቃለል ማድረግ ፣ ከጎንደር ጫፍ እስከ ጋምቤላ ድረስ ያለውን
መሬት ለሱዳን ሰጥቶ መሬቴን አለቅም ያለውን ሕዝብ የወያኔና የሱዳን ሠራዊት በትብብር እንዲያጠቁትና ለሌሎችም
ሰቆቃዎች ተጋላጭ እንዲሆን ስልት መቀየስ እንደፖሊሲ ተወስዷል።
በአርባጉጉ ፣ በወተር ፣ በአሶሳ ፣ በጂማ ፣ ------በአብዛኛው አማራዎች ላይ እንዲሁም በተወሰኑ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ
የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ ብዙ ዓይነት ግፍ ተካሂዶባቸዋል። አማራዎች ግን በተለይ ከነነፍሳቸው ገደል ውስጥ
ተጥለዋል ፤ ቤታቸው ተዘግቶ ተቃጥለዋል፤ ሰለባ ተፈጽሞባቸው እንደከብት ታርደዋል ፤ ሞት ሳያንሳቸው ለመጣፍ ይሉ
ለወናፍ የማይፈይድ ቆዳቸው ተገፏል። ይህ ሁሉ መዓት ሲወርድ በመንግሥት ስም የተቀመጠው አካል አልሰማም አላየም
ማለት ራስን ማሞኘት ነው። ይህ ሁሉ የጭካኔ ተግባር አማራ በመሆን ብቻ የተፈጸመና እየተፈጸም ከሆነ ነግ በኔን
አያስታውስም? የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ በዘር መደራጀትን ትተንና ባንድነት ሆነን ካልተነሳን ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያን
የማጥፋቱ ዕቅድ አያቆምም።
በዓለም አቀፍ ድንጋጌም በወያኔ ሕገመንግሥትም የተረጋገጠው ዜጎች በፈለጉበት ቦታ መርጠው የመኖር መብታቸው ተጥሶ
በጉራፋርዳ ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ አማራ የሆነ ጓዜን ጉዝጓዜን ሳይል ሲባረርና መድረሻ ሲያጣ ፣ ሲንከራተት ፣ ሲዘረፍ ፣
ሲደበደብ ፣ ሲገደል ፣ ማየትና መሰማት የሚሰቀጥጥ ነው። ነፍሰ ጡሮች አውላላ ሜዳ ላይ የጭንቅ ምጥ አምጠው
መገላገላቸውን ተመስገን የሚሉ ሳይሆን ሰው መሆናቸውን ፣ አማራ መባላቸውን እንደሚያማርሩና ተስፋቸው መጨለሙን
መገመት ይቻላል። ይህ በኢዮጵያዊነት ስነልቦነና ሰብአዊነት ሁነቶች ስናስበውና ስናስታውሰው በእጅጉ ይዘገንናል።
ቀደም ሲል ከላይ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ሌላ በኦሮሚያ ፣ በሱማሊያ ፣ -----ወዘተ የማፈናቀል እርምጃ ተወስዷል።
ለምሳሌ በኦሮሚያ ከሁሉም ብሔረሰብ ተወላጆች የሆኑ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ከክልሉ
ተባርረዋል። በአገሪቱ ሠርተው የመኖር መብታቸው ከመጣሱም በላይ በሌሎች ክልሎች ተጨማሪ የመምህራን ቁጥር
እንዲፈጠር ሆኖ ያለአግባብ የአገር ሀብት ብክነት ተከስቷል። የዚህ ማፈናቀል ዋና ዓላማ ብሔራዊ ቋንቋ የሆነውን የአማርኛ
ቋንቋን ማጥፋት ፣ ኢትዮጵታውያንን የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ማሳጣትና አንድነታቸውን የማላላት ስልት ነው።
ከአስርት አመታት በፊት አንድ የኦሮሞ ጎምቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሠርገኛ ጤፍ እንዳመሳሰሉት ይነገራል። አባባላቸው
ዕውነትና ልብን የሚነካ ነው። አሁን የሚታየው ግን የልዩነት ቁርሾ እየተሰበከ አገሪቱን ወደለየለት ዕልቂትና መበታተን
የሚያመራ መንግሥታዊ/ቡድናዊ አጀንዳ እንደሆነ ነው። ይህ አጀንዳና እኩይ ተግባር የቅርብና የሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን
ውጥን ቀጣይ እንቅስቃሴ እንደሆነ መጥቀስ ይቻላል። ፋሺስት ጣሊያን ፣ እንግሊዞችና ሌሎችም ኢትዮጵያ እንድትበታተን
የተለያዩ ካርታዎች እየሰሩ ማሳየታቸውን መዘንጋትና መዘናጋት የለብንም። ያለመታደል ሆኖ የነርሱ ጉዳይ አስፈጻሚ አካል
በትረ መንግሥቱን ጨብጧል። ሰለሆነም ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለሕዝብ አንድነት ይቆማል የሚባል ሁሉ ወርተረኛ ሆኖ
ፍዳ መቁጠሩ ይቀጥላል። በሂደቱም በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው በሌሎችም ያለጥርጥር ይደርሳል። ሲዳማውን ከወላይታ፣
ጉጂውን ከቡርጂ ፣ አፋሩን ከኢሣው ፣ አላባውን ከሀዲያ ፣------ ማጋጨት ሥራዬ ተብሎ ሲሰራ ያየነው የሰማነው አካሄድ
ነው። ለባዕድ አገር ከበርቴዎች መሬት ለመሸጥ ተብሎ በአንድ ጊዜ ከ140 በላይ ሙርሲዎች የጅምላ ግድያም ሌላው
የሥርዓቱ አራማጆች ፋሽስታዊ እርምጃ ነው። በጋምቤላ በታህሣሥ ወር 1995 ዓ.ም ለመብታቸው በመቆማቸው ብቻ
የወያኔ ጦር 424 አኙዋክ ዜጎቻችን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ፤ ከዚያም በተከታታይ ብዙ ግዲያ ታይቷል።
ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል፤ መሬታቸውም በኢንቬስትሜንት ስም ለውጭ አገር ከበርቴዎች ተሰጥቷል። በሂደቱም
መምህራንና ሌሎች የተማሩ ወገኖቻችን እንደጣሊያን ጊዜ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። ወንጀላቸውም ሕዝቡን ለመብቱ
እንዲቆም ማገዛቸው ነበር። አሁንም ጥቃቱ አላቋረጠም። በዚች አጭር መግለጫ ባለፉት ሃያ የመከራ ዓመታት በሕዝብ ላይ
የተፈጸመውን ዙሪያ ገብ ሰቆቃ ዘርዝሮ ማቅረብ ስለማይቻል እየቆነጠርን ለማሳየት ሞክረናል። ለሁሉም የስቃዩ ገፈት ቀማሽ
የሆነው ሕዝብ እማኝ ነው ብለን እናምናለን።
ዕውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሕዝብን በማደናገርና በማምታታት ከተካኑት የወያኔ/ኢህአዴግ ባለሥልጣናት አንዱ የፌዴራል
ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለማሪያም የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ ሪፖርት ለፓርላማ ባቀረቡበት
ወቅት “ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ አርሶአደሮችን ሕገወጥ በሆነ መንገድ በማፈናቀል የተጠረጠሩት 35 የቤንሻንጉልና
ጉሙዝ ክልል አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸውንና ከነዚህም 12ቱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። “ ብለዋል። ይህ
የወያኔ አብዮታዊ ርዕዮትና የተግባር እንቅስቃሴ አዲስ ክስተት አይደለም። ያሁኖቹ ግፈኞች በበረሃ እያሉ ጓዶቻቸውን
ለእርድ አቅርበው ጭዳ አድርገዋቸዋል። ትልቁ ዓሣ ትንሹን ውጦ ሕልውናው እንደሚቀጥል የወያኔ ተፈጥሯዊ ባሕርይ
መገለጫው ነው። ፖሊሲ አውጪ፣ ትዕዛዝ ሰጪ፣ ገምጋሚ፣ ------ሁሉንም ነገር በሁሉም ሥፍራ ፈጣሪና አድራጊዎች 3
የበላይ ሹማምንት መሆናቸው እየታወቀ የበታች ካድሬ ሹመኞችን ለይምሰል በማጋለጥ ሕዝብን ማሞኘት አይቻልም ፣
የፍትሕ አካሄዱም የሚያመረቃ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። በአንድ ወቅት ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ
ከአንድ የደቡብ ክልል ስለተፈናቀሉ የአማራ አርሶአደሮች ማብራሪያ ሲጠየቁ “ ክልሉ ምሥራቅ ጎጃም ሊሆን ምን ቀረው? “
ብለው ነበር የተሳለቁት። ዜጎች በፈለጉበት እንዲኖሩ እየለካ የሚሰጠውና የሚፈቅደው የሳቸው ድርጅት ይሆን ያሰኛል።
ከዚያም በላይ የመልሳቸው አንድምታ አርሶአደሮች በዚያ ክልል ሊኖሩ የማይችሉና የማይፈቀድ መሆኑን ነው የሚያሰየው።
ይህን ቡድናዊ እኩይ ተግባር ለማስወገድ ሙስናን ፣ ዘረፋን ፣ ዘለፋን፣ ውሸትንም እንቃወም ፤ ቂምን ፣ በቀልን ፣
እናውግዝ ፤ የጥንቱን የመተሳሰብ፣ የመሰባሰብና የመደጋገፍ፣ የመከባበርና አብሮነት ባህላችንን እናድስ። እነዚህ የሕዝብ
እሴቶች ከሌሉ እንደሕዝብና እንደአገር መቀጠል ይከብዳል። ስለሆነም ዜጎች ሁሉ በግልና በተሰባሰቡባቸው የፆታ ፣ የሙያ
፣ የአክሲዮን ፣ የዕድር ፣ የቀበሌ ማህበራት በመነጋገር ፣ የጥላቻ ግድግዳን በመስበር የውይይት በር ለመክፈት በመሞከርና
ፍቅርን በማሳየት ይህን የተሳሳተ አካሄድ ለመለወጥ መሥራት ይጠበቅባቸዋል። የደረቅ አጠገብ እርጥቡ ይጨሳል እንዲሉ
ያንደኛው ወገን ጥቃት በሁላችንም ላይ እንደተቃጣ ልንቆጥረው ሁኔታዎች ያስገድዳሉ። በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን
ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ የአገር ፣ የሕዝብ፣ የሰብአዊነትና የሰብአዊ መብቶች ፀር የሆነው ዘረኝነት የባሰ ጥፋት
ሳያደርስ ከሥሩ እንዲመነገል መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ገበሬዎች፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወታደሮች፣ የተለያዩ ዕምነት
ተከታይ ወገኖች በአጠቃላይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በጋራ እንዲቆሙና እንዲታገሉ ጥሪውን ያስተላልፋል።
የዘረኝነት ሰንኮፍ ይነቀል!!
ለጋራ ቤታችን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንታገል!!
የዘር መድሎ (አፓርታይድ ) በኢትዮጵያ ምድር አይለመልምም !!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar