tirsdag 21. mai 2013

ኢሕአዴግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሪዎችን እየመለመ ነው


ኢሕአዴግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሪዎችን እየመለመ ነው

ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው ምልመላውን እያከናወኑ ያሉት የሥልጣን ዘመናቸው በቅርቡ የሚያበቃው ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና ምክትላቸው አቶ አባተ ስጦታው፣ የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃንና ምክትላቸው አቶ ጀማል ረዲ ናቸው፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሩ  ድሪባ ኩማ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ  መኩሪያ ኃይሌ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ  ሲራጅ ፈርጌሳ፣ የፌዴራል ፖሊስ ጄነራል ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ተመራጮች ወደ ከተማው ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጋዜጣው ዘግቧል።
ወ/ሮ አዜብ በቅርቡ ቅዳሜና እሑድ ፒያሳ የሚገኘውን ማዘጋጃ ቤትና የከተማው አስተዳደር ያሠራውን የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከልን መጎብኘታቸውን ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በእስካሁኑ ሒደት የከተማው ቀጣዩ ከንቲባ ማነው የሚለው ጥያቄ ምላሽ ባያገኝም፣ ውስጥ አዋቂ ምንጮች አቶ ድሪባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ኢህአዴግ የአዲስ አበባን የምክር ቤት ወንበር ያለ ተፎካካሪ ሙሉ በሙሉ ማሸነፉ ይታወሳል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar