torsdag 16. mai 2013

በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ብራሰልስ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ


በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ብራሰልስ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

ኢሳት ዜና:-የሆላንድ እና የቤልጂየም የኢትዮጵያውያን ማህበሮች ባዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት አቅርበዋል።
ኢትዮጵያውያኑ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል እንዲሁም መንግስት በሀይማኖቶች ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል። የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲቆሙም ጠይቀዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar