የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ታሰረ
ኢሳት ዜና:-የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ግንቦት14፣ 2005 ጧት ላይ በደህንነቶች ተይዞ መወሰዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ሀብታሙ አያሌው ለኢሳት ገልጿል።
ወጣት ብርሀኑ ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መታሰሩን ወጣት ሀብታሙ ገልጿል።
ወጣት ሀብታሙ ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ እስረኛውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 9 ሰአት ላይ የወጣት ብርሀኑ ቤት እየተፈተሸ መሆኑን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጿል።
ምሽት 12 ሰአት ላይ ያነጋገርነው የማህበሩ ቦሌ ክፍለከተማ ምክትል ሀላፊ ወጣት ጥላየ ታረቀኝ እንደገለጸው ደግሞ ከዚህ ቀደም ታስረው በነበረበት ወቅት ሲዝትባቸው የነበረው ሳምሶን የተባለ የደህንነት ሰራተኛ ወጣት ብርሀኑን እንዳስያዘው ገልጿል። የወጣት ብርሀኑ ቤተሰቦች ቤት ሲፈተሽም በአንድ መጽሀፍ ውስጥ ራሳቸው ደህንነቶች ያስገቡትን ጽሁፍ ” ይሀው አገኘነው በማለት” ብርሀኑን እንዲፈርም እንደጠየቁትና ከጠበቃየ ጋር ሳልማከር አልፈርምም እንዳለ ወጣት ጥላየ ተናግሯል።
በጉዳዩ ዙሪያ የጉለሌን ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊዎች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar