አምቡላንሱ የባለስልጣኑን የሰርግ እቃ ሲያመላልስ የነፍሰጡሯ ህይወት አለፈ
አምቡላንሱ የባለስልጣኑን የሰርግ እቃ ሲያመላልስ የነፍሰጡሯ ህይወት አለፈ
---------------------------------------------------------
አሳዛኙ ዜና የተደመጠው በጎንደር ፎገራ ወረዳ አምባ ጊዮርጊስ ውስጥ ነው፡፡ ‹‹አንዲትም እናት በወሊድ የተነሳ መሞት የለባትም›› በሚል ፕሮግራም አማካኝነት የአምባ ጊዮርጊስ ጤና ጣብያ አንድ አምቡላንስ በስጦታ ተበርክቶለታል፡፡
ነገር ግን ሃላፊነት የጎደላቸው የወረዳው አመራሮች አምቡላንሱን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዳኜው ታደሰ የሰርግ ስነ ስርዓታቸውን በሚፈጽሙበት ዕለት ለሰርጉ የሚሆኑ እቃዎችን እንድታመላልስ ያደርጋሉ፡፡
በወረዳው የሚገኘው ጤና ጣብያ በወሳንሳ የመጣችለትን ነፍሰ ጡር ወ/ሮ የዝናን ማዋለድ እንደማይችል በመረዳቱ ወደ ሌላ ሆስፒታል እንድታመራ ሪፈር ይጽፍላታል፡፡
ነገር ግን ይህንን ተግባር እንድትፈጽም በልግስና የተሰጠችው አምቡላንስ የሰርግ ዕቃ እንድታመላልስ በመደረጓ ፈጣን እርዳታ ያስፈልጋት የነበረችው ነፍሰ ጡር ወደ ተመራችበት ሆስፒታል በሰዓቱ መድረስ አልቻለችም፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar