ገኖቼ እባካችሁ ለጥያቄዬ መልስ ስጡኝ (ተሾመ ደባልቄ)
ተሾመ ደባልቄ
ዲሞክራሲና ትግል
ዲሞክራሲ አገሮች የሚኖሩ የወያኔ ጉጅሌዎች የሚወዱትን መሪ መርጠው ለኢትዮጵያ ህዘብ ግን ወያኔ ይበቃዋል ማለታቸው ማሞ ቂሎ መሆናቸውን ያቁታል?
ለህዝብ ነፃነት እታገላለሁ የሚል የግለሰብም ሆነ የቡድን ልዩነት የሚመጣው ከህዘብ ይልቅ እራሴን ላስቀድም የሚል ስግብግብነት ነው ቢባል ዕውን አይሆንም?
ነጻነትና ዲሞክራሲ ሲባል ሆዱን የሚቆርጠውና የሚያስለፈልፈው ዜጋ የሌባ እንጀራ የበላ ብቻ ይሆን?
ወያኔስ በድንቢጥ ምስክሮቹ 99.6 በመቶ ህዝብ መረጠኝ ብሎ መንግስት ነኝ ሲል ደጋፊዎቹን ቆረቆሮ ራስ ደንቆሮዎች እያለ የሚፌዝባቸው ምን ያህል ቢንቃቸው ነው?
ይህ አቢዩታዊ ዲሞክራሲ የሚሉት የወያኔ ሥርዓት ፓርላማ መግባት እንጂ መውጣት አያቅም ማለት ነው? አብዮት ነፍስ ለመብላት ዲሞክራሲ ደግሞ ለማጭበርበር ቢባልስ ያስወነጅላል?
ወያኔ የትግራይ ሪፐብሊክ የሚለውን ክልል ከኢትዮጵያ ነፃ አወጣሁ ካለ ከርሟል መቼ ነው ክልሉን ከወያኔ ሌቦች ነፃ የሚያወጣው? ሽብር አትፍጠሩ ክልሉ በኮንስትቱሹኑ የብሄር ሌቦች ምሽግ ነው የሚለን?
የምርጫ ቦርድ የሞሉት ሙህሮች ከቀኝ ወደግራ እንዲቆጥሩ ያስተማራቸው የሕዋዕት ካድሬ ነው ወይስ መምህር?
ልማትና ኢኮኖሚ
ኑሮ የተወደደው ኢኮኖሚው በፈጣን ስላደገ ነው የሚሉ ሙሁራን አጥንተው ነው ወይስ ወያኔ አስጠንቷቸው?
ሌብነትን ልማት ነው የሚሉን የወያኔ ጉጅሌዎች ባቋራጭ ሌቦችን ከንጹህ ዜጋ እኩል ለማደረግ ይሆን?
የውጭ እንቭሰተሮች ወያኔ ላይ ነው ወይስ ሀገር ላይ እንቬሰት የሚያደርጉት?
አላሙዲ የሚባለው ኢንቨስተር ክልልም ገደብም የለውም ማለት ነው? ኮንስትትሹኑ ዶላር ያለውና ወያኔ ኢትዮጵያዊ ሌላው ደግሞ ብሄርና ብሄረሰቦች ናቸው የሚል ተጽፏል ማለት ነው? ታዲያ ወያኔ የትግሬ ነፃ አውጭ ነኝ ከሚል የሌቦች ነፃ አውጪ ነኝ ቢል አይቀልም?
አዲሱ የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር የአባይ ግድብን የሚቃወሙ ሀገራቸው እንዳያድግ የሚፈልጉ ናቸው እያለ የሚለፍፈው ወያኔ ወገንን ሽብርተኞች ማለት አልሰራ ስላለ ይሆን?
የትግራይ ልማት የሚባለው የልመና ድርጅት ትግራይን ሊያለማ ወይስ ኢትዮጵያን ሊያደማ የተቋቋመው? ካልሆነ ለምን በኢትዮጵያ ሥም ለምኖ በትግራይ ክልል ስም ይቸረችራል?
ልማት ተፋጥኗል የሚሉ ምሁሮች ኪሳቸውን እየዳበሱ ነው ወይስ ጥናት እያጠኑ?
በልመና እድገት አመጣለሁ የሚለው የወያኔ ሥርዓት ድህነትን ማስፋፋትን ለልመና ያመቻል ብሎ ይሆን? ድህነት ባይኖር በምን ሊኖር ነው፤ በማጅራት መች?
ሰባዊ መብት
የወያኔ የሰባዊ መብት ኮምሽን ሥራ የሚቀጠር ግለሰብ የራሱን መብት የማያውቅ ብቻ ይሆን?
የአለም መንግሥታትና ድርጅቶች ወያኔ ሰባዊ መብት ይጥሳል ሲሉ ጉጅሌዎቹ የስድብ ናዳ የሚያወርዱባቸው አንጥስም ወይስ ሰባዊ መብት አልገባንም ማለቱ ነው?
ፖሎቲካ
እኔ ፖሎቲካ አልወድም የሚሉ ግለሰቦች በአዙርኝ ወያኔ ተመችቶናል እንብላበት ተዉን ማለት አይሆንም?
የፖሎቲካ ፓርቲ ነኝ ማለት እራሴን ነፃ ላውጣና እንደወያኔን ልሁን ነው እንዴ?
ፖሎቲካ ምን ያደርጋል ልማት ነው ጥሩ የሚሉ፤ ሰርቄ ወድያለሁ ተወንጅዬ እስር ቤት መግባት አልፈልግም ማለታቸው ይሆን?
ወያኔ የዲያስፖራ ወገኖችን አክራሪ ፖለቲከኞች እያለ የሚዘፍነው ማሰርና መግደል ስላቃተኝ ሌላ ምርጫ የለኝም ማለቱ ይሆን?
ወያኔ ወገኖችን ተቀዋሚ ፖሎቲካ አትግቡ እያለ በካድሬዎቹ የሚያስፈራራው የውሸት መንግስት መሆኔን ይታወቅብኛል ማለቱ ነው?
ሙሥናና ሌብነት
የወያኔ ጉጅሌዎች ጆሮዋቸውን የደፈነው ከሌብነት እንጀራ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ዘረኛነት?
ሌባ…ሌባ ተብለው የተባረሩት የወያኔ ዲፕሎማቶች ወዴት፤ እስር ቤት ወይ ሹመት ?
የወያኔ መሪዎች እነደሙጫ ያጣበቃቸው ሌብነቱ ወይስ አቢዎታዊው ዲሞክራሲው?
ድሕነትን ሐጥያት ፣ ነፃነትን ወንጀል፣ ሌብነትን ልማት ያደረጉ የዘንድሮ ሙሁሮች የዕውቀት ድክመት ወይስ የሌብነት ቁረኛ?
ብሔርና ብሔረሰብ
ወያኔ የብሄርና ብሄረሰቦች ፌደራሊዝም እያለ በራሱ ‘ብሄር’ ላይ ከማፌዝ በላይ ያተረፈው ዘረፋ ብቻ ነው ቢባል አሸባሪዎች የሚላቸው ወገኖች አብረውት ዘረኛ፣ አሸባሪና ዘርፊ ያለሆኑቱን ማለቱ ይሆን?
በብሄሩ አንድን ሥርዓት የሚደግፍ ግለሰብ ወይ ቡድን ሌላ ባህሪ የሌለኝ ለሆጌ የምኖረ ዘረኛ ነኝ ማለቱ ይሆናል?
ብሄርና ብሄረሰቦች ብሎ ኢትዮጰያውያንን ለፖሎቲካ ጥቅም የሚቸረችር ሥርዓት ሆነ ቡድን ብሄሩንም ማንነቱንም የማያውቅ እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል ያለ ጠፍቼ አጠፋለሁ ያለ ሽብርተኛ ነው ቢባል በወያኔ ፍትህ በዘር ማጥፋት ያስወነጀል ይሆን?
የወያኔ የክልል ሥርዓት ቀስ በቀስ የቻይና የህንድና የአረብ ብሄረሰቦች ክልል ያስፍጋል ብሎ በአንቀፅ 39 መሠረት መገንጠል መብታቸው ነው ማለቱ ይቀራል?
አንድ ዜጋ ወያኔን የሚደግፈው በዘሩ ከሆነ ዘረኛ በስራው ከሆነ ቀማኛ ቢባል ትክክክ አይደለም?
አማራ እያጠቁ በአማራናቱ ኦሮሞን ባኦሮሞነቱ…ወዘተ ይደራጅ የሚሉ ጉጅሌዎች የወያኔን ኢትዮጰያኖችን ከፋፍል ሴራ ፍጻሜ ግብ አድርሱ የተባሉ አይመስሉም?
ትግሬ ነን የሚሉ የወያኔ ጉጅሌዎች ለምን በትግሬ ሥም ሀገርን ህዘብን መዝረፍና ማጥፋት መረጡ ብል ትግሬን ወይስ ሌባንና አጥፊን ጠላሁ ማለት ነው ?
ፍትህና ሕግ
ንጹህ ዜጋን አሸባሪ ብሎ መወነጀል የፈሪ በትር አይሆንም? ፍርሀት ደግሞ የሚመጣው በሰሩት ወንጀል ተሸብረው ንጹሃንን በማሸበር የሚሽሩ የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው ቢባል ሀሰት ይሆን?
በሀሰት ንጹሀን ላይ የሚመሰክሩ ግለሰቦች በቁም ሞተው በቁሙ ለሞተ ሥርዓት ያጎበደዱ ብቻ ናቸው ማለት አይቻላልም?
ሚሚ ስብሃቱ የተባለች የወያኔ ታናሻ የአፈ ጉባዬ ጉጅሊት (የበረከት ታናሽ) ‘ህግ ወጥ ሰፋሪ’ ያለቻቸው ዜጎች ከሬዲዎ ፈቃድ ሌላ የራሷን ህግ እንድታወጣ ፈቃድ የፍትህ ሚኒስተር ሰጥተዋት ይሆን? በወያኔ ሥርዓት ስንት ህግ አውጭ ነው ያለው?
ፍርድ ቤት የተጎለቱት ዳኞች እስር ቤት የላኳቸውን ዳኛ እነሱ ደግሞ እስር ቤት ቢወርዱ ፍትህና ነጻነት መጣ ማለት አይቻልም?
ወገንና ሀገር አጥፊዎች
የሀገሩን ህዝብ እነደጠላት የሚያይ ግለሰብ ሆነ ቡድን ሀገርም ዘርም ህሊናም ሀይማኖትም የሌለው ቅጥረኛ ነው ቢባል በወያኔ ሥርዓት ሽብርተኛ ወይ ትምከተኛ ያስብል ይሆን?
ወያኔ ጉጅሌዎች ለቅሶ የተቀመጡት ለሟቹ መሪያቸው ወይ እየተጋለጠ ላለው ወነጀላቸው?
ዘንድሮ ወያኔ ነኝ የሚል ግለሰብ ወንጀለኛ ነኝ ቢል በቶሎ ነጻ አይወጣም?
የኢትዮጵያን ኮንስትትሹን ያረቀቁት የወያኔ ጉጅሌ ሙህሮች እኒቨሰተርስ ወይ የውጭ ዜጎች ካልሆኑ በቀር እንዴት የሕዋዕት ማኒፈስቶ ሊመስል ቻለ?
የወያኔ ሙህሮች ከሥርሃቱ ጋር ሊሞቱ ካልቆረጡ በቀር እደመሀይም ለምን ደጅ ይጠናሉ?
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስተር ከወያኔ ባርነት ነጻ ልውጣ ብለው ከተቀዋሚውን ጎራ ቢቀላቀሉ ከአሻንጉሊነት ይድናሉ ማለት በስም ማጥፋት ያስወነጅል ይሆን?
በረከት ስሞን ምን ነካቸው ብሄራቸው ያልሆነውን ህዝብ እወክላለው ብለው ልባችንን በፕሮፖጋነዳ ከሚያደርቁን ያአማራ ፍቅር ነው ወይሰ ክልሉ ወያኔና ሻቢያ ክልልና ሀገር የነፈገው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ክልል ነው?
የቀድመው የወያኔ እመቤት የባለቤታቸው ለቅሶ አብቅቶ ላጠቁት የኢትዮጵያ ህዘብ ቢያለቅሱ እድገትና ትራነሰፎረሜሽን በፍጥነት ይመጣል ማለት ይቻላል?
ወያኔና ጉጅሌዎቹ ኢትዮጵያና አማራ ጠላት ነው ባንዲራም ጨርቅ ነው እያሉ ሲለፍፉ፣ ሲገሉ፡፣ ሲገፉ፣ ሲዘርፉና ሲዘፍኑ ከርመውና ሰንብተው ምነው ከአለማቸው ሽሽት መረጡ?
ዘር የማጥራት ወንጀል የሚፈጽሙ የወያኔ ባልስጣኖች ዘራቸውን ያውቃሉ ወይስ ወያኔ ነው የሚያድላቸው?
የመለሰ ፋውንዴሽንን የሚሉት አቋም ቻይና ወይ ህንድ አልያ ሳዓውዲ ሀገር ውስጥ ቢገነባ አይሻልም?
አስተዳደደር
ነፃ አውጭ ነኝ በሚል ስም የሚነግደው የገዠው ቡድን እንኳን ትግራይን ነፃ ሊያወጣ እራሱን ከሌብነት ነጻ ማውጣጥ ችሎታ የለውም ብል የግንቦት 7 ‘አሸባሪ’ ቡድን አባል ነህ ተብዬ በአሸባሪነት ልወነጀል እችል ይሆን?
ሠራዊቱ ተብዩ ለወያኔ ከህዘብ ዘበኛ ወይስ ህዘብን ከወያኔ ተከላካይ?
የመንግስት ሰራተኞች ሲባል ደሞዝ የሚከፍላቸው ህዘብ ወይስ ወያኔ?
በብሄር ሥልጣን የያዘ ሰው ማንን ነው የሚያስተዳድረው? እራሱን?
የኢትዮጵያን ኤምባሲ የሞሉት ዲፕሎማቶች ዜጋቸውን ወይስ ብሄረቸውን የሚወክሉት? አልያ ለምን ወያኔ ኤንባሲ አይሉትም?
ሐይማኖት
ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በሀይማኖት ስም ዳግም ተወለድኩኝ የሚሉ ባጠፉትን ወንጀል እንዳይጠየቁ ምሸግ ያገኙ መሰላቸው ወይስ ተጸጽተው? አይዣቹህ የሚላቸውስ የሃይማኖት ሥርዓት ወንጀል የፈጸመ ሁሉ ዳግም ከተወልዶ ነፃ መውጣት ትችላላቹህ ነው የሚሉት?
የዘመኑ ፓስተሮች የኢየሱስን ወይስ የወያኔን ቃል የሚሰብኩት?
ወያኔ የሾማቸው የሀይማኖት መሪዎች ሀይማኖትን ከሚያረክሱ ከመስቀል ይልቅ ጠመንጃ ታጥቀው ባለ ሀብት ነኝ ቢሉ አያምርባቸውም?
አቦይ ሰብሃት የሚባሉ የሽማግሌ ቅሌታም ንሳሃ እንዳይገቡ የነፍስ አባት የላቸው፣ እንዳይመኖክሱ ገዳሞች አፍርሰዋል፣ እዳያስቀድሱ ቤተ ክርስትያና እንደሕዋዓት ቢሮ የካድሬ መዋያ ሆነዋል፤ አንደኛውን ዳግም ተወለድኩ ብለው የየሱስ በግ ነኝ እያሉ እንደ ቀድሞው ጠ/ሚንስተር ቢሰብኩ አይሻልም? ለመሆኑ የኢየሱስ በግ መሆን ሌባንም ያድናል እንዴ?
ኢትዮጵያዊያን የእስላም ሀይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ሀገራችን ሀይማኖታችን ወገናችን ወይ ሞት ሲሉ እሰየው ከማለት ምን አስደነገጠው ወያኔ?
የኦርቶዶክስ ሀይማኖት የአማራ መመሸጊያ ነው ስሉ ወያኔዎች ለትግሬ ወገኖች ምንድነች ነው የሚሉት?
በዲያስፖራ ያሉ ቤተ ክርስቲያናት ገለልተኛ ነን ሲሉ ከማን ነው የሚገለሉት? ከሀይማኖት ወይስ ከወያኔ?
ያልሀበሽ የሚሉት ወያኔ ያመጣብን አዲሱ ሞዴል ሀይማኖት ከኢኮኖሚ እደገትና ትራንስፎርሜሽን ጋር አብሮ የሚሄድና ባቋራጭ አላህ ጋር እንዲያገናኘን ነው ወይስ ወያኔ አላህ ነው እንድንል?
ጋዜጠኞችና ብዙሃነ መገናኛ (ሚዲያ)
ወያኔ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጋር እሳትና ጭድ የሆነው በውሸት ህዝብና አገር ሲያቃጥል ሰንብቶ የእውነት እሳተ ሰደዶ ስለመጣበት እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
የበረሀ የጦረኛ ጀግናዎች ነን የሚሉ ወያኔዎች ኢሳት ቴሌቪዝን ፈርተው የተሸሸጉት የውሸት ጀግኖች ወይስ እውነቱ ፈሪዎች?
ሀገር ውስጥ የብዙሃን መገናኛ (ሚዲያ) አለን የሚሉ ግለሰቦች ወይ እውነቱን ተናግረው ወያኔ እሥር ቤት ቢገቡ አልያ እግራቸተውን ሰብስበው እቤታቸው ቢቀመጡ ከውሸት ጛደኝነት አይመረጥም?
ብሄር የሌላቸው በረከት ስምዖን የሚሏቸው የወያኔ የብሔር ብሔረሰብ ፌደራል ባልስልጣን የቡዙሀኑን መገናኛ ለ 22 አመት ሙጥኝ የሉት፤ ብሄር ስለሌላቸው ወያኔ ገለልተኛል ማስረጃ ያቀርባሉ ብሎ ወይስ የውሸት ባለሞያ ስለሆኑ?
ሚሚ ስህባቱ የሚባሉ በነጻ ሚዲያ ስም ወያኔ ብቸኛ ‘የግል’ ሬዲዎ ጣቢያ የለገሳቸው ግለሰብ ድሮ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጋዜጠኛ፣ ብሄራቸው ትግሬና ዜግነታቸው አሜሪካ ሆኖ የአማርኛ ሬዲዎ የከፈቱት ብሄራቸውንም ዜግነታቸውንም ለውጠው ነው ማለት ነው? የወያኔ ሥርዓት ብሄር መለወጥ ይቸሃላል እነዴ? የሁሉም ብሄር ያካተቱ የሚል ኢትዮጰያዊ ብሄር መታወቂያ አለ እንዴ?
ኢትዮጵያን ጋዜጠኞች በእስር ቤትና በስደት አልቀዋል የቀሩት ምንድናቸው ማለት ነው? የማስታወቂያ ሥራ ድርጅቶች?
ኢቲቪ የሚሉት የብዙሃን መገናኛ ከወያኔ ነፃ ቢወጣ ሥርዓቱ ሁለት ቀን ማደር ይችላል?
ያ ወፍራሙ ወያኔ ሬዲዎ ጣቢያ የከፈተለት ዘፋኙን ጋዜጠኛን የሚያዳምጡ ወገኖች በድምጹ ወይስ በዕውቀቱ ተማረከው? አብሮት የሚያጓራ ዶክተር ነኝ የሚል ግለሰብስ የውነት ዶክተር ነው ወይስ የእንድርያስ እሸቴ ጓደኛ?
በዲያስፖራ ያሉ አንዳንድ ድህረ ገጾች ስለ አሜሪካ ዲሞክራሲና ምርጫ ሲዘግቡ ደስ ይላሉ ግን የሀገር ድሞክራሲና ምርጫ ጉዳይ ሲሆን ቻይና እንዳሉ ጋዜጠኞች አይተነፍሱም፤ ፈሪ ከሆኑ ምን አስፈራቸው ወያኔስ ከሆኑስ ምን አስደበቃቸው ብሎ የሚጠይቃቸው እንዴት ጠፋ?
ታጋይ
ይሄ ታማኝ በየነ የሚባል ወገን ጦብያ ሀገራች ለዘላልም ትኑር እያለ የወያኔ ጉጅሌዎችን የሚያቃጥላቸው ለምን ደፈጣ ውጊያችሁን ተውና በህዝብ ፊት ኢሳት ላይ ግጠሙኝ አይላቸውም? ወገኖቼ እነዳይዋረዱ ብሎ አዝኖላቸው ይሆን?
ሕውዓቶች ጀግና ነን ተራራውን አመስነው እያሉ ባዶ ሜዳ ላይ የሚፎክሩትና ዳንኪራ የሚረግጡት እንዴት አንድ ኢትዮጵያዊ አርቲሲት ባዶ እጁን ፈረተው፣ ሸሸተውና እንቅልፍ አጥተው ሊደናበሩ ቻሉ?
ለምንድነው ወያኔ አገራቸውንና ህዝባቸውን በጣም የሚወዱ ኢትዮጵያኖችን ታጋዮች መርጦ መርጦ አሸባሪ የሚያላቸው?
ኦባንግ ሜቶ የሚሉት ኢትዮጵያዊው ቡልዶዘር ወያኔ የሚገነባውን የክልል ግንብ እያፈረሰ አንድ ህዝብ አንድ ሀገር ስላለ አሸባሪ ስም ያሸከሙት ወያኔን ወይስ ወገኑን ስላሸበረ ነው?
ዶ/ር ብርሃኑ የሚባሉት የግንቦት 7 መሪና ወገን በወያኔ አሸባሪ ተብለው የተፈረጀባቸው በግንቦት 7 ህዝብ ስለመረጣቸው ወይንስ ወያኔን ከግንቦት 7 ጀምረው ሽብር ስለጨመሩት?
ወገን በዲያስፖራ
በውጭ ያሉ የወያኔ ደጋፊ ኢትዮጵያውያን ከወያኔ በሓላ ሀገር አትኖርም ብለው ሀገር ሊከዱ አስበዋል እንዴ?
ዲያስፖራውን ፈሪ ያደረገው ወያኔ የሰጠውን መሬት ይወስድብኛል ብሎ ይሆን?
የሕዋት ካድሬዎች ስንት ብሄር ነው ያለቸው? አንደኛውን ኢትዮጽያ ነው ብሄሬ ቢሉ አይሻልም?
በውጭ ሀገር ለህዳሴ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚመጡ የወያኔ ጉጅሌዎች ኢትዮጵያንን ሁሉ ሲጋብዙ አባይ ክልል የለውም ማለት ነው? ለምን የትግራይ ክልል ግንባታ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አይጋበዙም?
ዲያስፖራ ያሉ የሕዋዓት አባሎች ዜግነታቸው ሕዋዓት ነው ወይስ ኢትዮጵያዊ?
ለምንድነው የወያኔ ጉጅሌዎች በዲያስፖራ ስማቸውንና ተግባራቸውን ደብቀው ድፍጢያ ውጊያ የያዙት፤ ስራቸው ወንጀል መሆኑን ያውቃሉ ማለት ነው?
ጥያቄው ይቀጥላል…
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar