fredag 31. mai 2013

የብአዴን ወጣቶች ሊግ አባላት ከኢህአዴግ ጎን ተሰልፈን ለመታገል እምነትም ጽናትም የለንም አሉ

የብአዴን ወጣቶች ሊግ አባላት ከኢህአዴግ ጎን ተሰልፈን ለመታገል እምነትም ጽናትም የለንም አሉ

ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ይህን የተናገሩት በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የብአዴን ወጣቶች 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡
በክልሉ ካለው 20 ሚልዮን ህዝብ መካከል 429 ሺ 520 የሚሆኑ ወጣቶችን አባል አለኝ የሚለው ብአዴን ከአደገኛ ቦዘኔነት እስከ ልማት አርበኛ ስም የሚነግድበት ወጣት ከገዥው ፓርቲ ያተረፈው ኪሳራ መሆኑን ተሰብሳቢዎች በአስተያየት አመልከተዋል፡፡
ከመላው የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ3000 በላይ ወጣቶች በጥቃቅን እና አነሰተኛ የዘርፉ ስኬታማነት በሚል ርዕስ የቀረበውን ሪፖርት ካደመጡ በሁዋላ የአህአዴግ ንግድ ትርፉ ኪሳራ ነው ብለውታል፡፡
በጥቃቅን እና አነሰተኛ ፖሊሲ ስም ፍጹም ክህደት ተፈጸመብን የሚሉት ወጣቶች መማራችን የጠቀመን ነገር የለምም ብለዋል፡፡
ኢህአዴግ ከ97 በፊት የገጠመውን የስራ አጥነት የተቃውሞ ፈተና በአደገኛ ቦዘኔ ስም በእስራት ሊፈታ የሞከረ ሲሆን ያኔ በተቀሰቀሰው የለውጥ ማዕበል ችግሩ እንዲስተካከል ለማድረግ ሞክሩ ሳይሳካለት ቀርቷል
“በሃሰት እንድንኖር እየተገደድን ነው” ያሉት ወጣቶች ፣  ከኢህአዴግ ጎን ቁሞ ለመሰለፍ ተስፋችን ተሞዋጦ አልቋዋል  እምነትም የለንም ብለዋል፡፡
በጉባኤው ላይ በ19 60 ዎቹ የነበሩትን የወጣቶች እንቅስቃሴ እንደነ ዋለልኝ እና ማርታ የመሳሰሉትን በማንሳት ሌላ ታሪክ ያሰፈልጋል ያሉም ነበሩ።
የግዳጅ  የድጋፍ ሰላማዊ  ሰልፍ እንዲሁም ትርፍ የሌለው የአዲስ ራዕይ መጽሄት ውይይት አሰልችና ጊዜ ጨራሺ ነው ያሉት ወጣቶች በመዋጮ ሰበብ የሚጠየቁት ክፍያ መብዛቱን፣  የሚናፍቁትን ስራ እንደላገኙና የቤተሰብ ሸክም ለመሆን ስርዓቱ እንዳሰገደዳቸው ተናግረዋል፡፡
ወጣቱ ቁርጠኛ አልሆነም ያሉት የሊጉ ለቀመንበር አቶ ስቡህ ገበያው በየደረጃው ያሉ አመራሮች የአድርባይነት እና የአቅም ክፍተት የወጣቱን ተጠቃሚነት ፈተና ውስጥ ከተውታል ብለዋል፡፡
ኪራይ ሰብሳቢነት፤ብልሹአሰራር ፤ሙስና በወረረው ዓመራር መሃል መታገል እና ለውጥ ማምጣት ትግሉን እንደ አዲስ ከመጀመር ይታሰባል ያሉት የወጣት አመራሮች ችግሩን ለመፍታት መታገል አለብን ብለዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየቱን የጠየቅነው አቶ ስቡህ ለኢሳት እንደገለጸው መድረኩ ፍጥጫ የበዛበት እንደነበር አምኖ፣ ወጣቶች ከኢህአዴግ ጎን አንቆምም ማለታቸውን ግን አስተባብሎአል። ( )
ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። እሳቸውም ” እናንተን ወጣቶች ይዘን የአውራ ፓርቲነታችንን እናረጋግጣለን “ብለዋል። ጉባኤውን ለማዘጋጀት 1 ሚሊዮን ብር መመደቡም ታውቋል።

Ethiopia holds reporter covering evictions in dam region

Ethiopia holds reporter covering evictions in dam region

New York, May 30, 2012–Ethiopian authorities have detained since Friday a reporter who sought to interview people evicted from their homes in a region where the government is building a contentioushydro-electric dam on the Blue Nile, according to a news report and the reporter’s editor. The Committee to Protect Journalists said today that the case highlights authorities’ disregard for the rule of law and its systematic efforts to suppress news critical of government officials.
Muluken Tesfahun, a reporter for the private weekly Ethio-Mehedar, is being held in a prison in the town of Asosa, capital of the Benishangul-Gumuz region, Getachew Worku, the paper’s editor-in-chief, told CPJ. Muluken has not been formally charged or presented in court, Getachew said. The detention appears to run counter to constitutional guarantees that a person be brought to court within 48 hours of arrest.
“By arresting journalist Muluken Tesfahun for gathering information from the victims of forced relocation, Ethiopia is once again criminalizing independent journalism,” said CPJ Africa Advocacy Coordinator Mohamed Keita. “Ethiopia should make good on its obligation as a member of the U.N. Human Rights Council to uphold citizens’ rights by releasing Muluken immediately.”
Local security forces picked up Muluken on Friday in the village of Dobi and confiscated his reporting equipment, the U.S. government-funded Voice of America reported, citing Getachew and members of the journalist’s family. Ethio-Mehedar assigned Muluken to report on the return of thousands of ethnic Amhara, Oromo, and Agew farmers who had been forcibly evicted from their land in mid-March, Getachew said.
Ethiopian state media have not reported in detail on the evictions, despite local testimony reported by VOA and accusations of ethnic cleansing made by opposition parties, according to local journalists. After weeks of silence, Prime Minister Hailemariam Desalegn acknowledged the evictions in an April speech in the House of Peoples Representatives. The prime minister called the action “illegal,” blaming it on lower-level officials and inviting the displaced to return. This month, Federal Affairs Minister Shiferaw Teklemariam announced the arrests of 35 Benishangul officials in connection with the evictions.
Neither federal or local authorities have provided an official explanation for the evictions, and it’s not immediately clear they were directly related to construction of the Grand Renaissance Dam, which the government says will be Africa’s biggest power plant. The dam’s impact on water supply has renewedinternational tensions between Ethiopia, Egypt and Sudan.
The Ethiopian government has denied allegations of coercion, abuse, and violence in unrelated resettlement programs, in which authorities have displaced small-scale farmers in order to lease large tracts of land to foreign commercial farmers, according to international news reports.
With eight journalists behind bars, Ethiopia trails only Eritrea among Africa’s worst jailers of journalists, CPJ research shows.

የዘረኝነትን ሰደድ እሳት እናጥፋ


የዘረኝነትን ሰደድ እሳት እናጥፋ

ብዙውን ጊዜ የነገሮች መነሻ መድረሻውን ሊያመለክት ይችላል ። በአገራችን በሕዝብ ላይ የተጫነው በዘር ላይ የተመሰረተ
የፖለቲካ ሥርዓት ከመነሻው የተሳሳተና ያለሕዝብም ይሁንታ የተቋቋመ በመሆኑ ቅቡልነት አልነበረውም፤ አሁንም የለውም።
ተቀባይነት የማጣቱ ዋነኛ ምክንያት ጎሣዎችን እንደፖለቲካ ማዋቀሪያነት መጠቀም በአገራችን የረዥም ጊዜ ታሪክ ቀርቶ
በሌላውም የዓለም ዳርቻ/ክፍል ታይቶም ተሰምቶም አለመታወቁ ነው።

ፖለቲካው በቋንቋና በዘር ሲዋቀር ሳንክ እንዳለበት የሚያሳይ ወጥነት የሌለው አካሄድ ከጅምሩ ተሰተውሏል። የትግራይ ፣
የአማራ፣ የኦሮሞ ፣ የአፋር፣ የሱማሌ ፣የሀድያ፣ የወላይታ ወዘተ ተብለው ክልሎችና ዞኖች ሲፈጠሩ እንደ ወያኔ/ አህአዴግ
የፖለቲካ ዓላማ መሰራት ካለበት በአገሪቱ በመላ ከ82 በላይ ጎሣዎች ስላሉ በዚያው ልክ የመንደር መንግሥታት መቋቋም
ግድ ሊል ሆነበት። በዚህ ግራ የተጋባው ወያኔ በርካታ ጎሣዎች የሚገኙበትን ደቡብና ደቡባዊ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል
ጨፍልቆ ደቡብ ሕዝቦች የሚል መጠሪያ አወጣላቸው ። በነገራችን ላይ ደቡብ የአቅጣጫ መጠሪያ እንጂ ሲዳማውን ፣
ወላይታውን፣ ጋሞውን፣ ኮንሶዉን ፣ ሀዲያውን፣ ከምባታውን፣ የሙን፣ ጋምቤላውን፣ ጉራጌውን፣----------ሊገልጽ አይችልም።
የወያኔ የአገዛዝ ክልል ሕዝብን ለማስተባበርና አገርን በልማት ጎዳና ለማራመድ የታቀደ ሳይሆን ሕብረተሰቡ በትንሽ በትልቁ
የሚናቆርበት ክስተት እንዲፈጠር ለማድረግ በመሆኑ ከሃያ ዓመታት በላይ በአገሪቱ የትርምስ ትርኢት እየታየ ነው።
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመዘርጋትና የሕዝብ ውክልና የተሰጠው መንግሥት ለማቋቋም በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተካተቱት
መርሆዎች “ ዘርን” ወይም “ ጎሣን” መነሻ ያደረጉ ሳይሆን ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ሆነው ነው የተቀረጹት። ጎሣ ፣ ነገድ ፣
የቆዳቀለም ፣ ዕምነት ፣ ባሕልና የኑሮ ዘይቤ አንድን ግለሰብ ወይም ማህበረሰብ ለጥቃት እንዲጋለጥ የሚያበቃ ምክንያት
የለም። አምባገነኖችና ዘረኞች ግን ከሞራልም ከሕግም በላይ ሆነው የከፋ ወንጀል በሕዝብና በአገር ላይ ይፈጽማሉ።
በአገራችንም እየታየ ያለው ይኸው ነው። አንዳንድ አእምሮቸውን ለጥፋት የሚያውሉ ግለሰቦች የጭካኔ መንፈስ አድሮባቸው
ኢሰብአዊ ድርጊት ሊፈጽሙ ቢነሳሱና በተግባር ቢገልጹት በማህበረሰብ የሚወገዝ ሲሆን በቡድን ተሰባስቦ ለጭካኔ ተግባርና
ጥፋት መስማማት ግን ከወንጀሎች ሁሉ የበለጠ ወንጀል ነው የሚሆነው። ለዚህም ነው የዓለም መንግሥታት ( UNITED
NATIONS) እንደነዚህ ያሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች እንዲዳኙ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ሸንጎ የሰየመው።
በአገራችን በጎሣ ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሥርዓት ጥንስሱ የሰብአዊ መብቶች ከግለሰብ ጀምሮ የሚከበርበት ሳይሆን
ሰዎች በጎሣቸው ተያይዘው ከዚያ ውጪ ላለ ግለሰብ ወይም ጎሣ ደንታ እንዳይኖራቸውና ልዩነታቸውን እንዲያሰፉ የሚያደርግ
ነው። ሰው ነኝ ማለት ከሁሉም የሰው ዘር ጋር ያስተሳስራል። የዚህ አገር ዜጋ ነኝ ማለት ደግሞ ሌላ ትስስርና የማንነት
መገለጫ ነው። ኦሮሞ ነኝ ፣ አማራ ነኝ ፣ ትግሬ ነኝ ፣ --------ወዘተ ማለቱ ወያኔ በሚጠቀምበት መልክ ለፖለቲካ ዓላማ
የሚውል ከሆነና ኢትዮዮጵያዊነትን በማደብዘዝ የበላይነትና የበታችነት፣ የአናሳና የብዙኃን ---------እያለ ለልዩነት በር
የሚከፍት ነው። የወቅቱ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግሥታዊ ቡድን ይህን የመለያየት አጥር ለማጠር የፈለገው ሆን ብሎ ነው።
በልዩነታችን እርስ በርስ ስንራኮት ይኸውና ከሃያ ዓመታት በላይ በሥልጣን መንበሩ ላይ ጉብ ብሎ ሕዝብን እየበደለ
ተጠቃሚ ሆኗል። በዚህ የተነሳም በተለይ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማያወላውል አቋምና ቀናኢም ናቸው ብሎ በፈረጃቸው
የሕብረተሰብ ክፍሎች ፣ ድርጅቶች፣ የሙያ ማህበራትና ግለሰቦች ላይ ጫናውና የጥፋቱ ዘመቻ እጅግ እየክፋ መጥቷል።
በወያኔ/ኢህአዴግ የክህደት ቁልቁለት አካሄድ በሺህ ዓመታት የሚቆጠር ታሪክ ፣ በማህበራዊ ፣ ባሕላዊና ኃይማኖታዊ
መስተጋብር የተጋመደና በሂደትም የተዋሃደ ሕዝብ የሚኖርባት ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም የሚል ነው። ስለኢትዮጵያ
አኩሪ ታሪክ፣ ስለሕዝቧ አንድነትና ውህደት አቀንቃኝ አማራ የሚባል ዘር እስካለ የማራምደው አገርን የማጥፋት አጀንዳ ግብ
አይመታም በሚል ገና በጫካ ማኒፌስቶው የጥፋት ዕቅድ መንደፉን ከወያኔ ድርጅት መስራች አባላት እየተነገረ ከመሆኑም ባሻገር ሰነዱም ምስጢር ሆኖ አልቀረም።

በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሥርዓት የላይ ሽፋኑ ሁሉንም ጎሣዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መስሎ ቢታይም መነሻ
ሰበቡ አማራ የሚባል ዘር ፣ የአማራ የገዢ መደብ የሚባል ሥርዓት በሌሎች ላይ ግፍ እንደፈጸመ ሰፊ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት
ይህን የህብረተሰብ ክፍል ከሥልጣን ማራቅ ፣ ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማገድ ፣ ሥነ-ተወልዶው እንዲመናመን መሥራት ፣
የሰፈረበት መሬት እየተቆረሳ ወደሌሎች ክልሎች እንዲጠቃለል ማድረግ ፣ ከጎንደር ጫፍ እስከ ጋምቤላ ድረስ ያለውን መሬት
ለሱዳን ሰጥቶ መሬቴን አለቅም ያለውን ሕዝብ የወያኔና የሱዳን ሠራዊት በትብብር እንዲያጠቁትና ለሌሎችም ሰቆቃዎች
ተጋላጭ እንዲሆን ስልት መቀየስ እንደፖሊሲ ተወስዷል።
በአርባጉጉ ፣ በወተር ፣ በአሶሳ ፣ በጂማ ፣ ------በአብዛኛው አማራዎች ላይ እንዲሁም በተወሰኑ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ 2
በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሥርዓት የላይ ሽፋኑ ሁሉንም ጎሣዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መስሎ ቢታይም መነሻ
ሰበቡ አማራ የሚባል ዘር ፣ የአማራ የገዢ መደብ የሚባል ሥርዓት በሌሎች ላይ ግፍ እንደፈጸመ ሰፊ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት
ይህን የህብረተሰብ ክፍል ከሥልጣን ማራቅ ፣ ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማገድ ፣ ሥነ-ተወልዶው እንዲመናመን መሥራት ፣
የሰፈረበት መሬት እየተቆረሰ ወደሌሎች ክልሎች እንዲጠቃለል ማድረግ ፣ ከጎንደር ጫፍ እስከ ጋምቤላ ድረስ ያለውን
መሬት ለሱዳን ሰጥቶ መሬቴን አለቅም ያለውን ሕዝብ የወያኔና የሱዳን ሠራዊት በትብብር እንዲያጠቁትና ለሌሎችም
ሰቆቃዎች ተጋላጭ እንዲሆን ስልት መቀየስ እንደፖሊሲ ተወስዷል።
በአርባጉጉ ፣ በወተር ፣ በአሶሳ ፣ በጂማ ፣ ------በአብዛኛው አማራዎች ላይ እንዲሁም በተወሰኑ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ
የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ ብዙ ዓይነት ግፍ ተካሂዶባቸዋል። አማራዎች ግን በተለይ ከነነፍሳቸው ገደል ውስጥ
ተጥለዋል ፤ ቤታቸው ተዘግቶ ተቃጥለዋል፤ ሰለባ ተፈጽሞባቸው እንደከብት ታርደዋል ፤ ሞት ሳያንሳቸው ለመጣፍ ይሉ
ለወናፍ የማይፈይድ ቆዳቸው ተገፏል። ይህ ሁሉ መዓት ሲወርድ በመንግሥት ስም የተቀመጠው አካል አልሰማም አላየም
ማለት ራስን ማሞኘት ነው። ይህ ሁሉ የጭካኔ ተግባር አማራ በመሆን ብቻ የተፈጸመና እየተፈጸም ከሆነ ነግ በኔን
አያስታውስም? የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ በዘር መደራጀትን ትተንና ባንድነት ሆነን ካልተነሳን ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያን
የማጥፋቱ ዕቅድ አያቆምም።
በዓለም አቀፍ ድንጋጌም በወያኔ ሕገመንግሥትም የተረጋገጠው ዜጎች በፈለጉበት ቦታ መርጠው የመኖር መብታቸው ተጥሶ
በጉራፋርዳ ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ አማራ የሆነ ጓዜን ጉዝጓዜን ሳይል ሲባረርና መድረሻ ሲያጣ ፣ ሲንከራተት ፣ ሲዘረፍ ፣
ሲደበደብ ፣ ሲገደል ፣ ማየትና መሰማት የሚሰቀጥጥ ነው። ነፍሰ ጡሮች አውላላ ሜዳ ላይ የጭንቅ ምጥ አምጠው
መገላገላቸውን ተመስገን የሚሉ ሳይሆን ሰው መሆናቸውን ፣ አማራ መባላቸውን እንደሚያማርሩና ተስፋቸው መጨለሙን
መገመት ይቻላል። ይህ በኢዮጵያዊነት ስነልቦነና ሰብአዊነት ሁነቶች ስናስበውና ስናስታውሰው በእጅጉ ይዘገንናል።
ቀደም ሲል ከላይ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ሌላ በኦሮሚያ ፣ በሱማሊያ ፣ -----ወዘተ የማፈናቀል እርምጃ ተወስዷል።
ለምሳሌ በኦሮሚያ ከሁሉም ብሔረሰብ ተወላጆች የሆኑ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ከክልሉ
ተባርረዋል። በአገሪቱ ሠርተው የመኖር መብታቸው ከመጣሱም በላይ በሌሎች ክልሎች ተጨማሪ የመምህራን ቁጥር
እንዲፈጠር ሆኖ ያለአግባብ የአገር ሀብት ብክነት ተከስቷል። የዚህ ማፈናቀል ዋና ዓላማ ብሔራዊ ቋንቋ የሆነውን የአማርኛ
ቋንቋን ማጥፋት ፣ ኢትዮጵታውያንን የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ማሳጣትና አንድነታቸውን የማላላት ስልት ነው።
ከአስርት አመታት በፊት አንድ የኦሮሞ ጎምቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሠርገኛ ጤፍ እንዳመሳሰሉት ይነገራል። አባባላቸው
ዕውነትና ልብን የሚነካ ነው። አሁን የሚታየው ግን የልዩነት ቁርሾ እየተሰበከ አገሪቱን ወደለየለት ዕልቂትና መበታተን
የሚያመራ መንግሥታዊ/ቡድናዊ አጀንዳ እንደሆነ ነው። ይህ አጀንዳና እኩይ ተግባር የቅርብና የሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን
ውጥን ቀጣይ እንቅስቃሴ እንደሆነ መጥቀስ ይቻላል። ፋሺስት ጣሊያን ፣ እንግሊዞችና ሌሎችም ኢትዮጵያ እንድትበታተን
የተለያዩ ካርታዎች እየሰሩ ማሳየታቸውን መዘንጋትና መዘናጋት የለብንም። ያለመታደል ሆኖ የነርሱ ጉዳይ አስፈጻሚ አካል
በትረ መንግሥቱን ጨብጧል። ሰለሆነም ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለሕዝብ አንድነት ይቆማል የሚባል ሁሉ ወርተረኛ ሆኖ
ፍዳ መቁጠሩ ይቀጥላል። በሂደቱም በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው በሌሎችም ያለጥርጥር ይደርሳል። ሲዳማውን ከወላይታ፣
ጉጂውን ከቡርጂ ፣ አፋሩን ከኢሣው ፣ አላባውን ከሀዲያ ፣------ ማጋጨት ሥራዬ ተብሎ ሲሰራ ያየነው የሰማነው አካሄድ
ነው። ለባዕድ አገር ከበርቴዎች መሬት ለመሸጥ ተብሎ በአንድ ጊዜ ከ140 በላይ ሙርሲዎች የጅምላ ግድያም ሌላው
የሥርዓቱ አራማጆች ፋሽስታዊ እርምጃ ነው። በጋምቤላ በታህሣሥ ወር 1995 ዓ.ም ለመብታቸው በመቆማቸው ብቻ
የወያኔ ጦር 424 አኙዋክ ዜጎቻችን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ፤ ከዚያም በተከታታይ ብዙ ግዲያ ታይቷል።
ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል፤ መሬታቸውም በኢንቬስትሜንት ስም ለውጭ አገር ከበርቴዎች ተሰጥቷል። በሂደቱም
መምህራንና ሌሎች የተማሩ ወገኖቻችን እንደጣሊያን ጊዜ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። ወንጀላቸውም ሕዝቡን ለመብቱ
እንዲቆም ማገዛቸው ነበር። አሁንም ጥቃቱ አላቋረጠም። በዚች አጭር መግለጫ ባለፉት ሃያ የመከራ ዓመታት በሕዝብ ላይ
የተፈጸመውን ዙሪያ ገብ ሰቆቃ ዘርዝሮ ማቅረብ ስለማይቻል እየቆነጠርን ለማሳየት ሞክረናል። ለሁሉም የስቃዩ ገፈት ቀማሽ
የሆነው ሕዝብ እማኝ ነው ብለን እናምናለን።

ዕውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሕዝብን በማደናገርና በማምታታት ከተካኑት የወያኔ/ኢህአዴግ ባለሥልጣናት አንዱ የፌዴራል
ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለማሪያም የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ ሪፖርት ለፓርላማ ባቀረቡበት
ወቅት “ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ አርሶአደሮችን ሕገወጥ በሆነ መንገድ በማፈናቀል የተጠረጠሩት 35 የቤንሻንጉልና
ጉሙዝ ክልል አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸውንና ከነዚህም 12ቱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። “ ብለዋል። ይህ
የወያኔ አብዮታዊ ርዕዮትና የተግባር እንቅስቃሴ አዲስ ክስተት አይደለም። ያሁኖቹ ግፈኞች በበረሃ እያሉ ጓዶቻቸውን
ለእርድ አቅርበው ጭዳ አድርገዋቸዋል። ትልቁ ዓሣ ትንሹን ውጦ ሕልውናው እንደሚቀጥል የወያኔ ተፈጥሯዊ ባሕርይ
መገለጫው ነው። ፖሊሲ አውጪ፣ ትዕዛዝ ሰጪ፣ ገምጋሚ፣ ------ሁሉንም ነገር በሁሉም ሥፍራ ፈጣሪና አድራጊዎች 3
የበላይ ሹማምንት መሆናቸው እየታወቀ የበታች ካድሬ ሹመኞችን ለይምሰል በማጋለጥ ሕዝብን ማሞኘት አይቻልም ፣
የፍትሕ አካሄዱም የሚያመረቃ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። በአንድ ወቅት ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ
ከአንድ የደቡብ ክልል ስለተፈናቀሉ የአማራ አርሶአደሮች ማብራሪያ ሲጠየቁ “ ክልሉ ምሥራቅ ጎጃም ሊሆን ምን ቀረው? “
ብለው ነበር የተሳለቁት። ዜጎች በፈለጉበት እንዲኖሩ እየለካ የሚሰጠውና የሚፈቅደው የሳቸው ድርጅት ይሆን ያሰኛል።
ከዚያም በላይ የመልሳቸው አንድምታ አርሶአደሮች በዚያ ክልል ሊኖሩ የማይችሉና የማይፈቀድ መሆኑን ነው የሚያሰየው።
ይህን ቡድናዊ እኩይ ተግባር ለማስወገድ ሙስናን ፣ ዘረፋን ፣ ዘለፋን፣ ውሸትንም እንቃወም ፤ ቂምን ፣ በቀልን ፣
እናውግዝ ፤ የጥንቱን የመተሳሰብ፣ የመሰባሰብና የመደጋገፍ፣ የመከባበርና አብሮነት ባህላችንን እናድስ። እነዚህ የሕዝብ
እሴቶች ከሌሉ እንደሕዝብና እንደአገር መቀጠል ይከብዳል። ስለሆነም ዜጎች ሁሉ በግልና በተሰባሰቡባቸው የፆታ ፣ የሙያ
፣ የአክሲዮን ፣ የዕድር ፣ የቀበሌ ማህበራት በመነጋገር ፣ የጥላቻ ግድግዳን በመስበር የውይይት በር ለመክፈት በመሞከርና
ፍቅርን በማሳየት ይህን የተሳሳተ አካሄድ ለመለወጥ መሥራት ይጠበቅባቸዋል። የደረቅ አጠገብ እርጥቡ ይጨሳል እንዲሉ
ያንደኛው ወገን ጥቃት በሁላችንም ላይ እንደተቃጣ ልንቆጥረው ሁኔታዎች ያስገድዳሉ። በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን
ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ የአገር ፣ የሕዝብ፣ የሰብአዊነትና የሰብአዊ መብቶች ፀር የሆነው ዘረኝነት የባሰ ጥፋት
ሳያደርስ ከሥሩ እንዲመነገል መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ገበሬዎች፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወታደሮች፣ የተለያዩ ዕምነት
ተከታይ ወገኖች በአጠቃላይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በጋራ እንዲቆሙና እንዲታገሉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

የዘረኝነት ሰንኮፍ ይነቀል!!
ለጋራ ቤታችን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንታገል!!
የዘር መድሎ (አፓርታይድ ) በኢትዮጵያ ምድር አይለመልምም !!

መኢአድ አንድነት ከሰማያዊ ጎን ቆሙ - መኢአድ አንድነት ከሰማያዊ ጎን ቆሙ

መኢአድ አንድነት ከሰማያዊ ጎን ቆሙ - መኢአድ አንድነት ከሰማያዊ ጎን ቆሙ 
 ግርማ ካሳ 

ዜጎች ሃሳባቸዉን በነጻነት የመግለጽ፣ የመሰባሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብት አላቸው። ይሄንን መብት 
በመጠቀም አገር ቤት የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ በአፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራል። 
ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት፣ ለባለስልጣናት ሰልፍ እንደተጠራ ማሳወቅ ብቻ ስለሚያስፈልግ፣ የፓርቲዉ አመራር 
አባላት ማስታወቂያ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር ይሄዳሉ። የአስተዳደሩ ሃላፊዎች ግን ሊያናግሯቸውም 
ሆነ ማስታወቂያዉን ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀረ። ተደጋግሞ ሙከራ ቢደረግም፣ በሕጉ መሰረት የሰማያዊ 
ፓርቲን ማስታወቂያ ተቀብለው፣ አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ የነበረባቸው የኩማ ደመቅሳ ሰራተኞች ግን 
ዜጎችን ማንገላታት መረጡ። 
ዜጎች ሰልፍ በሚጠሩበት ጊዜ ለባለስልጣናት የሚያሳዉቁት፣ ፍቃድ ለመጠየቅ ሳይሆን፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ 
የኮንስትራክሽን ግንባታዎች የመሳሰሉ ችግሮች ካሉ፣ አስፈላጋዊዉን ዝግጅት ማድረግ፣ ያም ካልተቻለም ደግሞ 
ሰልፉ የሚደረገበትን ሌላ አማራጭ ቦታ ወይንም ጊዜ በመግለጽ፣ እንዲተላለፍ መጠይቅ ይችሉ ዘንድ ነዉ። 
በአዲስ አበባ አስተዳደር እንግልት የደረሰባቸዉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ በፓስታ ቤት፣ በሬኮመንዴ 
ሰልፍ እንደሚያደርጉ የሚገለጸዉን ደብዳቤ ይልካሉ። ከአስተዳደሩ ግን ምንም አይነት ምላሽ አሁንም ሳይገኝ 
ይቀራል። የዚህን ጊዜ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንጂ ከማንም ፍቃድ መጠየቅ እንደሌለባቸው ጠንቅቀዉ ያወቁት 
ብሉዎች፣ ሰልፉ በተባለው ቀን (ግንቦት 17) እና ቦታ እንደሚደረግ ያሳውቃሉ። የዚህን ጊዜ፣ በሰማያዊ ፓርቲ 
ዉሳኔ ግራ የተጋቡትና የጨነቃቸው የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለስልጣናት፣ በርካታ የዉጭ አገር መሪዎች በአዲስ 
አበባ በመኖራቸውና ከፍተኛ መጨናነቅ በመኖሩ፣ ሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲደረግ ይጠይቃሉ። ሕግን 
የሚያከብረው ሰላማዊዉ የሰማያዊ ፓርቲ፣ በቀኑ መለወጥ ተስማምቶ፣ ሰልፉ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 ቀን 
2005 ዓ.ም እንደሚደረግ ይገልጻል። 
እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ፣ ለመብት፣ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገዉ ትግል ስር እየሰደደ መምጣቱን 
ነዉ። በዚሁ በሰላማዊዉ ትግል እንቅስቃሴ ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የኢትዮጵያዉያን መሰባሰባና መተባበር እየታየ 
ነዉ። ይሄም በራሱ ትልቅ ድል ነዉ። 
የመኢአድ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ ወንድሙ ፣ ድርጅታቸው መኢኣድ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው 
ሰልፍ ላይ አባላቱና ደጋፊዎች እንዲገኙ ጥሪ እንዳቀረበ፣ ከፍተኛ የማስተባበር ሥራ እንደሚሰራም 
አስረድተዋል። የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣ የተከበሩ አቶ ዳንኤል ተፈራ በበኩላቸው ፣ 
የአንድነት ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ከልብ እንደሚደግፍ፣ አባላቱም ከብሉ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር 
ሆነዉ ድምጻቸውን ለማሰማት እንደተዘጋጁ ገልጸዋል። ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የአንድነት አመራር አባላት የቅርበት 
ግንኙነት እንዳላቸው የገለጹት ሌላው የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባልና የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ፣ የተከበሩ አቶ 
ተመስገን ዘዉዴ « የሰማያዊ ፓርቲ ያናሳቸው ጥያቄዎች የአንድነት ጥያቄዎቹ ናቸው። በአዲስ አበባ በሚገኙ 23 
ወራዳዎች ባሉት ሴሎችና ጽ/ቤቶቹ አማክኝነት፣ የቅስቀሳ ሥራ ጀምሯል» ሲሉም የሰላማዊ እንቅስቃሴዉን ግለት 
ለማሳየት ሞክረዋል። 
ከመኢአድና ከአንድነት ፓርቲ በተጨማሪ የባላራዩ የወጣቶች ማህበር የተስኘው የሲቪክ ማህበርም በሰልፉ 
ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን፣ የአመራር አባላቱ ከሰልፉ ጋር በተገናኘም ከወዲሁ ከፍተኛ 
እንግልት እየደረሰባቸው ነዉ። የባላራእዩ ወጣቶች ማህበር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣ ወጣት ተክለ ያሬድ 
በአሁኑ ወቅት በአገዛዙ ፖሊሶች ተይዞ በእሥር ቤት ይገኛል። ይሄም የሚያሳየው ምን ያህል በአገር ቤት ያሉ 
ወገኖቻችን ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈሉ እንዳለ ነዉ። 
ወደ ዉጭ አገር ስንመጣ ደግሞ ኢትዮጵያዉያን በሚሰባሰቡበት በርካታ የፓልቶክ ክፍሎች ከመቼዉም ጊዜ 
በላይ፣ ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ ያልታወቀ፣ አገር ቤት እየተደረገ ላለዉ ትግል ትልቅ ድጋፍ እየተሰጠ ነዉ። 
ትላንት የተለያየ መስመር ይዘው እርስ በርስ ሲላተሙ የነበሩ፣ የቃሌ ክፍል፣ ከረንት አፌር፣ ደብትራዉ፣ ሲቪሊቲ 
….የመሳሰሉ ክፍሎች እየተግባቡ፣ እየተቀራረቡና ለአንድ አላማ በአንድ ላይ እየተሰባሰቡ ነዉ። ሁሉም 
ትኩረታቸውን አገር ቤት አድርገዉ፣ እየተደረገ ላለዉ ሰላማዊ ትግል ድጋፋቸውን እየለገሱ ነዉ። እንደ ኢሳት፣ ኢትዮጵያ ሪቪው፣ ዘሃበሻ፣ አቡጊዳ፣ ኢኤምኤፍ ያሉ ሜዲያዎችም፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ዘገባ እያቀረቡበት 
ሲሆን፣ ተስፋ ቆርጠው ፣ በነበሩት መከፋፈሎች አዝነዉ ፣ ዝምታን መርጠው የነበሩ ሁሉ እየተነቃነቁ ነዉ። 
በዉጭ አገር ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ካየን ደግሞ፣ በባህር ዳር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዳደረገ በኢሳት 
የተዘገበለት የሽግግር ምክር ቤት የተሰኘው ድርጅት፣ እንዲሁም ኢሕአፓ-ዴ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራዉ 
መኢአድና አንድነትን ለተቀላቀሉት የሰላማዊ ሰልፍ ያላቸዉን ድጋፍ ገልጸዋል። በስምንት የፓልቶክ ክፍሎች፣ 
በፌስቡክና ትዊተር በመተላለፍ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን ተከታትለውታል በተባለው፣ ግንቦት 17 እና 
18 2005 ዓ.ም የሲቪሊቲ ክፍል ባዘጋጀው የአለም አቀፍ የኢትዮጵያዉያን ኮንፍራንስ ላይ፣ የተገኙት የሽግግር 
ምክት ቤቱ ዋና ጸሃፊ የተከበሩ ዶር ፍስሐ እሸቱ፣ ድርጅታቸው በአገር ቤት ለሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል ሙሉ 
ድጋፍ እንዳለው አረጋግጠዋል። «ትግሉ ያለው አገር ቤት ነዉ። አገር ቤት የሚታገሉትን መርዳት አለብን» ሲሉ 
ነበር ዶር ፍስሐ ለአገር ቤቱ ትግል ያላቸዉን ጠንካራ ሶሊዳሪቲ የገለጹት። 
ይሄ ሁሉ እንግዲህ የሚያሳያዉ ጸሎታችን እየተሰማ እንደሆነ፣ እንደ ሕዝብ ለመብታችን፣ ለአገራችን አንድነት 
መከበር፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህ መስፈን ፣ ለሕግ የበላያነት ፥ ለመታገል በአንድ ላይ እየተሰባሰብን መሆኑን ነዉ። 
ሁለት ነጥቦች ጣል አድርጌ ላቁም። በጣም መሰረታዊና ሊሰመርባቸው የሚገባ ነጥቦች ! 
አንደኛ - የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 ቀን የሚደረገዉ ሰልፍ ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም። ቀጣይነት ያለው፣ 
የተደራጀ፣ የተጠና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ይቀጥላሉ። በዘጠና ሰባት በግፍ የተገደሉትን ፣ እነ ሽብሬ ደሳለኝ፣ 
ለማስታወስ፣ የአንድነት ፓርቲ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ዝግጅት ላይ እንዳለ የፍኖት ጋዜጣ በቅርቡ 
መዘገቡ ይታወሳል።። ለአንድነት ቅርበት ያላቸው እንደገለጹልኝ፣ የሚደረጉትን ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ሰላማዊ 
ሰልፎችን የሚያካትቱ ሲሆኑ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በማቀናጀት የሚሰራ እንደሆነም ለመረዳት ችያለሁ። 
መኢአድም እንደዚሁ የሚያደጋቸው ይኖራል። በአጭሩ ተከታታይ እንቅስቃሴዎች በሁሉም መስክ ይኖራሉ። 
ሁለተኛ- የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 የሚደረገዉ ሰልፍ፣ ሰማያዊ ፓርቲ ቢጠራዉም፣ የመኢአድ፣ የአንድነት፣ 
የሽግግር ምክር ቤቱ፣ የኢሕአፓ_ዴ፣ የባላራዩ ወጣቶች ማሕበር፣ ሰልፉን የምንደግፍ ዜጎች ሁሉ ሰልፍ ነዉ። 
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰልፍ ነዉ። ሰማያዊ ፓርቲ ለኮሰ። የተለኮሰውን ማቀጣጠል የእያንዳዳችን ነዉ። በድርጅቶች 
የሚጠሩት እንቅስቃሴዎች ዉጤት የሚያመጡት እያንዳንዳችን ስንተባበር ብቻ ነዉ። አገር ቤት ያለነዉ ወደ ሰልፉ 
መሄድ ይጠበቅብናል። ሰልፉ ሰላማዊና በሕግ የተፈቀደ ነዉ። «መብታችን ተረገጠ፣ ድህነት በዛ፣ ዘረኝነት በዛ፣ 
በአገራችን ባርያ ሆንን መኖር መረረን፣ ፍትህ ጎደለ፣ ቀንበርና ግፍ በዛ» የምንል ካለን ፣ እንግዲህ ጊዜው አሁን 
ነዉ። ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንነሳ። እንጩህ። ድምጻችን እንደ ነጎድጓድ ያስተጋባ። አንፍራ። 
በዉጭ አገር ያለነዉ ደግሞ፣ ስልክ እንደዉል፣ ኢሜል እንላክ። ዘመድ ወዳጆቻችንን እናበረታታ። ደብረጺዮን 
የስልክ መስመሩን እና ኢንተርኔቱን ሊዘጋው ይችላል። ግድ ይለም። መስመሮቹን እንዲዘጋ ማስደረጋችን በራሱ 
ትልቅ ድል ነዉ። 
ያኔ ኢትዮጵያም በልጆቿ ትኩራለች ! 

mandag 27. mai 2013

Injustice in Afar Region of Ethiopia is injustice in Germany


Injustice in Afar Region of Ethiopia is injustice in Germany

Afar Human Rights Statement
We learned from reliable sources that the dictator and President of Afar Regional State in Ethiopia, Mr Ismail Ali Sirro is currently visiting Berlin, the capital of Germany.The Core of Human Rights violation Areas in Afar Region of Ethiopia
The Afar people in Ethiopia have suffered a gross human rights violation during Mr Ismail Ali Sirros leadership. The number of people detained without fair trial has dramatically increased the latest years; people have been displaced from their homes and many were killed coldblooded. As highest leader of the Regional State, all crimes and corruption is taking place under President Isamails leadership, hence he is accountable for atrocities and human rights violation committed in Afar Region.
The Afar people whose majority are pastoralists, have been displaced from their land without any alternative for subsistence; they have lost their livestock and are exposed for starvation as a result of land grabbing policy of Mr Ismails leadership. There are documented testimonies that confirm the Mr Ismail personally threatened people to leave their home to facilitate sugar cane commercial farming, where those who refused were shot to death at spot. The order was given by the president of the region. Hence the crime committed by Mr Ismail Ali Sirro and the EPRDF Regime in Ethiopia is defined as crimes against humanity which is in line with the mission of the International Criminal Court.
The rampant corruption taking place in Afar Region has made Mr Ismail and his wife Mrs Fatuma Abdalla from having nothing to multimillionaires in ten years period. Moreover, there is information that the stolen many from starving population has been placed in foreign banks in Europe, North America and Asia.
Afar Human Right Organisation has been systematically following and voicing about the suffering, killings and detention of the voiceless Afar pastoralist. We believe that it’s unacceptable that dictators and murders are allowed to live in luxury in democratic countries like Germany. Therefore injustice in Afar Region should be considered as injustice in Germany and elsewhere. Hence, we appeal to German authorities and justice system to facilitate the handover of the criminals like Mr Ismail to the International Criminal Court.
Copy to:
  • Madame Sabine Leutheusser-Schnarrenberger, German Federal minster of Justice
  • Mr. Judge Sang-Hyun Song, President of the International Criminal Court (ICC)
  • Mrs. Mireille Ballestrazzi, President of INTERPOL
  • Deutsche Welle, Amharic program
  • Voice of America, Amharic program

የአያት ሪል እስቴት ባለቤት የ12 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው


የአያት ሪል እስቴት ባለቤት የ12 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው


ናፍቆት ዮሴፍ
ከሶስት ዓመት በፊት በቫት ማጭበርበር የባንክን ስራ በመስራት፣ ለግለሠቦች በዱቤ ቤት በመሸጥና በበርካታ ወንጀሎች በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ክስ የተመሠረተባቸውና እስካሁንም በእስር ላይ የሚገኙት የአያት አክሲዮን ማህበር መስራችና ባለቤት አቶ አያሌው ተሠማ የ12 ዓመት ፅኑ እስራትና 3.2 ሚሊዮን የገንዘብ ቅጣት ተፈረደባቸው፡፡ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል ችሎት በተጠቀሱት ወንጀሎች ጉዳያቸው ሲታይ የከረሙት 1ኛ ተከሣሽ አያት አክሲዮን ማህበርና ባለቤቱን ጨምሮ በዚሁ መዝገብ ውስጥ የተካተቱ ሌሎች ሁለት ግለሠቦችም ባለፈው ረቡዕ ግንቦት 14 ቀን 2005 በዋለው ችሎት ተፈርዶባቸዋል፡፡
ከአያት አክሲዮን ማህበር ቀጥሎ በሁለተኛነት የተከሠሡትና የማህበሩ መስራች የሆኑት አቶ አያሌው ተሠማ እጃቸው ከተያዘበት ጀምሮ የሚታሠብ የ12 ዓመት ፅኑ እስራትና 3 ሚሊዮን 235ሺህ 543ብር ከሀምሳ ሳንቲም፣ ሶስተኛ ተከሣሽ ዶ/ር መሀሪ መኮንን አካሉ የ12 ዓመት ፅኑ እስራትና 436ሺህ 969 ብር ከ60 ሣንቲም ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን አራተኛው ተከሣሽ አቶ ጌታቸው አጐናፍር ደግሞ የ10 ዓመት ፅኑ እስራትና የ411 ሺህ 969 ብር ከ60 ሳንቲም ቅጣት የተጣለባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

እነዚህ ተከሣሾች በበርካታ ወንጀሎች ተከሠው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን በተወሠኑት ክሶች ነፃ መባላቸውም ታውቋል፡፡ ከትላንት በስቲያ በከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ተከሣሾቹ ጥፋተኛ ከተባሉባቸዉ ጉዳዮች መካከል የባንክና የብድር አዋጅን በመተላለፍ፣ ሠዎች የመኖሪያ ቤት በዱቤ እንዲያገኙ በማድረግና የባንክን ሥራ በመስራት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ከላይ የተገለፀው ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

የጉምሩክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችና ሃላፊዎች በእስር እንዲቆዩ ተወሰነ


የጉምሩክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችና ሃላፊዎች በእስር እንዲቆዩ ተወሰነ

 አለማየሁ አንበሴ
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዋና ቅርንጫፎችን በስራ አስኪያጅነትና በህግ ክፍል ሃላፊነት ሲመሩ የነበሩ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ በዋስ ለመለቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አጣ፡፡ ዋና ዋና የንግድ መተላለፊያ ቅርንጫፎችን ሲመሩ የነበሩ ሁለት ስራ አስኪያጆችና ወንጀለኞችን የመክሰስ ሃላፊነት የተሰጣቸዉ ሁለት የህግ ክፍል ባለስልጣናት እንዲሁም ሌሎች ሃላፊዎችና ሰራተኞች በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት ሰሞኑን ነው፡፡ ገሚሶቹ ከውጭ የመጡ እቃዎች ሳይቀረጡ እንዲገቡ አድርገዋል ተብለው የታሰሩ ሲሆን፤ ገሚሶቹ ደግሞ ቀደም ሲል የተከሰሱ ሰዎችን አላግባብ ከክስ ነፃ እንዲሆኑ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራውን ለማጠናቀቅና በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ ለመመስረት የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት ጠይቆ የሁለት ሳምንት ጊዜ ተሰጥቶታል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ ግን ተቀባይነት ስላላገኘ፣ በእስር እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ በዚህ ሳምንት ታስረው በአዲስ የምርመራ መዝገብ ፍ/ቤት የቀረቡት 11 ተጠርጣሪዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ አቶ አምባውሰገድ አብርሃ፣ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የናዝሬት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የህግ ማስከበር ሃላፊ አቶ ተክለአብ ዘርአብሩክ፣ የሚሌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ያዴሳ ሚደቅሳ፣ የአዳማ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ እሸቱ ግረፍ፣ የሚሌ ቅርንጫፍ የህግ ማስከበር ሃላፊ አቶ ጌታሁን ቱጂ፣ የአዳማ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሃላፊ አቶ መባኩ ግርማ፣ የሞጆ ደረቅ ወደብ ትራንዚት ኤክስፐርት አቶ አስፋው ስዩም፣ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ላጋር ጉምሩክ መቅረጥ አስተባባሪ አቶ ጌታነህ ግደይ፣ የአቃቂ ቃሊቲ የመጋዘን ቡድን ሰራተኛ አቶ ዮሴፍ አዳዩ፣ የአቃቂ ቅርንጫፍ ሰራተኛ አቶ በእግዚያብሄር አለበል፣ የአልትሜት ፕላን የግል ድርጅት ከፍተኛ ባለድርሻና አማካሪ አርክቴክት አቶ ዘለቀ ልየው፣ የበምጫ ትራንዚት ባለቤት ናቸው፡፡

የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው መከራከሪያ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት እስካሁን ያከናወነውን ስራ ዘርዝሯል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ቃላቸውን እንደተቀበለ ኮሚሽኑ ጠቅሶ፣ በበቂ ሁኔታ የሰነድ ማስረጃ ሰብስበናል፣ የምስክሮችን ቃል መቀበል ጀምረናል ብሏል፡፡ ከምርመራው ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ከየመስሪያ ቤቱ እያሰባሰበ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሞ፣ ሰነዶችን ማደራጀትና የአይን እማኞችን ቃል መቀበል እንደጀመረ ገልጿል፡፡ የምርመራ ስራዎች እንደተጠናቀቁና የተጠርጣሪዎቹ ድርጊት በትብብር የተፈፀመ በመሆኑ፣ በርካታ ምርመራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልገው በመዘርዘር፣ ፍርድ ቤቱ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲፈቅድለት ኮሚሽኑ ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ በቂ ማስረጃ መሰብሰቡንና የቀሩትም ቢሆን እነሱ ሊያጠፏቸው የማይችሉ እንደሆነ በማመልከት በዋስ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡ በመስሪያ ቤት ያሉ ሰነዶችን እኔ ላጠፋቸው አልችልም ያሉት አቶ አምባውሰገድ አብርሃ፤ ከዚህ በተጨማሪም የልብ ታማሚ መሆናቸውን በመግለፅ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡ ሁለተኛ ተጠርጣሪም ሰነዶች በሙሉ ተበርብረው መወሰዳቸውን ጠቅሰው፤ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ጠይቀዋል፡፡ ሌሎች ተጠርጣሪዎችም የሰነድም ሆነ ሌሎች ማስረጃዎችን ለመደበቅና ለማሸሽ የሚያስችል ስልጣንና የኢኮኖሚ አቅም እንደሌላቸው ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ አመልክተዋል፡፡ 10ኛ ተከሳሽ አቶ በእግዚያብሄር አለበል፤ ከ60 በላይ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በአማካሪነት እንደሚያከናውኑ ገልፀው፣ ከገቢዎች እና ጉምሩክ መስሪያ ቤት ጋር የሚያገናኘኝ ጉዳይ የለም በማለት፣ ፍርድ ቤቱ የዋስ መብታቸውን ይፈቅድላቸው ዘንድ ጠይቀዋል፡፡

11ኛ ተጠርጣሪ በጠበቃቸው በኩል ባቀረቡት አስተያየት፤ ከተያዙ ስድስት ቀን ቢሆናቸውም ፍርድ ቤት እስከቀረቡበት ቀን ድረስ ቃላቸውን እንዳልሰጡ፣ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር ተያያዥነት የሌላቸው ሰነዶች መወሰዳቸውን እንዲሁም ቢሮአቸው እንደታሸገ እንደሚገኝ በማመልከት፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ተጠርጣሪው በግላቸው ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃልም፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከአንድ ጊዜ በስተቀር አለመገናኘታቸውን የገለፁ ሲሆን በቢሮአቸው የነበረ ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ የተወሰደ በመሆኑ ከተወሰደው ገንዘብ ላይ ለልጃቸው የወተት መግዣ አንድ ሺህ ብር ብቻ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን በበኩሉ፣ ማስረጃዎችን መሰብሰብ ጀምረናል አልን እንጂ በተሟላ መልኩ ሰብስበናል አላልንም፤ ብሏል፡፡

ከወንጀሉ ከባድነት አንፃር፣ ማስረጃዎች ተሰብስበው ካለመጠናቀቃቸው በተጨማሪ ተጠርጣሪዎቹ ሊጠፉ ስለሚችሉ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ መሆን አለበት ብሎ ተከራክሯል፡፡ ፍርድ ቤቱም በሰጠው ትዕዛዝ፤ የምርመራውን ውስብስብ ሂደት በመረዳት የ14 ቀን ቀጠሮ ፈቅዶ፣ ተጠርጣሪዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ከቀረቡበት ቀን ጀምሮ በሚታሠብ ለግንቦት 26 ቀን ቀጠሮ ሠጥቷል፡፡ ተጠርጣሪዎች ከቤተሠቦቻቸውና ከጠበቆቻቸው ጋር የመገናኘት መብት እንዳላቸው ፍ/ቤቱ ጠቅሶ፤ መብታቸው መከበሩን የፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዲከታተል አዟል፡፡

የተጠርጣሪዎች መብትን በሚመለከት ዝርዝር ሪፖርት እንዲቀርብለትም ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ እሽግ ይነሣልኝ የሚለው ጥያቄ አስተዳደራዊ ምላሽ ይሰጥበት ያለው ችሎት፤ ቀለብ ማጣት ስለማይገባ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተነሣው ጥያቄም አስተዳደራዊ ምላሽ እንዲሠጥበትና በቀጣይ ቀጠሮ ሪፖርት እንዲቀርብበት አዟል፡፡ በሌላ በኩል በእነ አቶ መላኩ ፋንታ መዝገብ ስር በ5ኛ ተጠርጣሪ የኬኬ ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ የቀረበውን የቢሮ እሽግ ይነሣልኝ ጥያቄን በተመለከተ፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በእሽጉ ላይ አስተያየቱን እንዲሠጥበት ለግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

torsdag 23. mai 2013

በጎንደር የሁለት ቀበሌ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ


በጎንደር የሁለት ቀበሌ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ኢሳት ዜና:-የቀበሌ 6 እና  7 ወጣቶች ዛሬ ግንቦት14፣ 2005 ዓም ባደረጉት ሰልፍ የመብራት፣ የውሀ፣ የስራ አጥነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አደራጅና የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሀ ወጣቶቹ ብሶታቸውን ለመሳማት ለሰልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል።
በሰልፉ መጨረሻ ላይ አንዳንድ ወጣቶች በፖሊሶች ሲዋከቡ መታየታቸውን በስፍራው የተገኘው ተባባሪ ዘጋቢያችን ገልጿል።

በጎንደር የሁለት ቀበሌ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ


በጎንደር የሁለት ቀበሌ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ኢሳት ዜና:-የቀበሌ 6 እና  7 ወጣቶች ዛሬ ግንቦት14፣ 2005 ዓም ባደረጉት ሰልፍ የመብራት፣ የውሀ፣ የስራ አጥነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አደራጅና የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሀ ወጣቶቹ ብሶታቸውን ለመሳማት ለሰልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል።
በሰልፉ መጨረሻ ላይ አንዳንድ ወጣቶች በፖሊሶች ሲዋከቡ መታየታቸውን በስፍራው የተገኘው ተባባሪ ዘጋቢያችን ገልጿል።

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ታሰረ


የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ታሰረ

ኢሳት ዜና:-የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ግንቦት14፣ 2005  ጧት ላይ በደህንነቶች ተይዞ መወሰዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ሀብታሙ አያሌው ለኢሳት ገልጿል።
ወጣት ብርሀኑ ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መታሰሩን ወጣት ሀብታሙ ገልጿል።
ወጣት ሀብታሙ ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ እስረኛውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 9 ሰአት ላይ የወጣት ብርሀኑ ቤት እየተፈተሸ መሆኑን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጿል።
ምሽት 12 ሰአት ላይ ያነጋገርነው የማህበሩ ቦሌ ክፍለከተማ ምክትል ሀላፊ ወጣት ጥላየ ታረቀኝ እንደገለጸው ደግሞ ከዚህ ቀደም ታስረው በነበረበት ወቅት ሲዝትባቸው የነበረው ሳምሶን የተባለ የደህንነት ሰራተኛ ወጣት ብርሀኑን እንዳስያዘው ገልጿል። የወጣት ብርሀኑ ቤተሰቦች ቤት ሲፈተሽም በአንድ መጽሀፍ ውስጥ ራሳቸው ደህንነቶች ያስገቡትን ጽሁፍ ” ይሀው አገኘነው በማለት” ብርሀኑን እንዲፈርም እንደጠየቁትና ከጠበቃየ ጋር ሳልማከር አልፈርምም እንዳለ ወጣት ጥላየ ተናግሯል።
በጉዳዩ ዙሪያ የጉለሌን ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊዎች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።

በገላሺ ከተማ የኢትዮጵያ ወታደሮች 10 ሰዎችን መግደላቸውን ኦብነግ አስታወቀ


በገላሺ ከተማ የኢትዮጵያ ወታደሮች 10 ሰዎችን መግደላቸውን ኦብነግ አስታወቀ

ኢሳት ዜና:-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ( ኦብነግ) ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ትናንት ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከልዩ ሚሊሺያ ጋር በመተባበር በወሰደው እርምጃ አቶ ማካሊ ሙስጠፋ ሀሰን፣ አቶ ሻፊ አው ካሊፍ፣ አቶ አብዱላሂ አብዲ፣ አቶ ሻኩል አብዲ፣ አቶ  ፋራህ ሙሀመድ፣ አቶ አብዲሀይ ሼክ አህመድኑር እና አቶ አብድራሺ ሻፊቺች የተባሉትን ነዋሪዎች ገድለዋል።
የግድያው ምክንያት በጋላሺ የጦር ምድብ የሚገኙ 70 የልዩ ሚሊሺያ አባላት ከድተው እጃቸውን ለግንባሩ መስጠታቸውን ተከትሎ ፣ ነዋሪዎቹ የጠፉትን ወታደሮች አድራሻ እንዲያወጡ ከተጠየቁ በሁዋላ ነው። ወታደሮቹ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 7 ሰዎችን እጆቻቸውን  ካሰሩ በሁዋላ እንደረሹኑዋቸው፣ 3ቱን ደግሞ ከከተማዋ 3 ማይል ርቅት በሚገኝ ቦታ ላይ እንደገደሉዋቸው ግንባሩ አስታውቋል።
ግንባሩ እንዳለው በዚህ አመት ብቻ ከ300 ያላነሱ የአካባቢው ተወላጆች በመከላከያ ሰራዊት እና በልዩ ፖሊስ አባላት ተገድለዋል። ጉዳዩን በማስመልከት ቃለምልልስ ያደረግንላቸው የግንባሩ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ፣ የከዱት ወታደሮች ግንባሩን መቀላቀላቸው እውነት ቢሆንም፣ የተገደሉት ነዋሪዎች ግን ድርጅቱ አባላት አለመሆናቸውን ገልጸዋል።
የግንባሩ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሀሰን አብዱላሂ በመከከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ሚሊሺያ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

onsdag 22. mai 2013

ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ዙሪያ ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን ወቀሱ


ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ዙሪያ ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን ወቀሱ

ኢሳት ዜና:- ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች  ጋር በተያያዘ ሕገወጥ ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉ 35 ተጠርጣሪዎች ከመንግስታዊ ኃላፊነታቸው መባረራቸውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም አስታወቁ፡፡
ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር የመ/ቤታቸውን የ2005 የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ለፓርላማው ሲያቀርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ3ሺ 248 ያህል የአማራ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት እንደሆኑ የተደረሰባቸው 35 ተጠርጣሪዎች ከያዙት ኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ መደረጉን ፤ከነዚህ ውስጥ በቂ መረጃና ማስረጃ የተገኘባቸው 12 ያህል ተጠርጣሪዎች ላይ በሕግ እንዲጠየቁ ክስ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡
በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም ከቤንሻንጉል ክልላዊ መንግስት ሕገወጥ በሆነ መልኩ ከተፈናቀሉ 3ሺ 248 የአማራ ተወላጆች መካከል 2 ሺ 412 ያህሉ ወደነበሩበት ቀዬ እንዲመለሱ ቀሪዎቹ 836 ያህል ሰዎች ደግሞ ድሮ ወደነበሩበት ቀዬ መመሳቸውን ለፓርላማው ሪፖርት አድርገዋል፡፡
እንደሚኒስትሩ ገለጻ እነዚህን ተፈናቃዮች መልሶ በማቋቋም ሂደት ላይ በክልሉ ከፍተኛ አመራር የሚመራ ቡድን በዞን፣በወረዳ፣በቀበሌ መዋቅር ያሉትን አመራሮችና በየቀበሌው በሚኖሩ ሕዝቦች ድረስ በመውረድ አመለካከት የማስተካከል ስራ እየተሰራ ሲሆን ንብረት የማስመለስ ስራም ተከናውኗል፡፡
በቤንሻንጉል ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ጀምሮ ችግሮች መኖራቸውን ከክልል እስከማዕከል አቤቱታ ሲቀርብ እንደነበረ ያስታወሱት አንድ የፓርላማ አባል ፣ ችግሩ የተከሰተው በመጋቢት ወር ሳይሆን በየካቲት ወር መሆኑን፣ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ ለምን እንዳልተፈታ ጥያቄ አዘል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ችግሩ ሲከሰት የክልሉ መንግስት ብቻም ሳይሆን የፌዴራል መንግስት ያውቃል ብለው እንደሚገምቱና መፍትሄ ለመስጠት ለምን እንደዘገዩ ጠይቀዋል፡፡
ዶ/ር ሽፈራው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት መልስ ሁሉም ነገር ከአንድ ደቂቃ በፊት ሊሰራ እንደሚችል ይታወቃል በማለት በተዘዋዋሪ ችግሩን ለመቅረፍ መዘግየት እንደነበር ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ አይይዘውም የመ/ቤታቸው ተልዕኮ ግጭትን መፍታት ብቻ ሳይሆን አስቀድሞ መከላከል መሆኑን በመጥቀስ መረጃዎች ሲገኙ እንዲህ ዓይነት የመከላከል ስራዎች
እንደሚሰሩ ጠቅሰዋል፡፡
ዶ/ር ሽፈራው የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ጉዳይ በአገር ውስጥም በውጪም ያሉ የትምክህትና የጸረ ሠላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሆኖ መክረሙን በመጥቀስ በእነሱ ምክንያት የወሰድነው ምንም ዓይነት እርምጃ የለም ብለዋል።
እነሱ ነገሩን በማጦዝ “20 ሺ የአማራ ተወላጆች ተፈናቀሉ፣አንድ አይሱዚ ሙሉ ሰው ገደል ገባ” እያሉ አዛኝ መስለው ሲቀሰቅሱበት መክረማቸውን ክፉኛ በማውገዝ እኛ ከሁለቱ ክልሎችና ከሕዝቡ ጋር በመሆን ችግሩን ፈትተነዋል ሲሉ አክለዋል።
ዶ/ር ሺፈራው ይህን ይበሉ እንጅ ተፈናቃዮች ንብረታቸው እንዳልተመለሰላቸው፣ ችግሩም እንዳልተፈታና ግጭት ይፈጠራል ብለው በስጋት ላይ እንዳሉ ኢሳት ባለፈው ሳምንት ተፈናቃዮችን አነጋግሮ መዘገቡ ይታወሳል።

ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ዙሪያ ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን ወቀሱ


ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ዙሪያ ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን ወቀሱ

ኢሳት ዜና:- ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች  ጋር በተያያዘ ሕገወጥ ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉ 35 ተጠርጣሪዎች ከመንግስታዊ ኃላፊነታቸው መባረራቸውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም አስታወቁ፡፡
ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር የመ/ቤታቸውን የ2005 የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ለፓርላማው ሲያቀርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ3ሺ 248 ያህል የአማራ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት እንደሆኑ የተደረሰባቸው 35 ተጠርጣሪዎች ከያዙት ኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ መደረጉን ፤ከነዚህ ውስጥ በቂ መረጃና ማስረጃ የተገኘባቸው 12 ያህል ተጠርጣሪዎች ላይ በሕግ እንዲጠየቁ ክስ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡
በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም ከቤንሻንጉል ክልላዊ መንግስት ሕገወጥ በሆነ መልኩ ከተፈናቀሉ 3ሺ 248 የአማራ ተወላጆች መካከል 2 ሺ 412 ያህሉ ወደነበሩበት ቀዬ እንዲመለሱ ቀሪዎቹ 836 ያህል ሰዎች ደግሞ ድሮ ወደነበሩበት ቀዬ መመሳቸውን ለፓርላማው ሪፖርት አድርገዋል፡፡
እንደሚኒስትሩ ገለጻ እነዚህን ተፈናቃዮች መልሶ በማቋቋም ሂደት ላይ በክልሉ ከፍተኛ አመራር የሚመራ ቡድን በዞን፣በወረዳ፣በቀበሌ መዋቅር ያሉትን አመራሮችና በየቀበሌው በሚኖሩ ሕዝቦች ድረስ በመውረድ አመለካከት የማስተካከል ስራ እየተሰራ ሲሆን ንብረት የማስመለስ ስራም ተከናውኗል፡፡
በቤንሻንጉል ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ጀምሮ ችግሮች መኖራቸውን ከክልል እስከማዕከል አቤቱታ ሲቀርብ እንደነበረ ያስታወሱት አንድ የፓርላማ አባል ፣ ችግሩ የተከሰተው በመጋቢት ወር ሳይሆን በየካቲት ወር መሆኑን፣ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ ለምን እንዳልተፈታ ጥያቄ አዘል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ችግሩ ሲከሰት የክልሉ መንግስት ብቻም ሳይሆን የፌዴራል መንግስት ያውቃል ብለው እንደሚገምቱና መፍትሄ ለመስጠት ለምን እንደዘገዩ ጠይቀዋል፡፡
ዶ/ር ሽፈራው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት መልስ ሁሉም ነገር ከአንድ ደቂቃ በፊት ሊሰራ እንደሚችል ይታወቃል በማለት በተዘዋዋሪ ችግሩን ለመቅረፍ መዘግየት እንደነበር ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ አይይዘውም የመ/ቤታቸው ተልዕኮ ግጭትን መፍታት ብቻ ሳይሆን አስቀድሞ መከላከል መሆኑን በመጥቀስ መረጃዎች ሲገኙ እንዲህ ዓይነት የመከላከል ስራዎች
እንደሚሰሩ ጠቅሰዋል፡፡
ዶ/ር ሽፈራው የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ጉዳይ በአገር ውስጥም በውጪም ያሉ የትምክህትና የጸረ ሠላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሆኖ መክረሙን በመጥቀስ በእነሱ ምክንያት የወሰድነው ምንም ዓይነት እርምጃ የለም ብለዋል።
እነሱ ነገሩን በማጦዝ “20 ሺ የአማራ ተወላጆች ተፈናቀሉ፣አንድ አይሱዚ ሙሉ ሰው ገደል ገባ” እያሉ አዛኝ መስለው ሲቀሰቅሱበት መክረማቸውን ክፉኛ በማውገዝ እኛ ከሁለቱ ክልሎችና ከሕዝቡ ጋር በመሆን ችግሩን ፈትተነዋል ሲሉ አክለዋል።
ዶ/ር ሺፈራው ይህን ይበሉ እንጅ ተፈናቃዮች ንብረታቸው እንዳልተመለሰላቸው፣ ችግሩም እንዳልተፈታና ግጭት ይፈጠራል ብለው በስጋት ላይ እንዳሉ ኢሳት ባለፈው ሳምንት ተፈናቃዮችን አነጋግሮ መዘገቡ ይታወሳል።

በደቡብ ክልል የደረጃ እድገት በኢህአዴግ አባልነት ብቻ እንደሚሰ ተጋለጠ

በደቡብ ክልል የደረጃ እድገት በኢህአዴግ አባልነት ብቻ እንደሚሰ ተጋለጠ 
-----------------------------------------------
በደቡብ ክልል ደራሼ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት የደረጃ ዕድገትም ሆነ ሱፐርቫይዘርነት በሙያ ብቃት ሳይሆን በኢህአዴግ አባልነት መሆኑን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች አጋለጡ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ለሱፐርቫይዘርነት ምደባ በሙያ ብቃት ሳይሆን በኢህአዴግ አባልነት ብቻ እንደሆነ የጠቆሙና እራሳቸውን ከኢህአዴግ አባልነት ያገለሉ ባለሙያዎች ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ እንዲደረጉ በደብዳቤ የተገለፀላቸው እንዳሉ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት የመምህራን ፣ የርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ንጋቱ በበኩላቸው “ማንም ሰው የደረጃ ዕድገትም ሆነ ሱፐርቫይዘርነት በውድድር እንጂ በኢህአዴግ አባልነት የሚል መመሪያም ሆነ የሲቭል ሰርቪስ ህግ የለም፤ አሁን ተፈፅሟል የምትለኝ ከሆነ ስህተተት ነው” ሲሉ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በወረዳው እንዲህ ዓይነት ችግር ከተፈጠረም ቅሬታውን በማቅረብ መፍትሄ እንደሚያገኝ ጠቁመዋል፡፡

ውጤት ተኮር አሞላልን በተመለከተ ቅሬታ ከቀረበባቸው ርዕሳነ መመህራን መካከል በወረዳው የጋሉ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ላገሩ አበበ ወ/አረጋይ “እኔ ውጤት ተኮር ያልሞላሁለት መምህር የለም፣ በስራ ላይ የቀረም ሆነ ቀረ ያልኩት መምህር የለም” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ በተለይ እኚሁ ርዕሰ መምህር የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ያላቸውን መምህራን ፀረ-ልማት፣ ፀረ- ህገመንግስት በማለትና በማስፈራራት በስራ የተገኙ ሰራተኞችን በስራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም በሚል ጫና እንደሚፈጥሩ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ የሰገን ህዝቦች ዞን መምህራን ማኀበር ሰብሳቢ መምህር ስንታየሁ ገ/ፃዲቅ በተለይ የመምህራኑ ቅሬታ ሲቀርብ እስካሁን ትብብር አለማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅናቸው የዞኑ ኢመማ ሰብሳቢ መምህር ስንታየሁ ገ/ፃዲቅ በተለይ ከደራሼ ወረዳ መምህራን ቅሬታ ይዘው የቀረቡት ሁለት ብቻ ሲሆኑ እነሱም መፍትሄ እንዳገኙ በመግለፅ መምህር አሸብር ታደሰ የሚባሉ ግን ምንም ዓይነት ቅሬታ ይዘው ለዞኑ መምህራን ማኀበር ያቀረቡበት ቀን እንደሌለ ምላሽ ከመስጠታቸው በተጨማሪ መምህሩ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ፈፅመዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳው አንድ መምህር ግንቦት 1 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢህአዴግ አባል መምህር የድብደባ ወንጀል ተፈፅሞበት ክስ ሲመሰረት ደኢህዴን/ኢህአዴግ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ማስቻሉም ተጠቁሟል፡፡

tirsdag 21. mai 2013

ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅ


ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅ 
ታይቶ ተሰምቶ አይታውቅ በዓለም እንዲህ ያለ ነገር 
ከመቃብር ሆኖ ሰው ሲመራ ሀገር 
በአሁን ጊዜ ታየ በኢትዮጵያ ምድር። 
ምን ነካህ ወገኔ አማራ ኦሮሞው 
እስላም ክርስቲያኑ ሐረሬ ሲዳማው 
ጉራጌ ከንባታ አፋሩ ጋንቤላው 
እንዴት ትገዛለህ በሞተ በድን ሰው። 
ያስጠይቅሃል ያስጠይቅሃል በፈጠረህ አምላክ 
ይቆጠርብሃል ይቆጠርብሃል ጣዖት እንዳመለክ 
በድን በሆነ ሰው በሞተ ስታመልክ። 
መራብ መጠማት የሰው እጅ ማየትም 
ከሀገር ተሰዶ መከራተት በዓለም 
መከራ ችግሩ ከአንተ አይላቀቅህም። 
እምብኝ ለእምነቴ ብለህ ካልተነሳህ 
እምብኝ ለነጻነት ብለህ አሻፈረኝ ካላልህ 
ሁልህም በአንድነት በአደባባይ ወጥተህ 
መብቴ ይከበር ብለህ ካልተናገርህ ካልተናገርህ ካልተናገርህ 
ሁሌ በሙገጫ እንደ እህል ሲወግጥህ 
ይኖራል ወያኔ እረግጦ ሲገዛህ። 
አንድነትን ንዶ በብሄር ከፋፍሎህ 
ያልነበረ ታሪክ እሱ ታሪክ ሰጥቶህ፤ 
ወርዶአል ወደ መቃብር ፎቶውን ትቶልህ 
በሱ እንድታመልክ እንድታመልክ እንድታመልክ ፈጣሪህን ትተህ። 
ይህንም ሳያደርግ ጭፍራው አይለቅህም፤ 
ካልተባበርክበት ካልተባበርክበት ተሎ በአንድነት ሁልህም፤ 
እጅ ለእጅ ተያይዘህ በፍቅር በሰላም። በቋንቋ በብሄር እንዲሁም በሃይማኖት 
ጣልቃ ያልገባ የአመነ በአንድነት 
እውነተኛ መሪ የድኀዎች አባት 
ሌባና ቀጣፊን የአጠፋ መሳፍንት 
አንድ ጀግና ነበር የቋራ ባለ አባት። 
 ምን አለ ቢመጣ እሱን የመሰለ 
ድኀም በአለፈለት ቀመኛ ቀጣፊም እጁ በሰለለ 
ሀገር አማን ሆኖ ሰው በሰላም በአደረ በዋለ። 
የዘር ልክፍት ይዞት በቋንቋ የሚያምን 
የውሸት ቆብ ጭኖ የሚያደናግር የሚያደናግር የሚያደናግር ሕዝብን 
አሁን ባየህልን አስመሳዩን ካህን 
ትገርፈው ነበረ አስወልቀህ ቆቡን። 
ታሪክና ሃይማኖት ሁሉንም አጥፍተህ 
የእግዚአብሔርን የእግዚአብሔርን ቃል ወንጌልን አቃጥለህ 
ከላይ እሳት፣ ወርዶ አመድ ዶግ ያድርግህ 
ወያኔ የሚሉህ ቡድን ከትግራይ የበቀልህ። 
ትግሬም አታመልጥ ከተጠያቂነት ከተጠያቂነት ከተጠያቂነት 
አጥፍተሃል ኢትዮጵያን ዘምተህ በአንድነት 
አስጨፍጭፈሃል አስጨፍጭፈሃል ሕዝቧን ለሃያ ሁለት ዓመት 
አዝለህ ያመጣህው ከትግራይ በረሃ ከዚያ ከደደቢት። 
            (ተስፋሁን ሞላ)

እናንት ወያኔዎች በጐጥ ያበዳቹህ፤


እናንት ወያኔዎች በጐጥ ያበዳቹህ፤
ዓርባ ዓመት የማይሽር የዘር ልክፍታቹህ፤
አጥንት የምትሰብሩ ደም ሥጋ ጠልቃቹህ፤
ስትወጉት ስትሰቅሉት ከአገሩ አሳዳቹህ፤
ታግሶ፤ ተማጽኖ ከጸብ ቢሸሻቹህ፤
የጥፋት ሰራዊት ባቢሎን ቀጥራቹህ፤
እንደ እባብ እራሱን አስቀጠቀጣቹህ፤
የሞት መቀጣጫ ዒላማ አድርጋቹህ፤
ዘር ፍጅት ዘመቻ በአማራ አውጃቹህ፤
ሞት በተገኘበት በአደን መንጥራቹህ፤
በአራቱም ማዕዘን አስጨፈጨፋቹህ፤
እናንት ጥቁር አይሁድ ትግሬም አይደላቹህ። 
እምነት ኃይማኖቱን ክብሩን አርክሳቹህ፤
የኤይድስ ደዌ በመርፌ ከትባቹህ፤
ትውልድ በሚሊዮን ዘር ያስጨረሳቹህ፤
በሃያ ዓመት በትር አላልቅ ቢላቹህ፤
በርሃብ ልትፈጁት ሜዳ በትናቹህ፤
ከቀየው ማሳደድ ሆኗል ዘመቻቹህ፤
ቤት ትዳሩን ማፍረስ በሞት ሽረታቹህ፤
ኦጋዴን፤ ማጆ ዞን፤ ቤሻንጉል አዛቹህ፤
በአገር በመዲናው ቤቱን አፍርሳቹህ፤
ሦስት ትውልድ አማራ ሜዳ በትናቹህ፤
ቀነኞች በምቾት እንቅልፍ ወሰዳቹህ፤
እናንት ጥቁር አይሁድ ትግሬም አይደላቹህ።
የጊዜ ሎተሪ ቀን በለስ ሰጥቷቹህ፤
በመስተዋት ቪላ ከፎቅ ከትማቹህ፤
ዘር ማንዝር መሰላል ሰገነት ወጥታቹህ፤
በሚሎዮን ሲቃ ድሎት ሸምታቹህ፤
በጥጋብ ዳንኪራ ባጥ የረገጣቹህ፤
መሰረት ግድግዳ አጥር አፍርሳቹህ፤
አገር ሕዝብ ሃይማኖት ታሪክ አጥፍታቹህ፤
በመሸበት ዘመን ቆጥ ሙጥኝ ብላቹህ፤
መበቃቀያችን ዋሻ አፈር ምሳቹህ፤
እንድንቀባበር ትገፉናችላቹህ፤
ቀን በሰቀላቹህ አንወርድም መስሏቹህ፤
ጽዋቹህ ተሞልቷል እንደየስፍራቹህ፤
እናንት ጥቁር አይሁድ ነግቷል ወዮላቹህ፤
ዛሬ ምሕረት ሻቱ ስለ አምላክ ብላቹህ። 

በኢትዮጵያ አራቱ ማዕዘን እየተሳደዱ የድረሱልንና የስቃይ ጥሪያቸውን 
እያሰሙ ለሚገኙት አማራ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ድጋፍ፤ አጋርነትና 
የትግል ጥሪ ትሁንልኝ። 

የጐንቻው! yegonchaw@yahoo.co.uk 

አዘነ አሉ ጎጃም የበላይ አገር


አዘነ አሉ ጎጃም የበላይ አገር፤
ማቅ ጥለቱን ለብሶ እርቃኑን በክር፤
ዙፋን ሲጎናጠፍ ጐጠኛው ሲከብር፤
እራፊ አደሩበት በዘር መደውር፤
‘እንደ ማሪያም ጠላት’ ተባሮ እንዲኖር፤
ጐጆው እንዳይጠና ተሳዶ በዙር፤
በእምነቱ እዳ ከፋይ ለአገሩ ድንበር፤
አርባ ተገረፈ በክህደት መንደር፤
በደሙ በአጥንቱ በዘሩ በትር፤
ማዕት አወርዱበት ሰው እንዳልነበር፤
በቆዳው አለንጋ በዓይኖቹ ስንጥር፤
ገርፈው ያጠቁታል ታግሶ ቢያድር፤
የቀን በለሶኞች ሊያክስሙት ከምድር፤
ሃያ ዓመት ሲወጉት እትብት አምካኝ ዘር፤
ዳግም በላይ ላይዘልቅ ከትበው ነፍሰ ጡር፤
አድባሩን አርክሰው በወንድ ደንገጡር፤
ሺህ ጭንጋፍ አንጋግተው ሆዳም ከርስ ጉጥር፤
አልወለድ ብሎ አንድ በላይ ለአሳር፤
ጎጃም አዘነ አሉ ማህጸን ሲቀብር። 
ጥምጥም ትጥቁን ፈቶ ሌጣውን ሲያድር፤
በጨለማ ሲጋዝ በቀን ሲደፈር፤
ዋስ የለው ጠበቃ እድሜ ልክ አሳር፤
የፊታውራሪ አበሻ የመጃሌ አድባር፤
ካባ ሸማ ልብሱ የክት የሐገር፤
በርኖሱን ማን ለካው? የነጩን ግብር፤
ለሰንደቁ ሙቶ በአጥሙ አጥሮ ድንበር፤
እንቅልፍ ሰላም ነሱት የጓዳ አይጦች ሸር፤
የተዳፈነ እሳት ከእምድጃው ሳይጭር፤
ይዞታው ቢቆጨው የቤቱ አባወራ ምሰሶው ማገር፤
አዳራሹን ለቆ ውጭ በረንዳ ቁር፤
ተፈራረቁበት ውግዘትና ስደት ጥቃት ቸነፈር፤
አዘነ አሉ ጎጃም ማቅ ለብሶ ጥላሸት የኮስትር አገር። 
በሸብል በረንታ በእነማይ ምድር፤
አጥሙ መሬት ሲያርድ የሺፈራው ጦር፤
ሙሉ ጎጃም ቢያንጥ ጋራው ሸንተረር፤
አረንዛው ዳሞቴ ፋኖው አቸፈር፤
እነብሴና እነሴ ቢቸና ሳር ምድር፤ማርቆስ አገው ምድር፤
እንኳንስ ለጓዳ ግድግዳ እሚቆሙ ለኢትዮጵያ አጥር፤
ዛሬ ግን ተጋዙ የፍጥኝ ተሳስረው በእፉኝት መንደር፤
ቢያጠቃም ቢያጠቁት ኪሳራው ለአገር፤
ቆርጠው በማይጥሉት የእጅ ቁስል ኪንታር፤
ሕመም የውስጥ ደዌ አንጀት አሳርር፤
የትውልድ ጸብ ቁርሾ መርገምት ውል እድር፤
ሰብዕን የሚያመክን አረማሞ ዘር፤
አድዋው ገኖበት ሰብል አብቃዩ አፈር፤
ሳማ አረም ቢወረው የጀግኖች መቃብር፤
አዘነ አሉ ጎጃም አልቦው ባለአገር። ፈርዶበት ወያኔ ግዞት ቁም አሳር፤
ቁልቋል እያስወጋው በዘር እሾህ አጥር፤
የአማራ ደም አጥንት እሚያብጠረጥር፤
ከእርስቱ ከቤቱ ከአገሩ እንዳይኖር፤
ሃያ ዓመት ሲያስግዘው አዋክቦ በጦር፤
ባንዳ የባንዳ ልጅ የፋሽስት አሽከር፤
ዜጋ እያሳደደ ባዕዳንን ሲያከብር፤
ኩርማን አያጋራም እሸት አያዞር፤
ከጣሊያን መስጥሮ ወንዛችን ቢያቁር፤
አርቆ መቀመቅ ጦስ እሚቆፍር፤
አባይን አስግሮ ጊዮንን ሊቀብር፡፡ 
ንገረው ለጐንደር ለቴዎድሮስ ልጅ፤
ተነስ ታጠቅ በለው ሃዝን ለቅሶ አይበጅ፤
የክፉ ቀን ደራሽ ደመላሽ ነው እንጅ፤
ለወሎም ላኩበት ደሴ ወራይሉ ከሚሴ መሽጉ፤
የባንዳን መሹለኪያ በራበሩን ዝጉ፤
ሸዋ መሃል አገር አዲስ አቦች ንቁ፤
ወያኔው እንዲያዝ ከነቀለብ ስንቁ፤
ሐረር ሃዲድ ዝጋ አፋር ጀግናው ውጣ፤
ወለጋና ከፋ ግስግሶ እስኪመጣ፤
ደቡብም በመላው ፈጥነህ ድረስ ቶሎ፤
ትግራይ ሸክሙን ያውርድ እርሙን ተገላግሎ፤
ለወገኑ እንዲደርስ በአንድነት ሆ! ብሎ፤
ኢትዮጵያዊ ያብር መሃል - ዳር ወጥሮ፤
ነፃነት ይቀዳጅ በትግል ተባብሮ፤
አንድ ቤት! አንድ ሃገር! ኢትዮጵያ ዘንድሮ፤
ጎጃም አዝኖ አይቀርም ይነሳል ፎክሮ። 

የጐንቻው! yegonchaw@yahoo.co.uk

እየተስተዋለ


እየተስተዋለ

ላለፉት 22 ዓመታት በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ሀገራችን በጉልበት መመራት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ
በህዝባችንና በሀገራችን ላይ በመፈጸም ላይ የሚገኘው እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ሁኔታዎች ተባብሰው
ይገኛሉ።

ይህ የወንበዴ ስብስብ ይህን ሁሉ ግፍ እየፈጸመ የሚገኘው በሀገራችን ውስጥ ምንም ዓይነት ነጻ የፍትህና
የነጻ ፕሬስ ተቋማት እንዳይኖሩ በማድረጉ ነው።የህዝባችን መብት መረገጥ፣የሀገራችን ህልውና እጅግ
ያሳሰባችው ቆራጥና ደፋር ጥቂት ኢትዮጵያውያን ይህን ዘረኛ የወንበዴ መንግስት ፊት ለፊት በመጋፈጥ
ታግለዋል፣ህዝቡን በማስተባበር ሥርዓቱን ለመጣል ሞክረዋል፣ለዓለም ህብረተሰብ በኢትዮጵያ ህዝብ
ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለማስረዳት ጥረዋል።ይህን በማድረጋቸው በገዢው የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን
መታሰር፣መደብደብ፣የአካል መጉደል፣መሰደድና መገደል ደርሶባቸዋል።በተለይም ዛሬ በሀገራችን ውስጥ
በነጻነት ተምሮ ሰርቶ መኖር የማይቻልባት ሀገር በመሆንዋ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ወገኖቻችን ጨምሮ
ህዝባችን በብዛት እየተሰደደና ሀገሩን እየተወ በመሸሽ ላይ ይገኛል።
የሀገራችን ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሉዓላዊነትዋ አሳሳቢ ደረጃ ደርስዋል።በውጭ ወራሪዎች እስከ
21ኛው ክፍለ ዘመን ያልተደፈረችው ሐገራችን የናት ጡት ነካሽ በሆኑ የማሕጸነ መርገምት ልጆችዋ
በውጭ ሐይል እርዳታ በተደራጀ ተገንጣይና አስገንጣይ ቡድን በግልጽ ለጨረታ ቀርባ እየተቸበቸበች
ትገኛለች።ይህን ድርጊት ተባብረን ካላቆምነው አባቶቻችን ድማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው
በነጻነት ሐገራችንን ጠብቀው ለኛ ያስተላለፉልንን አደራ እኛም ለተተኪው ትውልድ ሣናስተላልፍ ብንቀር
ታሪክ ተጠያቂና ተወቃሽ ከመሆን አንድንም።
ይህ ስርዓት ላለፉት 22 ዓመታት ያለ ምንም ተቀናቃኝ በሥልጣን ላይ የቆየው በሱ ጥንካሬና ሀይል
ሳይሆን በኛ ያለመተባበር፣ከሁሉም በላይ በፍርሀት፣በሽሽት፣በልዩነትና ሀላፊነትን ለመወጣት
መስዋዕትነትን ለመክፈል በመፍራታችን ጭምር ነው።ካለፉት ህዝባዊ እምቢተኝነትና በዘረኝነት
ላለመገዛት ህዝብ የወሰደውን የጋራ ትግል ስሜት ትግሉን በሚመሩት አካሎች ቆራጥ አመራር ለመስጠት
አለመቻል፣መስዋዕትነትን በመፍራታቸው ምክንያት አሸናፊ ለመሆን አልቻልንም።
በሀገራችን ውስጥ በየክፍለ ሀገሩ፣በየቀበሌው እየደረሰ ያለው በደል መጠኑ ይለያይ እንጂ በሁሉም
የሀገራችን ክፍል ተመሳሳይ ነው። በየዕለቱ ከሐገር ቤት የምንሰማው ዜና ሁሉ እጅግ አሳዛኝና የወገን ያለህ
የሚያሰኝ ሁንዋል።ገዢው የወያኔ ሐይል ይህንን ሁሉ በደል በሕዝባችን ላይ የሚፈጽመው ባለው
መሳሪያ፣መረጃና ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የህዝብን ሚድያ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩና በነጻው ፕሬስ ላይም
እገዳ በማድረግ ሕዝባችን ምንም ዓይነት መረጃ እንዳያገኝ በመዝጋቱ ነው።
በውጭ ሐገር በስደት የሚኖሩ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የሐገራቸውን ህልውና ለመታደግና የሕዝቡን
ጭቆና ለማስወገድ በድርጅት፣በቡድንና በግል ጭምር ብዙ እየጣሩ ይገኛሉ።በተለይም ሕዝቡ ትክክለኛ
መረጃ እንዲያገኝ ወደ ሐገር ቤት የሚተላለፍ የሬድዮ አገልግሎት ለመስጠት ሲሞክሩ ረጂም ጊዜ
አሳልፈዋል።ብዙዎቹ ሬድዮኖች ተጠናክረው መቀጠል ባይችሉም ጥቂቶቹ አሁንም እየሞክሩ
ይገኛሉ።እስካሁን ያደረጉት አስተዋጽኦ ቀላል ባለመሆኑ ሊደገፉና ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።በቅርቡ ደግሞ በእድሜ ለጋ የሆነው ኢሳት የቴሌቪዥንና የሬድዮ አገልግሎት ወደ ሐገር ቤት እየሰጠ
ይገኛል።ይህ ድርጅት ወደ ሐገር ቤት በተለያዩ መንገድ ለሕዝብ የተጣራ መረጃ በማቀበል በኩል እያደረገ
ያለውና በየሰዓቱ ሐገር ውስጥ የሚደረገውን ድርጊት ውጭ የምንገኘው ኢትዮጵያውያን እንድናውቅ
የሚደረገው ጥረት ብዙ አድማጭና ተመልካች እንዲኖረው ከማስቻሉም በላይ ድጋፋችንን እንድንሰጠው
አድርጎናል።
ይህ ለጋ ድርጅት እስካሁን በሚሰራው እሰይ እደግ ተመንደግ አስብሎታል።በዚህ ሥራ ላይ
እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውንም እየሰጡ ኢሳት እንዲጠናከር ለሚያደርጉት
ኢትዮጵያውያን በግሌ አክብሮትና ምስጋና አቀርባለሁ።
ድርጅቱ ገና ወጣት ተቋም በመሆኑ በስራው ሂደት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚደረጉ ጥቃቅን
ስህተቶች እንደሚኖሩ ብገምትም አንዳንዶቹ ግን ሀገርም ሆነ ህዝብ የማይጠቅሙ ከመሆናቸው በላይ
በኢሳት ደጋፊዎች ላይ እምነትን የሚያሳጡ እንዳይሆኑ እሰጋለሁ።
ከነዚህም ውስጥ ቢያንስ ሁለቱን ለመጥቀስ እወዳለሁ።
፩ኛ። ካሁን በፊት በዜና ከተላለፈው ውስጥ አክራሪና ተገንጣይ የፖለቲካ አቋም ለመተግበር ሲል
ሀገራችንንና ህዝባችንን ሲጎዳ የነበረው በተለይ በሀረር ጋራ ሙለታና አካባቢው ንጹሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ
ጭፍጨፋ ያደረገውን የእስላሚክ ኦሮሚያ መሪ ጃራ አባ ገዳን የኦሮሞ ሌጀንድ የሆኑት አረፉ ሲል በእሳት
ቲቪ ያቀረበውን ዜና ስሰማ እኔን ያሳዘነኝን ያህል ብዙ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኖቸዋል ብዬ እገምታለሁ።
እኔም እንደ ኢሳት የሆላንድ ድጋፍ ሰጭ አባልነቴ ለኢዲቶሪያል ቦርዱ ቅሬታየን በወቅቱ በኢ፡ሜይል
አሳውቄለሁ።
፪ኛ ሜይ 13 ቀን 2013 በተላለፈው እንወያይ ፕሮግራም በጋዜጠኛ ደረጀ ሀ/ወልድ፣ፋሲል የኔዓለምና
አፈወርቅ አግደው የተካሄደው ውይይት ርዕስና በውይይቱም ሂደት የተንጸባረቀው ሀሳብ ፍጹም ግራ
የሚያጋባ ሁኖ አግኝቼዋለሁ። ምክንያቱም የውይይቱም ርዕስ እንደሚያስረዳው በሀገር ቤት ውስጥ
በሰላማዊ ትግል ለመታገል በህጋዊነት ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ በ50ኛው
የአፍሪካ ህብረት በዓል ላይ የአ.አ ህዝብ ጥቁር በመልበስ በገዢው ፓርቲ (ወያኔ) በህዝብና በሀገራችን ላይ
እየደረሰ ያለውን በደል በመቃወም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በመመርኮዝ ነበር።በተደረገው ውይይት
የተጠራው ሰልፍ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት፣የተመረጠው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ከሰላማዊ ሰልፉ ማን
ሊጠቀም ይችላል? በሚል አብዛኛው በአፍራሽ እይታ የተሞላ ውይይት ነበር።ለመሆኑ የሁላችንም
ፍላጎት የሆነውና ይህንን ሥርዓት ለመጣል በሀገር ቤት ውስጥ መሰረት ያደረገ ህዝባዊ ትግል መኖር
ለትግሉ አስፈላጊ መሆኑ እየታወቀ ሀገር ውስጥ ያለውን መነሳሳት የሚያኮላሽና ሰልፍ እንዳይወጣ
ጥርጣሬን የሚያጎላ ውይይት ጠቀሜታው ለማነው? የጋዜጠኝነት ሙያ ባይኖረኝም የቅድመ ትንበያው
አተናተናዊ ሁኔታ ሰልፍ አትውጡ የሚል አንድምታ ያለው መልክት ለማስተላለፍ የተፈለግ
አስመስሎታል።ይህ ሁኔታ ራሱን የህዝብ አይንና ጆሮ ለማድረግ ከሚሰራ ተቋም የማይጠበቅ ማስተዋል
የጎደለው ዝግጅት ሁኖ አግኝቼዋለሁ።
በተለይ እንደ ኢሳት አይነት አማራጭ የሌለውና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ህዝብ በከፍተኛ ትኩረት
የሚከታተለው የመረጃ ተቋም ላይ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች በሙሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው
ይገባል። አስገራሚው ደግሞ ጋዜጠኛ ፋሲል፣ አፈወርቅና ደረጀ ያደረጉት ውይይት እኛን እንጂ
ኢሳትን አይወክልም ሲሉ ይሰማሉ።ግን ማወቅ ያለባቸው እነሱ የኢሳት ባልደረቦችና የሙያ
ተጠያቂዎች መሆናቸውን ጭምር ግንዛቤ ውስጥ አለማስገባታቸውና ኢሳትንም ተጠያቂ የሚያደርገው
መሆኑን አለመረዳታቸው ነው።ለግንዛቤ እንዲረዳ አንድ የቆየ በBBC የተላለፈ ዜና ትዝ አለኝ።በቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያው አካባቢ
ዓለም ላይ ከፍተኛ ሥጋት ጥሎ የነበረው የኑክሊየር ፍጥጫ አስመልክቶ በመግቢያ ዜና ላይ
ሰበር/Breaking news/ በሚል ዜና መሀል አንባቢው አዝናለሁ የእንግሊዝ ህዝብ በማለት ከሩሲያ
የተተኮሱ የኑክሊየር ሚሳይሎች ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ ለንደን ይደርሳሉ ብሎ በማስተላለፉ በእንግሊዝ
ህዝብ ላይ ምን ያህል መደናገጥ አስከትሎ እንደነበረና ጥቂት ቆይቶ ዛሬ እኮ April the fool ነው
በማለት እየሳቀ መናገሩ ብዙ ሰው ያስቆጣ ነበረ። ዜናውን ያነበበው ጋዜጠኛና ፕሮግራሙን ያዘጋጀው
ሀላፊ ከሥራ ከመወገዳቸውም በላይ በህግ ተጠያቂ ሁነዋል።
ለማጠቃለል ያህል በዚህ ምክንያት በሚድያ የሚቀርቡ ነገሮች በሙሉ ህዝብ እውነት ናቸው ብሎ
ስለሚያምን በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል።ይህንን ጽሁፍ በምጽፍበት ሰዓት የኢሳት ጠንካራ ሥራዎች
እንዲጎለብቱ ድክመቶች ደግሞ ሊታረሙ ይገባቸዋል ብዬ ስለማምን ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
ወንድስን ገ/ህይወት (ቪ.ሚ)

በደሴ ዙሪያ አንድ ህዝብን ያሰቃያል የተባለ ሹም ተገደለ


በደሴ ዙሪያ አንድ ህዝብን ያሰቃያል የተባለ ሹም ተገደለ

ኢሳት ዜና:-ግንቦት6 ቀን 2005 ዓም ከቀኑ ስድስት ሰአት ላይ ሙሀመድ የሱፍ የተባለ የደሴ ከተማ ቀበሌ 12 ነዋሪ የ ቀበሌያቸውን የመሬት አስተዳደር ሹም አቶ አህመድ እንድሪስን በ2 ጥይቶች በመግደል ማምለጡ ታውቋል።
ገዳይ አቶ ሙሀመድ የጦር መሳሪያ ከሌላ ታጣቂ ላይ በመቀማት ነው የቀበሌ ሹሙን ገድለው የተሰወሩት። ሟቹ ባለስልጣን የአካባቢውን አርሶአደሮች መሬት በመቀማት፣ ማዳበሪያ በግድ እንዲወስዱ በማስደረግ እንዲሁም ጉቦ በማስከፈል ከፍተኛ በደል ሲፈጽም እንደነበር ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ገዳይ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ድርጊቱ ሲፈጽም የነበረ አንድ ግለሰብ ለኢሳት ገልጿል። ገዳይ ከሟች ጋር ምንም አይነት የግል ጸብ ያልነበራቸው ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመው የህዝቡን ስቃይ ተመልክቶ መሆኑን እኝሁ ግለሰብ አክለው ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የደሴን ፖሊስ ጽህፈት ቤት ባለስልጣናት ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ ሰዎች በግፍ እየታሰሩ ነው


በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ ሰዎች በግፍ እየታሰሩ ነው

ኢሳት ዜና:-ፍኖተ ነጻነት እንደዘገበው ሚያዚያ 18 ቀን 2005ዓ.ም. በሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል አቶ አንሙት እና አቶ መንግስት በቀለ የተባሉ ወጣቶች በሌሊት በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል።
ግንቦት 3 ቀን 2005ዓ.ም. ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት መኮንን     አድማስ በሚባል የፀጥታ ኃላፊ እና ወ/ሮ አሰለፈ ከበደ በሚባሉ የወረዳው ካቢኔ በመራዊ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን ወ/ሮ ሙሉ ሲሳይን በሁለት ተሸከርካሪዎች በሄዱ የፀጥታ ኃይሎች አሽባሪ ነሽ፣ የደበቅሽውን ቦምብ አምጭ በሚል ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመውባት ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዷት ጋዜጣው ዘግቧል።
በመራዊ ከተማ ከግንቦት7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አንድ ግለሰብም እጅ አልሰጠም በማለት መሸፈታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ኢሕአዴግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሪዎችን እየመለመ ነው


ኢሕአዴግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሪዎችን እየመለመ ነው

ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው ምልመላውን እያከናወኑ ያሉት የሥልጣን ዘመናቸው በቅርቡ የሚያበቃው ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና ምክትላቸው አቶ አባተ ስጦታው፣ የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃንና ምክትላቸው አቶ ጀማል ረዲ ናቸው፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሩ  ድሪባ ኩማ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ  መኩሪያ ኃይሌ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ  ሲራጅ ፈርጌሳ፣ የፌዴራል ፖሊስ ጄነራል ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ተመራጮች ወደ ከተማው ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጋዜጣው ዘግቧል።
ወ/ሮ አዜብ በቅርቡ ቅዳሜና እሑድ ፒያሳ የሚገኘውን ማዘጋጃ ቤትና የከተማው አስተዳደር ያሠራውን የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከልን መጎብኘታቸውን ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በእስካሁኑ ሒደት የከተማው ቀጣዩ ከንቲባ ማነው የሚለው ጥያቄ ምላሽ ባያገኝም፣ ውስጥ አዋቂ ምንጮች አቶ ድሪባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ኢህአዴግ የአዲስ አበባን የምክር ቤት ወንበር ያለ ተፎካካሪ ሙሉ በሙሉ ማሸነፉ ይታወሳል።

በአትዮጵያ የሚታየው የሀኪሞች እጥረት እየጨመረ ነው


በአትዮጵያ የሚታየው የሀኪሞች እጥረት እየጨመረ ነው

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጽያ ሐኪሞችን የማሰልጠኑ ስራ ከታሰበው ግብ አኳያ አፈጻጸሙ ደካማና አሁንም የባለሙያ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ እየታየ መሆኑን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ አመለከተ፡፡
በጤና ዘርፍ ከሰው ኃይል አኳያ ከፍተኛ እጥረት እየታየ ያለው በሐኪሞች፣በአዋላጅ ነርሶች እና በሰመመን ሰጪ ነርሶች ደረጃ ያለው ነው ያለው ሰነዱ ባለፉት ጊዜያት በመደበኛ ፕሮግራም ሐኪሞችን ለማሰልጠን የሚወስደው ጊዜ ረጅም ከመሆኑና ሥልጠናውን የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥርም አነስተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሀገሪቱ ማሰልጠን የቻለችው የሐኪሞች ቁጥር በጣም አነስተኛ እንደነበርና ያሉትም ባለሙያዎች ቢሆኑ የተሻለ ጥቅማጥቅም ፍለጋ ሃገር ጥለው የሚሰደዱ በመሆናቸው ችግሩን መቅረፍ ሳይቻል መቆየቱን ያትታል፡፡
በመሆኑም አንድ ሐኪም ለ10ሺ ህዝብ ጥመርታ ለማድረስ ቢታቀድም በአሁኑ ወቅት ግን አንድ ሐኪም ለ30 ሺ158 ሕዝብ ጥምርታ ሆኗል፡፡
ይህ ከስታንዳርዱ በታች የሆነ አፈጻጸም ለማስተካከል አዲስ ስርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት በጠቅላላው በ27 አዲስና ነባር ዩኒቨርሲቲዎች ከ9 ሺ በላይ ሐኪሞች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ሰነዱ ያብራራል፡፡
የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ በወሊድ ወቅት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመቆጣጠር በመካከለኛ ደረጃ ባሉ የጤና ባለሙያዎች ለማሟላት የጤና መኮንኖችን በተቀናጀ የድንገተኛ የማህጸንና ጽንስ ቀዶ ህክምና አሰልጥኖ በማሰማራት ክፍተቱን ለመሙላት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡
እስካሁን 43 ባለሙያዎች ስልጠና መከታተላቸውን በአሁኑ ወቅትም 489 ያህሉ በስልጠና ላይ ናቸው ብሏል፡፡
የድንገተኛ ሕክምና በተሟላ መልኩ ለማቅረብ ቁልፍ ሚና የቡድኑ አካል የሆኑት የሰመመን ሰጪ ነርሶች መሆናቸውን ያስታወሰው ሰነዱ የእነዚህን ባለሙያዎች ተደራሽነት ለማስፋት በአሁኑ ሰዓት በስምንት የጦና ኮሌጆች 158 ባለሙያዎች በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ ሲል ያትታል፡፡
በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ ያለውን የባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ በብቃት በሰለጠነ የሰው ኃይልና ቁሳቁስ ባልተደራጁት፣እምብዛም ልምድና ክህሎት በሌላቸው አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች በገፍ ማሰልጠን መጀመሩና መንግስትም ይህንን በከፍተኛ ደረጃ ማበረታታቱ በዘርፉ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ቀጣይነት ባለው መልኩ በመጉዳት መዳን የሚችሉ ወገኖች ጥራት ባለው የሕክምና እጦት ምክንያት ሊሞቱ ይችላል በሚሉ ተቆርቋሪ ወገኖች ከፍተኛ ትችት እየደረሰበት ይገኛል፡፡
በርካታ ሀኪሞች ከአስተዳደር በደልና ከክፍያ ማነስ የተነሳ ስራቸውን እየለቀቁ ወደ ውጭ እንደሚሄዱ ይታወቃል።

በጣና ሀይቅ ላይ አንድ ጀልባ ሰጥሞ ከ10 ያላነሱ ሰዎች ሞቱ


በጣና ሀይቅ ላይ አንድ ጀልባ ሰጥሞ ከ10 ያላነሱ ሰዎች ሞቱ

ኢሳት ዜና:-በጣና ሃይቅ ላይ ከ 100 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ ፋሲለደስ እየተባለ የሚጠራው ጀልባ በማእበል ተመቶ በመስጠሙ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ  ከ10 ያላነሱ  ሰዎች መሞታቸን ለማወቅ ተችሎአል። 
የአደጋው መንስኤም ከባድ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተ ማእበል መሆኑን ነው አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የድርጅቱ ሰራተ ለኢሳት የገለጹት ። ይሁን እንጀ ኢሳት ትክክለኛውን ምክንያት ለማጣራት ሙከራ እያደረገ ነው። በባህርዳር ከተማ ዝናብ አለመዝነቡን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያሳያል
አደጋው የደረሰው አመታዊ የክርስቶስ ሰምራን የንግስ በዐዓል አክብረው ከደልጊ ወደ ባህርዳር በማምራት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ነው።
በባህርዳር ከተማ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ አደጋ ሲደርስ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ከወዲሁ ያስመዘገባቸው ድሎች


የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ከወዲሁ ያስመዘገባቸው ድሎች 

ግርማ ካሳ

አገር ዉስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም፣ በአፍሪካ ሕብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አውጇል። ከግንቦት 15 እስከ 17 ባሉት ቀናት ደግሞ፣ ኢትዮጵያዉያን ጥቁር አልባሳት በመልበስ፣ አገዛዙ በሚያራምዳቸውን ጎጂ ተግባራት ላይ፣ ያላቸውን ተቃዉሞ እንዲገልጹ ጥሪ አስተላልፏል።
ፓርቲዉ በቅርቡ የተመሰረተ፣ ብዙ አገር አቀፍ መዋቅር ገና ያልዘረጋ፣ ተስፋ የሚሰጥና በወጣቶች የተሞላ ለጋ ፓርቲ ነዉ። ጥሪዉ ከቀረበ ገና ሶስት ሳምንት ብቻ እንደመሆኑም፣ ምን ያህል አስቀድሞ ሕዝቡን በማደራጀት አንጻር በቂ ዝግጅት እንደተደረገ ፣ ጥሪው በይፋ ለሕዝብ ከመተላለፉ በፊትም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር (እነርሱም ዝግጅት እንዲያደርጉ) ምን ያህል ዉይይት እንደተካሄደ አላውቅም። በመሆኑም በግንቦት 17 ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመተንበይ አስቸጋሪ ነዉ።
እንደዚያም ሆኖ ግን፣ ከወዲሁ በርካታ ድሎችን ተመዝግበዋል ባይ ነኝ። የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ ይሄን ጥሪ ሲያቀርቡ፣ ምን ያህል ድፍረትና ጀግንነት እንዳላቸው ለማረጋገጥ ችለዋል። ሊታሰሩ፣ ሊደበደቡ፣ ሊገደሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ። እነርሱ መካከል ያሉ፣ ብዙዎቹ ኢንጂነሮች፣ ጠበቃዎች ..ናቸው። የገዢው ፓርቲን ተቀላቅለው፣ የስርዓቱ ተጠቃሚዎች መሆን የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን ኢትዮጵያንና ሕዝባቸውን አስቀድመዉ፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት በመቆም፣ ከፊት በመቅደም፣ ትግል ምን ማለት እንደሆነ እያሳዩን ነዉ።
በዚህም ምክንያት፣ በፈታኝና ትእግስት አስጨራሽ ሁኔታ ዉስጥ ተኩኖም፣ አገር ቤት የሚደረገዉን የሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ መግለጫ ከማዉጣትና ገዢው ፓርቲን ከማውገዝ ያለፈ፣ አንድ ምእራፍ ወደፊት እንዲሄድ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አድርጓል። አንድ በሉ።
ለበርካታ አመታት የዳያስፖራዉ ትኩረት አዲስ አበባ ሳይሆን አስመራ ነበር። አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን ምንም እንደማይሰሩ፣ መስራት ቢፈልጉም መስራት እንደማይችሉ፣ አገር ቤት የሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል «ቅዠት» እንደሆነ ነበር የሚነገረን። ነገር ግን በቅርቡ በተለያዩ ሜዲያዎች እንዳነበብነው፣ እንደ ኢሕአፓ-ዴሞክራሲያዊና የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት ያሉ አንጋፋ በዉጭ አገር ያሉ ድርጅቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ጥሪ ያላቸውን ኢትዮጵያዊና ወቅታዊ አጋርነት ገልጸዋል። በተለያዩ የፓልቶክ ክፍሎች፣ በኢሳት፣ በራዲዮኖች፣ በድህር ገጾች የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትልቅ ትኩረት ስቦ ውይይትን ጭሯል። ይሄ ሁሉ እንግዲህ የሚያሳየዉ ዳያስፖራው ትኩረቱን አገር ቤት ወደሚደረገው የሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንዲያዞር ማድረጉን ነዉ።
በዉጭ የሚገኘው ወገን ብዙ ሊረዳ፣ ብዙ ሊደግፍ፣ ትልቅም ሚና ሊጫወት የሚችል ነዉ። ይህ ኃይል አገር ቤት ካለው ኃይል ተነጥሎ፣ አገር ቤት ከሚደረገዉ ትግል እራሱን ለይቶ መቆየቱ ብዙ ጉዳት በትግሉ ላይ አምጥቷል። አገዛዙን በእጅጉ ጠቅሟል። በሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ምክንያት፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ለመደገፍ ፣ በዳያስፖራ የሚደረገዉን እንቅሳሴ ማየታችን በራሱ ትልቅ ድል ነው። ብዙዎቻችንን አስደስቶናል። በመካከላችን የነበረዉን መከፋፈል አስወግዶ ከዚህ በፊት በቅንጅት ጊዜ እንደነበረው፣ በአንድነት እንድንሰማራ የማድረግ ትልቅ ኃይል አለዉ። ሁለት በሉ።
በድርጅታዊ መዋቅርና በአባላት ብዛት ከሰማያዊ ፓርቲ እጅግ የላቁ እንደ አንድነት ፓርቲ ያሉ በአገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አሉ። እነዚህ ድርጅቶች ተመሳሳይ አላማ እንዳላቸው፣ በዚያም ረገድ ሁሉንም አስተባብረው፣ የተጠናና የተደራጀ የሰላማዊ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ለማድረግ እቅድ እንዳወጡ እንሰማለን። የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ በነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ በእቅድና በጥናት ደረጃ የተቀመጡ እቅዶች ወደ ተግባራዊነት እንዲሄዱ የሚያበረታታና አሉታዊ አስተዋጾ የሚኖረው ሆኖ ነዉ ያገኘሁት። ሶስት በሉ።
የሰማያዊ ፓርቲን ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን አስከትሎ ገዢዉ ፓርቲ እጅግ በጣም በርካታ ወታደሮች አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳስገባ እየተዘገበ ነዉ። «ከሕዝብ ሊነሳብኝ የሚችለዉን ዉጥረት እንዴት አድርጌ ነዉ የማከሽፈው?» በሚል አገዛዙ ውጥረት ላይ ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ። እንግዲህ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ ከወዲሁ ለአገዛዙ ትልቅ መልእክት እንዲደርሰው እያደረገ ነዉ። መልእክቱም «ዝም ብለን አንቀመጥም። ለመብታችን፣ ለነጻነታችን እንሞታለን። ከአሁን በኋላ አንፈራችሁም» የሚል ነዉ። ይሄም በራሱ ትልቅ ዉጤት ነዉ። አራት በሉ።
ሁለት ነገር ብዬ ላቁም። የመጀመሪያዉ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበዉ ጥሪ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ቢያቀርበዉም፣ ጉዳዩ ሁላችንምም የሚመለከት እንደሆነ ነው። ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለብን። በኢሜል፣ በስልክ፣ በኢንተርኔት፣ በቫይበር …ለምናውቃቸው በሙሉ ጥሪ እናስተላልፍ። ሰማያዊዎች ለመታሰር ተዘጋጅተዋል። እኛ ቢያንስ 5፣ 10፣ 20 አገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ጥቁር አልባሳት እንዲለብሱ ማበረታት ሊያቅተን አይገባም። እንረባረብ። «አይ እኔ የማደርገዉ ምን ለዉጥ አያመጣም» በጭራሽ አንበል። ግድ የለም ማድረግ የምንችላትን ትንሿን እናድርግ።
ሁለተኛው ነጥብ፣ ይሄ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የመጀመሪያዉ እንጂ የመጨረሻዉ እንደማይሆን ነዉ። ከአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትምህርት ተወስዶ፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ አረና ትግራይ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ..የመሳሰሉ አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች በአንድ በኩል፣ እንደ ኢህአፓ-ዴ፣ የሽግግር ምክር ምክር ቤት፣ ሸንጎ ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የመሳሰሉ በሌላ በኩል ሆነው፣ ትግሉን በማቀናጀት፣ አገረ ሰፊ፣ ተከታታይ፣ የተቀናጀ፣ በዲፕሎማሲና በሕዝብ ግንኙነት የተደገፈ፣ የተጠና፣ ሰላማዊ የእምቢተኘት ዘመቻዎች መደረግ አለባቸው፤ ይደረጋሉምም። አብረን ተያይዘን እስከሰራን ድረስ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማሸነፋችን አይቀርም።
ሰላማዊ እንቅስቃሴ ማድረጉ የዜጎች ሙሉ አለም አቀፋዊ መብት ነዉ። አሁን ያለው ገዢው ፓርቲ የሚመጻደቅበት ግን እራሱ የማያካብረው ሕገ መንግስት ሁሉ ሳይቀር፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብትን ይደነግጋል። በመሆኑም አንዳንድ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲን እንቅስቅሴ ሊያጣጥሉት ይችላሉ። ጸረ-ልማት፣ ሽብርተኘንት፣ ጽረ-ሕገ መንግስታዊ፣ አመጽ ቀስቃሽ ወዘተ የሚሉ ክሶችን ሊሰነዝሩ ይችላሉ። ነገር ግን ይሄን በማድረጋቸው የሚነገሩን ነገር ቢኖር ዘመናዊ ፖለቲካ ያልገባቸው፣ የኋላ ቀር የጫካ ፖለቲካ የሚያራምዱና በራሳቸው የማይተማመኑ መሆናቸውን ነዉ።
ተቃውሟችን በልማት ላይ አይደለም። ተቃዉሟችን በአባይ ግድብ ላይ አይደለም። ኢሕአዴግን እንደ ድርጅት አንቃወምም። የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ኢሕአዴግን የመደገፍ፣ በኢሕአዴግ ፖሊሲ ዙሪያ የመንቀሳቀስና የመደራጀት ሙሉ መብታቸው እንደሆነ እናምናለን። እንደዉም ኢሕአዴግን ከሚደግፉ ፣ ኢሕአዴግ በመልካም አስተዳደርና በደሞክራሲ ረገድ እንዲያሻሻል ከሚፈልጉ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል እንላለን። (እንደዉም እንደታዘብነዉ በርካታ የኢሕ፤አዴግ ደጋፊዎች በይፋ የሚደግፉትን ድርጅት እየጠየቁ ያሉበት ወቅት ነዉ)
ነገር ግን የአገዛዙ ባለስልጣናት ሌላዉን የመርገጥ፣ የማሰር፣ የማንገላታት ፣ የማፈናቀልና የመግደል ስልጣን የላቸውም። በዚህ ረግድ የሚፈጽሙትንም እኩይ ተግባራት «ያቁሙ» ብለን ነዉ ተቃዉሞ የምናሰማዉ።
የምንቃወመው፣ ለሕንዶችን ለአረቦች መሬት እየተሰጠ፣ ዜጎችንን ከዚህ ዘር ናቸው በሚል፣ ከቅያቸው በማፈናቀል የሚደረግን አሳዛኝና ጨካኝ የዘር ማጥራት ወንጀልን ነዉ።
የምንቃወመው፣ ድሃዉ ሕዝባችን፣ ታንቆ ከአመት ወደ አመት፣ ለአባይ ገንዘብ እንዲከፍል እየተደረገ፣ ቢሊዮን ዶላሮች ከአገር ቤት መዘረፋቸውን፣ በቱባ የአገዛዙ ጀነራሎችና ባለስልጣናት፣ በአደባባይ ኬት እንዳመጡት በማይታወቅ ገንዘብ የሚሰሩት ፎቆችንና የሚያንቀሳቀሱ ቢዝነሶችን ነዉ።
የምንቃወመው ዜጎች በአገራችን ብእር ስላነሱ ብቻ፣ ወይም «በሃይማኖት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ አይገባ» በማለታቸው፣ ሽብርተኞች እየተባሉ በግፍ መታሰራቸውን ነዉ።
እንግዲህ መብቴ ተረገጠ የሚል ኢትዮጵያዊ ካለ ፣ ይነሳ። መብቱንም ያስከብር።

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የ ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ከላይፍ መጽሄት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ


ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የ ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ከላይፍ መጽሄት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ

 ላይፍ መጽሄት
ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የ ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡ ፓርቲው ከተመሰረተ ጥቂት እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚነሳ ለመሆን በቅቷል፡፡ የላይፍ መጽሄት አዘጋጅ የሆነው ዳዊት ሰለሞን ግንፍሌ አካባቢ በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ ቤት በመገኘት ኢንጅነሩን በዋናነት ስለ አማሮች መፈናቀል አነጋግሯቸዋል፡፡Interview Eng. Yilkal Getnet
ላይፍ ፡- ለፖለቲካ ስራ ሙሉ ጊዜን መስጠት በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ አይሆንም?
ኢንጅነር ይልቃል ፡- መኖር ስላለብኝ ጥቂት ስራ እሰራለሁ፣ የሚበዛውን ጊዜዬን ግን የማሳልፈው ለፓርቲው ስራ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ለምርጫ አስቸጋሪ ሲሆኑ የምትወስደው ውሳኔ አንዱን በማጠፍ ለአንደኛው ብቻ ራስህን መስጠት ይሆናል፡፡
ላይፍ ፡- የሚመሩት ፓርቲ ሰማያዊ የፖለቲካ ፍልስፍናው በምን ላይ የተመሰረተ ነው?
ኢንጅነር ፡- ጥያቄው ሰፋ ያለ ነው፡፡ በዋናነት ግን የፖለቲካ ፍልስፍናችን በግለሰብ መብት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሴንተር ራይት ሞደሬት ሊበራሊዝምን የፖለቲካ አመለካከት እናራምዳን ብለን ነው የምናምነው፣ የግለሰብ መብት ከተከበረ የሁሉም መብት ይከበራል እንላለን፣ መብት ከግለሰብ ይጀምራል፡፡ ለምሳሌ ይልቃል ወንድ ነው ስለዚህ ጾታ አለው፣ ይልቃል ቋንቋ፣ ትምህርትና ሞያ ያሉት በመሆኑ ሌላ የተለየ ነገር አያስፈልግም፡፡ የእኔ መብት ከተከበረ የምናገረውም ቋንቋ ይከበራል ማለት ነው፡፡ ቡድንና ግለሰብ እኩል ይታያሉ የሚለው አመለካከት ምክንያታዊ አይደለም፡፡ ከቡድን በፊት ግለሰብ ይቀድማል፡፡ እናም የግለሰቡ መብት ሲከበር የቡድኑ ይከበራል ብለን እናምናለን፡፡ የፖለቲካ ድርጅት በየጊዜው ራሱን እያረመ የሚሄድ እንጂ በቅድመ ድንጋጌ ላይ ተመስርቶ ፖለቲካ ሊሰራ አይችልም፡፡ ለምሳሌ የጎሳ ድርጅት እንጂ የጎሳ ፓርቲ መሆን አይቻልም፡፡ እዚህ አገር ጉዳዩ በጣም ስስ በመሆኑ አንነካውም እንጂ አንድ ሰው የኦሮሞ ድርጅት ነኝ ብሎ ከተነሳ ከኦሮሞ ወዴት መሄድ ይችላል? ምክንያቱም ከመነሻው የተወሰነ ነው፡፡ በጎሳ መደራጀት አሁን እየተፈጠሩ ያሉ ነገሮች መነሻ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በቡድን መብቶች መከበር እናምናለን፡፡ ነገር ግን የሁሉ ነገር ማጠንጠኛ በኢትዮጵያችን ውስጥ ጎሳ መሆን ይገባዋል የሚል አመለካከት የለንም፡፡
ላይፍ ፡ ገዢው ፓርቲ ዜጎችን ከመደራጀት ውጪ የማያውቅ የማይመስልበት ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ነው፡፡ የፌደራል ስርዓቱም ክልላዊነት፣ ቡድናዊነትና መንደርተኝነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል በማለት የፖቲካ ምሁራን ይተቻሉ፡፡ እናንተ ደግሞ የሁሉ ነገር መነሻ ግለሰብ ነው እያላችሁ ነው፡፡ እነዚህ ጫፎች እንዴት ይታረቃሉ?
ኢንጅነር ፡- ፖለቲካ ለጊዜው በሚፈጠር ንፋስ የሚነሳ መሆን የለበትም፡፡ ሩቅ አሻግረህ በማየትም አሰላለፍህን መቅረጽ ይኖርብሃል፡፡ ጎሰኝነት እዚህ አገር ውስጥ ከሰፋ አንተ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለህ ብትሄድ ተቃውሞ ሊያጋጥምህ ይችላል፡፡ ይህ በመሆኑ ግን በቃ በማለት ነገሩን ተቀብለህ እንድትሄድ ሊያደርግህ አይገባም፡፡ የጎሰኝነት አመለካከት የመጣው ከቅኝ ገዢዎች ጋር ተያይዞ ነው፡፡ ቅኝ ገዢዎች ተገዢዎቹን ከፋፍለው ለመግዛት ያመቻቸው ዘንድ ተጠቅመውበታል፡፡ እንግሊዞች በዚህ መንገድ ብዙ ርቀት መጓዝ ችለዋል፡፡ ነገር ግን አሁን ይህ አመለካከት ስልጣንና አቅም ያገኘ በመሆኑ አገር እያተራመሰ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን የእኔ እበልጥ የእኔ እበልጥ ፉክክር ነግሶ አገራችንን ሊያጠፋብን የተቃረበ ቢሆንም የግለሰብ መብት መከበር ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል በማለት እየታገልን እንገኛለን፡፡ ኢትዮጵያዊያን ታላቅ ነበርን፣ ኢንተርኔት ውስጥ ገብተህ ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ ብትፈልግ ከአለማችን ጥንታዊ ህዝብ አንዷ ስለመሆኗ ትገነዘባለህ፡፡ ይህ የጎሳ አመለካከት ግን አሁን የተፈጠረና የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡ህዝቡ ወደቀደመው ታላቅነቱ መመለስ ይኖርበታል፡፡
ላይፍ ፡ – የነበረንን ብሔራዊና የአንድነት መንፈስ ያላላና ወደ ቡድናዊነት እንድናዘነብል ያደረገን ነገር በአንተ ዕይታ ምንድን ነው?
ኢንጅነር ፡- አንዳንድ ሰው ደርግን ብሔራዊ ስሜት የነበረው በማለት ሲያቀርበው እገረማለሁ፡፡ ደርግ አለም የወዛድሮች ትሆናለች የሚል አመለካከት ነበረው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአለም አቀፋዊ ወዛደራዊነት ጥላ ስር ገብቶ ነበር፡፡ ኢህአዴግ የደርግን አለም አቀፋዊ ወዛደራዊነት በብሔር ብሔረሰቦች ለወጠው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ ይህንን አመለካከቱን ለማስረጽ በብዙ ነገሮች ላይ ዘምቷል፡፡ እኔ ዩኒቨርስቲ የገባሁት ኢህአዴግ ስልጣን በያዘበት ወቅት ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ይሰጥ የነበረን የታሪክ ትምህርት አፋለሰ፣ ትልቅ ክብር ይሰጣቸው የነበሩ መመህራንን ከዩኒቨርስቲዎች እንዲባረሩ አደረገ፣ ከዚያ በመቀጠልም በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ትርጉም የነበረውን ሽምግልና አጠፋ፡፡ ሕዝቡ ሃይማኖተኛ በመሆኑ ለሃይማኖቱ ላቅ ያለ ግምት ይሰጣል፣ ኢህአዴግ በዚህ ዙሪያ ያሉ ሰዎችን በመያዝ የሃይማኖት ቤቶችን በካድሬዎች እንዲሞሉ አደረገ፡፡ የአገሪቱ አንኳር ነገሮችን በመያዝ ሚዲያውን በመቆጣጠር ለህዝቡ ውሸት መመገብ ጀመረ፡፡ እንግዲህ በዚህ ውስጥ ያለፈ አንድ የ20 አመት ወጣት ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ሽምግልና እና ትምህርት ከሌለው እንዴት ማንነቱን ማግኘት ይችላል? በእነዚህ ነገሮች ላይ በአቋም ደረጃ ተዘምቷል፡፡ የአገሪቱ ምሰሶ የነበሩ ነገሮች አሁን በቦታቸው አይገኙም፡፡ በአንድነት ውስጥ የነበረን ህዝብ በጎሳው እንዲሰባሰብ በማድረግ በህዝቡ መካከል አለመተማመን እንዲሰፍን ተደርጓል፡፡ የፖለቲካው ዋነኛ ኃይል ደግሞ ከጥቅም ጋር እንዲተሳሰር በመደረጉ አንድ ሰው ለምን ኢህአዴግ እንደሆነ ብትጠይቀው ምላሽ አይሰጥህም፡፡ ምክንያቱም ወደዚያ የሚሄደው የስራ ዕድል፣ የትምህርትና ሌሎች ጥቅሞችን እንደሚያገኝ የሚሰበክ በመሆኑ ነው፡፡ ብሔራዊ ስሜት የምንለውን ነገር ይህ መንግስት ያሳሳው በአጋጣሚ ሳይሆን ሆን ብሎ አስልቶ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
ላይፍ ፡- ነገር ግን ኢህአዴግ የመንግስትነቱን ሚና መጫወት ከጀመረ ወዲህ ማንነታችን ተከበረ፣ በራሳችን ቋንቋ መናገር ጀመርን የሚሉ ቡድኖች ተፈጥረዋል፡፡ ኢህአዴግም የደርግን የአንድነት ፍልስፍና በመተቸት በልዩነታችን ውስጥ አንድነታችን እንዲወጣ አድርጊያለሁ ይላል፡፡
ኢንጅነር ፡- እኔ ምን እንደተገኘ አይገባኝም፡፡ በቋንቋ መናገር የሚባለውም ነገር አዲስ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ደቡብ ኢትዮጵያ ብትሄድ ህዝቡ በአማርኛ ሲናገር ታገኘዋለህ፡፡ አማርኛን ድሮ ይናገር ከነበረው ህዝብ አሁን የሚበልጠው ይናገረው እንዲሆን እንጂ አያንስም፡፡ መጻህፍት ከድሮ ይልቅ አሁን በአማርኛ በብዛት ይጻፋሉ፡፡ ድሮ ብዙ መጽሔት አልነበረም፡፡ አሁን ግን በዛ ያሉ መጽሄቶችን በአማርኛ ማግኘት ይቻላል፡፡ የተወሰኑ የየጎሳዎቹ ልሂቃን የራሳቸውን ጥቅም በማግኘታቸው ብቻ ካልሆነ በስተቀር አዲስ ነገር ተፈጥሯል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ኦሮምኛ እኮ በኢህአዴግ ዘመን አልተፈጠረም፡፡ ድሮም ይነገር ነበር፡፡ ነገር ግን ቋንቋውን ለማስፋፋት የላቲን ፊደል ከመጠቀም የግእዝ ፊደልን ብንጠቀም ይሻል ነበር፡፡ ኢህአዴግ ሆን ብሎ ቅኝ ገዢዎች እንዳደረጉት ህዝቡን ለመግዛት እነዚህን ነገሮች ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ኢህአዴግን በመጠጋት በአንድ ሌሊት ሚልየነር የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ ግን ደሀው ኢትዮጵያዊ ኦሮምኛ፣ አማርኛ ወይም ሲዳምኛ ይናገር የእርሱ ችግር አይደለም፡፡ ከስንዝር መሬቱ ጋር ተጣብቆ ከመኖር ውጪ ጠብ ያለለት ነገር የለም፡፡ ድሮም ገጠር ውስጥ ኦሮምኛ ይናገር ነበር አሁንም ይናገራል፡፡ ድሮም የከለከለው የለም፣ አሁንም ምንም አላገኘም፡፡ ተራ ፕሮፓጋንዳ እንጂ መሬት የያዘ ምንም ነገር የለም፡፡
ላይፍ ፡- ክልሎች የራሳቸውን አስተዳደር መርጠው ህግ በማውጣት እንዲተዳደሩ ስለመደረጋቸው ይነገራል፡፡ ማዕከላዊ የነበረው የመንግስት አወቃቀር ፌደራላዊ በመሆን ስልጣኑን ለክልሎች መስጠቱን ሰማያዊ ፓርቲ የሚመለከተው እንዴት ነው?
ኢንጅነር ፡- የፌደራል ስርዓት በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለፌደራል አስተዳደር አዲስ አይደለንም፡፡ በየክልሉ ከድሮ ጀምሮ አስተዳዳሪዎች ነበሩ፡፡ ከ90 ሚልዮን ህዝብ በላይ የሚገኝባትን አገር በአሀዳዊ አስተዳደር ለመምራት መሞከር ትልቅ ችግር ነው፡፡ ክልሎች የራሳቸውን አስተዳደር በመመስረት ስልጣን ከማዕከላዊው መንግስት መጋራታቸው ጥሩ ነገር ነው፡፡ ችግሩ ግን ህዝቡን በጎሳ ከረጢት ውስጥ በመክተት በመከራውና በደስታው ወቅት አንድ የነበረውን ህዝብ ማለያየት ነው፡፡ ዘውዴ ነሲቡ የሚባሉ ሸዋ ውስጥ 130 አመት ኖረው ያረፉ ሰው ሲናገሩ ‹‹እርሱ የሲዳማ፣ የጎጃምና የወለጋ ሰው ነው›› ይሉ ነበር፡፡ ያኔ ሰውን በጎሳው ሳይሆን በሚኖርበት አካባቢ ባለው ተቀባይነት በመነሳት ይጠራ እንደነበር መረዳት እንችላለን፡፡ እኛም ብንሆን የፌደራል ስርአቱን በመቀበል የየክልሉ ሰዎች ክልላቸውን ያስተዳድሩ መባሉን እንደግፋለን፡፡ ድሮም እኮ የሸዋ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞ ንጉስ የሚባሉ ነበሩ፡፡ እነዚህ የየክልሉ ንጉሶች የነበሩ ቢሆንም ለንጉሰ ነገስቱ ይገብሩ ነበር እንጂ እንገነጠላለን አይሉም፡፡ ቴክኖሎጂው ባልነበረበት ዘመን የነበሩ ነገስታት ከምንም በላይ ለአገራዊ አንድነት ቅድሚያ ሲሰጡ አሁን ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ነን የሚሉ ግን ኦሮሞን እንገነጥላለን ይላሉ፡፡ የኢህአዴግ ፌደራሊዝም የይስሙላ ነው፡፡ ፓርቲው ሶሻሊስት በመሆኑ መሰረቱ ማዕከላዊነት ነው፡፡ ጥቂት የበላይ አመራሮች ሁሉን ነገር የሚወስኑበት ፓርቲ ነው፡፡ ለክልሎች ሰጠሁ ያለውን ስልጣን ጣልቃ በመግባት ብዙ ጊዜ ሲያፍን ተመልክተነዋል፡፡ እንደውም ከኢህአዴግ ዘመን ይልቅ በድሮ ጊዜ የየክልሉ ገዢዎች የተሻለ ስልጣን ነበራቸው፡፡ የራሳቸውን ጦር በማደራጀት ያስተዳድሩ ነበር፡፡ አገራዊ በሆነ አጀንዳ ላይ ግን በህብረት ከሌሎች ጋር ይሰሩ ነበር፡፡ የኢህአዴግ የድርጅት ባህሪና ፌደራሊዝም አብረው መሄድ የሚችሉ ነገሮች አይደሉም፡፡ ይህ የአስመሳይነትና የአታላይነት የፖለቲካ ባህል ነው፡፡ በአጭሩ በእኛ አመለካከት የፌደራል ስርአት ጂኦግራፊውን፣ በውስጡ የሚኖሩ ህዝቦች በስነ ልቦና የተገናኙ መሆናቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ ለአስተዳደር ምቹ መሆኑን የመዘነ መሆን ይገባዋል፡፡ በአንድ አገር ውስጥ ክፍላተ ሀገራት እንዲኖሩ በማድረግ ስልጣኑ የክፍላተ ሀገራቱ እንዲሆን እንታገላለን፡፡
ላይፍ ፡- ኢህአዴግ እኔ ባልኖር አገሪቱ ትበታተናለች በማለት ሁልጊዜም ሲናገር ይደመጣል፡፡ የመበታተን ስጋት ተጋርጦባት ለነበረች አገር የመሰረትነው የፌደራል አወቃቀር ፍቱን መድሀኒት ሆኗል ማለቱን እንዴት ይመለከቱታል?
ኢንጅነር ፡- እኛ የምንከተለው የአስተሳሰብ መስመር ከኢህአዴግ የተለየ ነው፡፡ ከጋራ ጉዳይ ይልቅ ልዩነትን በማጉላት አገርን እጠብቃለሁ ማለት አታላይነት ብቻ ነው፡፡ አሁን ባለው እውነታ የብሔረሰብ አስተዳደር አለን በማለት ብትጠይቀኝ ምላሼ የለም ነው፡፡ አገሪቱን እየመሩ የሚገኙት ጥቂት ቡድኖች ናቸው፡፡ ባንኩን፣ መከላከያውንና ሌሎቹን ቁልፍ ቦታዎች እየመሩ የሚገኙት ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ የብሄር ጭቆና ከየትኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ያለው በዚህ አገዛዝ ነው፡፡ ብዛት ያላቸው ነጻ አውጪ ድርጅቶች የተፈጠሩት እኮ በዚህ ወቅት ነው፡፡ የብሄር ጥያቄ ከተመለሰ እነ ኦብነግን የመሳሰሉ ድርጅቶች እንዴት ሊፈጠሩ ቻሉ፡፡ መከላከያው ውስጥ ምን ያህል የብሄር ብሔረሰብ ተወካዮች በአመራር ቦታው ላይ ይገኛሉ? ፖለቲካን ትንተና ብቻ ማድረግ የለብንም፡፡ መሬት ላይ ያለውን እውነታም ልንመለከትበት ይገባል፡፡
ላይፍ ፡- የአንድ ቡድን የበላይነት ወይም ከአንድ ክልል የወጡ ሰዎች የስልጣን መደላደሉን በመያዝ የወጡበት ክልል ወይም ብሄር ስልጣን መያዝ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል?
ኢንጅነር ፡- የቡድኑን ተጠያቂነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በላይም ለማደናገሪያነት ይውላል፡፡ ለምሳሌ ህወሃት ይህን ነገር ተጠቅሞበታል፡፡ አንደኛ ስልጣን የያዙት የእኛ ልጆች ናቸው፡፡ ተዋግተዋል፣ ደምተዋል መስዋዕትነት በመክፈላቸው ስልጣኑን መያዝ አለባቸው የሚል ስነ ልቦና እንዲፈጠር ሆኗል፡፡ የትግራይ ሰዎች ከዚህ በመነሳት ነገሮችን በዝምታ ማየቱ በስሙ እንዲነገድበት ሆኗል፡፡ ነገር ግን ጥቂቶች ይህንን ተገን በማድረግ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ህወሃቶች ለትግራይ ህዝብ እኛ ከሌለን ሌላው ያጠፋሃል በማለት ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዲቃረን እያደረጉት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ተጠቅሟል ለማለትም አመራር ላይ ያለው ቡድን በተወሰነ ደረጃ የሚያደርገው ነገር አለ፡፡ ማደናገሪያ ቢኖረውም በዚያ አካባቢ ያለው ሰው ፊት ለፊት ወጥቶ መናገር አለበት፡፡ ሌላው ሰው በእነርሱ ቅር እንዲሰኝ እያደረገ የሚገኘው ነገርም ለዘብተኝነታቸው ይመስለኛል፡፡ አሁን አሁን ግን ይህ ነገር እየተቀረፈ ነው፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲና በአረና ፓርቲ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወጣቶች ብቅ እያሉ ነው፡፡
ላይፍ ፡- በቅርቡ በጉራፈርዳና ቤኒሻንጉል አካባቢ ወደተከሰቱ መፈናቀሎች እንምጣ፡፡ ዜጎች የአንድ ክልል ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ ይህ ነገር በእርስዎ እይታ በምን መንስኤነት የተፈጠረ ነው?
ኢንጅነር ፡- ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለፓርላማው ቀርበው ሲናገሩ እንደሰማሁት ችግሩ የተፈጠረው በአቅም ማነስና በብቃት ችግር አይደለም፡፡ ወይም እዚያ አካባቢ ያሉ ኃላፊዎች በሙስና ከመጨማለቃቸው የተነሳ የተፈጠረ ነው ማለታቸውንም አልቀበልም፡፡ ነገሩ የተፈጠረው በፖሊሲ ደረጃ በደንብ ተጠንቶ ነው፡፡ አንደኛ ይህ ነገር አሁን የተፈጠረ አይደለም፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ፓርላማ ቀርበው ‹‹ ደቡብ ውስጥ ለመኖር በመጀመሪያ የደቡብን አስተዳደር መጠየቅ ይገባል›› ብለው ነበር፡፡ ስለዚህ ከክልላችን ውጡ የሚለው ነገር ፖሊሲው ከተቀረጸበት እውነታ በመነሳት የተፈጠረ ነው፡፡
ላይፍ ፡- ፖሊሲውን ወይም ንድፉን ያወጣው ማን ነው ?
ኢንጅነር ፡- ህወሃት ነዋ፡፡ አንተ ለመጽሔትህ በደንብ እንድናገርልህ ፈልገህ ካልሆነ በስተቀር ይህ የሚታወቅ ነው፡፡ የተጨቆነ ብሄረሰብ እንዳለ ካመንክ እኮ ጨቋኝ የምትለው አካል የግዴታ ይኖራል፡፡ ከዚህ አንጻር ድርጅቱ አማራን በጨቋኝነት በመፈረጅ የአማራን አከርካሪ እሰብራለሁ በማለት ተነስቷል፡፡ በ1997 ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ በዋናነት በከተሞች አካባባቢ ከፍተኛ ሽንፈት ሲያስተናግድ መለስ አሁንም የአማራና የቀድሞ መንግስት ናፋቂዎች እንዳልጠፉ ተረድቻለሁ በማለት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ እነዚህ ንግግሮች እየዋሉ እያደሩ እንዲህ አይነት ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል፡፡ በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያነጣጠረ ማፈናቀል መከሰቱ ትልቅ ትኩረት ማግኘት ይኖርበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ ነው የሚለውን ክስ ለማስቀረት ሲሉ ችግሩ የተፈጠረው በጥቂት ሃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች ነው በማለት ነገሩን ለማድበስበስ ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን ኢህአዴግን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው አንድ ተራ ባለ ስልጣን ከመሬት ተነስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዲፈናቀሉ ያደርጋል በማለት ለመናገር ይቸገራል፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር በአሁኑ ሰአት አማራ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞም ተፈናቅሏል ለማለት ኦሮሞ ነን የሚሉ ሰዎች ከቤኒሻንጉል እንደተፈናቀሉ ሲናገሩ እያደመጥን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እስካሁን ድረስ የት ነበሩ ? ኢህአዴግ የመሬት ባለቤቶች ብሄር ብሄረሰቦችና ብሄሮች ናቸው ብሏል፡፡ በኢህአዴግ አመለካከት መሰረት እኔ የመሬት ባለቤት መሆን አልችልም፡፡በኢህአዴግ አስተሳሰብ ሁላችንም በህግ እኩል አይደለንም፡፡ ያለ ብሄርህ በመሄድ መሬት የምትዘው አንተ ማን ነህ? የሚለው አስተሳሰብ የመነጨው ስርኣቱ ከሚከተለው ፖሊሲ ነው፡፡
ላይፍ ፡- አንዳንዶች አቶ ኃይለማርያም በፓርላማው በመቅረብ ችግሩን በማመን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ኃላፊነቱን የሚወስድ አካል እንደሚኖር መጠቆማቸውን እንደ በጎ ጅምር በመውሰድ መለስ ቢሆኑ ኖሮ ተፈናቃዮቹን መሬት ወራሪዎችና ተስፋፊዎች በማለት ይነቅፏቸው ነበር ይላሉ፡፡ በዚህ አስተያየት ይስማማሉ፡፡
ኢንጅነር ፡- አንዳንድ ሰው እንግዲህ ያለበትን ሁኔታ መቀየር ያስፈልገው ይሆናል፡፡ መለስም እኮ በተወሰነ ደረጃ አቋማቸውን እንደቀያየሩ የመጡበት መንገድ ማሳያ ሆኖ መቅረብ ይችላል፡፡ እንደውም እንደ መለስ ተገለባባጭ አይነት ሰው ተመልክቼ አላውቅም፡፡ ሲመጡ ሊበራል ዴሞክራሲ፣ ነጭ ካፒታሊዝም ነው የምናራምደው አሉ፡፡ መጀመሪያ ማሌለት ነበሩ፡፡ ከዛ 1997 ላይ ታማኝ ጠንካራ ተቃዋሚ ብናገኝ ግማሽ መንገድ ድረስ ተጉዝን እንቀበላለን አሉ፡፡ ነገር ግን የሆነው ከሆነ በኋላ ልማታዊ መንግስት ነን፣ መስመሩም ዴሞክራሲ ነው አሉን፡፡ አሁንም ቢሆን በህይወት ቢኖሩ ኖሮ የማይጠበቅ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ አውቃለሁ መለስ መሸነፍ የማይፈልጉ እልኸኛ ሰው ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን አለም አቀፍ ጫናው የማያምኑበትን እንኳን እንዲናገሩ ሊያደርጋቸው እንደሚችል አምናለሁ፡፡ መለስ ወጥ አቋም የነበራቸው የመርህ ሰው አይደሉም፡፡ ዛሬ ያነበቡትን መጽሀፍ በመያዝ የሚከራከሩ ነገ ደግሞ የትናንቱን በመተው የሚቀየሩ በጓደኞቻቸው ዘንድም ተለዋዋጭ ተደርገው የሚወሰዱ ነበሩ፡፡ በእርግጥ የአቶ መለስ አይነት የትግል መሰረትና መነሳሳት አቶ ኃይለማርያም ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ምክንያቱም የመጡት ከትምህርት አካባቢ ነው ፡፡ ስለዚህ አማራውን ጨቋኝ በማድረግ በመሳል የመከትከት አላማ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ከዚህ በመነሳት ነባራዊውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት የተወለጠ ነገር ተናግረዋል፡፡ መለስም አቅም ሲያጡና የሚገቡበት ሲጠፋቸው እንዲህ ሊናገሩ ይችሉ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ግን ከንግግር ያለፈ ነገር አለመደረጉ መሰመር ይገባዋል፡፡ ተፈናቅለው ለነበሩ ሰዎች ምን ተደረገ ? ንብረታቸውን በትነውና የልጆቻቸውን ትምህርት አቋርጠው ለሶስት ወራት ያህል ሲንከራተቱ መንግስት ምን ይሰራ ነበር ? የአሁኑ ንግግር ከጫና የመጣ እንጂ አምነውበት የተናገሩት አይደለም፡፡ ኃይለማርያም ምናልባት የአፈጻጸም ችግር በማለት በግልጽ ተናግረው ይሆናል፡፡ መለስ በዚህ ቦታ ቢሆኑ ኖሮ ነገሩን በብልጣብልጥነት ለማለፍ ይሞክሩት እንደነበር ይሰማኛል፡፡
ላይፍ ፡- ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ቤንሻንጉል ክልል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ማምራታችሁንና ለተወሰኑ ሰዓታትም መታሰራችሁን ሰምተናል፡፡ እስኪ በአጠቃላይ ስለተፈጠረው ነገር ይንገሩን?
ኢንጅነር ፡- እውነት ለመናገር ስራ ስትሰራና ስትንቀሳቀስ ለአምስት ሰዓታት ያህል ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንድትቆይ መደረግህ ያን ያህል የሚወራለት አይሆንም፡፡ ይህ ግን የሚያሳየው ዜጎች በነጻነት ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው መረጃ ማግኘት እንደማይችሉ ነው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ በእኛ ላይ እንዲህ አይነት ነገር ያደረጉ ሰዎች እዛ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ከዜጎች ጋር በመገናኘታችን ብቻ ይህንን እርምጃ ከወሰዱ መሬታችንን ወስዳችኋል በሚሏቸው ሰዎች ላይማ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ማሰብ በራሱ ይከብዳል፡፡ ተፈናቃዮቹ በአፋጣኝ ይዞታቸውን እንዲለቁ በመደረጋቸው ዘጠኝ ሺ ብር የምትሸጥ ላም በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሸጠዋል፡፡ ተንቀሳቅሰን የተመለከትነው ሶስት ቀበሌዎችን ነው፡፡በአንድ ቀበሌ 58 ሰው በህገ ወጥ መንገድ ስለገባችሁ እንድትለቁ የሚል ወረቀት በይፋ ነው የተለጠፈባቸው፡፡
ላይፍ ፡- የትና ማን ነው የለጠፈው ? ወረቀቱስ ማህተም ነበረው ?
ኢንጅነር ፡- ማህተሙ የቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው፡፡ ወረቀቱ ሌላው ቀርቶ ያላችሁን ንብረት ሸጣችሁ እንድትለቁ በማለት ያዛል፡፡ እቃቸውን እንኳን ይዘው የመውጣት መብት አልነበራቸውም፡፡
ላይፍ ፡- ንብረታቸውን እንዲህ በወረደ ዋጋ የገዛው የአካባቢው ማህበረሰብ ነው ?
ኢንጅነር ፡- የሚገዛ በማጣታቸው እኮ ነው ከመጣል ብለው የሸጡት፡፡ ዘጠኝ ሺህ ብር የሚያወጣ ላም በአንድ ሺህ ብር ስለተሸጠ ሸጠው ወጡ በማለት መናገር አይቻልም፡፡ እኔ ጥለው በትነው ወጡ ነው የምለው፡፡ እንዲመለሱ ከተደረገ በኋላ የአማራ ክልል ኃላፊዎች መጡ ተባለ፡፡ ነገር ግን ምንም ያደረጉላቸው ነገር የለም፡፡ ሰዎቹ እኮ ዝርፊያና ድብደባ ጭምር ተፈጽሞባቸዋል፡፡
ላይፍ ፡- ድብደባውን የፈፀሙት ይታወቃሉ ?
ኢንጅነር ፡- ፖሊሶችና የአካባቢው ታጣቂዎች ናቸው፡፡ እኔ ካናገርኳቸው ተፈናቃዮች መካከል 60 ሺህ ብር የተወሰደበትና 60 መሃለቅ የአንገት ወርቅ የተነጠቀች እናት ይገኙበታል፡፡ በሰደፍ የተደበደቡ ሰዎች ቁስላቸው ገና ባለመድረቁ ድብደባው ያደረሰባቸውን ጉዳት መመልከት ይቻላል፡፡
ላይፍ ፡- ያለ ፍላጎታቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማራ ብሄር ተወላጆች በድጋሚ ያለ ፍላጎታቸው ተገድደው ወደ ቤንሻንጉል እንዲመለሱ ስለመደረጋቸው አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እርስዎ በዚህ ዙሪያ የተመለከቱት ምንድን ነው ?
ኢንጅነር ፡ እነርሱ ምንም አይነት ስልጣን እዚህ ውስጥ የላቸውም፡፡ በኃይል እንዲወጡ እንደተደረጉ ሁሉ በኃይል እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ሲሄዱም ሆነ ሲወጡ የእነርሱ ፈቃድ አልተጠየቀም፡፡
ላይፍ ፡- ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ይህንን ድርጊት የፈፀሙ ኃላፊዎችን በማንሳት ብቻ መፈናቀሉ እንዲቆም ማድረግ ይቻላል ብለው ያምናሉ ?
ኢንጅነር ፡- አይቆምም፡፡ አንድ ሰው በኢሳት ተጠይቆ እኮ ‹‹ ምንግዜም ችግር ሲመጣባቸው በእኛ ላይ መለጠፋቸው የተለመደ ካልሆነ በስተቀር ክልሉ ሳያውቀው የተሰራ ምንም ነገር የለም›› ብሏል፡፡ ነገሩ በፖሊሲ ደረጃ ተይዞበት የተሰራ ስለመሆኑ ምንም መከራከርያ አያስፈልግም፡፡
ላይፍ ፡- የአማራው ውክልና አለኝ የሚለው ብአዴን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታን መምረጡን እንዴት ተመለከቱት ?
ኢንጅነር ፡- ቅድም እኮ ብዬሃለሁ፡፡ እዚህ አገር የፌደራል አስተዳደርም ሆነ ስልጣን ያላቸው ፓርቲዎች የሉም፡፡ አገሩን የሚመራው የተወሰነ የፖለቲካ ቡድን ነው፡፡ ጣልያን በወረራው ወቅት የተወሰኑ የጎሳ መሪዎችን በመሾም ቅኝ ግዛቱ ሊያደርግን ሞክሮ ነበር፡፡ ሌላው አማራ የሚባል ጎሳ(ብሄር) መኖሩን አማሮች የምትላቸው ሳይቀሩ አያምኑም፡፡ ለምሳሌ እኔ ጎጃም ነው የተወለድኩት፣ ከጓደኞቼ ጋር ስንጨዋወት እስላም አማራ እንላለን እንጂ አማራ ጎሳ ስለመሆኑ አናውቅም፡፡ እኔ አማራ የሚባል ጎሳ ስለመኖሩ የሰማሁት ዩኒቨርስቲ ከገባሁ በኋላ ነው፡፡ አማርኛ ተናጋሪው በብሔረሰብ የሚያምን አይደለም፡፡ እንደው ከአንዳንድ አክራሪዎች ጋር እንዳታጣለኝ እንጂ አማራ የሚባል ጎሳ(ብሄር) ስለመኖሩ የሚያሳይ ማስረጃ የለም፡፡ ልክ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ ከዚህ ወጣ እዚህ ገባ እንደሚባለው አይነት ማስረጃ የለም፡፡ አማራ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙበት እስላም ክርስቲያን ለማለት ነው፡፡ ይህ የህብረተሰብ ክፍል ከበሮ ተመትቶ አገር ተወረረች ሲባል ሆ ብሎ ተነስቶ ጦርነት ይገጥማል፡፡ባህሉ፣ ሃይማኖቱና አመለካከቱ ሁሉ በኢትዮጵያዊነት የታጠረ ነው፡፡ ይህንን የሚያደርገው የተለየ ጥቅም በማግኘቱ አይደለም፡፡ ከኩርማ መሬት ውጪ በየትኛውም ስርዓት ተጠቃሚ አልሆነም፡፡
ላይፍ ፡- ምናልባት ግን መፈናቀሉ በዋናነት አማራው ላይ ያነጣጠረው አማራውን የሚወክል ድርጅት ባለመኖሩ ይሆን ?
ኢንጅነር ፡- እኔ እንዲህ አይነት ድርጅት መኖር አለበት ብዬ አላምንም፡፡ የእነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ በጎሳው ለማያምን ሰው የሆነ የጎሳ ድርጅት ማቋቋም ተገቢ ነው ብዬ አላስብም፡፡ አማራው በጎሳ እንዲታጠር ከተደረገም ኢትዮጵያ አለቀላት ብዬ ነው የማምነው፡፡
ላይፍ ፡- በቅርቡ የቀድሞው የህወሃት አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ ኢህአዴግ የአፍሪካ ምርጡ ፓርቲ ነው በማለት መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ በእርስዎ ደረጃ ኢህአዴግ ግን የት ያስቀምጡታል ?
ኢንጅነር ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ የሆነ የፖለቲካ መስመር የሚከተል ድርጀት አይደለም፡፡ ከህወሃት አንስቶ ዝብርቅርቅ ያለ መስመር የሚከተል አንድ አይድኦሎጂ የሌለው ነው፡፡ ቀደም ብዬ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ብሄራዊ ስሜት፣ ታሪክን፣ ባህልንና ማንነትን ያዋረደ ነው፡፡ ጉልበት በእጁ በማስገባቱም ሁሉንም አዳክሞ እየገዛ ነው፡፡ አዎን ከዚህ አንጻር ከሆነ ስብሃት እንዳሉት የአፍሪካ ምርጡ ፓርቲ ነው፡፡