በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ።
በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል።
የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar