torsdag 16. mai 2013

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ከአንድ መቶ በላይ ተማሪዎች ተይዘው ታሰሩ


በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ከአንድ መቶ በላይ ተማሪዎች ተይዘው ታሰሩ

ኢሳት ዜና:-ከሶስት ቀናት በፊት የተነሳው የተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ቀጥሎ የፌደራል ፖሊሶች አድማውን መርተዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን   ከ100 በላይ ተማሪዎች ወስደው በጋሞጎፋ ዞን ፖሊስ መመሪያ ግቢ ውስጥ ማጎራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
የተለያዩ የትምህርትና አስተዳዳራዊ በደሎችን ያነሱት ተማሪዎች ትናንት ቀኑን ሙሉ በፖሊሶች ተከበው መዋላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። በዛሬው እለትም ተማሪዎቹ ትምህርት ያልጀመሩ ሲሆን፣ የታሰሩ ጓደኞቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያዎች ያመሩ ተማሪዎች ጓደኞቻቸውን እንዳይጠይቁ በፖሊስ ተባረዋል።
ተማሪዎች የትምህርት ጥራት እንዲጠበቅ፣ አስተዳዳራዊ ችግሮች እንዲፈቱ እና መብታቸው እንዲከበርላቸው መጠየቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar