ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።
* ትላንት ማምሻውን በ 17 አውቶብስ ከሪያድ ድንበር ግዜያዊ መጠለያ ተጭነው አሚራ ኑራ እይተባለ የሚጠራ ዩንቨርስቲ ግቢ ባዶ ሜዳ ላይ አንተኛም ኤርፖርት ውሰዱን ብለው ከተሳፈሩበት አውቶብስ አንወርድም ብለው ያመጹ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ዛሬ ረፋዱ ላይ ሪያድ ሺሜሲ አካባቢ ወደ ሚገኝ አስርቤት ተወስደው የጣት አሻራ ሰጥተው መጨረሳቸውን እና ሊሴ ፓሴ መቀበላቸውን ማረጋጋጥ ተችሏል።
* በሌላ በኩል እዚሁ ግቢ ውስጥ አሁንም ከሳምንት በላይ የሆናቸው ከ 5 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ዳስ መጠለያ እና የመጸዳጃ ቦታ ሜዳ ላይ ተበትነው ቀን ጸሃይ ማታ ብርድ እይተፈራረቀባቸው እየተሰቃዩ መሆናቸው ከምንጮቻችን መረዳት ተችሏል።
* ትላንት ማምሻውን እዚህ ግቢ ግዜያዊ መጠለያ ሜዳ ላይ የተፈጠረውን ሁከት ለማርገብ የኤንባሲው ሃላፊዎች እና የመንግስት ሉኦካን ቡድን አባላቶች ቦታው ላይ መገኘታቸውን ምንጮች ይገልጻሉ ።
* ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።
* በትጠቀሱት ወገኖቻችን ስም ዲፕሎማቱ ከ 3 ወር በፌት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡ ለነዚህ ወገኖቻችን የአይሮፕላን ትኬት መግዣ የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማድረግ እስከ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ፡ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የሚናገሩ ወገኖች ይህ ጥሬ ገንዘብ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እጅ ላይ እንደሚገኝ፡ አክለው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar