ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።
* በሌላ በኩል እዚሁ ግቢ ውስጥ አሁንም ከሳምንት በላይ የሆናቸው ከ 5 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ዳስ መጠለያ እና የመጸዳጃ ቦታ ሜዳ ላይ ተበትነው ቀን ጸሃይ ማታ ብርድ እይተፈራረቀባቸው እየተሰቃዩ መሆናቸው ከምንጮቻችን መረዳት ተችሏል።
* ትላንት ማምሻውን እዚህ ግቢ ግዜያዊ መጠለያ ሜዳ ላይ የተፈጠረውን ሁከት ለማርገብ የኤንባሲው ሃላፊዎች እና የመንግስት ሉኦካን ቡድን አባላቶች ቦታው ላይ መገኘታቸውን ምንጮች ይገልጻሉ ።
* ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።
* በትጠቀሱት ወገኖቻችን ስም ዲፕሎማቱ ከ 3 ወር በፌት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡ ለነዚህ ወገኖቻችን የአይሮፕላን ትኬት መግዣ የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማድረግ እስከ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ፡ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የሚናገሩ ወገኖች ይህ ጥሬ ገንዘብ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እጅ ላይ እንደሚገኝ፡ አክለው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar