lørdag 30. november 2013

Ana Gmes Speaks: Addis Standard’s exclusive interview

Ana Gomez


 ADDISSTANDARD   

Ana Gomes is coordinator and spokesperson of the foreign affairs committee for her political group, the Social-Democrat. With 200 members the Social-Democrat is the second largest group within the European Parliament. For Ethiopia and Ethiopians though Ana Gomes is best remembered for her role as the leader of the EU election observers’ team during the 2005 crisis-induced general election in Ethiopia. She has had a troubled relationship with Ethiopia’s late Prime Minister Meles Zenawi, who she still calls “a dictator,” after she published her report in which wrote the election was massively rigged. Eight years later, Ana Gomes came to Ethiopia to participate in the just concluded 26th ACP-EU parliamentary meeting. Her arrival in Addis Ababa caught many, who thought she would never be allowed to set foot in Ethiopia, by a surprise. Addis Standard’s deputy-editor-in-chief Tesfaye Ejigu met Ana Gomes during the meeting and held an exclusive interview. Excerpts:
AS - Your question to the development commissioner Andris Piebalgs was on Ethio-Djibouti road project funded by the EU. The commissioner replied EU no longer funds road projects in Ethiopia because construction work is given to companies without auction or given to friendly companies. What happened to the Ethio-Djibouti road project at the end?
Ana- Gomes - I don’t know if it was the auction. I raised the issue because some very concerned European friends told me about that because there is a lot of money from the European taxpayers which was supposed to be directed to development that was diverted. I only talked about the road. But I just confirmed with the EU commission representative that it’s indeed two contracts; one, a railway between Addis Ababa and Djibouti; the EU funding was around 45 million Euros, and two, 50 water tunnels project, by the same company worth 20 million Euros. The company was an Italian company called CONSTAT. That company adds Ethiopian Contractors/subcontractors. Obviously it was chosen by the ministry of finance with EU agreement. It’s a project that has gone very wrong because nothing has been achieved, and the money has been deviated.  EU has started investigation, arbitration is going on; it also involved your government.  And support has been cancelled. They are apparently trying to recover the money from the company. But the money has gone, so the investigation goes on. I was promised for the details by the European commission. It doesn’t mention road. It’s a bit weird however that the EU development commissioner mentioned road construction. And the EU signing new agreement to fund road projects in Ethiopia is contradictory. I think it’s important to clarify all these contradictions for the sake of taxpayers in Europe and also for the Ethiopian people. I am heartened by the fact that PM Hailemariam [Desalegn] has started taking measures even against the high officials who are involved in corruption. So I have to find out. In fighting corruption the main element is transparency. So this element has to be put out for the people to know. There are some things to be checked.qoute2
AS - EU funded hydropower project-Gilgel gibe 3 was given without auction to Salini Construction, an Italian company. A few months after it went operational part of it caved in and was closed. The EU criticized openly the handing out of the construction without auction. But it didn’t decide not to fund hydropower projects.
Ana Gomes - I am very interested to learn about that. I need to note down that information. I will find out about it and ask the EU.  I am glad you asked this. I have not been able to follow in detail all this development processes because I was not in the EU development committee.
AS - ACP-EU joint parliamentary assembly has democratic agenda. The speaker of the house of people’s representative of Ethiopia Abadula Gemeda said, “we have achieved a lot in building democracy, peace and good governance.” Do you buy that? Do you think a lot has been achieve?  
Ana Gomes - No! In many respect I see a lot of the old ways. Meles was an expert in using jargons such as good governance, the rule of law, democracy, sustainable development, but in practice doing just the opposite. It was a smart leadership which uses politically correct languages for Europeans and Americans consumption. But the practice was really oppressive. What I saw during Meles Zenawi was a dictatorship. I have lived in dictatorship in my own country. I believe this persists in the mind set of many authorities.
But at the same time, I realize there is indeed some opening, some realization [that] Ethiopia can’t continue this way.  Ethiopia needs change. Even some of the people who have that politically correct speech that everything has been achieved in Ethiopia in public, in private conversation with me they acknowledged that Ethiopia needs change, and that it is the time to really promote important, drastic changes. In that sense I welcome the move that the PM Hailemariam has initiated the prosecution of high officials, even a minister charged with corruption. I hope this will be the first step in the right direction. At the debate we were discussing the independence of the judiciary.  I used the debate to say that Judicial Independence doesn’t exist in Ethiopia, although it’s stated. I recalled the judges who flee the country in 2005 because they refuse to tamper with the conclusion on the inquiry about the massacre in 2005. They were pressed by the [late] PM and the government to do that. These were very courageous people who put all their lives and their families [at risk].  I also highlighted that trials of all political prisoners but in particular journalists Eskinder Nega, Wubeshet Taye, Riyot Alemu and others like DebebeEshetu; [political] leaders Andualem Arage e.t.c. were not fair; all the people [including] Europeans who were able to be present at some of these trials said they [the prosecutors] never produced any significant evidence against them and indeed the trials were not fair.  So I hope I have made this appeal today here.
AS - But they faced terrorism charges…?
These terrorist charges are not credible, so I appeal for their liberation in the spirit of openness. You have now a sort of dual register. In public it said one thing in private it acknowledges that Ethiopia must change. Or Ethiopia needs support to change. In that context, indeed bold decisions should be taken to liberate these people, because some of these people are icons of the younger generation. Very educated, qualified generation which Ethiopia needs to develop itself. I receive a mail, a standard letter everyday from an Ethiopian who manages to flee the country and who is somewhere in Kenya, Uganda ….Nigeria asking me to write a letter to the UNHCR saying they need political asylum. So I know Ethiopia looses the best, most qualified generation not only because of lack of jobs but because there is politically closed environment with which these young qualified people cannot live. I know Ethiopia faces serious terrorist threat as we all do, Ethiopia in particular because of the neighborhood and the tension that has been built up by Meles Zenawi between Muslims and Christians inside Ethiopia which was not an issue in 2005 but in the meantime became a big source of concern.  If the government continues the old ways repressing this bright, younger people who are now connected to the world in a way the regime cannot control them via the twitter, and facebook, and so on. Obviously many of these young people will be driven into the hands of radicals and extremists. Even to be recruited by terrorists.  It is what we see happening in other countries in the region. So, it is very important to open up democratically for the security of the country.
AS - in 2015 Ethiopia will hold a general election. Do you think it will be democratic, free and fair given the situation now?
qoute1 Ana Gomes - I don’t know, but I hope it could be good. Meles died, he was the source of the repression;his own supporting group are divided. They are fighting with each other. There is indeed an opportunity to see Ethiopia change progressively, peacefully. Nobody wants to see Ethiopia destabilized. But to create the conditions for the election to be held democratically it requires the opposition to be allowed to operate, which is not the case in the moment. In the moment you have only one member of the opposition [in the parliament]. I recall in 2005 at least there were some results that were not disputed. And these are the results of Addis Ababa where all the 23 seats went in a shocking landslide victory to the opposition. Well, where are these people? In exile.
They say the opposition is weak, of course it is weak. “it is weak, it is fragmented, it is not loyal…” are the same kind of things that I used to hear in 2005 from Meles Zenawi. But any opposition in that condition in any country would be weak. In my own country do you think the opposition in the days of the dictator was stronger? No!  Most of it was underground. In order to have the conditions to operate I believe it is important to allow the opposition to operate, not just those inside the country but also those forced into exile. They need guarantee to operate. There is no media freedom, only an opening seen. I read the Ethiopian herald and it’s all the same thing only better because PM Meles Zenawi is not writing now. There is no condition for NGOs or civil societies to operate. I believe EU will not accept to come back and observe election and give its temp of credibility unless basic elements are met; such as liberating political prisoners or allowing the judiciary to operate independently.
AS - “Europe could definitely make the difference for democracy in Ethiopia. Instead, current European leaders are choosing to fail it. In doing so they are not just failing Ethiopians. They are also failing Europe.” This is taken from a letter you wrote to AP. By this do you mean Europeans aren’t trustworthy? They don’t like democracy to thrive in Ethiopia?
Ana Gomes - No! European citizens, European taxpayers, European Parliamentarians  care about Ethiopia, democracy, development in  Ethiopia, the efficiency of development assistance but the problem is they don’t know what happens in Ethiopia. They are fooled by the leaders; leaders in the council of ministers and in the European commission. And also the development industry prevailing should continue without trouble. That is their vested interest. The tragedy is many people don’t understand what is happening in Ethiopia.  I was very happy that finally EU human rights sub-committee came last July. They are very serious, knowledgeable colleagues of mine. It was eye opener. They asked to visit Kalite Prison and the PM allowed them but was rudely treated by the Prison administration. That is an eye opener.
AS - EU and Ethiopia are development partners today as well as then. When you were not on good terms with the regime in 2005 did EU stand by your side?
Ana Gomes - The then commissioner in charge of foreign affairs and human rights stood by me always. She was not from my party but very serious. I appreciated. But the then development commissioner Mr. Louis Michel didn’t support me. Some people from his services in Brussels even tried to rewrite my report to water it down. I didn’t accept that. Several moments, my views were attacked. They supported the campaign against me which the government of MelesZ enawi spread. But Meles has gone! This is a new timing. I am pleased I was granted visa without preconditions.
AS - You were lobbying with the EU member states accusing the Ethiopian government of violating human rights. Do you think the situation has improved now?
 Ana Gomes - I know it was not easy for the new PM to assert his role as PM.  I know there was a lot of internal fighting within the power. He is not a Tigrian.  I value the visa I was given. I value the move against corruption. I sense some change.
AS - I saw you with the speaker of the house of people’s representative, AbadulaGemeda and Ambassador Teshome Toga. You had lunch with them may be. But you were not on good terms with them?
Ana Gomes - There was nothing personal; even with Meles Zenawi.  Even these professionals who were instrumental, I have nothing personal against them.  I don’t pretend to know well this country.  Ethiopian people really marveled me. Ethiopia has a great resonance in my country.  My ancestors 500 years ago were looking for Prester John.  However, Ethiopia has a magical resonance in my childhood. Ethiopia is special. Ethiopia is a civilization; not any country. It is a civilization.
 AS – You said “the EU is not only misusing European taxpayer’s money, but supporting an illegitimate status-quo, letting down all those who fight for justice and democracy and increasing the potential for conflict in Ethiopia and Africa.” But conflict in Ethiopia rises sometimes due to terrorist threats. Do you agree?
Ana Gomes - Not only the Muslim-Christian conflict Meles Zenawi fueled by trying to interfere in the Muslim community leadership but also in Ogaden.  All the report we receive in the EU are disastrous, horrendous and I am very sorry to see the Ethiopian army involved in all of thatTerrorism is an excuse; subversion was in the days of the dictatorship in my country.  Now the buzzword is terrorism. It serves to excuse, and to erase any rules, principles and values. I don’t accept it. I am very conscience of the terrorist threat. It is strong democratic societies who are better empowered to fight terrorism, not those with high level of poverty, unemployment and of internal conflict. That is the situation in Ethiopia now. I hope this can be sorted out.
AS - “Western leaders resist speaking up against Zenawi’s regime by invoking stability interests. Besides attempting to depict Ethiopia as a success story of development assistance, EU and the US like to portray their ‘aid darling’ as a partner in the fight against terrorism and a crucial actor for stability in the horn Africa,” do you still believe in this statement of yours?
Ana Gomes - I hope Ethiopian people will be able to make the distinction between this bankrupt leadership in Europe which brought us into the big economic crises which is also political crises and the people of Europe who really are serious about democracy, human rights and the rule of law.
 AS - Do you think the EU and the USA still see the regime as a partner and a crucial actor for stability or do you see any change in their position?
Ana Gomes -  I think they do. But on the other hand they also appreciate the limits of that partnership in the sense that they understand the big tensions that have been developing in Ethiopia and in the region; namely lack of effectiveness in fighting terrorism and deterring terrorism to infiltrate. I think the Americans understand it better.
Within the Obama administration there is a realization that you cannot have security without real development, not fake development and numbers but without democracy. The Americans were much more effective in getting people out of jail. The American’s pressure had political prisoners freed; opposition leaders and Birtukan Medeksa and others. They realized these three elements are linked, although they have their own flout in fighting terrorism. I was told the new American ambassador to Ethiopia is outspoken about human rights. I hope it translates into a more principled approach on the part of the Obama administration.
AS – a lot of Ethiopians respect you. They gave you an Ethiopian name. Ethiopians like honesty. Are you aware of your name? Do you know what it means?
Ana Gomes - Yes! I am aware of it. Ethiopian friends told me about it. They told me “Ana Gobeze” I am flattered, I don’t deserve it. They told me that ‘Gobez’ means brave. I have been happy meeting Ethiopian community in different countries and also received fantastic ‘Kaba’ as a gift from Ethiopians inSweden.

የ“ሎሚ” መፅሄት ዋና አዘጋጅ ክስ ቀረበበት



ሎሚበትግራይ ክልል ፖሊስ ክስ የቀረበበት የ“ሎሚ” መፅሄት ዋና አዘጋጅ ሰናይ አባተ የክሱ መነሻ በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም “የትግራይ እስር ቤትና ጓንታናሞ” በሚል ርዕስ የታተመ የአቶ አስገደ ገብረስላሴ ፅሁፍ እንደሆነ ገለፀ። በትግራይ ክልል ሁለት ልጆቻቸው መታሰራቸውን በመጥቀስ አቶ አስገደ ባቀረቡት ጽሑፍ፣ እስር ቤቱ በተራራ የተከበበ አስጨናቂ ሸለቆ በማተት አሸባሪዎች ከሚታሰሩበት፣ ከጓንታናም ጋር አመሳስለውታል፡፡ የትግራይ ፖሊስ በበኩሉ፣ የአቶ አሰገደ ጽሑፍ የእስረኞች አያያዛችንን ለማጠልሸት እና የፖሊስን ተአማኒነት ጥርጣሬ ላይ ለመጣል ያለመ ነው ሲል ክስ ማቅረቡን የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ተናግሯል፡፡ ሐሙስ ረፋድ ላይ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተገኝቶ ቃሉን የሰጠው ዋና አዘጋጁ፤ “ፅሁፉ በሎሚ መፅሄት ከመታተሙ በፊት በኢትዮ ምህዳር ጋዜጣም ላይ ተስተናግዷል” ብሏል፡፡ ታተመ የመጣ ጽሑፍ በህግ ሊያስጠይቅ የሚችለው ከስድስት ወር ላልበለጠ ጊዜ እንደሆነ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ላይ የተገለፀ ሲሆን፤ ፅሁፉ ከተስተናገደ ከሰባት ወራት በኋላ ክስ የቀረበበት ምክንያት አልገባኝም ብሏል – ሲሳይ አባተ፡፡ “አቶ አሰገደ ትግራይ ውስጥ እየበጠበጠ ያለ ሰው ነው፤ ፅሁፉን እንዴት አግኝታችሁ አስተናገዳችሁ” በሚል በመርማሪዎች ጥያቄ እንደቀረበበት የገለፀው ዋና አዘጋጁ ሲሳይ አባተ፤ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች ላይ በመፃፍ የሚታወቁት አቶ አሰገደ ፅሁፉን ልከውልን እንዳስተናገድን ተናግሬያለሁ ብሏል፡፡
ናፍቆት ዮሴፍ

ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር በተያያዘ በሳውድ አረቢያ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ማንዣበቡን ኢትዮጵያውያን ተናገሩ


በሳውድ አረቢያ የሚታየው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ዜጎች። ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያን በእስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ። ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀናቸውን ይጠባባቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺ Africansየሚቆጠረውን ስደተኛ ለማስተናገድ የመደበው የሰው ሀይል 40 ብቻ ነው። የሳውድ አረቢያ መንግስት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ምድር ተጠራርገው እንዲወጡ እየቀሰቀሰ ነው። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አደጋ ሊፈጠር ይችላል ብሏል  አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ጋዜጠኛ።
በዛሬው እለት በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተነው የኤስ ኤም ኤስ መልዕክት  ህጋዊ ለተባሉትም ሆነ ህገወጥ ለሚባሉት ኢትዮጵያውያን የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ይላሉ እኝህ ጋዜጠኛ።
በሞባይል ስልኮች የተበተነው ኤስ ኤም ኤስ ኢትዮጵያውያንን ቀጥራችሁ የምታሰሩ እንዲሁም መኖሪያ ቤት ያከራያችሁ ሁሉ በአስቸኳይ እንድታስወጡ፣ ይህን ባታደርጉ ግን 100 ሺ ረያል ትከፍላለችሁ የሚል እንደሆነ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ይህን መልእክት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተከራዩበት ቤት ተባረዋል። 9 ኢትዮጵያውያንን ወደ አስጠጋው ኢትዮጵያዊ በመደወል መታሰቢያ ቀጸላ አነጋግራቸዋለች። እርሱ እንደሚለው መልክቱ መተላለፉን ተከትሎ ጓደኞቹ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርጎ በእርሱ ቤት ተጠልለዋል::
ከቤታቸው ከተባረሩት መካከል አንዱ ከ8 ወራት በፊት አባቱ ቤታቸውን ሸጠው ፣ በኪራይ ቤት እየኖሩ በህጋዊ መንገድ እንደላኩት ይናገራል። አሁን ቤትክን ለቀህ ውጣ ተብሎ ህይወቱ አደጋ ላይ ወድቋል::
የሳውዲ መንግስት በኦፊሴል እንዲህ አይነት መልክት ያስተላልፍ እንደሆነ የጠየቅነው ጋዜጠኛ፣ መንግስት በቀጥታ እንዲህ አያደርግም ነገር ግን እርሱ ባሰማራቸው ሰዎች አማካኝነት መልክቶችን እንደሚሰድ ይታወቃል ብሎአል።
የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ዘመቻ በማድረግ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት መታደግ ሲችል በቀን ይህን ያክል ሰው አስመጣሁ በማለት ፕሮፓጋንዳ ይነዛል የሚለው ጋዜጠኛው፣ በሳውዲ የቀረው ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት የተመለሰውን በብዙ እጥፍ ይበልጣል ሲል በአገሪቱ ያለውን እውነታ አስረድቷል።
በሌላ በኩል ከሳውድ አረቢያ ወደ የመን የገቡ 3 ሺ ያክል ኢትዮጵያውያን በምግብ እጥረት ተጎሳቁለው እንደሚገኙ እስር ቤት ድረስ በመሄድ ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሀይማኖት ጎብኝቷቸዋል።

fredag 29. november 2013



ESAT NEWS 28/11/2013
ESAT NEWS 29/11/2013
ESAT NEWS 27/11/2013

ተዋርደን አንቀርም!!!

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡

ወቅታዊ ችግሮቻችን የራሳችን መንግሥት ባለቤቶች እንድንሆን 

ይበልጥ ሊያበረቱን ይገባል!


በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ ሳቢያ ከሀገራቸውና ከትውልድ ቀያቸው ተፈናቅለው በዐረቡ ዓለም በተለይም በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ ሰሞኑን እየደረሰ የሚገኘውን ዘግናኝ ሰቆቃና ግድያ በመሪር ስሜትና በንቃት እየተከታልን ነው። አበው “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳው አይቀበለውም” እንዲሉ እነዚህ ወገኖቻችን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ‹የሀገራቸው መንግሥት ነው› የሚባልለት የወያኔው መንግሥት እንኳንስ በባዕድ ሀገር በሚገዛው ሀገርም ውስጥ የሚያካሂደውን የመብት ገፈፋና ሕዝቤ በሚለው ዜጋ ላይ በዘር እየከፋፈለ የሚያራምደውን የግፍ አገዛዝ ዐረቦቹም ሆኑ ቀሪው ዓለም ያውቁታል። በመሆኑም ለነዚህ ምሥኪን ዜጎች የሚጮኽላቸውም ሆነ ለመብታቸው መከበር የሚቆረቆርላቸው አንድም መንግሥታዊ አካል እንደሌለ ከበፊት የተገነዘቡት እውነታ ነው። በወገኖቻችን ላይ ይህን ሁሉ ሰማይና ምድር የማይችሉት የግፍ ቁልል እነዚህ የዐረብ መንግሥታት የፀጥታ ኃይሎች ሲከምሩባቸው ማንም ዝምባቸውን እሽ የሚል ወይም ጠንከር ባሉ ቃላት እንኳን ተቃውሞ የሚያቀርብ አካል እንደማይር ያውቃሉ። ለዚህም ነው ታላላቅ የሚዲያ አውታሮች ሳይቀሩ ሀገሪቷንና ሕዝን በመናቅ በዝምታቸው መግፋትን የወደዱት። ይህ ነገር ከሃይማኖትም ይሁን ከቀለም፣ ከዘርና ከፖለቲካዊ እሳቤዎች አኳያ የሰው ልጅ ተፈጥሮን ባሕርይና የሀገራትንና የመንግሥታትን ተጻራሪ ድርብ አቋሞችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። “ሰው ለሰው የሚጨነቀው፣ ምን ዓይነት ሰው ሲጎዳ ወይም ምን ዓይነት ሕዝብና የትኛው ሀገር ችግር ላይ ሲወድቅ/ሲወድቁ ይሆን?” በሚል ከፍተኛ ፍልስፍና ውስጥ የሚያስባ ልዩ አጋጣሚ ፈጥሯል። በእውኑ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ በበለፀጉ ሀገሮች የአንድ ንጉሥ-ንግሥት ንብረት ከሆነች ውሻ ያንሳሉን? ንግሥት ኤልሣቤጥ የሚወዷት የቤት ድመት ወይም የንጉሥ አብደላ የቤተ መንግሥት ውሻ ቢሞቱ ሲኤንኤንንና ቢቢሲን የመሳሰሉ ላለው የሚያሽቃብጡ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት የመክፈቻ ዜናቸው እንደሚያደርጓቸው አይጠረጠርም። ወትሮም ብሂሉ “ላለው ይጨመርለታል” ነውና። እንደዚህ ያለው አካሄድ በውነቱ ቅስምን የሚሰብርና ከ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሰለጠነ የሚባል ማኅበረሰብ የሚጠበቅ አልነበረም።

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)

Ginbot_7_Logo_Lሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።
ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።
ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።
እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus, the Minister of Foreign Affairs of Ethiopia.
እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።
በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።
የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።
ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።
ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።
እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።
ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?

«አንድነታችንና እኩልነታችን በኢህአዴግ መቃብር ላይ ይረጋገጣል» የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን)

«አንድነታችንና እኩልነታችን በኢህአዴግ መቃብር ላይ ይረጋገጣል» የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን)

ከትህዴን የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

በህዝብ የተተፋው የኢህኣዴግ ስርአት። የተለያየ ምክንያቶችን እየፈጠረ ህዝብን በማደናገር የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል እንደ አንድ አላማ ይዞ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፣ ይህንንም አላማው ከግቡ ለማድረስ እየተጠቀመባቸው ካሉ ዘዴዎች መካከል። በተለያዩ ስሞች የተሰየሙ በዓላትን በአዋጅ መልክ እያወጣ። ህዝቡን የቤቱን ጉዳይ ትቶ በነዚህ በዓላት እንዲያተኩር ማድረግ ነው፣ በዚህም በእያንዳዱ ወር በዓላት ተሰይመው እንዲቀመጡ ተደርጓል፣ እነዚህ በአዋጅ የተቀመጡ በዓላት። 
ስርአቱ ለስልጣኑ አስጊ የሆነ ነገር ሲፈጠር የህዝቡን የአተኩሮ አቅጣጫን ለመቀየር አስቦ ከሚያቅዳቸው ሲሆን እንደ አብነት ለመጥቀስ ያክል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በስርአቱ ተግባሮች ተማሮ ስርአቱን በመቃወም እንዳይነሳሳና በመስጋት ለሰራዊቱ ተቆርቋሪ በመምሰል የካቲት 7 የሃገር መከላከያ ሰራዊት በዓል ቀን ሲል ሰየመ። ስርአቱ በአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች መሃል እየገባ እየፈጠረው ያለው የመበታተን እርምጃ። ህዝቡ ሊነቃበት በጀመረበት ግዜም ቢሆን። በማሃከላቸው ገብቶ ፍቅር፤ አንድነትና መቻቻልን እንዲሰፍን እንደሚፈልግ መስሎ በመቅረብ ህዳር 29 ቀን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብሎ በመሰየም በየአመቱ እንዲከበር በማድረግ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ በማሰብ ብቻ በሃገርና በህዝብ ሃብት ይጫወታል፣ በሌላ በኩል የአገራችን ከተሞች በመብራትና ንፁህ የመጠጥ ውሃ፤ የኑሮ ውድነትና ሌሎች መሰረተ ልማት እጥረት ባጋጠማቸው ግዜ። የከተማው ነዋሪ ህዝብ ከማንም ግዜ በላይ ተማሮ የስርአቱን እውነተኛ ገፅታና ምስል ሊረዳ በጀመረበት ግዜም። ህዳር 11 የከተሞች ቀን ብሎ በመሰየም። በብዙ ሚልዮን የሚገመት ገንዘብ እንዲወጣ በማድረግ። ዛሬም እንደተለመደው በባህርዳር ከተማ በዓሉን ለማክበር ሽሩጉድ ሲል ይታያል፣ ለመሆኑ በየትኞቹ ከተሞች ነው በዓላቱ እየተከበሩ ያሉት? እነዚህ ብንፁህ ውሃ እጥረት እየተሰቃዩና ለተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች ነዋሪዎቻቸውን በማጋለጥ ለሞት እየዳረጉ ያሉ ከተሞች? እነዛ በመብራት ሃይል እጥረት የምግብ ማብሰያ አጥተው በጨለማ ቤታቸው ሆነው በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ በሚኖሩባቸው ከተሞች? ወይስ በመልካም አስተዳደር እጦትና በተወሰኑ ፈላጭ ቆራጭ ባለስልጣናት አበሳውን እያየ ያለው የከተማው ነዋሪ? በየትኞቹ የማይታወቁ የኢትዮጵያ ከተሞች ነው ይህንን የማታለያ በዓልና ዳንኬራ እየተደረገ የሰነበተው፣ ከኢህአዴግ የተማርናቸው ተግባራት ካሉ በእያንዳንዱ ወራት የተለያዩ በዓላት በማስቀመጥ ህዝባችንን ከስራ ውጭ ማድረግና በተለይም ለአያሌ ዓመታት ተምሮ ስራ አጥቶ እየተንከራተተ የሚውል የተማረ ወጣት ሃይል በስርአቱ ላይ ተቃውሞ እንዳያስነሳ በዓሎች በመጡበት ቁጥር ተደናግሮ እየጨፈረ እንዲውል ለማድረግ ሆን ተብሎ እየተካሄደ ያለ ነው። 

አሁንም ለመጪው ህዳር 29 ቀን የሚከበረው የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሶማሌ ክልል እንድያዘጋጅ እየተደረገ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፣ ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለምን ይሆን የተመረጠው? ተረኛ ስለሆነ ወይስ በዓሉን ለማዘጋጀት የሃላፊነት እጣ ስለደረሰው? እዚህ ላይ ልንረዳው የሚገባን ነጥብ አለ። የኢህአዴግ ስርአት ሁሉንም የሚያደርገው እንቅስቃሴ ጥቅሙን ማእከል ያደረገ ስለሆነ። በያዝነው ዓመት የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንዲደረግ መወሰኑ ዋነኛው ምክንያት። የኦጋዴን ህዝብ የስርአቱን ፀረ ህዝብ ተግባሮች ከመጠን በላይ ስላንገፈገፈውና ከዚህም በመነሳትም የተለያዩ አመፆችና ትግል በማድረግ ላይ በመሆኑ። በክልሉ ሰላም እንዳለና የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን እንደሆነ ለማስመሰል፤ በሚከበረው በዓል አሳብቦ የህዝቡን ቀልብ ለመሳብና እኩልነታቸው እንደተረጋገጠላቸው አስመስሎ። ለአገራችን ህዝብና ለአለም ማህበረሰብ ለማደናገር ያለመ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ የስርአቱ ተንኮል ነው።

ለማጠቃለል የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጭ ስርአት አገርንና ህዝብን ወደ ውድቀትና ኋላ ቀርነት ለማስገባት የተዘጋጀ ስርአት ስለሆነ። የአገር መከላከያ፤ የከተሞች፤ የብሄር ብሄረሰቦችና የባንዴራ ቀን ወ.ዘ.ተ እያለ በዓላት ቢደረድርም። ለህዝብና ለሃገር አስቦ ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች ጥቅም ለማረጋገጥና ስልጣኑን ለማራዘም አልሞ መሆኑን የሚታወቅ ነው። ስለዚህ ዛሬም ይሁን ነገ የኢህአዴግ ስርአት በዓላት ለመፈብርክ ስለማይቸግረው ህዝባችን በስርአቱ እኩይ ተግባሮች ሳይደናገር። አንድነቱን ለማጠናከርና እኩልነቱን ለማረጋገጥ፤ ብሄሮችና ብሄረሰቦች በፍቅርና በአንድነት ተቃቅፎው እንዲኖሩ፤ኢትዮጵያዊነታችን እንዲከበር፤ በማንነታችን እንድንኮራና ችግራችን እንዲያበቃ ከተፈለገ። የስርኣቱ ግብኣተ መሬትን ማቀላጠፍ ይገባናል።

የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ

የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ
---------------------------------------------------
ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡
ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. የፓርቲዎች ቁጥርስ ለምን በዛ?
2. በህግ አግባብ የተመዘገቡ ስንት ናቸው?
3. በፕሮግራምና በርዕዮተ ዓለም ልዩነታቸውና ተመሳሳይነታቸው ምን ይመስላል?
4. የምርጫ ሥርዓታችሁ የትኛው ነው?
5. በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር ስንት ይሆናል?
6. ተቃዋሚዎች ከህዝብ ጋር ለመገናኘት ምን ዘዴ ትጠቀማላችሁ? በገጠርና በከተማስ ምን ይማስላል?
7. ከዲያስፖራ ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ እንዴት ያለ ነው?
8. ከሌሎች ሀገራት ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ ወይ?
9. የአውሮፓ ህብረት ምን ማድረግ (ማገዝ) ይችላል?
10. ህብረ-ብሄራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የቁጥራችሁ ምጣኔ

ከተሰጡት መልሶች የሚከተሉት የዶ/ር ነጋሶ ሀሳብ ይገኙበታል፡-
ኢህአዴግና የመሰረተው መንግስት ህገ መንግስቱን በመጣስ መካናቸውን፤
ህገ- መንግስቱን የሚጥሱ ህጎችን ማውጣት ብርቁ እንዳልሆነ፤
የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ጥግ ድረስ ማድረሱን፤
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በውሸት ክስ እያሰሩ ፓርቲዎችን እንደሚያዳክሙ ለምሳሌ አንዱአለም አራጌና በቀለ ገርባ፤
ተቃወሚዎች ልሳን እንዳያሳትሙ እንደሚደረግና እንደሚዘጋባቸው ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲዋ ፍኖተ-ነፃነት፤
የቢሮና የአደራሽ ኪራይ መከለልከል፤
የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማድረግ መከልከል፤
ቅስቀሳ ማድረግ መከልከል (ሰዎች፣ የቅስቀሳ መሳሪያዎችና መኪኖች እንደሚታሰሩ)፣
ሁል ጊዜ ያለው ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ድብደባ፣ ጠለፋ፣ ማሰቃየት፤
አባላትን ከመሬት፣ ከስራና ከቤታቸው ማፈናቀል፤
በውሸት ተቃዋሚዎችን ከአሸባሪዎች ጋር ማዛመድ፤
የስም ማጥፊያ ፊልሞችን መፈብረክ፤
እንቅስቃሴን መገደብ፤
መንግስት ፍትሃዊ የሆነና በህግ አግባብ የተቀመጠ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ ሲገባው ያለማድረግ፤
ዜጎችን ዘር ማጥፋት እስኪመስል ድረስ ከይዞታቸው ማፈናቀል፤
ለውይይትና ለድርድር እንቢ ባይ መሆን የሚሉ የኢህአዴግ ባህሪያት ቀርበዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ምን ማድረግ ይችላል ለሚለው ደግሞ የሚከተሉት ማሳሰቢያዎች ተሰጥተዋል፡-
------------------------------------------

ለልማትና ለማህበራዊ ጉዳዮች ድጋፍ አትሥጡ ባይባልም ኢህአዴግ ግን የተሰጠውን ዕርዳታ
1. የራሱን ቢሮክራሲ እንደሚያጠናክርበት
2. አፋኝ የፀጥታና የፖሊስ ኃይሉን እንደሚያጠናክርበት
3. የፓርቲውን መዋቅሮች እንደሚያደራጅበት እንዲያውቁ ተብሏል፡፡ በቅርቡ እንኳ የአውሮፓ ህብረት የሰጠውን 217 ሚሊዮን ዩሮ ይህ ሳይጠና መሆን እንዳልነበረበት

ተቃዋሚዎቹ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር ሥልጣን ተቆርሶ እንዲሰጣቸው ሳይሆን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው እንዳይገደብና እውነተኛ ምርጫ እንዲደረግ ምህዳሩ መስተካከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በአጠቃላይ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲከበር ጫና እንዲያደርጉ፤ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲደራደር እንዲያግባቡ የሚሉ ናቸው፡፡
አቶ ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሁኔታው ወደ አስከፊ ደረጃ እያዘገመ በመሆኑና የኢህአዴግ ባህሪ ፍፁም አምባገነናዊ በመሆኑ ከንግዲህ ኢህአዴግ አጋር እንደማይሆናቸው ገልፀዋል፡፡
አቶ ልደቱ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የታይታ (window dressing)፣ በህብረተሰቡ፣ በተቃዋሚዎችና በመንግስት በኩል ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል እንዳለ፣ ድህነት በበኩሉ የዴሞክራሲ ጠንቅ መሆኑ፣ ነፃ የዴሞክራሲ ተቋማት እንደሌሉና መንግስትና ፓርቲ እንደማይለዩ አስረድተዋል፡፡

ሰብሳቢዋ በበኩላቸው “COMPREHENSIVE SYSTEM OF DIALOGUE” እንዳላቸው፣ ጠ/ሚ/ሩን በአመት ሁለቴ እንደሚያገኟቸው፣ በፀረ ሽብር ህጉ ህገ ወጥነት እንደሚያምኑ፣ ለ2007ቱ ምርጫ ከወዲሁ ዝግጅት እንደጀመሩና የምርጫ ግብረኃይል
እንዳቋቋሙ ገልጸዋል፡፡ አና ጎሜዝ በበኩላቸው ከኢትዮጵያኑ ባልተናነሰ የመንግስትን ባህሪያት ሲተነትኑ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ውይይት ብዙ ነገር እንደማይጠብቁ በማጠቃለያ ሀሳባቸው ገልጸውልናል፡፡

የኢህአዴግ ህገ ወጥነት ኃ/ማሪያም አሁንም ከህገ ወጥ ስደቱ አልተመለሱም፡፡ኃ/ማሪያም እያሉ ቴወድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን በቲውተር ሲመራው ሰንብቷል፡

የኢህአዴግ ህገ ወጥነት
ኃ/ማሪያም አሁንም ከህገ ወጥ ስደቱ አልተመለሱም፡፡ኃ/ማሪያም እያሉ ቴወድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን በቲውተር ሲመራው ሰንብቷል፡፡

ወደ ሳውዲ አረቢያ ተሰደው በደል ተፈጽሞባቸው የተመለሱትን ዜጎቻችን መንግስት የተባለው አካል ሳይቀር ‹‹ህገ ወጦቹ ተመለሱ!›› ሲል ዜና አሰምቶናል፡፡ እነዚህ ዜጎች በሳውዲም በኢትዮጵያም ባይተዋር ናቸው፡፡ ተሰደውም ስደተኞች፣ ሳይሰደዱም ስደተኞች ናቸው፡፡ ዜጋ ሆነው እንኳን የዜግነት መብት አይሰጣቸውም፡፡ ስደተኞች ሆነው የስደተኛ መብት የላቸውም፡፡ ሰብአዊ ፍጥረት ሆነው ሰብአዊ መብት የላቸውም፡፡ ሰራተኛ ሆነው የሰራተኛ መብትና ጥቅም አልተከበረላቸውም፡፡ ልክ እንደ ኃ/ማሪያም የሚባሉትና የሆኑት የተለያዩ ናቸው፡፡

አቶ ኃ/ማሪያም ኢትዮጵያውያኑ ድሆች ዜጋ ተብለው ዜጋ እንዳልሆኑት፣ ስደተኛ ተብለው ዓለም አቀፍ የስደተኛ መብት ያልተከበረላቸው፣ ሰርተው የድካማቸው ያልተከፈላቸው፣ መንግስት አላቸው እየተባለ መንግስት ያልደረሰላቸው፣ ኤምባሲ ተከፍቶ ስቃያቸውን ያላቀለለላቸው አይነት ኢትዮጵያውያን፡፡ አቶ ኃ/ማሪያም ልክ እንደነዚህ ኢትዮጵያውያን የስም እንጅ ተግባራዊ ጥቅም፣ ተግባራዊ መብት፣ ተግባራዊ ስልጣን የላቸውም፡፡

እንደ ስም ቢሆንማ ህገ መንግስቱ አቶኃ/ማሪያም ለተሸከሙት ስልጣን የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመምራትና በመቆጣጠር ስልጣን ይሰጣል፡፡ ዜጎች በሌሎች አገራት ሲሰቃዩ፣ ችግር ሲደርስባቸው የውጭ ጉዳይን ይመራል፡፡ ለጉዳዩ አፋጣይ ምልሽ ይሰጣል፡፡ ዜጎችን ይታደጋል፡፡ ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል፡፡

አቶ ኃ/ማሪያም ልክ ዜጎቻችን መብቶቻቸው ሁሉ ተደፍጥጦ ታስረው እንደነበሩት ሁሉ ህገ መንግስቱ የሰጣቸውን ስልጣን እንዳይወጡ ተደርገው ቆይተዋል፡፡ በእርግጥ ይህ የኢህአዴግ ህገ ወጥነት ነው፡፡ የእርሳቸውም ቢሆን ያው ነው፡፡ ስልጣን ካልሰሩበት ለምን ይቀበላሉ? የውጭ ጉዳዩን መምራት ያለባቸው ኃ/ማሪያም እያሉ በእርሳቸው ትዕዛዝ ስራውን ማከናወን የነበረበት ቴወድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን በቲውተር ሲመራው ሰንብቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን መብታቸውን ተነፍገውና ሲሰቃዩ ቆይተው ‹‹ህገ ወጥ›› ተብለው ከተመለሱ በኋላ አቶ ኃ/ማሪያም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲመስሉ ተደርገዋል፡፡ በህገ መንግሰቱ መሰረት የውጭ ጉዳይን እንደሚመሩ ተነግሯቸው፣ ዜጎች እየሞቱ በዓመት 2 ዲግሪ ስለሚጨምረው የዓለም ሙቀት ሲያወሩ ሰንብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን እየሞቱ የጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውን ሳይወጡ ለራሳቸው ስለማያንሱት ደቡብ አፍሪካን የመሰሉ አገራትን ወክለው ሲናገሩ ሰንብተው ተመልሰዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ ስለ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለ ዜጎቻችን ስቃይ ሊያወሩ የተፈቀደላቸው፡፡ ያም ሆኖ ተመጥኖ ተሰጥቷቸው፡፡ ያም ሆኖ እነ ሳውዲን እያደነቁ፡፡ ያም ሆኖ ለዜጎች ያልቆመውን መንግስት እያወደሱ፡፡

ይህን ያየ አቶ ኃ/ማሪያም እራሱ ስደተኛ ነው መሆናቸውን ለመረዳት አይከብደውም፡፡ አብዛኛዎቹ ዜጎቻችን ተመልሰዋል፡፡ ህገ ወጥ ተብለውም ባይተዋር ወደሆኑባት አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ አቶ ኃ/ማሪያም ከስልጣን ባይተዋርነታቸው ባይወጡም፣ በትዕዛዝ መናገራቸውን ባያቆሙም፣ በካድሬዎች መታዘዝ ባይቀርላቸውም እጅግ ዘግይተው ተመልሰዋል፡፡ ዜጎቻችን ዘግይተው ተመልሰው ሳይገባቸው ‹‹ህገ ወጦች›› ተብለዋል፡፡ አቶ ኃ/ማሪያም ወደ መናገር ተመልሰውም የሚናገሩት ለሳውዲዎች ነው፡፡ በእርግጥ ካለመናገር መናገር ይሻላል፡፡ ግን ከተለመደው ህገ ህገ ወጥነት አልተመለሱም፡፡

#‎Miniliksalsawi‬

torsdag 28. november 2013

ከሳዑዲ የተመለሱ 7000 በላይ ኢትዮጵያዊያ በአደገኛ ሁኔታ የመን ውስጥ…

ከሳዑዲ የተመለሱ 7000 በላይ ኢትዮጵያዊያ በአደገኛ ሁኔታ የመን ውስጥ…


በባህር ተሻግረው በየመን በኩል ያንን እልህ አስጨራሽ በረሃና ፈተና አልፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ከአበሀ፣ ከሚስ ምሽት፣ ናጂራንና አሲር… ከመሳሰሉት የመን ድንበር አቅራቢያ ያሉ የሳዑዲ ከተማዎች ላይ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን እየገቡ ነው፡፡ ጅዳ ሄደው ወደ ሀገራቸው ለመግባት የማይችሉ በመሆኑ የመን መግባት አማራጭ ሆኖባቸዋል፡፡ 
ምክንያቱም ወደ ጅዳ ለመሄድ በየቦታው ሊፍጸምባቸው ወይም ሊገጥማቸው የሚችለውን ችግር በማሰብ ነው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያዊያ ወደ የመን የገቡት በሁለት መንገድ ሲሆን አንደኛው ከላይ እንዳልኩት ያላቸው አማራጭ በመሆኑ ባሳቸው ፍላጎት ሲሆን ሁልተኛው እና ወደ 3000 የሚጠጉትን ግን የሳዒዲያ መንግስት የመናዊያኑን እንደ ቆሻሻ በጭነት መኪና አምጥቶ ድንበር ላይ ሲገለብጣቸው አብሮ የጫናቸው ናቸው፡፡
እነዚህ የሳዑዲ መንግስት አምጥቶ የገለበጣቸው ራሱ በሁለት መንገድ ይከፈላሉ፡፡ ድንበር ድረስ እንሂድ ብለው ለምነው የተጫኑ መኖራቸውን ካናገርኳቸው ልጆች ተረድቻለሁ፡፡ ሁለተኞቹ የሳዑዲ ፖሊሶች አፍነው ጭነዋቸው የሚያመጧቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከጅዳ ታፍነው የተጫኑ ሁለት ልጆች በስልክ አግኝቻለሁ፡፡ እርጉዞች የተደበደቡ የተደፈሩ ሁሉ ህዝቡ፣ መንግስት እንዳዳያቸው ተብሎ ወደ የመን እንደተጣሉ ነው ያናገርኩት ልጅ የገለጸልኝ፡፡
ሀረድ የሚገኘው IOM (International organization of migrant) ካምፕ እየተቀበላቸው ሲሆን በአሁኑጊዜ በፊት MSF( medical san frontan) ያዘጋጀውን ካምፕ IOM እየተጠቀመበት ስለሆነ እሱንም ከፍተውታል፡፡ ቢሆንም ይህ ቦታ ከሳዑዲ እና የመን ድንበር ከ 100 ኪ.ሜ በላይ ርቀት ስላለው ይህን ሁሉ መንገድ በእግር መጓዝ ግድ ብሏቸዋል፡፡ ያም ቢሆን መንገዱ በሰላም እንዳያልቅ መካከል ላይ አፋኞች ከሳዑዲ ገንዘብ ይዘው ነው የሚመጡት በማለት የተለያየ ጉዳት እያደረሱባቸው ነው፡፡ ዘርፈው፣ ደብድበው፣ ደፍረው ለፖሊስ ስለሚያስረክባቸው እንዲሁም መንገድ ላይ በቁጥጥር ስር ስለሚያውላቸው በአሁኑ ሰዓት ሰነዓ ኢሚግሬሽን (ጀዋዛት) እስር ቤት ከ3200 በላይ እንደሚገኙ አይቻለሁ፡፡
ባለፈው እርብ በወርሃዊ ፕሮግራማችን መሰረት እስረኞች ለመጠየቅ ስንሄድ 2700 አካባቢ ኢትዮጵዊያን ስደተኞች እስር ቤቱን አጣበውት ነበር፡፡ አሁን ግን ከ3200 በላይ በመሆናቸው እስር ቤቱ ሞልቶ ጊቢው ውስጥ እና ከጊቢው ውጭ ሁሉ ፈሰው ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ወገኖች በርሃብ እንዳይሞቱ ሁላችንም ማድረግ ያለብንን ማድረግ አለብን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሳዑዲ ላለው ስደተኛ በኢሳት ቴሌቪዥን አሰባሳቢነት የተጀመረው ነገር ከሳዑዲ ሸሽተው የመን ለሚገቡትም በርሃብ ሊያልቁ ነው እና ትኩረት እንዲደረግበት ጥያቄዬን አቀርባለሁ፡፡ በይበልጥ ሰሞኑን ወደ ቦታው በድጋሚ ሄጄ ማየት ስለምፈልግ ያለውን ሁኔታ አሳውቃለሁ::
በግሩም ተ/ሀይማኖት

ኢቴቪ ጠፍቷል ያለውን የአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልም ሙሉ ቅጂ አቀረበ

ኢቴቪ ጠፍቷል ያለውን የአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልም ሙሉ ቅጂ አቀረበ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር የሆነው አንዷለም አራጌና የብሄራዊ ምክር ቤት አባል ናትናኤል መኮንን በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ እነ አንዷለምን የያዝነው በቂ ማስረጃ ሰብስበን ነው ሲሉ ከቆዩ በኌላ የኢትዩጵያ ቴሌቪዥን ‹‹አኬልዳማ››የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም በማስረጃ መልክ ለእይታ ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡
በፊልሙ የአንድነት የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ የሆነው አንዷለም አራጌ ከግንቦት ሰባት ጋር ግኑኝነት እንዳለው በማስመሰል ከመቅረቡም በላይ የአንድነት አባላት ያልነበሩ በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦችን የፓርቲያችን አባላት መሆናቸውን እንዲመሰክሩ ተደርገዋል፡፡
በህጋዊ መንገድ ፓርቲያችን ከህዝብ ጋር ለመወያየት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የጥናት ጽሁፍ አቅራቢነት አዘጋጅቶት የነበረውን ውይይት በህቡዕ የተዘጋጀ በማስመሰል በፊልሙ ለክስ በሚመች መልኩ መቅረቡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረጃ አሰባስበን ነው የያዝናቸው ማለታቸውን ትዝብት ውስጥ የከተተ ነበር፡፡
አኬልዳማ ፊልም ለህዝቡ በቀረበበት ወቅት በፍርድ ቤት ጉዳያቸው መታየት ያልጀመረን ተጠርጣሪዎች ሽብርተኞች በማለት መፈረጁና በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲያችንን ጭምር ‹‹የግንቦት ሰባት ጉዳይ አስፈጻሚና የሽብርተኞች ተላላኪ››በማለት መፈረጁም አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ የጣብያው ሃላፊዎች እርምት እንዲያደርጉና በአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀን ፊልም ለህዝብ እንዲያሳዩ በደብዳቤ ጭምር ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ፓርቲያችን ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ተገድዷል፡፡
ጉዳዩን በ2004 ወርሃ ታህሳስ መመልከት የጀመረው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ልደታ የፍትሃ ብሔር ምድብ ችሎት መዝገቡን ለ15 ጊዜያት ከሳሽና ተከሳሽን ሲያከራክር ከቆየ በኋላ ለታህሳስ 11/2006 ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል፡፡ከትናንቱ ቀጠሮ ቀደም ብሎ የኢቴቪው ጠበቃ አኬልዳማ የተባለው ዶክመንተሪ ፊልም መጥፋቱን እንዲሁም የዶክመንተሪው ሃላፊ የነበሩት ግለሰብ ወደ ውጪ አገር በመሄዳቸው የተነሳ ቅጂውን ለማቅረብ ደምበኞቹ መቸገራቸውን ገልጾ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ዶክመንተሪውን የግዴታ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው በማዘዛቸው በተለዋጭ ቀጠሮ ቅጂውን ይዘው ቀርበዋል፡፡
የአንድነት ጠበቃ ተከሳሽ ያቀረቡትን ፊልም ቅጂ ለማመሳከር እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ይህንን ማዘዝ እንደማይችል በመጥቀስ ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 
ከዳዊት ሰለሞን

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር የሚሆኑት መቸ ነው?!!!

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር የሚሆኑት መቸ ነው?!!!

du_pm_haile_mar_desነፍሳቸውን ይማረውና(ድንገት ነፍስ ካላቸው፣መንፈስ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ነው)የቀድሞውና ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሞት ካረፉና ካረፍናቸው ጀምሮ ታላቋ ኢትዮጵያ ያለ ሀገረ ገዥ የቀረች ይመስላል፡፡ሆደ ቡቡነታቸውን ለመለስ ዜናዊ ሲነፋረቁ ያረጋገጥንላቸው ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ወንበሩ ላይ ቢቀመጡም እንደ ሁለት ወር ህጻን ከተጎለቱበት አላንቀሳቅስ ያላቸውን እርኩስ መንፈስ ሁለት ሰባት ቢታዘዝለት መልካም ነበር፣ነገር ግን ሰውየው በኢየሱሴ የዳኑ ናቸውና ጸበልን ከዚያው በጸበልህ የሚሉ መሆናቸው እኛ የእርሳቸውን ታማኞች መፍትሄ እንዳናዘጋጅ አድርጎናል፡፡ከሰሞኑ ደግሞ ይህ እርኩስ መንፈስ ምንም አላናግራቸው በማለቱ ጭንቀታችን የከፋ አድርጎታል፣መላ ያለህ ሁሉ ወዲ በል፡፡እርስዎስ ቢሆኑ በዚህ ቀውጢ ሰኣት ያልነገሱ መቸ ሊነግሱ ነው፡፡እኔ እንደው የእርስወ ነገር አያስችለኝምና ትንሽ ምክር ቢጤ ጣል ላድርግለዎት፣የ2007 ምርጫ ደርሶ ሱናሜው ሳይጠርግዎት ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቢሞክሯት መልካም ነው እላለው፡፡አይተ በረከት ስሞንስ እስከመቸ ነው የስሁል ሚካኤልን መንበር ተረክበው ሲሽሩና ሲሾሙ ምን አለበት አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚንስትር ቢያደርጓቸው፡፡(ስሁል ሚካኤል በጎንደር የነገስታት ዘመን ከትግራይ የመጡ መስፍን ሲሆኑ ከኋላ ሆነው ሲሾሙና ሲሽሩ የነበሩ ጉልበታም ናቸው)፡፡በመጨረሻም ለሃይለማሪያም ደሳለኝ የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖረኝ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፣ታሪክዎ ሲጻፍ ቤተ መንግስቱን ከሚጠብቁት ወታደሮች የተለየ አይሆንምና በጊዜ መላ ቢያበጁ፣ባይሆን ምን ማድረግ እንዳለብዎት ከጠፋብዎ አኔን ያማክሩኝ፡፡የሚሰማን የለምእንጅ ባለ ራዕይውንም መክረናቸው ነበር፡፡ምን ያደርጋል ምክራችን ይዘውት ሽል አሉ እንጅ፡፡
GASHAW MERSHA ZEGONDER


onsdag 27. november 2013

የሳዑዲ ጉዳይ የዛሬ አዳዲስ መረጃዎች

የሳዑዲ ጉዳይ የዛሬ አዳዲስ መረጃዎች – በነብዩ ሲራክ (ጋዜጠኛ)

foreign-workers- Arabiaዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከ40 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ገብተዋል ይሉናል፤ የሳዑዲ ባለስልጣናት ደግሞ 28 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ነው ወደ ሃገራቸው የላክነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ 13 ሺህ ሰው ከየት ሸቅበው ነው?… ለማንኛውም ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሚሰጠንን አዳዲስ መረጃዎች ይመልከቱ…
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ እነዚህን አዳዲስ ነገሮች አካፍሎናል፦
* ጅዳ …. ትናንት ከጅዳ ቆንስል አካባቢ ወደ ሽሜሲ ማቆያ እስር ቤት ከሌሊት እስከ ምሽት የሔዱት ወገኖች ቁጥር 1.500 እንደሆነ ታውቋል። መሔዳቸውን ተከትሎ በርካታ የተጨበጡና ያልተጨበጡ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው ።
በሚቀርቡት ቅሬታዎችን ለማረጋገጥ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እዚያው ሺሜሲ ካሉት ጥቂት እህቶች አነጋግሬ ነበር። የምግብና የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለና ፣ ምግብ እና ውሃ ሲታድ ጉልበት ያለው ብቻ ተጋፍቶ እንደሚበላ እና እንደሚጠጣ ገልጸውልኛል። የሻንጣ ኪሎውን ክፍያ ጉዳይም ነግረውኛል ። እዚህ ላይ እኔም ግራ የተጋባሁ ቢሆንም በቀጣይ ሰአታት ሁሉም ግልጽ ይሆናል። ምሬታቸውን ግን ለሚመለከታቸው አሳውቄያለሁ። ትልቁ ነገር በአሁኑ ሰአት ሰነዶች እየተሰሩላቸውና አሻራ በወረፋ እየሰጡ መሆኑን ከሃላፊዎች የሰማሁትን ከእህቶች ማረጋገጤ ነው! በአጠቃላይ ጅዳ ያለው ሁኔታ በተሻለ መንገድ መሔድ መጀመሩን ከሚደርሱኝ መረጃዎች ተነስቶ መናገር ይቻላል። ምክርና ዝክሩ ሰሚ ቢያገኝ በሽሜሲ ያለውን ሃይል አጠናክሮ በአጭር ጊዜ የበለጠ መስራት ይቻል ይመስለኛል !
* መካና መዲና … በትናንትናው እለት በመካ “ወደ ሃገራችን እንግባ! ” በሚል ተከስቶ የነበረው ድጥጫና አለመግባባት ዛሬ ገብ ብሎ ታይቷል ። በተመሳይ ሁኔታ በተከሰተው የትናንቱ ፍጥጫ ለየት ያለ እንደነበርና በሁከቱ ምክንያት ሰበብ አጠይባ ዩኒቨርሲቱ ተዘግቶ እንደ ነበር ተመልክቷል።
ሪያድ … ባሳለፍናቸው ስምንት ቀናት 28.000 ኢትዮጵያውን ወደ ሃገር ቤት መሸኘታቸውን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይህ በእንዲህ አንዳለ በርካታ ኢትዮጵያውያን በየመጠለያው የመጸዳጃ ፣ የምግብና የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለ ችግሩ በሰፊው እንዳለ ወደሚነገርበት አሚራ ኑራ መጠለያ ስልክ በመደወል ያነጋገርኳቸው ሳይቀር ገልጸውልኛል። በሪያድ ሃላፊዎችን ላማነጋገር ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም ።
* ደማም … ወደ ሳውዲ ሰራተኛ መላክ አቁሟል ቢባልም በኤጀንሲዎች መሰሪ የተቀነባበረ ሴራ ዜጎች ወደ ሳውዲ እየገቡ ነው ። 60 ያህል በአብዛኛው ኦሮምኛ እንጅ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ እህቶች በኩዌት በኩል ወደ ሳውዲ ደማም መግባታቸውንና መኖሪያና የስራ ፈቃድ ለመውሰድ ምርመራ ማከናዎናቸውን መረጃ ደርሶኛል። ወደፊት ዘርዘር አድርገን እናወራዋልን …
ቸር ያሰማን
ነቢዩ ሲራክ

tirsdag 26. november 2013

EU Member of Parliament Ana Gomes in Addis Ababa

EU Member of Parliament Ana Gomes in Addis Ababa


Ana Gomes, known for publicly criticising Ethiopia following the 2005 government crackdown
Serious talk! EU Member of Parliament Ana Gomes, known for publicly criticising Ethiopia following the 2005 government crackdown, which claimed over 200 lives, in a seemingly serious discussion during lunch break with Ethiopian MP and Speaker of the House Abadulla Gemeda in Addis Ababa, November 25, 2013. ANDUALEM SISAY | NATION MEDIA GROUP
The 26th European Union (EU) and African Caribbean Pacific (ACP) Joint Parliamentary Assembly (JPA) opened in Addis Ababa, Ethiopia Monday morning.
The assembly is expected to debate several issues, ranging from use of natural resources to fiscal reform and redistribution of wealth and decentralised cooperation.
The gathering is also expected to discuss respect for the rule of law and the role of an impartial and independent judiciary and South-South and triangular cooperation.
The assembly that will be concluded on Wednesday, has no decision-making powers.
However, it allows elected representatives of ACP countries to address their concerns directly to the EU Commission and be updated on the negotiations on trade deal, such as the Cotonou Agreement.
“There is an ample room for more enhanced partnership in many areas of interest to both sides,” said Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, while opening the assembly.
“But in a large sense, this relationship should not in any way be based on the rather obsolete assumption that one side is the ultimate provider and the other perennial receiver of resources whatever the object of the relationship might be – economic or political.”
JPA comprises 78 members of parliament and 12 vice-presidents from both sides (EU and ACP).
The assembly is expected to be concluded after discussing social and environmental impacts of pastoralism on ACP countries on the last day.
JPA meets twice a year, once in the EU, traditionally in the country holding the presidency of the Council of the EU and once in an ACP country, determined by the group of ACP countries.
Source: AFRICA REVIEW

ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።

ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።

fp01_big* ትላንት ማምሻውን በ 17 አውቶብስ ከሪያድ ድንበር ግዜያዊ መጠለያ ተጭነው አሚራ ኑራ እይተባለ የሚጠራ ዩንቨርስቲ ግቢ ባዶ ሜዳ ላይ አንተኛም ኤርፖርት ውሰዱን ብለው ከተሳፈሩበት አውቶብስ አንወርድም ብለው ያመጹ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ዛሬ ረፋዱ ላይ ሪያድ ሺሜሲ አካባቢ ወደ ሚገኝ አስርቤት ተወስደው የጣት አሻራ ሰጥተው መጨረሳቸውን እና ሊሴ ፓሴ መቀበላቸውን ማረጋጋጥ ተችሏል።
* በሌላ በኩል እዚሁ ግቢ ውስጥ አሁንም ከሳምንት በላይ የሆናቸው ከ 5 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ዳስ መጠለያ እና የመጸዳጃ ቦታ ሜዳ ላይ ተበትነው ቀን ጸሃይ ማታ ብርድ እይተፈራረቀባቸው እየተሰቃዩ መሆናቸው ከምንጮቻችን መረዳት ተችሏል።
* ትላንት ማምሻውን እዚህ ግቢ ግዜያዊ መጠለያ ሜዳ ላይ የተፈጠረውን ሁከት ለማርገብ የኤንባሲው ሃላፊዎች እና የመንግስት ሉኦካን ቡድን አባላቶች ቦታው ላይ መገኘታቸውን ምንጮች ይገልጻሉ ።
* ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።
* በትጠቀሱት ወገኖቻችን ስም ዲፕሎማቱ ከ 3 ወር በፌት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡ ለነዚህ ወገኖቻችን የአይሮፕላን ትኬት መግዣ የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማድረግ እስከ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ፡ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የሚናገሩ ወገኖች ይህ ጥሬ ገንዘብ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እጅ ላይ እንደሚገኝ፡ አክለው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ

ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።

ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።

fp01_big* ትላንት ማምሻውን በ 17 አውቶብስ ከሪያድ ድንበር ግዜያዊ መጠለያ ተጭነው አሚራ ኑራ እይተባለ የሚጠራ ዩንቨርስቲ ግቢ ባዶ ሜዳ ላይ አንተኛም ኤርፖርት ውሰዱን ብለው ከተሳፈሩበት አውቶብስ አንወርድም ብለው ያመጹ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ዛሬ ረፋዱ ላይ ሪያድ ሺሜሲ አካባቢ ወደ ሚገኝ አስርቤት ተወስደው የጣት አሻራ ሰጥተው መጨረሳቸውን እና ሊሴ ፓሴ መቀበላቸውን ማረጋጋጥ ተችሏል።
* በሌላ በኩል እዚሁ ግቢ ውስጥ አሁንም ከሳምንት በላይ የሆናቸው ከ 5 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ዳስ መጠለያ እና የመጸዳጃ ቦታ ሜዳ ላይ ተበትነው ቀን ጸሃይ ማታ ብርድ እይተፈራረቀባቸው እየተሰቃዩ መሆናቸው ከምንጮቻችን መረዳት ተችሏል።
* ትላንት ማምሻውን እዚህ ግቢ ግዜያዊ መጠለያ ሜዳ ላይ የተፈጠረውን ሁከት ለማርገብ የኤንባሲው ሃላፊዎች እና የመንግስት ሉኦካን ቡድን አባላቶች ቦታው ላይ መገኘታቸውን ምንጮች ይገልጻሉ ።
* ሰሞኑንን ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው ባሉበት አልቆ ለሃገራቸው መብቃት እየቻሉ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ መጠለያ መወሰዳቸው እያነጋገረ ነው ።
* በትጠቀሱት ወገኖቻችን ስም ዲፕሎማቱ ከ 3 ወር በፌት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡ ለነዚህ ወገኖቻችን የአይሮፕላን ትኬት መግዣ የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማድረግ እስከ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ፡ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የሚናገሩ ወገኖች ይህ ጥሬ ገንዘብ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እጅ ላይ እንደሚገኝ፡ አክለው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ጀዳ በዋዲ

በሽብርተንነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

በሽብርተንነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!


ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው።
በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ሰላማዊ ዜጎችን አግባብ ባልሆነና ባልተጨበጠ ክስና ዉንጀላ ማሰር፣ አፍኖ መሰወር፣ ንብረትን ማዉደምና መዉረስ እንዲሁም የአደባባይ ግድያ ባለፉት 22 የወያኔ  የአገዛዝ ዘመናት የተለመዱ ተግባሮች ሆነዉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይህ አምባገነናዊና ኢፍትሀዊ ተግባር በህግ ሽፋን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለገዥዉ ስርአት የአፈናና የጥርነፋ መዋቅር ተባባሪ ያልሆኑና ለመብታቸዉ መከበር የሚታገሉ ዜጎች በአሸባሪነት ስም በጅምላ እየታፈሱና እየታሰሩ ይገኛሉ። ታፍነዉ የተወሰዱና ያሉበት ቦታ የማይታወቀዉም ጥቂቶች አይደሉም። ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሽብርተኝነት ተወንጅለዉ ታስረዋል። ሰብአዊ መብታቸዉም በማንአለብኝነት እየተረገጠ ይገኛል። ከነዚህ ንፁሀን ዜጎች ዉስጥ ብዙዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች፤ የእምነት መሪዎችና ለሞያቸዉ ታማኝ የሆኑ ጋዜጠኞች መሆናቸዉን ስናይ ደግሞ ዘመቻዉ በሀገራችን ተጠናክሮ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ለመጨፍለቅና ህዝብን ከትክክለኛ መረጃ አርቆና አፍኖ ለመግዛት ታስቦበትና ሆነ ተብሎ የተያዘ ስልት መሆኑን ግልፅ ነው።
በሽብርትኝነት ያለመከሰስ መብቱን በጠመንጃ ያስከበረው ወያኔ ግን ሰላማዊውን ህዝቡ በተለያዩ መንገዶች  እያሸበረ የስልጣን ቆይታውን ለማርዘም ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ዜጐችን በማፈናቀል፤ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባትና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈል እያፋጀ የሽብር ሴራውን እየፈፀመ ይገኛል። ሰላማዊ ዜጋውን ፣አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን በልማት ስም ተወልዶ ባደገበት እትብቱ ከተቀበረበት ሃገር እያፈናቀለ ለስደት እየዳረገው ይገኛል፡፡ ለዚህም የሽብር ሴራው ሰለባ የሆኑት፤ የሚበሉት፤ የሚጠጡት እና በመጠለያ እጦት በየአደባባዩ ሰፍረው የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ የሚገኙት የአማራ ብሔረሰብ ወገኖቻችን ናቸው፤ እነዚህ ወገኖቻችን በሃገሪቱ አራቱም ማዕዘናት እየተፈናቀሉና እየተዋከቡ ይገኛሉ። ማፈናቀለ አልበቃ ያለው የወያኔ የሽብር መረብ ወደ እምነት ቦታዎችም በመዛመት ዋልድባን እና የተለያዩ የሃይማኖት ቦታዎችን በማፈራረስ በአለም ደረጃ እውቅና እና አድናቆት የተሰጣቸውን የሃገሪቱን የሃይማኖት፤ የታሪክ ቅርሶች በማውደም፤ ኢትዮጵያውያን በቀደምትነት በምንታወቅበት እምነታችን ላይ አደጋ በመፍጠር፤ አዋራጅ ድርጊቶችን በንቀት እና በጥላቻ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ ከእምነት ቦታዎች ባሻገር በአለም ደረጃ እውቅናን ካገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ ተጠቃሹ የታችኛው አዋሽ እና ኦሞ ሸለቆዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ቦታ ያራዊቶች እና የተለያዩ የደኖች ስብስብ ያለበት ሰፊ የሃገራችን ቅርስ የነበረው ሲሆን ዛሬ ላይ ግን ወያኔዎች በልማት ስም ለውጭ ባለሃብቶች አስረክበውት ድብዛው እየጠፋ ነው፡፡ አምባገነኑ ወያኔ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ያነሱትን የመብት ጥያቄ ወደ ጎን በመተው በእኔ አውቅላችኋለሁ እብሪት የተሞላ አስተሳሰብ በማፈን ንፁሃኑን ሙስሊም እየገደሉ ብሎም በሽብርተኝነት በመወንጀል እያሰቃዩት ይገኛሉ። ሙስሊሙ ህብረተሰብ የተቃውሞ ድምፁን ያሰማበትን አላማ ምንድነው? ችግሩስ ከምን የመነጨ ነው? ብሎ እልባት ከመስጠት ይልቅ ጥያቄአቸውን በማንቋሸሽ እና በማጥላላት በጠመንጃ አፈ ሙዝ የሚመልሱት ይመስል ህዝበሙስሊሙን ለከፋ መከራና ስቃይ ዳርገውታል። ለዚህ ድርጊታቸው ደግሞ ሚስጥሩ ንፁሃኑ ህዝበ ሙስሊም ላይ የሃሰት ታርጋ በመለጠፍ አሸባሪነትንና አክራሪነትን እየተዋጋው ነው በሚል የማስመሰልና የማታለል ስራው የምዕራባውያን ሃገራትንና የአሜሪካ ቀልብ ለመሳብና እርዳታ ለማጋበስ ነው። ቢያውቁት ግን ይህ ድርጊታቸው አውሬ እንጅ ሰው አለመሆናቸውን ቁልጭ አድርጐ ያሳያል። ለገንዘብ ሲባል ሰውን ያክል ፍጡር መግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት ከአንድ ሰው የሆነ ሰብአዊ ፍጡር አይጠበቅምና።
ሌላው ወያኔዎች 22 ዓመታት በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ ሲጠነስሱት የነበረው ሽብር የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈልና በማፋጀት የኢትዮጵያን ህልውና አንድነትን፣ ማንነትን በማናወጥ፤ የስልጣን እድሜያቸውን ማርዘም ነው። ይህ ስራቸው ከምን ጊዜውም በላይ በአሁኑ ሰአት እያፋፋሙትና፤ ሰላማዊውን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በማጋጨት የሽብር ሴራቸውን እያስፋፉ ይገኛሉ። ዳሩ ግን ለወያኔዎች ህዝብን መከፋፈል የሚበጅ ቢመስላቸውም የዚህ የሽብር ድራማቸው ተጠቂዎች ግን በፍፁም ልንሆን አልቻልንም፤ ወደፊትም ልንሆን አንችልምም። ምክንያቱም መቻቻል እና በፍቅር አብሮ መኖር መለዬ ባህላችንን በፍፁም ይህ ሰይጣናዊ ድርጊታቸው ሊያመክነው ስለማይችል ነው። ይህንን አንድነታችንን፤ ፍቅራችንን የመቻቻል ባህላችንን የበለጠ በማጎልበት፤ ባህላችንን፣ አንድነታችንን፣ ሃይማኖታችንን እየተፈታተነ ያለው የወያኔን የሽብር ስልት በማክሸፍ፤ ለበለጠ ድል እስክንበቃ ትግላችንን ማጠናከር ይኖርብናል።
በመጨረሻም የወያኔ ባለስልጣናት በፈረጠመ አምባገነናዊ ክንድ ህዝብን በማሸበርና በማፈን የስልጣን ዘመንን ለማራዘም መሞከር አወዳደቅን ማክፋት መሆኑን ካለፉት አምባገነናዊ ስርአቶች ሊማሩ ይገባል! አሁንም በድጋሚ ወያኔዎች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባ እውነት የኢትዮጵያ ህዝብ ሽብኝነትን በጽናትና በቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ያወግዛልም፡፡ በፀረ -ሽብርተኝነት ሽፋን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እየጣሰ ያለውን የወያኔ አገዛዝንም በተመሳሳይ ጽናትና ቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ይታገላልም!!!
ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ! 
ከቅዱስ ዬሃንስ