søndag 7. juli 2013

Zone9 እሁድ ጠዋትን በዝዋይ ማረሚያ ቤት — በቀለ ገርባን አገኘነው።

Zone9
እሁድ ጠዋትን በዝዋይ ማረሚያ ቤት — በቀለ ገርባን አገኘነው።

የዞን ዘጠኝ አባላትና ወዳጆቻችን ደርዘን ሆነን ዛሬ (ሰኔ 30/2013) ወደዝዋይ የተዛወሩ እስረኞችን ለመጠየቅ ሄድን።

በመጀመሪያ ያገኘነው በቀለ ገርባን ነበር። መልከ መልካሙ በቀለ አውርተው የሚጠግቡት ዓይነት ሰው እንደሆነ ለማወቅ ሄዶ ማየት ያስፈልጋል። ከእሱጋ ስናወራ ከሌሎችጋ ለመገናኘት ያቀድንበት ሰዓት እስከሚጣበብ ድረስ ዘግይተናል።

በቀለ ገርባ ስለሰላማዊ ትግል አብዝቶ ያወራል። ከ32 እስረኞችጋ አንድ ቦታ እንደታሰረ እና በተንጣለለው የዝዋይ ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ በተለይ እነሱ በአንዲት ውሱን፣ በተለምዶ ጨለማ ቤት የሚባለው ክፍል ውስጥ እንዳለ አጫውቶናል። (እዚህ ቦታ በግንቦት ሰባትነት ክስ የተፈረደባቸው ጄነራሎችና በነአንዱአለም አራጌ መዝገብ የተከሰሱት እዚሁ ይኖራሉ) ሆኖም ከቃሊቲ አንፃር ሲታይ ዝዋይ በጣም የተሻለ ምቹ እና ሠላማዊ እንደሆነ፤ ሌላው ቀርቶ ለሕክምና አዲስ አበባ መዛወር ኖሮበት ይቅርብኝ እንዳለ ጨምሮ ነግሮኛል።

በቀለ አሁን ከእስር ለመፈታት አመክሮው ተቀንሶ 2 ዓመት ከአራት ወር ከዘጠኝ ቀን ነውም ብሎናል። በእስሩ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም ድጋፍ እያደረገለት በመሆኑ እንደሚበረታና አሁንም ወደፊትም ብቸኛው የለውጥ መንገድ ሠላማዊ ትግል መሆኑን ለሕዝብ በምታስተላልፉት መልዕክት ላይ አስፍሩልኝ ብሎናል። በፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ቅጣት ማቅለያ ንግግሩን አስመልክቶ ስንጠይቀው ለማለት ብቻ ሳይሆን የማምንበት የሕይወት ፍልስፍናዬ ነው ሲል ነግሮኛል።

ከዚያ በኋላ ጋዜጠኛ ውብሸት፣ ናትናኤል፣ ዘሪሁንን እና አበበ ቀስቶን አግኝተን አነጋግረናቸው በጥንካሬያቸው ተበራትተናል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar