fredag 29. november 2013

የኢህአዴግ ህገ ወጥነት ኃ/ማሪያም አሁንም ከህገ ወጥ ስደቱ አልተመለሱም፡፡ኃ/ማሪያም እያሉ ቴወድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን በቲውተር ሲመራው ሰንብቷል፡

የኢህአዴግ ህገ ወጥነት
ኃ/ማሪያም አሁንም ከህገ ወጥ ስደቱ አልተመለሱም፡፡ኃ/ማሪያም እያሉ ቴወድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን በቲውተር ሲመራው ሰንብቷል፡፡

ወደ ሳውዲ አረቢያ ተሰደው በደል ተፈጽሞባቸው የተመለሱትን ዜጎቻችን መንግስት የተባለው አካል ሳይቀር ‹‹ህገ ወጦቹ ተመለሱ!›› ሲል ዜና አሰምቶናል፡፡ እነዚህ ዜጎች በሳውዲም በኢትዮጵያም ባይተዋር ናቸው፡፡ ተሰደውም ስደተኞች፣ ሳይሰደዱም ስደተኞች ናቸው፡፡ ዜጋ ሆነው እንኳን የዜግነት መብት አይሰጣቸውም፡፡ ስደተኞች ሆነው የስደተኛ መብት የላቸውም፡፡ ሰብአዊ ፍጥረት ሆነው ሰብአዊ መብት የላቸውም፡፡ ሰራተኛ ሆነው የሰራተኛ መብትና ጥቅም አልተከበረላቸውም፡፡ ልክ እንደ ኃ/ማሪያም የሚባሉትና የሆኑት የተለያዩ ናቸው፡፡

አቶ ኃ/ማሪያም ኢትዮጵያውያኑ ድሆች ዜጋ ተብለው ዜጋ እንዳልሆኑት፣ ስደተኛ ተብለው ዓለም አቀፍ የስደተኛ መብት ያልተከበረላቸው፣ ሰርተው የድካማቸው ያልተከፈላቸው፣ መንግስት አላቸው እየተባለ መንግስት ያልደረሰላቸው፣ ኤምባሲ ተከፍቶ ስቃያቸውን ያላቀለለላቸው አይነት ኢትዮጵያውያን፡፡ አቶ ኃ/ማሪያም ልክ እንደነዚህ ኢትዮጵያውያን የስም እንጅ ተግባራዊ ጥቅም፣ ተግባራዊ መብት፣ ተግባራዊ ስልጣን የላቸውም፡፡

እንደ ስም ቢሆንማ ህገ መንግስቱ አቶኃ/ማሪያም ለተሸከሙት ስልጣን የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመምራትና በመቆጣጠር ስልጣን ይሰጣል፡፡ ዜጎች በሌሎች አገራት ሲሰቃዩ፣ ችግር ሲደርስባቸው የውጭ ጉዳይን ይመራል፡፡ ለጉዳዩ አፋጣይ ምልሽ ይሰጣል፡፡ ዜጎችን ይታደጋል፡፡ ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል፡፡

አቶ ኃ/ማሪያም ልክ ዜጎቻችን መብቶቻቸው ሁሉ ተደፍጥጦ ታስረው እንደነበሩት ሁሉ ህገ መንግስቱ የሰጣቸውን ስልጣን እንዳይወጡ ተደርገው ቆይተዋል፡፡ በእርግጥ ይህ የኢህአዴግ ህገ ወጥነት ነው፡፡ የእርሳቸውም ቢሆን ያው ነው፡፡ ስልጣን ካልሰሩበት ለምን ይቀበላሉ? የውጭ ጉዳዩን መምራት ያለባቸው ኃ/ማሪያም እያሉ በእርሳቸው ትዕዛዝ ስራውን ማከናወን የነበረበት ቴወድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን በቲውተር ሲመራው ሰንብቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን መብታቸውን ተነፍገውና ሲሰቃዩ ቆይተው ‹‹ህገ ወጥ›› ተብለው ከተመለሱ በኋላ አቶ ኃ/ማሪያም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲመስሉ ተደርገዋል፡፡ በህገ መንግሰቱ መሰረት የውጭ ጉዳይን እንደሚመሩ ተነግሯቸው፣ ዜጎች እየሞቱ በዓመት 2 ዲግሪ ስለሚጨምረው የዓለም ሙቀት ሲያወሩ ሰንብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን እየሞቱ የጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውን ሳይወጡ ለራሳቸው ስለማያንሱት ደቡብ አፍሪካን የመሰሉ አገራትን ወክለው ሲናገሩ ሰንብተው ተመልሰዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ ስለ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለ ዜጎቻችን ስቃይ ሊያወሩ የተፈቀደላቸው፡፡ ያም ሆኖ ተመጥኖ ተሰጥቷቸው፡፡ ያም ሆኖ እነ ሳውዲን እያደነቁ፡፡ ያም ሆኖ ለዜጎች ያልቆመውን መንግስት እያወደሱ፡፡

ይህን ያየ አቶ ኃ/ማሪያም እራሱ ስደተኛ ነው መሆናቸውን ለመረዳት አይከብደውም፡፡ አብዛኛዎቹ ዜጎቻችን ተመልሰዋል፡፡ ህገ ወጥ ተብለውም ባይተዋር ወደሆኑባት አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ አቶ ኃ/ማሪያም ከስልጣን ባይተዋርነታቸው ባይወጡም፣ በትዕዛዝ መናገራቸውን ባያቆሙም፣ በካድሬዎች መታዘዝ ባይቀርላቸውም እጅግ ዘግይተው ተመልሰዋል፡፡ ዜጎቻችን ዘግይተው ተመልሰው ሳይገባቸው ‹‹ህገ ወጦች›› ተብለዋል፡፡ አቶ ኃ/ማሪያም ወደ መናገር ተመልሰውም የሚናገሩት ለሳውዲዎች ነው፡፡ በእርግጥ ካለመናገር መናገር ይሻላል፡፡ ግን ከተለመደው ህገ ህገ ወጥነት አልተመለሱም፡፡

#‎Miniliksalsawi‬

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar