torsdag 18. august 2016

Democracy, Justice and Freedom for Ethiopian: በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!

Democracy, Justice and Freedom for Ethiopian: በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!:                     በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!                                    ቃልኪዳን ካሳ...

በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!

                    በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!! 

                                                                           ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ


በሀገራችን ኢትዮጵያ ከአራት ጊዜ ምርጫ ቢደረግም ያው እንደሚታወቀው ምርጫውን በማጭበርበር ስልጣኑ በሃይል ከተቆጣጠሩት ይህው ሁለት አስርት አመታትን አስቆጥሯል። ምርጫውን በሃይል ስልጣን መያዛቸውን እየታወቀ ለይመሰል የሚዘጋጁ ቅድመ ዝግጅቶችና የፓርቲዎች ተሳትፎ በጣም የሚያስገርም ነው። በአምባገነን ስርዓት የምትገዛ ሀገር የህዝቦችን ድምፅ ያከብራ ተብሎ አይገመትም። ለዚህም በህወሓት የሚመራው መንግስት ትልቁ ማሳያ ይሆናል።

ይህን ፁሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ነገር በሀገራቸን ውስጥ እየታየ ስላለው ህዝባዊ እንቢተኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ከቦታ ወደ ቦታ እንዲሁም ከከተማ ወደ ከተማ  በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፋ መቷል። ይህ ህዝባዊ እንቢተኝነት በህወሓት ወገን የተለያዩ ስሞች ቢሰጠውም ህዝቡ የህወሓት አገዛዝ በቃን ብሎ የተነሳበት ወቅት ነው። ይህን ተከተሎ ባሳለፍናቸው ወራቶች ውስጥ በመላው ኦሮሚያ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እንቢተኝነት እስካአሁን ድረስ አለ። የተዳፈነ ቢመስልም ረመጡ ግን ጊዜ እየጠበቀ መቀጣጠሉ የማይቀር ነው። በተመሳሳይ በወልቃይት የአማራ ማንነት ዙሪያ ላይ ውስጥ ውስጡን ሲቀጣጠል ቆይቶ ያልታሰበ እና ያልተጠበቀ የተቃውሞ የታየበት የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ በመላው አማራ ህዝብ የተነሳበት ተቃውሞ ነበር።

በሀገራችን ህወሓት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በህዝቦቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍና መከራ ጊዜውን ጠብቆ በእራሱ ጊዜና ሰዓት ገንፍሎ ወቷል። ጭቆናና በደል አልሸከምም ያለ ህዝብ ለነፃነቱ ህይወቱ መሰዋዓት እያደረገ ያለበት ሁኔታ ላይ ነው ያለነው። ህወሓቶች በሁሉም ብሄሮች ላይ ዘግንኛ የሆን ግፍና በደል ፈፅመዋል እየፈፀሙም ነው። ይህን ስል በአማራና በኦሮሞ እንዲሁም በጋምቤላ ህዝቦች የሰሯቸው ዘግናኝ ግፍና በደሎች ከሎሎች ብሄሮች ጋር እኩል ማድረጌ እንዳልሆን ትረዱኛላቹህ ብዬ ገምታለሁ። በአማራና በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈፀመው በደል የአደባባይ ሚስጥር ነው። ህወሓቶች ሁለቱ ህዝቦች "ለስልጣኔ ያሰጉኛል" የሚል ትልቅ ስጋት አለው። ሌላኛው ሁለቱን ህዝብ በማናከስ ካልቻለ ደግሞ ከሁለት ህዝቦች የሚነሱ ጥያቄዎችን መልሳቸው ጥይት በማድረግ ተያይዞታል።

በህወሓት የሚመራው መንግስት መቶ ፐርሰንት መርጦናል ብለው ያስቡት ይሆን ባያስቡት ይሻላል። በህዝብ የተመረጠ ስርዓት ቢሆንማ ኖሮ ያ ሁሉ ህዝብ ባልተገደለ፣ ባልታሰረ፣ ባልታፈነ ነገሩ በህዝብ የተመረጡ ሳይሆን በጉልበትና በሃይል ስልጣን ላይ የተቀመጡ ስለሆን ለስልጣናችን ያሰጋናል የሚሉት ህዝብ ላይ እነሱ እንደሚሉት "የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን" እንዳሉት እያደረጉ ያለበት ሁኔታ ነው። ይህ ስርዓት የለየለት ሆኖል፤ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ህዝብ ላይ እንዲህ ያለ አረመኔያዊ ድርጊት መፈፀሙ ምን ያህል የለየለት ስርዓት እንደሆነ አጉልቶ አሳይቶናል። በህወሓት የሚምራው መንግስት በህዝቦች ላይ ሁሉንም ነገር በአፈናና በመግደል ወይም በማሰር መፍትሄ የሚሆን መስሎቸው ህዝቡን ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲቆም እያደረጉት እንደሆነ ልብ አላሉ። 

በዚህ ወቅት ህዝቡና በህወሓት የሚመራው መንግስት አይጥና ድመት ሁኔታ ውስጥ ተገብቷል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ከዚህ በፊት ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲታሰብ ፍቃድ በማለት ህብረተሰቡን ማጉላላት ነበር። አሁን ግን ህብረተሰቡ ከማስፈቀድ ማሰወቅ ብቻ ይጠበቅበናል በማለት የተለያዩ ህዝባዊ ሰልፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል። መብቱና ነፃነቱ ሲነጠቅ የነበረ ህብረተሰብ ከአሁን በኋላ ወይ ነፃነት ወይ ሞት ብሎ የተነሳ ህዝብ መሆኑ በተጨባጭ አሳይቷ። 

በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለብጥ የግድ የሆነበት ምክንያት በህወሓት የሚመራው መንግስት በህዝቦች ላይ የሚፈፅሙት እየፈፀሙት ያለው ዘግናኝ ግፍና በደል ህዝቡን በማስቆጣት ሁሉም ለነፃነቱና ለመብቱ እንዲቆም አድርጎታል። በህዝብ ያልተመረጠ አምባገነናዊ ስርዓት ለህዝቦች ከመክራና ከስቃይ ያልዘለለ ምንም ሲያደርጉ አይስተዋሉም። ለዚህም በህወሓት የሚመራው መንግስት በኢትዮያዊያን ወገኖች ላይ የሚፈፅመውን ግድያም ሆን እስራት እንዲሁም አፈና አጥብቄ እቃወማለሁ። 



ድል ጭቁን ህዝብ!!
ውርደት ለአምባገኑ ህወሓት!!

tirsdag 24. mai 2016

ሳይገነባ የፈረሰ ዲሞክራሲ!

ሳይገነባ የፈረሰ ዲሞክራሲ!

ህወሃት 25 አመታት ሙሉ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብቻለው እያለ መደስኮሩን ተያይዞታል። የህወሓት ገንብቻለው የሚለው ዲሞክራሲው ከወረቀትና ከአፍ ባልዘለለ መልኩ ሲነገርለት የሚኖረው ይህ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አንድም ቀን በህዝቦች መካከል በስራ ላይ ሳይወል ይህው በወሬ ብቻ ሆኖ ቀረ።

ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር እንደታገሉ የሚነግሩን ህወሓቶች አንዲትም ቀን ለህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት በተሞላበት መልኩ ለህዝቡም ሆን ለሀገሪቱ ሲሰሩ አይስተዋሉም። ከላይ እንደገለፅኩት የህወሓት ዲሞክራሲ ከወረቀትና ከአፍ ባልዘለለ መልኩ በምንም ላይ ሲተገበር አይታይም።

ዲሞክራሲ ማለት የመናገር መብት፣ የመፃፍ መበት፣  የመደራጀት መብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እነዚህ ሁኔታ በሌሉበት እንዴት ነው ዲሞክራሲን በሀገሪቱ ላይ አምጥተናል ብለው መነገሩ። እውን ህወሓት ዲሞክራሲን እንዴት አድርጎ ቢተረጉመው ነው የታገልነው ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ነው ሲል። እርግጥ ነው በህወሓት ለህዝቡ የመታሰር፣ የመገደል፣ የመታፈን፣ የመሰደድ፣ የመፈናቀል፣ የመታፈን ስርዓት ገንብቷል ይህ የማይካድ ሀቀ ነው።

ዲሞክራሲ በሌለበት ሀገር ውስጥ ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቷል ብሎ ማሰቡ እጅግ ሞኝነት ነው። ዜጎች የመኖር ህልውናቸው አጣብቂኝ ውስጥ ባለበት ሀገር ውስጥ ዲሞክራሲ አለ ብሎ መናገሩ እራስን እያታለሉ መኖር ማለት ነው። ለህዝቡ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንደታገሉ ቢናገሩም ነገር ግን እነሱ የታገሉለት ዋነኛ አላማ የህዝቦችንና የሀገር ታሪክ ማጥፋትና የህዝቡን ሀብት ለመዝበር ነው። ህወሓት ስልጣኑን የያዘው በዲሞክራሲያዊ ስርዓት በህዝብ ተመርጦ የህዝብን ይሁንታ አግኝቶ የመጣ ስርዓት አይደለም፤ በሃይል ስልጣን ያዘ፤ በሃይል ሀገርና ህዝብን የገዛ ያለ ስርዓት ነው።


በእነዚህ ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት ክ፫ ያላነሱ ምርጫዎችን ቢያደርግም አንዱንም ጊዜ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አላደረገም። ይህ ባለበት ሁኔታ ላይ እለት ተዕለት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገነቡ ቢነግሩንም ሀቁ ግን በሀገሪቱና በህዝቦቹ ላይ የሚፈፀመው ኢፍት ሃዊ ድርጊቶች ሲፈፀሙና እየተፈፀሙ ያሉ ናቸው። ከ1997  ምርጫ ወዲህ በሀገሪቱ ላይ ምንም አይነት የዲሞክራሲ ባልታየበት ገነባነው ያሉትም ዲሞክራሲ ለዜጎች ፍትህ ሲያጓድል እንጂ ፍትህ ሲሰጥ አልተመለከትንም። የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ ህወሓት ለስልጣኑ በመስጋት የተለያዩ አዋጆችን በማፅደቅ የመፃፍም ሆን የመናገር እንዲሁም የመደራጀት መብት እንዳይኖራቸው በማድረግ ህግ አውጥቶ አፅድቋል።

ይህን ተከትሎ ለዚሁ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ቀላል የሚባሉ አይደለም። በተለይ ፀረ ሽብር ህጉ አዋጅ ሆኖ ከፀደቀ ወዲህ ብዙን ምክንያትና አጋጣሚን እየጠበቁ ህዝቡን ለእስር እየተዳረጉ ይገኛል። ለዚህም ይህ አዋጅ ለሚፅፉ፣ ለሚደራጁ እንዲሁም ሀሳብን በነፃ ለሚገልፁ ለማፈን የወጣ ህግ ነው። ይህ ባለበት ሁኔታም ከህወሓት ጋር እየተናነቁ ያሉም ሀገርና ህዝብ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እጅግ የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው። ይህና መሰል ችግሮች ባለበት ሀገራችን ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቷል ብሎ ከማለት "ሳይገነባ የፈረሰ ዲሞክራሲ" ቢባል ጥሩ ነው። ባይ ነኝ እኔ

ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ

tirsdag 17. mai 2016

የግንቦት 20 ፍሬዎች ከብዙ በጥቂቱ!

የግንቦት 20 ፍሬዎች ከብዙ በጥቂቱ!

ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ!
የዘንድሮን የግንቦት 20 በአል ስታከብሩ እነዚህ ስቃይና በደሎች ያሰባቹ መሆን አለበት። ግንቦት 20 የህዝብ በአል ነው ብሎ ማሰብ በህዝቡ ደምና በሞቱት ህይወት መቀለድ ነው።ህወሓት የስልጣን ዘመኑ ለማራዘም የገደለውን ገድሎ፣ያሰረውን አስሮ፣ያፈነውን አፍኖ ስልጣኑን በሃይል በመጠቀም ላይ ነው። ገና ከጅምሩ በጫካ በነበሩ ጊዜ ሲያቅዱ የነበረውን ነው አሁን እየፈፀሙ የሚገኙት ይህ ደግሞ እውነታ ከቀድሞ የህወሓት ሃላፊ የነበሩ አቶ ገ/መድህን አርያ የተናገሩት ሀቅ ነው።
Ginbot 20 Ferewoche
ይህን በአል ልታከብሩት የምትችሉት ህወሓቶችና ቤተሰቦቻችሁን እንዲሁም የትግራይ ካድሬዎች ብቻና ብቻ ነው። ይህን ያልኩበት ምክንያት ግልፅና ግልፅ ነው። በዚህ ስርዓት ውስጥ አብዛኛው ለትግራይ ተወላጆች ጥሩ እድል ፈጥሯል። ይህ የማይካድ ሀቅ ነው። ታዲያ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የአንድ ብሄር ቢባል ምኑ ነው ውሽት!

የኢትዮጵያን ህዝብ በግንቦት 20 ያገኛው ድል ሳይሆን ውርደት ነው፤ይህን ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው። ስለግንቦት 20 ከድል ይልቅ ወርደቱ ጎልቶ የታየበት ወቅት ነው። እውነት በዚህ ወቅት በህወሓት በህዝቡ ላይ የሚፈፅመው ግፍና መከራ ተዘንግቶን ነው? በቅርቡ እንኳን በኦሮሚያ፣በአማራ በደቡብ ኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ፣በኮንሶ፣በጋምቤላ ወገኖቻን ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እንዲሁም ቀን በቀን የሚታሰረው ወገኖች እነዚህ ታዲያ የግንቦት 20 ፍሬዎች ቢባሉ ምን ይወጣላቸዋል።


ይሄን እውነታ ሁላችንም ጠንቅቀን እንረዳለን ዳሩ ግን ዝምታችን ወደር አቶ ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ክፉኛ ተለማመድ ነው መሰል ስምተንም ሆነ አይተን እኛ ግን እዛው የተቀመጥንበት ላይ ነን!!!!! ታዲያ የእኛ ተቃውሞ ምኑ ጋር ነው? መቃወም ብቻ ለውጥ አያመጣም፤እየተቃወምን ያለው ተደራጅተን ነው ወይስ እንዲሁ ነው? ሳንደራጅ፣ሳንሰባሰብ መቃወሙ ትርጉም አይኖረውም።
ስለዚህ እንሰባሰብ፣እንደራጅ፣እንመከከር . . . . . . . ከዛን ተቃውሟችን ለአንድ ህዝብ እስከሆነ ድረስ አሁን እየደረሰብን ያለውን ግፍና መከራ ከወሬ በዘለለ መልኩ ወደተግባር እንለውጠው።

ህወሓቶች ህዝብና ሀገር ለማጥፋት አንድ ሆነዋል። እኛ ሀገርና ህዝብን ለማዳን እንዴት እንድ መሆን አቃተን? ለነገሩ ለጥሩ ነገር ህብረት ሃይል የለውም፤ለመጥፎ ነገር ግን ህብረት ሃይል አለው። አሁንም ጊዜው አልረፈደም ወቅቱ የሚፈልገው ህብረትና አንድነት ነው። ይህን ህብረትና አንድነት ህወሓቶች ደግሞ አይፈልጉትም። ይህ ስርዓት በዚህ አይነት ከቀጠለ የህዝባችን ስቃይና መከራ እንደሚቀጥል እሙን ነው።

የግንቦት 20 ፍሬዎች መግደል፣መታሰር፣መታፈን፣መፈናቀል እንዲሁም መሰደድ ሲሆኑ በ25 አመታት ውስጥ እነዚሁ በህወሓት ሲተገበሩና እየተተገበሩ ያሉ ናቸው።


 የሁላችንም ችግር ህወሓትና ስርዓቱ ነው!



ፎቶዎችን በመሰብሰብና በማስተካከል የፌስቡክ ጓደኞቼ የረዱኝ ናትናኤል መኮንን እና ጥላዬ ታረቀኝ ከልብ አመሰግናለሁ።


የግንቦት 20 ፍሬዎች ከብዙ በጥቂቱ!

የግንቦት 20 ፍሬዎች ከብዙ በጥቂቱ!

የዘንድሮን የግንቦት 20 በአል ስታከብሩ እነዚህ ስቃይና በደሎች ያሰባቹ መሆን አለበት። ግንቦት 20 የህዝብ በአል ነው ብሎ ማሰብ በህዝቡ ደምና በሞቱት ህይወት መቀለድ ነው።ህወሓት የስልጣን ዘመኑ ለማራዘም የገደለውን ገድሎ፣ያሰረውን አስሮ፣ያፈነውን አፍኖ ስልጣኑን በሃይል በመጠቀም ላይ ነው። ገና ከጅምሩ በጫካ በነበሩ ጊዜ ሲያቅዱ የነበረውን ነው አሁን እየፈፀሙ የሚገኙት ይህ ደግሞ እውነታ ከቀድሞ የህወሓት ሃላፊ የነበሩ አቶ ገ/መድህን አርያ የተናገሩት ሀቅ ነው።

ይህን በአል ልታከብሩት የምትችሉት ህወሓቶችና ቤተሰቦቻችሁን እንዲሁም የትግራይ ካድሬዎች ብቻና ብቻ ነው። ይህን ያልኩበት ምክንያት ግልፅና ግልፅ ነው። በዚህ ስርዓት ውስጥ አብዛኛው ለትግራይ ተወላጆች ጥሩ እድል ፈጥሯል። ይህ የማይካድ ሀቅ ነው። ታዲያ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የአንድ ብሄር ቢባል ምኑ ነው ውሽት!
የኢትዮጵያን ህዝብ በግንቦት 20 ያገኛው ድል ሳይሆን ውርደት ነው፤ይህን ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው። ስለግንቦት 20 ከድል ይልቅ ወርደቱ ጎልቶ የታየበት ወቅት ነው። እውነት በዚህ ወቅት በህወሓት በህዝቡ ላይ የሚፈፅመው ግፍና መከራ ተዘንግቶን ነው? በቅርቡ እንኳን በኦሮሚያ፣በአማራ በደቡብ ኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ፣በኮንሶ፣በጋምቤላ ወገኖቻን ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እንዲሁም ቀን በቀን የሚታሰረው ወገኖች እነዚህ ታዲያ የግንቦት 20 ፍሬዎች ቢባሉ ምን ይወጣላቸዋል።

ይሄን እውነታ ሁላችንም ጠንቅቀን እንረዳለን ዳሩ ግን ዝምታችን ወደር አቶ ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ክፉኛ ተለማመድ ነው መሰል ስምተንም ሆነ አይተን እኛ ግን እዛው የተቀመጥንበት ላይ ነን!!!!! ታዲያ የእኛ ተቃውሞ ምኑ ጋር ነው? መቃወም ብቻ ለውጥ አያመጣም፤እየተቃወምን ያለው ተደራጅተን ነው ወይስ እንዲሁ ነው? ሳንደራጅ፣ሳንሰባሰብ መቃወሙ ትርጉም አይኖረውም።
ስለዚህ እንሰባሰብ፣እንደራጅ፣እንመከከር . . . . . . . ከዛን ተቃውሟችን ለአንድ ህዝብ እስከሆነ ድረስ አሁን እየደረሰብን ያለውን ግፍና መከራ ከወሬ በዘለለ መልኩ ወደተግባር እንለውጠው።

ህወሓቶች ህዝብና ሀገር ለማጥፋት አንድ ሆነዋል። እኛ ሀገርና ህዝብን ለማዳን እንዴት እንድ መሆን አቃተን? ለነገሩ ለጥሩ ነገር ህብረት ሃይል የለውም፤ለመጥፎ ነገር ግን ህብረት ሃይል አለው። አሁንም ጊዜው አልረፈደም ወቅቱ የሚፈልገው ህብረትና አንድነት ነው። ይህን ህብረትና አንድነት ህወሓቶች ደግሞ አይፈልጉትም። ይህ ስርዓት በዚህ አይነት ከቀጠለ የህዝባችን ስቃይና መከራ እንደሚቀጥል እሙን ነው።

የግንቦት 20 ፍሬዎች መግደል፣መታሰር፣መታፈን፣መፈናቀል እንዲሁም መሰደድ ሲሆኑ በ25  አመታት ውስጥ እነዚሁ በህወሓት ሲተገበሩና እየተተገበሩ ያሉ ናቸው።

ፎቶዎችን በመሰብሰብና በማስተካከል የፌስቡክ ጓደኞቼ የረዱኝ ናትናኤል መኮንን እና ጥላዬ ታረቀኝ ከልብ አመሰግናለሁ።

ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ!

የሁላችንም ችግር ህወሓትና ስርዓቱ ነው!

tirsdag 26. april 2016

ኢሳት እንወያይ ፕሮግራም!!


በኢሳት እንወያይ ፕሮግራም ላይ እኔ ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ እና ሀና ለገሰ ከአውስትራሊያ እንዲሁም የእንወያይ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተወልድ ጋር በመሆን በሀገራችንና በህዝቦቻችን እየደረሰ ግፍና መከራ በተለይ በአሁን ወቅት በተለዩ ቦታዎች ህወሓት ሲፈፅምና እየፈፀመ ያለው ኢሰብዓዊ ድርጊት በመቃወም ተወያይተናል።

የዛሬው እንወያይ ፕሮግራም ከ10 ቀን በፊት በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ እና አሰቃቂ እንደነበር ሁላችንም የተመለከትነው ጉዳይ ነው። በውይይታችን ውስጥ ከመንግሥት የተሰጠው የሀዘን መግለጫ፣በመከላከያ ሰራዊቱ በክልሉ በተደጋጋሚ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋዎች እንዳሉ እየታወቁ በመንግስት ለነዋሪዎቹ በቂ ጥበቃ እንዳላደረገላቸው እንዴት ድንበር ያለጠባቂዎች እንዲሆን ለምን ተደረገ፣ ታፍነው ስለተወሰዱ ህፃናት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ከዚህ ጭፍጨፋ በስተጀርባ የህወሓት እጅ እንዳለበት እንዲሁም ጊዜውን ያልጠበቀ የሀዘን ቀን መታወጁ በተጨማሪ በሶሻል ሚዲያው ስለኢትዮጵያዊነት እጅግ በጣም ደስ እንደሚል እና ይህን በሶሻል ሚዲያ ላይ ያለውን አንድነት ወደ አንድ ነገር መደረስ እንዳለበት እና እነዚህና መሰል ችግሮችን በማንሳት ተወያይተናል።





søndag 27. mars 2016

ከብሄር በፊት ሀገር!!!

ከብሄር በፊት ሀገር!!!

በሀገራችና በህዝባችን ህወሓት ከሚፈፅማቸው ግፍና በደል በተጨማሪ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ሁኔታ የብሄርተኝነትን መርዝ አሰራጭቶል እያሰራጨም ይገኛል። ይህንም ያደረገበት ዋነኛ ምክንያት የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም ሆን ብሎ ያደረገው ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የራሱ የሆነ ብሄር እንዳለሁ ሁሉ ሰው ብሄርተኝነቱን እራሱ ፈልጎት የመጣ ነገር አይደለም፤ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው። ስለዚህ ህወሓት አሁን ላይ ስልጣኑን ለማራዘም ብሎ ብሄርን ከብሄር ማናከስ ትልቁ ስራው አድርጎታል፤ እያናከሰም ይገኛል። እስከመቼ በብሄር ፖለቲካ እያጫወተን እንዘልቀዋልን። ህወሓት ገና ጫካ እያለ አላማ አድርጎ የተነሳው የህዝቦችን አንድነት የመበጣጠስ አላማ አድርጎ የተነሳ ቡድን ነው።

አሁን ላይ በሀገራችን ያለው ስልጣን የአንድ ብሄር ስልጣን ነው። ይህ የአንድ ብሄር ስልጣን ለ25 አመታት በኢትዮጵያና በህዝቦቾ ታሪክ ግፍና በደል እንዲፈፀም አድርጓል። ህወሓት ብሄር ተደራጅቶ በሀገርና በህዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል ኢፍትሃዊ ግፍና በደል ፈፅሟል፤ እየፈፀመም ይገኛል። መቼም አሁን አሁን እየተፈፀመ ያለው ግፍና በደል በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ይህም የሆነበት ምክንያት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በዜጎች ላይ የተወሰደው እኩይ ተግባር ይህ ነው የሚባል አይደለም።

የአንድ ብሄር ስልጣን ላይ መቀመጥ በዜጎች ላይ የሚደርሱ ግፍና በደሎች ሰሚ አካል የላቸውም። ምክንያቱም ሀገሪቱና ህዝቦቾን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር አድርገውታል። ህግ አውጪ እነሱ፣ ህግ ተርጓሚ እነሱ፣ ህግ አስፈፃሚ እነሱ ይህ ሁኔታ ባለበት ሀገር ላይ የዜጎች የመኖር ዋስትና አጣብቂኝ ውስጥ ይገኛሉ። ይህን የፈጠረው የአንድ ብሄር ስልጣን ስለሆነ በህዝባቸው የሚፈፀምባቸውን በደል ወይም ግፍ ለመቃወም የብሄር ትግል እንዲያስቡ ያስገድዳቸዋል። ነገር ግን የብሄር ትግሉ መደረጉ ባይጠላም፤ ሀገራዊ ትግል እንዲሆን መፈጠሩ ሁሉምንም ብሄር ያካተተ ያደርገዋል።

ህወሓት ሲታገል የነበርው አንድን ብሄር ነፃ ለማውጣት ታግሎ፤ አንድን ብሄር ለስልጣን አብቅቷል። ይህ ስርዓት አብዛኛውን ብሄር ብሄረሰብ  ጎድቶታል እየጎዳውም ነው። አንዳንቺን ለአንዳንቺን እንዳንያያዝ፣ እንዳንግባባ፣ እንዳንሰማማ፣ እንዳንተማመን…………….. ያደረገ ስርዓት ነው። የአንድ ብሄር ስልጣን የፈጠርውን ችግር እያየን የብሄር ትግል ውስጥ የገባን ልብ ብለን ልንገነዘብ ይገባናል። "አንድ ተረት አለ እሳትን ያየ በአመድ አይስቅም!!"

ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ሀገር ናት። እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ የራሱ የሆን ቋንቋና ባህል ወግ አለው። ለዘመናት ተከባብሮና ተፋቅሮ የኖረ ማህበረሰብ ነው። አሁን አሁን ህወሓት በፈጠረው ስርዓት ብሄር ከብሄር ጋር ሲያስማማ ወይም ሲያከባብር አልተስተዋለም። ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት በሀገሪቱ የአንድ ብሄር ስልጣን ዘመን እንዲራዘም ሆን ተብሎ የሚደረግ ድርጊት ነው።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚስተዋሉ ነገሮች አሉ። እነዚሁ ነገሮች ብሄር እና ሀገር እየታገልን ያለነው ስለብሄር ነው ወይስ ስለሀገር የሚለውን ነገር እንድመለከት አድርጎኛል። ሁላችንም የእኔ የምንለው ብሄር አለን። እንዱሁም ሁላችንም በአንድ ስም ሊያስጠራን የሚችል ሀገርም አለን!! ታዲያ ትግላችን ከሀገር ወደ ብሄር እየሄደ ይመስላል።  አንድ ብሄር ብቻውን ህወሓት ተቃውሞ ከስልጣን ያስወግዳል የሚል እምነት የለኝም። ባይሆን ሁሉም በተቃውሞ ቢሳተፍ አንድ ደረጃ ላይ እንደርስ ነበር። እርግጥ ነው በብሄራችን ላይ የሚፈፀሙ ግፍና በደሎች ስለብሄራችን እንድንቆም ያደርጉናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ተቃውሞ የለኝም። ነገር ግን እየሆነ ያለው ሁሉም   ስለእራሱ ብሄሩ የሚታገል ከሆነ ስለሀገራዊ ትግል እንዴት ልናስብ እንችላለን። እዚህ ጋር ቆም ብለን እናስብ!!  

ከብሄር በፊት ሀገር!! ሀገር እየፈረሰ ብሄር ይኖራል ማለት ዘበት ነው!! ይህ ደግሞ ማንም ሰው ሊያውቀውና ሊገነዘበው ግድ ይላል። ሀገርን ውስጥ ብዙ ህዝቦች አሉ!! አሁን ላይ ህወሓት ሀገርና ህዝብ እያጠፋ የሚገኝበት ሰዓት ላይ ነን ፤ይህ ደግሞ ከማንም የተደበቀ አይደለም። እርግጥ ነው ህወሓትና ቤተሰቦቻቸው ይህን እውነታ አይቀበሉትም። ምክንያቱ አላማ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ያሉት በሀገሪቱ ህዝብ ንብረትና ሀብት ላይ ስለሆን በህወሓት ላይ ምንም አይነት ተቃውሞ መስማትም ሆን ማየት አይፈልጉም።

ስለሆነም የምናደርገው ትግል ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች  ያማከለ መሆን አለበት ለጋምቤላው ህዝብ ኦሮሞው ካልጮህለት፣ ለኮንሶ ህዝብ አማራው ካልጮህለት፣ ለሀረሪ ህዝብ ትግሬው ካልጮህለት. . . . . . . . ጩህታችን ለመላው ለህዝባችን ካላደረግነው ተመልሶ እንደ ህወሓት አይነት ስርዓት መገንባቱ የማይቀር ነው።  ህወሓት ግፍና በደል መላው ህዝባችን ላይ ነው። ድምፅ ለሌላቸው ህዝቦች ድምፅ መሆን ካልቻልን አሁንም ይህ ፋሺስት ስርዓት በሀገሪቱና በህዝቡ ላይ የሚያደረሰውን መከራ ይቀጥላል። ይህ እንዳይሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከብሄር በፊት ለሀገሩና ለመላው ህዝብ  መቆም አለበት!! ሀገር ሲኖር ብሄር ይኖራል። አንድ ብሄር ሀገር መሆን አይችልም!! ሀገር ግን የብዙ ብሄር ብሄረሰብ ናት!!



እግዚሐብሄር ኢትዮጵያና ህዝቦቾን ይባርክ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!


ቃልኪዳን ካሳሁን (ከኖርዌ)