tirsdag 17. mai 2016

የግንቦት 20 ፍሬዎች ከብዙ በጥቂቱ!

የግንቦት 20 ፍሬዎች ከብዙ በጥቂቱ!

የዘንድሮን የግንቦት 20 በአል ስታከብሩ እነዚህ ስቃይና በደሎች ያሰባቹ መሆን አለበት። ግንቦት 20 የህዝብ በአል ነው ብሎ ማሰብ በህዝቡ ደምና በሞቱት ህይወት መቀለድ ነው።ህወሓት የስልጣን ዘመኑ ለማራዘም የገደለውን ገድሎ፣ያሰረውን አስሮ፣ያፈነውን አፍኖ ስልጣኑን በሃይል በመጠቀም ላይ ነው። ገና ከጅምሩ በጫካ በነበሩ ጊዜ ሲያቅዱ የነበረውን ነው አሁን እየፈፀሙ የሚገኙት ይህ ደግሞ እውነታ ከቀድሞ የህወሓት ሃላፊ የነበሩ አቶ ገ/መድህን አርያ የተናገሩት ሀቅ ነው።

ይህን በአል ልታከብሩት የምትችሉት ህወሓቶችና ቤተሰቦቻችሁን እንዲሁም የትግራይ ካድሬዎች ብቻና ብቻ ነው። ይህን ያልኩበት ምክንያት ግልፅና ግልፅ ነው። በዚህ ስርዓት ውስጥ አብዛኛው ለትግራይ ተወላጆች ጥሩ እድል ፈጥሯል። ይህ የማይካድ ሀቅ ነው። ታዲያ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የአንድ ብሄር ቢባል ምኑ ነው ውሽት!
የኢትዮጵያን ህዝብ በግንቦት 20 ያገኛው ድል ሳይሆን ውርደት ነው፤ይህን ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው። ስለግንቦት 20 ከድል ይልቅ ወርደቱ ጎልቶ የታየበት ወቅት ነው። እውነት በዚህ ወቅት በህወሓት በህዝቡ ላይ የሚፈፅመው ግፍና መከራ ተዘንግቶን ነው? በቅርቡ እንኳን በኦሮሚያ፣በአማራ በደቡብ ኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ፣በኮንሶ፣በጋምቤላ ወገኖቻን ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እንዲሁም ቀን በቀን የሚታሰረው ወገኖች እነዚህ ታዲያ የግንቦት 20 ፍሬዎች ቢባሉ ምን ይወጣላቸዋል።

ይሄን እውነታ ሁላችንም ጠንቅቀን እንረዳለን ዳሩ ግን ዝምታችን ወደር አቶ ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ክፉኛ ተለማመድ ነው መሰል ስምተንም ሆነ አይተን እኛ ግን እዛው የተቀመጥንበት ላይ ነን!!!!! ታዲያ የእኛ ተቃውሞ ምኑ ጋር ነው? መቃወም ብቻ ለውጥ አያመጣም፤እየተቃወምን ያለው ተደራጅተን ነው ወይስ እንዲሁ ነው? ሳንደራጅ፣ሳንሰባሰብ መቃወሙ ትርጉም አይኖረውም።
ስለዚህ እንሰባሰብ፣እንደራጅ፣እንመከከር . . . . . . . ከዛን ተቃውሟችን ለአንድ ህዝብ እስከሆነ ድረስ አሁን እየደረሰብን ያለውን ግፍና መከራ ከወሬ በዘለለ መልኩ ወደተግባር እንለውጠው።

ህወሓቶች ህዝብና ሀገር ለማጥፋት አንድ ሆነዋል። እኛ ሀገርና ህዝብን ለማዳን እንዴት እንድ መሆን አቃተን? ለነገሩ ለጥሩ ነገር ህብረት ሃይል የለውም፤ለመጥፎ ነገር ግን ህብረት ሃይል አለው። አሁንም ጊዜው አልረፈደም ወቅቱ የሚፈልገው ህብረትና አንድነት ነው። ይህን ህብረትና አንድነት ህወሓቶች ደግሞ አይፈልጉትም። ይህ ስርዓት በዚህ አይነት ከቀጠለ የህዝባችን ስቃይና መከራ እንደሚቀጥል እሙን ነው።

የግንቦት 20 ፍሬዎች መግደል፣መታሰር፣መታፈን፣መፈናቀል እንዲሁም መሰደድ ሲሆኑ በ25  አመታት ውስጥ እነዚሁ በህወሓት ሲተገበሩና እየተተገበሩ ያሉ ናቸው።

ፎቶዎችን በመሰብሰብና በማስተካከል የፌስቡክ ጓደኞቼ የረዱኝ ናትናኤል መኮንን እና ጥላዬ ታረቀኝ ከልብ አመሰግናለሁ።

ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ!

የሁላችንም ችግር ህወሓትና ስርዓቱ ነው!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar