tirsdag 24. mai 2016

ሳይገነባ የፈረሰ ዲሞክራሲ!

ሳይገነባ የፈረሰ ዲሞክራሲ!

ህወሃት 25 አመታት ሙሉ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብቻለው እያለ መደስኮሩን ተያይዞታል። የህወሓት ገንብቻለው የሚለው ዲሞክራሲው ከወረቀትና ከአፍ ባልዘለለ መልኩ ሲነገርለት የሚኖረው ይህ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አንድም ቀን በህዝቦች መካከል በስራ ላይ ሳይወል ይህው በወሬ ብቻ ሆኖ ቀረ።

ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር እንደታገሉ የሚነግሩን ህወሓቶች አንዲትም ቀን ለህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት በተሞላበት መልኩ ለህዝቡም ሆን ለሀገሪቱ ሲሰሩ አይስተዋሉም። ከላይ እንደገለፅኩት የህወሓት ዲሞክራሲ ከወረቀትና ከአፍ ባልዘለለ መልኩ በምንም ላይ ሲተገበር አይታይም።

ዲሞክራሲ ማለት የመናገር መብት፣ የመፃፍ መበት፣  የመደራጀት መብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እነዚህ ሁኔታ በሌሉበት እንዴት ነው ዲሞክራሲን በሀገሪቱ ላይ አምጥተናል ብለው መነገሩ። እውን ህወሓት ዲሞክራሲን እንዴት አድርጎ ቢተረጉመው ነው የታገልነው ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ነው ሲል። እርግጥ ነው በህወሓት ለህዝቡ የመታሰር፣ የመገደል፣ የመታፈን፣ የመሰደድ፣ የመፈናቀል፣ የመታፈን ስርዓት ገንብቷል ይህ የማይካድ ሀቀ ነው።

ዲሞክራሲ በሌለበት ሀገር ውስጥ ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቷል ብሎ ማሰቡ እጅግ ሞኝነት ነው። ዜጎች የመኖር ህልውናቸው አጣብቂኝ ውስጥ ባለበት ሀገር ውስጥ ዲሞክራሲ አለ ብሎ መናገሩ እራስን እያታለሉ መኖር ማለት ነው። ለህዝቡ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንደታገሉ ቢናገሩም ነገር ግን እነሱ የታገሉለት ዋነኛ አላማ የህዝቦችንና የሀገር ታሪክ ማጥፋትና የህዝቡን ሀብት ለመዝበር ነው። ህወሓት ስልጣኑን የያዘው በዲሞክራሲያዊ ስርዓት በህዝብ ተመርጦ የህዝብን ይሁንታ አግኝቶ የመጣ ስርዓት አይደለም፤ በሃይል ስልጣን ያዘ፤ በሃይል ሀገርና ህዝብን የገዛ ያለ ስርዓት ነው።


በእነዚህ ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት ክ፫ ያላነሱ ምርጫዎችን ቢያደርግም አንዱንም ጊዜ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አላደረገም። ይህ ባለበት ሁኔታ ላይ እለት ተዕለት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገነቡ ቢነግሩንም ሀቁ ግን በሀገሪቱና በህዝቦቹ ላይ የሚፈፀመው ኢፍት ሃዊ ድርጊቶች ሲፈፀሙና እየተፈፀሙ ያሉ ናቸው። ከ1997  ምርጫ ወዲህ በሀገሪቱ ላይ ምንም አይነት የዲሞክራሲ ባልታየበት ገነባነው ያሉትም ዲሞክራሲ ለዜጎች ፍትህ ሲያጓድል እንጂ ፍትህ ሲሰጥ አልተመለከትንም። የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ ህወሓት ለስልጣኑ በመስጋት የተለያዩ አዋጆችን በማፅደቅ የመፃፍም ሆን የመናገር እንዲሁም የመደራጀት መብት እንዳይኖራቸው በማድረግ ህግ አውጥቶ አፅድቋል።

ይህን ተከትሎ ለዚሁ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ቀላል የሚባሉ አይደለም። በተለይ ፀረ ሽብር ህጉ አዋጅ ሆኖ ከፀደቀ ወዲህ ብዙን ምክንያትና አጋጣሚን እየጠበቁ ህዝቡን ለእስር እየተዳረጉ ይገኛል። ለዚህም ይህ አዋጅ ለሚፅፉ፣ ለሚደራጁ እንዲሁም ሀሳብን በነፃ ለሚገልፁ ለማፈን የወጣ ህግ ነው። ይህ ባለበት ሁኔታም ከህወሓት ጋር እየተናነቁ ያሉም ሀገርና ህዝብ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እጅግ የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው። ይህና መሰል ችግሮች ባለበት ሀገራችን ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቷል ብሎ ከማለት "ሳይገነባ የፈረሰ ዲሞክራሲ" ቢባል ጥሩ ነው። ባይ ነኝ እኔ

ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar