ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን ለነፃነት መታገል ያስፈልጋል !!
እኔ እምለው ኢትዮጵያውያን አንድ እንዳይሆኑ ተረግመዋል እንዴ?
ከቃልኪዳን ካሳሁን (ኖርዌ)
Ethnic Politics Split US Ethiopians እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በመላው አለም በተለይ በአሜሪካ፣ እንደገና በተለይ በዋሽንግተንየሚኖሩ ብዙ ዜጎች አሎዋት፡፡ ከትግራይ ይሁን ከሶማላ፤ ከኦሮሚያ ይሁን ከአማራ፣አፋር፣ደቡብ፣ቤን ሻንጉል፣ ድሬ፣ ሸገር… ብቻ ከየትምይሂደ ከየት የሁለም ኢትዮጵያውያን የስደት መነሾ “በፖለቲካ አልያም የተሻለ ህይወት” ፍልጋ ከመሆን አይዘልም፡፡
(በሀገሩ መኖርማ ማን ይጠላል …)
ብዙ ጊዜ የማስበው ታዲያ ኢትዮጵያውያኑ በሰው ሀገር ሲኖሩ እንዴውምከሀገር ውስጥ የበለጠ አንድነትና መግባባት ወይም አብሮ የመኖር ስሜትይኖራቸዋል ብዬ ነው፡፡ በሰው ሀገር የመኖርን የህይወት ትግል ለመልመድና ለማሸነፍም ከሀገር ልጅ የበለጠ አለኝታ፣ አይዞህ/ሽ ባይ እናአጋዥ የለምና፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች የምሰማው ግን ከዚህ በተቃራኒውየሆኑ እውነታዎችን ነው፡፡ በጥርጣሬ መተያየት፣ የብሔርና የፖለቲካክፍፍል …ሌላም ሌላም፡፡ እርግጥ ነው ሁላችንም አንድ አይነት አቋምሉኖረን አይችሌም፤ ከመሰረታዊ ጉዳዮች በስተቀር በእያንዲንደ ጉዲይሊይ የግድ ተመሳሳይ ሀሳብ እንዱኖረንም አይጠበቅም፡፡
የተለያየ የፖለቲካ አቋም ሉኖረን ይችላል፣ የተለያዩ ብሔሮች ልጆችምልንሆን እንችላለን፤ ኢትዮጵያውያን በመሆናችን ግን እነዚህ ሁለ ነገሮችበህልውናችን ላይ አንደጥላ ማጥላት የለባቸውም፡፡ ደግሞም ከተቀራረብንእነዚህ ሁለ ነገሮች ሊታረቁና ሁላችንንም የሚያስማሙ ሀሳቦችን ለመፍጠር ይቻላል። የአፍሪካ የነፃነት ምሳሌ የሆንን ዜጎች ህብረ ብሔራዊ ውበታችንን በእያንዳንዳችን ፓስፖርት ላይ ካለውኢትዮጵያዊነታችን ጋር የተጣበቁ የጋራ ተቀፅሊዎቻችንን (stereotypes) በማጥፋት የትም ቦታ አንገታችንን ቀና አድርገን ለመኖር ምቹሁኔታዎችን ልንፈጥርበት ይገባል፡፡
ልዩነቶቻችንን በማቻቻል የትም ይሁን የት በአንድነት መስራቱ ለዜጎቿና ለኑሮ ምቹ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠርና ዳግም ኢትዮጵያንታላቅ ለማድረግ ያስችለናል፡፡ ይሄም በቅርቡ እውን እንደሚሆን ተስፋ አለኝ!
ይኧዉ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተዳድረዉ ወያኔ/ህውሃት የህዝብ መብት በመንቀፍ ፣ዘረኝነትን በማስፋፋት ፣ሃገርን በመከፋፈል፣ጎሰኝነትን በማስተማር፣ አገር በመዝረፍ ፣አገርን በመሽጥ፣ ሰዉን ከሚኖርበት ቀዬ በማፈናቀል፣ በመቻቻል እንዳይኖር በማድረግ፣ ዘርከዘር ጥሊቻን ማስፈን፣ ቀጥሎበት ሃያ ሁለት ዓመታትን አስቆጠረ። እስከመቸ ይኧን ነገር ዝምብለን ማየት እንችላለን ።
እዚህ ጋር የሌለች ሀገራት ዜጎችን በሚያስቀና መልኩ አብሮ የመኖርና የመተባበር ባህልና ማህበራዊ ህይወት ያላቸው ባህር ማዶ አገርኢትዮጵያውያን እንዳሉ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይሁንና እነሱም ቢሆን እነዚህንና መሰል በኢትዮጵያውያን እህትና ወንድማማቾች መካከልእየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
ነጻነታችንን የቀሙን የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን እንደቀሙን ለረጂም አመታት ለመግዛት እንዲመቻቸዉ በዘር፤ በቋንቋ፤ በክልልናበሃይማኖት ከፋፍለዉን ከሃያ አንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የጀመሩትን እስራት፤ እግልት፤ ግድያና ዝርፍያ አሁንምእንደቀጠለ ነዉ። የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን ቀምተዉ እየገዙን ቢሆንም ገዛናቸዉ ብለዉ እጃቸዉን አጣጥፈዉ አልተቀመጡም። ዜጎችነጻነታቸዉንና መብታቸዉን እንዳይጠይቁ አፋቸዉን ያዘጋሉ፤ ለሌላዉ አንዳይቆም አገር፤ ስንደቅና ኢትዮጵያዊነት የሚባለ ትልልቆቹንየጋራ እሴቶቻችንን በየቀኑ ያፈርሳለ። ይህ የሚያሳየን ዜጎች ትልቅ ተስፋ ይዘዉ ቤተሰብ መስርተዉ ለራሳቸዉና ለአገራቸዉ የሚኖሩበትግዜ እየጠፋ ተስፋ መቁረጥ፤ ስልትና የመከራ ኑሮ ዘመን እየከበበን መምጣቱን ነዉ። ይህ ከሆነ የነገዋን የነጻነት፣ የፍትህ፣ የዳሞክራሲባለጸጋ ኢትዮጵያን ለማየት እያንዳንዱ ዜጋ በቻለው አቅሙ ሁለ ጠንክሮ በመታገል እና ከራሱ ባለፈ ለሌላው ዜጋ የነጻነት ትግለን ጎራእንዲቀላቀል ብልም የዚህ ትግሌ ባለቤት እንድሆን ያስፈልጋል፡፡የሀገራችን ህዝብ የነጻነት ችቦአቀጣጣይ የትግለ አካል በመሆን መስራትእንጅ፣ ከቶ ሌላ አካል፣ ሌላ ኃይል መጦ ነጻ ያወጣኛል በሚል በባርነት እየተገዛ መጠበቅ የለበትም። ነጻነትና ዳሞክራሲ በችሮታ አልያምከሰማይ እንደሚወርድ መና የሚጠበቅ ስጦታ አይደለም። ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል። አለበለዚያ “ላም አለኝ በሰማይወተትዋንም አላይ” እንዳይሆን ያስፈልጋል።
ነጻነት እኛ ሰዎች በቀደመት ወደዚህ አለም ስንመጣ አብሮን የሚመጣ የተፈጥሮ ፀጋ ነዉ። ነጻነት ከሌሎች የምንጠብቀዉ ወይም ማንንምስጠን ብለን የማንጠይቀዉ ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለንን፤ በዚህ አለም ቆይታችን ለደቂቃም ቢሆን እንዲነፍገን መፍቀድ የሌለብንኃብት ነዉ። ነጻነታችን እጃችን ላይ ሲኖር በግለሰብ ለረጃ የምንደሰትበት፤ እንድንቀማ በጋራ የምንጠብቀዉና እንደ ወያኔ አይነቱ ፀረህዝብ ኃይል ሲቀማን ደግሞ በጋራ ታግልን ማስመለስ የሚገባን የግልና የጋራ ኃብት ነዉ። ዛሬ ከ22 የወያኔ አመታት በኋሊ እኛኢትዮጵያዉያን በድህነትና በረሀብ የምንጠቃዉ፤ በዘረኝነት አለንጋ የምንገረፈዉ፤ የምንሰደደዉ፤ የምንታሰረዉና የምንገደለዉ ይህንንፈጣሪ ያደለንን ነጻነት የሚባል ኃብት ወያኔ አንድ፤ ሁለትና ሦስት እያለ ሲቀማን አፋችንን ዘግተንና እጃችንን አጥፈን ስለተመለከትንነዉ። መፈናቀላችን፤ስደታችን፤ ዉርደታችንና በገዛ አገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖራችን እንዲያበቃ ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭሌሎች መጥተዉ ነጻ ያወጡናል ከሚለዉ አመለካከት ተላቅቀን ነጻነታችንን ለማስመለስ ህዝባዊ ትግለን መቀላቀል ብቻ ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ የዘር በትር አለንጋ የሚደርስበት ግርፋት፣ ስቃይ፣ ርሃብ፣ ስደት፣ እንግልት በራሱ በህዝቡ ላይ ነው። ስለዚህህዝቡ ራሱ ለራሱ ነጻነት፣ በእምቢ አልገዛም ባይነት የሚነሳበት ጊዜው አሁን ነው። ነጻነትን ከነጻ አውጭዎች በመጠበቅ እስከመቼ የወያኔየጥይት ሰለባዎች እንሆናለን?
ወገን ሁለ ለራሱ ነጻነት፣ ህልውና ሲል የለውጡ እንቅስቃሴ ታጋይ የመሆን ኢትዮጵያዊ ግዴታውን እንዲፈጽም ጥሪ ማድረግ ይገባል ፡፡ለአገሩ፣ለማንነነቱ መሰዋእትነት ለመሆን እንደሚኮራ ሁለ አገሩም በሱ ትኮራለች ፡፡
ወያኔ በ 22 ዓመት ውስጥ የሰራው ወንጀል በወገናችን ላይ እንዲህ በቃላት ተዘርዘሮ አያልቅም።ይህ አልበቃ ብሎን። ታድያ ምንድን ነውአንድ ሆነን ከመታገል ፈንታ መለያየትን መረጥን!
ኢትዮጵያውያን አንድ እንዲይሆኑ ተረግመዋል እንዴ?
ከቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar