mandag 30. september 2013

በኖርዌይ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ በስኬት ተከናወነ::

በኖርዌይ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ በስኬት ተከናወነ::

ሴፕቴምበር 28, 2013 በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በኖርዌ ኦስሎ ከተማ የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የህዝባዊ ሃይሉ ከፍተኛ አመራር ኮማንደር አሰፋ እና የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንንና ጥሪ የተደረገላቸ እንግዶችና ከተለያየ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሃገሮች መጡና በጣም በርካታ የሆኑ በኖርዌ በሚኖሩ ከተለያየ ከተማ የመጡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በታላቅ ወኔና የሃገር ፍቅር ስሜት በስኬት ተከናወኖ አመሸ።


በዝግጅቱ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይሉ አመራር ስለድርጅታቸው በሰፊው ህዝቡን ያስደሰተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከታዳሚው የቀረባላቸውንም ጥያቄዎች በስፋት በማብራራት ለታዳሚው ከፍተኛ ግንዛቤ አስጨብጠዋል። በተመሳሳይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በምስል የተደገፈ ከፍተኛ ማብራሪያ ሰጥተው ከህዝብ የቀረበላቸውን ጥያቄዎች ሰፋ አድርገው አስረድተዋል።

በአንፃሩ እጃችን እረጅም ነው ብለው የሚያስቡ ጠባብ አስተሳሰብ ያላቸው የወያኔ ተላላኪ ቡድኖች ዲሞክራሲ ባለበት በኖርዌ ምድር መጥተ እንኳን የማይቀየሩ አምባገነኖች እዚህም ዝግጅታችን እንዳይሳካ ለማበላሸት እንቅልፍ ሳይተኙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን እየነፉ ህዝብ ለማደናገር የአሸባሪ ድርጅት ለመርዳት የገቢ ማሰባሰቢያ ሊያደርጉ ነበር ነገር ግን ፕሮግራሙ ተሰረዘ በማለት ዜና ቢያሰራጩም እኛ ግን እየረዳን ያለነው የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል በየትኛውም አለም በአሸባሪነት መዝገብ ውስጥ ያልተመዘገበ ድርጅት መሆኑን የኖርዌ ፕሮፌሰር በሃገሪቱ ውስጥ ለሚታተም አንድ ጋዜጣ አስተያየታቸውን የገለፁ ሲሆን በእለቱም ዝገጅቱ በደማቅ ሁኔታ ተከናውኖ ከዚህ ቀደም በየተኛውም የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮገራም ያልታየ ከፍተኛ የገንዘብ ገቢም ተደርጓል።

በአጠቃላይ በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ጨረታዎች፤ ቀስቃሽ ሙዚቃ፤ ባህላዊ ምግብና መጠጥ እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ለሽያጭ ቀርበው የነበረ ሲሆን በተጨማሪም የትጥቅ ትግል ለምን አስፈለገ በሚል አጭር ገላጭ ድራማ ቀርቦ ህዝቡን በጣም አስደስቷል። በዝግጅቱ መክፈቻና መዝጊያ ላይም የህዝባዊ ሃይሉ መዝሙር ላንቺ ነው ሃገሬ ላንቺ ነው የሚለው በህዝቡ ተዘምሮ ዝገጅቱም እኩለ ለሊት በድምቅት ተጠናቋል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ለወያኔ


Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar