tirsdag 3. desember 2013

ኢትዮጵያ ”ብሔር ብሄረሰብ” እያለች እንድትዘምር ሲፈረድባት ጎረቤቶቿ ግን በብሄር ስም የፖለቲካ ድርጅት መመስረትን በሕግ ከልክለው በአንድ ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ላይ ደረሱ


ኢትዮጵያ ያረጀ ያፈጀውን የማርክሲስት አስተሳሰብ ”ብሔር ብሄረሰብ” ርዕዮት እንድትዘምር ተፈርዶበታል።ህዳር 29 ቀን ጅጅጋ ላይ የቀለጠ ድግስ ተዘጋጅቷል።የእዚህ አይነት ዝግጅት commoncurrበኢትዮጵያ ወጣቶች መካከል ለምሳሌ በትምህርት ቤቶች መካከል የሚደረግ ከፖለቲካዊ ይዘት የራቀ ግን ወጣቶች የሚቀራረቡበት መልክ ቢኖረው ብዙ ፍሬ ባፈራ ነበር።የኢህአዲግ ዝግጅት ግን ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርጋቸው እልፍ ነገሮችን ማውሳት ትቶ የሚለያዩበት ነገር እየተነቀሰ የሚነገርበት መርሃ ግበር መሆኑ ነው አሳዛኙ ነገር።
ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ይሁን እንጂ ጎረቤቶቻችን ግን በሀገራቸው በብሄር ስም የፖለቲካ ድርጅት መመስረትን በሕግ ከልክለው በአንድ ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ላይ ደረሱ ።ቅዳሜ ህዳር 21/2006 ዓም የኬንያ፣ዩጋንዳ፣ታንዛንያ፣ቡሩንዲ እና ሩዋንዳ መሪዎች በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ተገናኝተው በአስር ዓመት ውስጥ የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራቸው የፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ማለት ኢትዮጵያን የሚቀናቀን ትልቅ ገበያ እንደሚፈጥሩ ይታመናል።ኢትዮጵያ በእዚህ ጊዜ ቢያንስ በታዛቢነት አለዝያም ከደቡብ ሱዳን፣ጅቡቲ፣ሱማልያ ወዘተ ጋር የጋራ ገበያ የምትፈጥርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባት ነበር።ከእዚህ ይልቅ ”ምኑ ቀርቶብኝ በወጉ በኮነነኝ” እንደሚባለው የጎረቤት የጋራ ገበያ ቀርቶ ጠንካራ ሃገራዊ አንድነት እንዳትፈጥር በብሄር እንድታስብ ተፈርዶባታል።ህዳር 29 በቴሌቭዥን እያዘፈነች እበላ ባይ አፈጮሌ ካድሬዎቿ ስሽሞነሞኑ ማየት የሰሞኑ አሳዛኝ ድርጊት ነው። ጉዳያችን

 | 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar