onsdag 11. desember 2013

የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የመንግሥት ተቋማት የኢንተርኔት መረጃዎችን ሚስጥራዊ ሊያደርግ ነው

ተቋማቱ በኤጀንሲው የተሠራውን ‹‹ዳጉ ሜይል›› መጠቀም ይገደዳሉ

የመረጃ ደኅንነት ኤጀንሲ በቅርቡ በፀደቀው አዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችና ኢንተርኔትን መሠረት ያደረጉ የመረጃ ልውውጦች ከኢንተርኔት ‹‹ሃከሮች›› (በርባሪዎች) ለመከላከል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ሊያደርግ ነው፡፡
ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት ተቋማት እንደ ጂ-ሜይል (Gmail) ያሉ የኢንተርኔት መልዕክት ማስተላለፊያዎችን እንዳይጠቀሙ ሊገደዱ ነው፡፡
insa-ethiopia1-620x310
ኤጀንሲው በቅርቡ ተግባራዊ ለማድረግ እያበለፀገ የሚገኘው ቴክኖሎጂ ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የመረጃ ልውውጥንና የመረጃ ማኅደርን ሚስጥራዊ የሚያደርግ መሆኑን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በእንግሊዝኛ ስያሜው ‹‹ፐብሊክ ኪይ ኢንፍራስትራክቸር›› በሚል የሚታወቀውና በርካታ የዓለም አገሮችና ግዙፍ የሚባሉ ተቋማት በአሁኑ ወቅት የሚጠቀሙበት ውድ የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፣ ኤጀንሲው ይህንን ቴክኖሎጂ በራሱ የሰው ኃይል እንዳበለፀገው ለመረዳት ተችሏል፡፡
የቴክኖሎጂ ውጤቱ በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ሲገመት፣ ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅትም ቁልፍ የሆኑ የመንግሥት ተቋማት የመረጃ ልውውጣቸውን በዚህ ቴክኖሎጂ ለማድረግ ይገደዳሉ፡፡
ቴክኖሎጂው በኢንፎርሜሽን ደኅንነት መስክ ‹‹ክሪፕቶግራፊ›› በሚል የሚታወቀውን የመረጃ ደኅንነት አገልግሎት በተቋማቱ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ ‹‹ክሪፕቶግራፊ›› ማለት በኢንተርኔት ወይም በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የሚተላለፍ ወይም የተቀመጡ መረጃዎችን መረጃው ከሚላክለት ተቀባይ በስተቀር ማንኛውም አካል ወይም የቴክኖሎጂ ውጤት መረጃውን እንዳያነበው ወይም እንዳይቀይረው የሚያስችል የመረጃ ምስጠራ ሳይንስ ነው፡፡
ኤጀንሲውን በድጋሚ እንዲቋቋም ያደረገው በቅርቡ የፀደቀው አዋጅ ለኤጀንሲው ከሰጣቸው ኃላፊነቶች መካከል ይህ የ‹‹ክሪፕቶግራፊ›› ወይም የመረጃ ምስጠራ ተግባር አንዱ ነው፡፡
ይህ ኃላፊነት ለኤጀንሲው የተሰጠበትን ምክንያት ለማብራራት በደጋፊ ማስረጃነት ከአዋጁ ጋር የተያያዘው ማብራሪያ የተሻለ ደኅንነት አላቸው የሚባሉ አገሮች በራሳቸው ቴክኖሎጂ ላይ ብቻ ጥገኛ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ኢትዮጵያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና የቴክኖሎጂውን እውቀት ያካበቱ ዜጎችም በጣም ውስን መሆናቸውን ያብራራል፡፡
በዚህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ በእጅጉ ኋላ የቀረች መሆኗንና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስፋት አገልግሎት ላይ የዋሉ የኢንተርኔት መረጃ መለዋወጫ መንገዶች (ቴክኖሎጂዎች) አሜሪካ በሚገኙ ኩባንያዎች መበልፀጋቸውን ይገልጻል፡፡ እነዚህም የጐግል፣ የያሁና የቢንግ ሰርች ኢንጂኖች እንዲሁም የፌስቡክ ማኅበራዊ ድረ ገጽ በአጠቃላይ የሁሉም ሰርቨሮች የሚገኘው በአሜሪካ መሆኑን ያትታል፡፡
ከላይ በተጠቀሱ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ሰርቨሮች በአሜሪካ የሚገኙ ናቸው ማለት አሜሪካ በሰርቨሮቹ የሚገኙ መረጃዎችን እንደልቧ ማግኘት የምትችል መሆኑን የአዋጁ አባሪ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡ ሌላው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ለአደጋ ተጋላጭ የሚያደርገው የቴክኖሎጂው መገልገያ መሣሪያዎች (እንደ ኮምፒውተርና ተዛማጅ መሣሪያዎች) በአምራቾች በሚፈበረኩበት ወቅት የተጋላጭነት ቀዳዳ (Back Doors) እንዲኖራቸው የሚደረግ እንደሆነና ይህም አምራቾች በፈለጉበት ወቅት በፈጠሩት ቀዳዳ ሠርገው በመግባት መረጃዎችን ከባለቤቱ ዕውቅና ውጭ እንደፈለጉ ማድረግ የሚያስችላቸው ነው፡፡
ኤጀንሲው በማገባደድ ላይ የሚገኘው የ‹‹ክሪፕቶግራፊ›› ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገው አገር አቀፍ የ‹‹ፐብሊክ ኢንፍራክትራክቸር›› ቢያንስ ቢያንስ ቁልፍ የሆኑ የመንግሥት ተቋማት መረጃዎችን ሚስጥራዊነት ወይም የመረጃው ባለቤትና ተቀባይ ባልሆኑ አካላት መነበብ ወይም መለወጥ እንዳይቻል ማድረግን በመሠረታዊነት ያካተተ ነው፡፡
በዚህ መሠረተ ልማት ከሚካተቱ የመንግሥት ተቋማት መካከል ፍርድ ቤቶች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ ኮምፒዩተራይዝድ የሆኑ ሥርዓቶችን የሚከተሉ ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት ካካሄደው ዓውደ ርዕይ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኤጀንሲው በራሱ የሰው ኃይል ያበለፀገው ‹‹ዳጉ ኢሜይል›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው እንደ ‹‹ያሁ›› እና ‹‹ጂሜይል›› የኢንተርኔት መልዕክት መለዋወጫ ቴክኖሎጂ ማበልፀጉን ለመረዳት ተችሏል፡፡ ‹‹ዳጉ ኢሜይል›› ከአፋር ብሔረሰብ የመረጃ መለዋወጫ ‹‹ዳጉ›› የተባለ ባህላዊ ሥርዓት መጠሪያ ስያሜውን እንዳገኘ በዓውደ ርዕዩ የተገለጸ ሲሆን፣ የሙከራ ትግበራው ተጠናቆ በኤጀንሲው ግቢ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በቅርብ ጊዜ ውስጥ ‹‹ዳጉ ኢሜይል›› ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑንና ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት በዚህ ቴክኖሎጂ ብቻ የመጠቀም ግዴታ እንደሚጣልባቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡
በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋሉ ተብለው የሚጠበቁት እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ኤጀንሲው ሰሞኑን አካሂዶ በነበረው ዓውደ ርዕይ ላይ ይፋ ሆነዋል፡፡ ኤጀንሲው የቴሌኮም ማጭበርበርን የመከላከል ኃላፊነት በአዋጅ ካገኛቸው ሥልጣኖች አንዱ ሲሆን፣ በዚህ የደኅነነት አገልግሎት ላይ በስፋት መሥራት በጀመረ በጥቂት ዓመታት ጊዜ ውስጥ 1.75 ቢሊዮን ብር ኪሳራ መታደጉን አስረድቷል፡፡
ከኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውጭ የስልክ ግንኙነት ከሌላው ዓለም ጋር በመፍጠር የተሰማሩ ወንጀለኞች መኖራቸውን የሚያስረዳው ኤጀንሲው የወንጀለኞቹ መረብ ከሕገወጥ ንግድ፣ ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርና ከሽብር ጋር የተገናኘ መሆኑን አሳውቋል፡፡ በመሆኑም በዚህ የቴሌኮም ማጭበርበር አገሪቱ 2.7 ቢሊዮን ብር ማጣቷን፣ ኤጀንሲው በስፋት ከተንቀሳቀሰ በኋላ ግን 1.75 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉንና 125 ሰዎችም በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጿል፡፡
በመረጃ ደኅንነት ዘርፍ በኢትዮጵያ ውስን እውቀት መኖሩ በገሃድ ያለ እውነት በመሆኑ፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍም የመረጃ ደኅንነት ትምህርት በትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት እንዳለበትና በዚህ ዙሪያም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመወያየት ላይ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ reporter

 

søndag 8. desember 2013

ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት


ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡

‹‹ይህ ህገ-መንግስቱን የመነዳ ተግባር ነው!!!›› ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ ለመፈረጅ ወይም ለመከሰስ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ ‹‹ ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው ?›› በማለት ሲተች ሰምቸዋለው፡፡በመናድ እና ደግፎ በማቆየት ላይ የተመሠረተሁን  ህገ መንግስት እጅግ በጣም ብዙ ነገር ተብሎለታል፡፡
እየተንገዳገደ ያለው ህገ መንግስት ከአፀዳደቁ ጀምሮ የሚቀሩት ድንጋጌዎች መኖራቸው ለማንም ግልፅነው፡፡ ቢሆንም ፀድቆ በተግባር ላይ የሚገኘው ህገ መንግስት ዋጋ እንዳይኖረው እያደረገ ያለው የገዢው መንግስት አካሄድና ተግባር መሆኑ በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለው፡፡
1ኛ. መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለው በሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ይሁን እንጂ ገዢው መንግስት በሃይማኖት ላይ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እየፈፀመ ይገኛል፤ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በእስልምና አይማኖታ እየተፈፀመ ያለው በደል ነው፡፡በደሉ በይፋ የወጣ ሲሆን በተለይ ለእምነታችን እንቢኝ ያሉ ለሞት፣ለእስርና ለእንግልት ተዳርገው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥም ጣልቃ ገብነቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡ገዳማትና አድባራት በልማት ስም ፈርሰዋል የተቀሩት ቦታቸው ተጎምዶ ተወስዶል በዚህም ምክንያት የሀይማኖት አባቶችና ጥቂት የማይባሉ የእምነቱ ተከታዮች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ በሁሉም በተለይ በኦርቶዶክስና በእስልምና የሀይማኖቱ መሪዎች (አባቶች) ሹመታቸው ከሚያመልኩት አምላክ እና ከምዕመናኖ የመነጨ ሳይሆን በመንግስት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት የተፈፀመ ነው፡፡
2ኛ. የመንግስት አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት፡፤ በሕገ መንግስት አንቀጽ 12 ንዕሱ አንቀፅ 1 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ቢሆንም ከታችኛው የስልጣን እርከን ከሆነው ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይኛው የመንግስት ባለስልጣናት አማከኝነት የሚከናወኑ የመንግስት አሰራሮች ግልፅነት እጅግ በጣም ጠባብ ነው፡፡በመሆኑም ህብረተሰብ በአገሩ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን በመንገስት አሠራር ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አልተደረገም፡፡
በዚህም ምክንያት የመንግስት አሠራር ለሙሱና የተጋለጠ ነው፤ሙሱና በአሁን ወቅት በአገራችን ህጋዊ እስከመሆን ደርሷል፡፡በመሆኑም ማናኛውም የመንግስት ኃላፊ ኃላፊነቱን ወይም ስልጣኑን መሠረት አድርጎ ሲበድል እንጂ ለበደሉ ተጠያቂ ሲሆን አልታየም፡፡ስለዚህም የመንግስት አሠራር በየትኛውም ደረጃ ለህዝብ ግልፅ አይደለም ይህ ደግሞ የህገመንግስቱ ድንጋጌ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
3ኛ. ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው፡፡ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 14 ተፅፎ ይገኛል፡፡ነገር ግን የሰው ደህንነትን ለመጠበቅ የተቋቋመው የደህንነት መስሪያ ቤት በየደኑና በየጫካው የስንቱን ሰው ህይወት እንዳጠፋና የአካል ጉዳት እንዳደረስ የሚያውቀው ያውቀዋል፡፡ በተጨማሪ ይህ የነፃነት መብት ገዢው መንግስት በችሮታ ወይም በፍቃዱ የሰጠን እንጂ ሰው በመሆናችን ያገኘነው መብት እንዳልሆነ በሚያሳብቅ መልኩ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት በገዢው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረተ እስከሚመስል ደረስ ተደርሷል፡፡
4ኛ. ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት ፣ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 18 ላይ ይገኛል፤ ይህ የህገመንግስት ድንጋጌ መሸራረፍ ሳይሆን መገርሰስ የሚጀምረው በህገመንግስቱ በተቋቋመው በህግ አስፈጻሚው አካል ነው፡፡
በመሆኑም ክብርን ለማወረድና ጭካኔን ለማሳየት የሰለጠኑ አሰቃዮችና ማሰቃያ ቦታዎች መኖራቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ነገሩን ለማነፃፀር እንዲረዳ  ፖለቲከኛ ወይም በህግ ጥላ ስር ያለ ሰውን ይቅርና ስታዲዮም እግር ኳስ ለመመልከት ወራፋ የሚጠብቅ በወረፋ ምክንያት ለተነሳ አለመግባባት ፖሊስ እንዴት አድርጎ እንደሚቀጠቅጥ ዱላውን የቀመሰ ያውቃል፡፡
5ኛ. በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ እና ከሰዎች ወይም ከጠያቂዎቻቸው የመገናኘት መብት አላቸው፡፡ በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 21/1እና2 ተፅፎ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ ነፃ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች አያያዛቸው ክብርን ከመንካት አልፎ በህይወታቸው ላይ አደጋ የሚያስከትል ነው፡፡በተጨማሪ ከቤተሰብ፣ከወዳጅ መጠየቅ የማይሞከር ነገር ነው፤ የመጠየቅ እድል ያላቸው እስረኞች እድላቸው በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
6ኛ. ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? እርግጥ ነው ገብያውኑ መሰረት ያደረጉ መዝናኛ ላይ ያተኮሩ መፅሔትና ጋዜጣ ለቁጥር በዝተው ይሆናል፡፡ ግን ሁሉ ነገር በአገር ነው የሚያምረው! ታዲያ ስለ አገር በነፃ አሳብ የሚንሸራሸርበት መፅሔትና ጋዜጣ ምን ያኸል ነው ? ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ መጥፎ ሪከረድ አስመዝግባለች፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ተጠራርጎ ቃሊቲ የሚገባበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
7ኛ. ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ ሠላማዊ ሠልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 30/1 ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆን የቅርብ ጊዜ አይን ያወጣ የህገመንግስት ጥሰት ማቀረብ ይቻላል፡፡በሳውዑዲ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍና በደል ይቁም፣ይህንንም የፈፀሙ ለፍርድ ይቅረብ በማለት አቤቱታ ለማቅረብ የተጀመረው ሠላማዊ ሠልፍ በፖሊስ ዱላ እና እስራት ነው የተጠናቀቀው፡፡ በተጨማሪ በመንግስት እየታየ ያለው የአስተዳደር ብሉሹነት ለማመልከት እና ምላሽ ለማገኘት የተጠሩ የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች እና ስብሰባዎች በመንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ ተከልክሏአል፡፡ሠላማዊ ሰልፍ ማድረግ እና አቤቱታ ማቅረብ መብት ነው! በማለት ክልከላውን ወደ ጎን በመተው አደባባይ ለመውጣት የሞከሩ ለእስርና ለድብደባ ተዳርገዋል፡፡በመሆኑም የተቃውሞ ሠልፍና ስብሰባ በማድረግ አቤቱታ በኢትዮጵያ ማድረግ የሞት ሽረት ትግልና ጥያቄ ከሆነ ሰንብቷል፡፡
8ኛ. የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ሆነ አካል ተፅዕኖ ነጻ በመሆን በሙሉ ነፃነት ከህግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም፡፡በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 79 እና በተከታዮቹ ንዑስ አንቀፅ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች የመንግስት አስፈፃሚ አካል ከሆነው ነው ሹመታቸውን የሚያገኙት፡፡በመሆኑም ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ግኝኙነት ያላቸው የፍርድ ውሳኔዎች ምንያኽሉ በህግ እና በህሊና ላይ የተመሠረቱ ናቸው ? በተለይ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የፍርድ ሂደታቸው ምን ይመስል ነበር ? እነዚህን እና መሰል ዳኝነቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በህገመንግስቱ የሰፈረው ነጻ ዳኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
9ኛ. የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የጎሳዎች ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡፡ ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 87/1 ተደንግጎ ይታያል፡፡ነገር ግን በየድንበር እና በተልኮ ጭዳ ከሚሆነው ውጪ አብዛኛው የሠራዊቴ አባል እና አዛዥ የአንድ ጎሳ ስብስብ ነው፡፡ ስለዚህም ሠራዊቱ የማነው የኢትዮጵያ ወይስ ወደሚል ጥያቄ እያመራ ይገኛል፡፡
10ኛ. በየደረጃው ትክክለኛ ምርጫ እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 102 ላይ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሹመታቸው ከመንግስት መልካም ፍቃድ የመነጨ ሲሆን አሰራራቸውም ለገዥው መንግስ በእጅጉ በጣም ያደላ ነው፡፡ስለዚህም ምርጫ ቦርድ ህገመንግስቱን መሠረት አድርጎ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ለማለት ከበድ ድፍረትን የሚጠይቅ ነው፡፡
በመሆኑም እነዚህ እና መሰል የህገመንግስቱ ድንጋጌዎች ጥሰት ወይም በእነሱ ቋንቋ የመንድ ተግባር እየተፈፀመ ያለው በህገመንግስቱ በየወንዙ ዳር የሚማማለው ገዥው መንገስት ነው፡፡ ህገመንግስት የበላይ ህግ ነው፡፡ማንኛውም ህግ፣ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን አሰራር ከህገመንግስቱ የሚቃረነረ ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም ፡፡ የሚለው አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 የገዥው መንግስት ደራሽ ዉሃ ጠራርጎ ወስዶታል፡፡ ስለዚህም የብሔሮ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የሚለውን መጠሪያ ስም በመስጠት ከበሮ ተይዞ የሚደለቅለት እና የሚከበረው ህገመንገስት መልሶ ካላስከበረ ፌሽታው እና ቀረርቶው ከምን የመነጨ ነው  ?
ይድነቃቸው ከበደ

ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታቸው በጉምሩክ እንደተወሰደባቸው ተናገሩ

ህገወጥ ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ 

radar_homeward_bound

የፍተሻ ሰራተኞች ሻንጣዎቻቸውን በመፈተሽ፣ ሞባይል ከአንድ በላይ ከያዙ ትርፉን በማስቀረት፣ አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቁሶች የተወሰኑትን ብቻ በመፍቀድ እና ያመጡትን ወርቆች ግራም በመቀነስ ንብረታቸውን እየወሰዱባቸው እንደሆነ ተመላሾቹ ገልፀዋል፡፡ መሃመድ አባመጫ የተባለ የሳኡዲ ተመላሽ፤ ከሳውዲ ስድስት ሻንጣ ይዞ መምጣቱን ገልፆ፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ግን ከሁለት ሻንጣ በላይ ይዞ መግባት እንደማይችል፣ ከአምስት ሞባይሎችም ሁለቱ ብቻ እነደተፈቀደለት ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ የሳውዲ መንግስት ከአንድ ኪሎ በላይ ወርቅ ይዛችሁ መውጣት አትችሉም የሚል መመሪያ ማሳለፉን የጠቆመው ተመላሹ፤ ንብረቱን እዚያው ጥሎ ለመመለስ መገደዱን ገልጿል፡፡ የሳኡዲ መንግስት እንኳን ከወርቅ በስተቀር ሌላ ንብረታቸውን ሁሉ ይዘው እንዲወጡ መፍቀዱን የገለፀው መሃመድ፤ በአገራቸው ንብረታቸውን እንዳያስገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘነው ይናገራል፡፡

ኤሌክትሮኒክስና ለቤተሰቦቹ ያመጣውን ልብሶች ቀረጥ ከፍለህ ነው የምትወስደው በመባሉ፣ ለሁለት ቀን በስደት ተመላሾች በተዘጋጀው ድንኳን ውስጥ ያለምንም ፍራሽና ልብስ ተኝቶ ንብረቱን ቢጠብቅም ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል፡፡ “ሳዑዲም እዚህም ሀገራችን ስንደርስ እየበደሉን ያሉት ሃበሾች ናቸው” ያለው መሃመድ፤ መንግስት በሚዲያ በተሟላና በተደላደለ መንገድ እንደሚቀበለን ቢገልፅም እዚህ የጠበቀን ግን ሌላ ነው ሲል ቅሬታውን ገልፆ “ሌላው ቢቀር እስካሁን ተመላሾቹን የሚያመላልሰው እንኳን የሳዑዲ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት አይደለም” ብሏል፡፡ ከሳኡዲ ካመጣችው ወርቅ ላይ ሃምሳ ግራሙን ብቻ እንደምትወስድ የተነገራት ተኪያ ሙሃመድን ያገኘናት በቁጭት መሬት ላይ እየተንከባለለች ነበር፡፡
ተኪያ እያለቀሰች እንደነገረችን፤ ለ14 ዓመት ሰርታ ከሶስት መቶ ሃምሳ ግራም በላይ ወርቅ እንዳጠራቀመች ገልፃ፤ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከሳውዲ እንድትወጣ ከመገደዷ በፊት ሙሉ ንብረቷን አስቀድማ ብትልክም እስካሁን እንዳልደረሰላት ትናገራለች፡፡ አሁንም፤ ከተመለሰች በኋላ የያዘቻቸውን ሻንጣዎች ለመውሰድ እንዳልቻለች የምትገልፀው ተኪያ፤ በፍተሻ ስም ሰራተኞቹ ሻንጣዋን በርብረው በማየት፣ ያመጣቻቸውን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ሶስት ሞባይሎች መውሰዳቸው ሳይንስ፣ ሶስት መቶ ግራም የሚመዝን የወርቅ ንብረቷን እንዳታስገባ መከልከሏን በጩኸት ትናገራለች፡፡ ለምን ንብረቷን እንደከለከሏት ስትጠይቅም “እናንተ ነጋዴዎች ናችሁ፤ በስደተኞች ስም ያለቀረጥ ንብረት ለማስገባት ትፈልጋላችሁ” በማለት ሰራተኞቹ እንደመለሱላት ገልፃ፤ ጉዳዩን ለአለቆቻቸው ለማመልከት ብትፈልግም የሚያናግራት ሰው አለማግኘቷን ጠቁማለች፡፡ በዚሁ ስፍራ ያገኘናቸው በርካታ ተመላሾች፤ የንብረታቸው ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ይናገራሉ። ንብረታቸውን ሳይዙ ወደቤተሰቦቻቸው ላለመቀላቀል በሚል የተሰበሰቡበት ካምፕ፣ ምንም ለማረፊያ የተመቻቸ አገልግሎት ባለመኖሩ መቸገራቸውንም ገልፀዋል፡፡ መንግስት የሚሰጣቸውን 900 ብር፣ በትራንስፖርትና በስልክ አገልግሎት እንደሚጨርሱ አክለው ተናግረዋል፡፡
በርካቶች በእቃዎቻቸው መታገድ በመበሳጨታቸው ጭቅጭቅና አላስፈላጊ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት መገደዳቸውን ተመላሾቹ ይናገራሉ፡፡ “ስንመጣ የሚሰጠንን ሊሴ ፓሴን አይተው ማስተናገድ ሲገባቸው እነሱ ግን ንብረታችንን እየወሰዱብን ነው” በማለት የሚናገሩት ተመላሽ ዜጎቹ፤ “ምናልባትም ንብረት የላቸውም ብለው አስበውን ይሆናል፤ ነገር ግን በርካታ አመታት ስንቆይ መቼም ባዶ እጃችንን አንመጣም” በማለት በምሬት ይናገራሉ፡፡ “ዛሬ እቃችንን የከለከሉን ነገ ምን ተስፋ ይዘን ነው ተደራጅታችሁ ስራ ስሩ ለሚሉን?” የሚሉት እነዚህ ተመላሾች፤ “በመንግስት ላይ አመኔታ የጣልነው ሳውዲ ድረስ በተወካዮቹ አማካኝነት መጥቶ ባናገረን መሰረት ነበር፤ ነገር ግን የተገባልን ቃል ታጥፏል” ይላሉ፡፡ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠቱ እና ለቤተሰብ መርዶ ባለመነገሩ፣ ለሚያውቋቸው ቤተሰቦች መርዶ ለመንገር ጭንቀት ላይ መሆናቸው ሌላ ችግራቸው እንደሆነ የተናገሩት ተመላሾች፤ አሁንም ቢሆን ሳውዲ ላይ ሃበሻዎችን በመኪና እየገጩ መግደል የሳውዲ ፖሊሶች የቀን ተቀን ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ታዲያ በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አምልጠው የሚመለሱ ዜጐችን ንብረት መቀማት ምን የሚሉት ተግባር እንደሆነ አልገባንም፤ በማለት አማርረዋል-ተመላሾቹ፡፡ ምናልባትም የፖለቲካ ማራመጃ ሊያደርጉን ነው በማለትም ስጋታቸውን አንፀባርቀዋል፡፡
ተመላሾቹ የተሟላ መጠለያ ተዘጋጅቶላችኋል በተባለበት ቦታ ሳይቀር፣ መተኛ ሥፍራ እንኳን እንዳልተዘጋጀ ሲረዱ ተስፋ መቁረጣቸውን እና ንብረታቸውን እንዳያስገቡ ሲከለከሉ፣ ተመልሰው በህገወጥ መንገድ ለመሰደድ ሙከራ መጀመራቸውን ይገልፃሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው፤ “ተመላሾቹ ስለንብረት የሚያነሱትን ጥያቄን በተመለከተ፤ እኛ ተመላሾች በሙሉ ንብረት እንደሌላቸው ነው የምናውቀው“ በማለት ተናግረዋል፡፡ አምባሳደሩ አልፎ አልፎ ባዶ እግራቸውን ከሳዑዲ የተመለሱ እንዳሉ ጠቁመው፤ በሳኡዲ መንግስት ጓዛችሁን ይዛችሁ እንዳትወጡ ተከልክላችኋል በመባላቸው፣ መጀመሪያውኑም ንብረት ይዘው ባለመምጣታቸው ነው፤ ብለዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች ከመደበኛ የአየር መንገዱ ተጓዦች እኩል እንደማይስተናገዱና ለብቻቸው ተጠብቀው እንደሚስተናገዱ ገልፀው፤ ምናልባት ከነዚህ ዜጎች ጋር ተቀላቅለው የሚመጡ ሌሎች ሰዎች ስለሚኖሩ እሱን ለማጣራት ንብረታቸው ይፈተሻል እንጂ ማንም የእነሱን ንብረት የሚወስድ እንደሌለ የተናገሩት አምባሳደሩ፤ እንኳን በሀገር ውስጥ የገባ ንብረት፣ ሳዑዲ ያለውንም የላባቸውን ውጤት ለማስመጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የሟቾችን ቁጥር እና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ አለመንገርን በተመለከተ አምባሳደሩ በሰጡት ምላሽ፣ አሁን ሙሉ በሙሉ ትኩረታችን በህይወት ያሉ፣ ንብረታቸውን ያጡ እና ጉዳት የደረሰባቸው ላይ ነው፤ ብለዋል፡፡ የሟቾቹን ቁጥር በተመለከተ ግን መንግስት ከገለፀው በኋላ፣ የተፈጠሩ ነገሮች መኖራቸውን አምነው፤ ነገር ግን ቁጥሩ ላይ ተመላሾች የሚሉትና አንዳንድ ሚዲያዎች የሚያወሩት ትክክል ሊሆን ቢችልም የተጣራ ነገር እስካላገኘን ድረስ የሞቱበትን ሁኔታ ለማወቅ ያስቸግራል፤ ብለዋል፡፡ የሳውዲ አየር መንገድ እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመመለሱ ሂደት ምንም አስተዋፅአ ለስደተኞቹ አላደረገም ለተባለው አምባሳደሩ መልስ ሲሰጡ፡- የሳውዲ አውሮፕላን የሚያመላልሰው እራሱ በማባረሩ ምክንያት ነው፤ ወጪውን የሚችለውም እራሱ ነው ብለዋል፡፡ addisadmas

ሚሚ ስብሃቱ ጠረጴዛ ምን ያደርግላታል?


mimi-sibehatuጠረጴዛ ከመመገቢያነት፣ለመጻፊያ ማስደገፊያነትና ከቁሳቁስ ማስቀመጫነት በተጨማሪ በዙሪያው በሚኮለኮሉት ወንበሮች የተነሳ ሰዎችን በአንድነት መሰብሰብ በመቻሉ የሐሳብ መንሸራሸሪያ መድረክ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡ ግለሰቦችና ቡድኖች በፊት ለፊታቸው በተዘረጋው ጠረጴዛ ላይ ሐሳባቸውን፣አመለካከታቸውንና አይዶሎጂያቸውን ያቀርባሉ፡፡የተጣሉ፣ልዩነት ያለባቸው ወገኖችም በጠረጴዛ ዙሪያ ቅራኔያቸውን ለማጥበብ ይደራደራሉ፡፡
ሚሚ ስብሃቱ ከቪኦኤ መልስ በታደለችው ዛሚ ራዲዩ ጣቢያ አማካኝነት ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ››የተባለ መርሃ ግብር ታዘጋጃለች፡፡በሚሚ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲታደሙ የሚፈቀድላቸው ወይም በቋሚነት በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ጋዜጠኝነታቸው‹‹በጠረጴዛው››የተወሰነ መሆኑም ድንቅ ይለኛል፡፡
ጋዜጠኞቹ ሚሚ ስታሽካካ አብረዋት የሚያሽካኩ የራሳቸው ሳቅ ወይም ለቅሶ የሌላቸው ‹‹እንገላበጥ››በማለት የሚጠይቁ ሁሌም ባለችው ላይ የሚጨምሩ መሆናቸውም ‹‹ጠረጴዛው››እውነት ከብበውታልን በማለት እንድጠይቅ ያደርገኛል፡፡
ሚሚ ዳዊት ከበደ መታሰር ይገባዋል ካለች ቀሪዎቹ የጠረጴዛው ታዳሚዎች‹‹እስካሁን አለመታሰሩ እንደሚገርማቸው ያክላሉ፣አንድነት ፓርቲ የግንቦት 7 ትርፍራፊን ለማግኘት ይሰራል ካለች አጃቢዎቿ ‹‹ለዚህ እኮ ነው የጸረ ሽብር አዋጁ ይሰረዝ የሚለው ይላሉ፡፡
ዛሬ አንድ ወዳጄ ደውሎ ሚሚን ስማት አለኝ፡፡ወሪያቸው ሚስ አና ጎሜዝን የተመለከተ ነበር ፡፡ሚሚ የስድብ መዝገበ ቃላቷን ጠረጴዛዋ ላይ ከፍታ ፖርቹጋላዊቷን የሰብዓዊ መብት ታጋይና የአውሮፓ ፓርላማ አባል ታወርድባታለች፡፡አና ሚሚን ባትሰማትም ሚሚ በተሳደበች ቁጥር ማንነቷን የምትገኝበትን ስብዕና የበለጠ እመለከት ነበር፡፡ማን ነበር ሰው አፉን ሲከፍት ሆዱ ይታያል ያለው፡፡
ሚሚ አና ጎሜዝ ወደ አገራችን እንድትገባ በመደረጓ ብዙ ኢትዮጵያዊያን አዝነዋል፡፡ብላለች የእርሷ ብዙ ስንት እንደሆነ ባይገባኝም፡፡አና ለሚዲያዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች መለስን መረር ባሉ ቃላቶች መግለጻቸው ሚሚን አንጨርጭሯታል፡፡እንዲህ በመናገሯ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ተቆጥተዋል ከማለትም አልተመለሰችም ‹‹መለስ መላጣ ብሎ ማንም ሊሰድበኝ ይችላል መላጣዬን ግን እንዲነካ አልፈቅድለትም››ማለታቸውን ሚሚ እንዴት እንደረሳቸው አልገባኝም፡፡አና መለስን ‹‹አጭበርባሪ ነበር››በማለት ገልጸውታል፡፡አያጭበረብርም የሚል ካለ አናን መሞገት እንጂ‹‹እንዴት ብሎ በጠረጴዛ ዙሪያ የስድብ መዓት ማዝነብ የሚቻል አይመስለኝም ፡፡
አና መለስን እንዲህ ያሉት ከመሬት ተነስተው አልነበረም፡፡ያው ምርጫ 2005ን ማስታወስ ብቻ ይበቃል፡፡እነ ሚሚ የመለስን የቲና ተርነር ዘፈን በማስታወስም ወይዘሮዋ ብርሃኑ ነጋ ጋር ስለነበራቸው ግኑኝነት ለመሳለቅ ሞክረዋል፡፡እንግዲህ አና በዘንድሮው የአዲስ አበባ አመጣጣቸው ደመቅ ያሉ ፎቶ ግራፎችን ከአባ ዱላ ገመደና ከተሾመ ቶጋ ጋር ተነስተው ተመልክተናል፡፡አና አባዱላን ወይም ተሾመን አፈቀሩ ወይስ ሁለቱ ሰዎች አናን ከብርሃኑ ነጠቁ?
እነሚሚ ይህንን ሊያነሱ አልቻሉም፡፡ከዚህ ይልቅ ተዘባዝበው አድማጮቻቸውን ተሰናበቱ፡፡እኔ ልጠይቅ በዛሚ ጠረጴዛ የሚሰባሰቡ ሰዎች አንድ አይነት ዘፈን የሚዘፍኑ ሚሚ ያለችውን እንደ በቀቀን የሚደግሙ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ ናቸው፡፡ታዲያ ጠረጴዛ ምን ያደርግላቸዋል፡፡ባዶ ቤት አይሻልም፡፡ለእስክስታውም ይመቻል ብዬ እኮ ነው፡፡
ከዳዊት ሰለሞን

tirsdag 3. desember 2013

ዜጋ አገሩን እንዲጠላና ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረጉ ያሉ ችግሮች መፍትሔ ያላገኘ ችግር እየተባባሰ ሄዶ አገርንና ሕዝብን ለአደጋ ይዳርጋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በቅድሚያ መፍትሄ ማግኘት ያለበት የመንግስት አመራር እና ፖሊሲ ሊታለፍ የማይገባው ጉዳይ ነው:: ወያኔ ተሸክሜዋለሁ ከሚለው መንግስታዊ የህዝብ ሃላፊነት አንጻር ሲታል ለዜኦች እና ለሃገሪቱ ደንታ ቢስ በሆኑ ብድናዊ የማይናበቡ አመራሮች ታጥሮ ከፊቱ የማይፈታው ከባድ አደጋ በራሱ እና በሃገኢቱ ላይ ጋርጧል::በሃገራችን ውስጥ ጠንካራ እና የጋራ የሆነ ንቁ መንግስት አለመኖሩ ህዝቦች ነገን በጭለማ እንዲያማትሩ እያደረገ ሲሆን በፖለቲካ ዱላ እየታሸ ያለው ህዝብ በኑር ውድነት እየተገረፈ ያለው ህዝብ ከአደጋ ራሱን ለማዳን እየተራወተ እየታገለ ይገኛል::

የወያኔ ገዢዎች ሃገርና ሕዝብን ሳያወያዩ እና ሳያማክሩ በሚፈጥሩት የሰነድ እና የጥናት የእቅድ ጋጋታ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ መቃብር ውስጥ ከመክተታቸውም አልፈው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ራሳቸው የፈጠሯቸው ፕሮጀክቶች በገንዘብ እጥረት ምክንያት እየቆሙ ሲሆን የፖለቲካ ጡዘት በወሕኒ እንዲገደብ መደረጉ የሃይማኖት ጥያቄዎች መፍትሄ አለማግኘታቸው የሰው ልጅ መብቶች ሕጋዊ መሰረት አለመያዛቸው እንዲህና የመሳሰሉት ጉዳዮች መፍትሄ ስላልተሰጣቸው ተስፋፍተው ሃገሪቱን አደጋ ውስጥ መንግስት ነኝ ባዩንም አጣብቂኝ ውስጥ ከተውታል::

ገዢው ፓርቲ ውስጣዊ አንድነቱ ተናግቶ በሃገር አመራር ላይ በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው አለመናበብ እናም መራራቅ በሃገሪቱ እየተስፋፋ ለመጣው ችግር ዋነኛ መንስኤ ከመሆኑም በላይ የህዝብ አካል ነኝ የሚል ዝግጁነት ከነኣካቴው ጠፍቷል::የገዢው ፓርቲ ሰዎች በሙስና ተጨማልቀዋል::ይህ ሙስና ከመስፋፋቱ በፊት ምንም አይነት እርምጃ ሲወሰድ አይታይም የሙስና ምንጩን ማድረቅ ሳይሆን የተያዘው በፓርቲ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ባላንጣዎችን እና ወዳጆቻቸውን መንከስ አስመስሎታል:: ከሙስና አንዱ አካል የሆነው የፖለቲካ ሙስናም በአመራሮቹ ውስጥ ተስፋፍቶ የህዝብ ጩኸት ሰሚ አቷል::በተለያዩ መስኮች የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሙስናዎች እንደአዲስ እየተፈጠሩ ነው:;ይህ አደገኛ አደጋ መፍትሄ ካልተበጀለት....
የወያኔው ጁንታ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለበት የሃገሪቱ በጀት ጸደቀ ለዚህ ፕሮጀክት ይህን ያህል ተመደበ እየተባለ በቃላት ጣፍጦ ቢወራም ተግባር ላይ ግን ተመደበ የተባለውን ለመልቀቅ ከባድ ፈተናዎች ውስጥ ገብቷል::የበጀት አፈጻጸም እንዳይኖር ከባድ እንቅፋቶች እየገጠሙ ነው የባንጎች እንቅስቃሴ ከመድከሙም በላይ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ከባድ እና የማይፈታ የገንዘብ ግሽበት እና መፍትሄ ተብለው የሚወሰዱ ውሳኔዎች ወያኔን ናላውን አዙሮታል::

ህዝቡ አቤቱታውን የሚያሰማበት አካል የለም:; መልካም አስተዳደር ፖለቲካን የተመረኮዘ እንጂ ህዝባዊነትን ያቀፈ አይደለም የመንግስት ባለስልጣናት እና የህዝብ አገልጋዮች በፓርቲ ስብሰባ ተጠምደው እለት ከእለት የህዝኡን አቤቱአይደለም የቤተሰቦቻቸውን ፍቅር እና እንክብካበ ሊያስተናግዱ አልቻሉም::የፓርቲ ስራ እና የመንግስት አገልግሎች በጋራ መማከሉ አለመለየቱ ከባድ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየፈጠሩ ናቸው ይህ ደግሞ የገዢው ፓርቲ አደገኛ አካሄድ የፈጠረው አደጋ ነው:: ...የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች መፈታት ሃገርን ከአደጋ ይታደጋታል ሰላምንም ይሰጣታል::

በአሁን ሰአት ከበፊቱ በባሰ መልኩ ከፍተኛ የተማረ የሰው ሃይል እንዲሁም የሰለጠነው በተጨማሪም ከስደት ተመላሹ ዜጋ በስራ አጥነት ተወጥሮ ስለሚገኝ የስራ እድሎች እንዴት እንደሚፈጥር ወያኔን ግራ ገብቶታል:: ዜጎች በሃገራቸው የሚገባቸውን መብት ማግኘት ከጀመሩ እና ባወጡት ህግ መገዛት ከቻሉ እንዲሁም እያንዳንዱ ዜጋ በሃገሩ እንዲያገባው ተደርጎ ከተገራ እና እኔ አውቅልሃለሁ ማለት ከቆመ በተጨማሪም ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች ተደርገው በሃሳብ አማራኝ ላይ ለሃገር የሚበጀው ከተሰራ ሁላችንም በነጻነት መኖር እንደምንችል ማረጋገጥ እወዳለሁ::


ምንሊክ ሳልሳዊ

ESAT Special Mesay With Dr Berhanu Nega Dec 02, 2013


ESAT DC Daily 2 Dec 2013


የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ


አውሮፕላኑ ቅዳሜ ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ደርሶ ከተርሚናሉ ስወጣ፣ ተጠራጥሬ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ የድሬ የጠዋት ፀሐይ ከተለመደው ለእናት ሀገር ሲባል!›ን እየዘመሩ ወራሪውን የሶማሊያ ወታደር የኢትዮጵያ ምድር ግዛቱ ሳይሆን፣ መቀበሪያው ማድረጋቸውን ታሪክ መዝግቦታል፡፡ንዳዷ ጋር የአዲስ አበባን የቀትር መራራ ፀሀይን ታስከነዳለች፤ እናም አጥበርባሪ ጨረሯን ያለምህረት ስትለቅብኝ፣ ጓደኛዬ መኪና ይዞ እቦታው እስኪደርስ መጠበቁ በገዛ ፍቃድ መለብለብ ስለመሰለኝ፣ በቀጥታ ከተደረደሩት ታክሲዎች አንዱን ይዤ ወደ ከዚራ አመራሁ፤ ድሬ የሄድኩት በዋናነት ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት በመሆኑ ሊቀበለኝ የተዘጋጀውን
ጓደኛዬን ደውዬ ከማውቃቸው የአንዱን ሆቴል ስም ጠቅሼ እዚያ እንድንገናኝ ነገርኩት፡፡
የሆቴሉ ፍተሻ ከወትሮው ጠንከር፣ ጠጠር ያለ በመሆኑ ትዕግስትን ይፈትናል፡፡ እንዲህም ሆኖ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ማረፊያ ክፍሎች በሙሉ መያዛቸው ተነግሮን ቀኝ ኋላ ለመዞር ተገደድን፤ ይሄኔም ነው የጓደኛዬ ፊት ልውጥውጥ ሲል ያስተዋልኩት፤ ጭንቅላቴን በማነቃነቅ በምልክት ምን እንደተፈጠረ ጠየኩት፤ ለአፍታ አመንትቶ ከፊት ለፊታችን በግምት አስር ሜትር ርቀት ላይ ወደቆሙ ሁለት ሰዎች ጠቆመኝ፤ ልብ ብዬ አየኋቸው፤ ሁለቱንም ከዚህ ቀደም አይቻቸው አላውቅም፤ ደግሞም በዙሪያችን ከሚርመሰመሱ ሰዎች የተለየ ምንም አይነት ሁኔታ ላስተውልባቸው አልቻልኩም፤ እናም ወደ ጓደኛዬ ዞሬ በግርታ ግንባሬን ቋጥሬ ጥያቄ በተሞላ ዓይን አተኮርኩበት፤ ጓደኛዬም ከሁኔታዬ እንዳልገባኝ ተረድቶ ከሹክሹክታም ዝቅ ባለ ድምፅ ‹‹ደህንነቶች ናቸው፣ እየተከታተሉህ ነው›› አለኝ፤ ቢሆኑስ ታዲያ!? በግዴለሽነት ትከሻዬን እየሰበቅሁ ‹‹ለራሳቸው ጉዳይ መጥተው ሊሆን ይችላል›› ብዬው ወደ ሌላ ሆቴል አቀናን፤ እዛም የተለቀቀ ክፍል አለመኖሩ ተነግሮን ፊታችንን ከእንግዳ መቀበያው ‹‹ዴስክ›› ዘወር ስናደርግ እነዛ ‹ደህንንቶች› ቆመው ተመለከትኳቸው፡፡ አሁን ከልምዴ በመነሳት ክትትል ሊሆን እንደሚችል ለማመን በተቃረበ ጥርጣሬ ተውጬ ሌላ ሆቴል ደርሰን ክፍል ጠየቅን፤ በለስ ቀናንና የሆቴሉን መስፈርት አሟልቼ ሳበቃ ጓደኛዬን ቡና ቤቱ ውስጥ እንዲጠብቀኝ አድርጌ፣ ክፍሉን ከተረከብኩ በኋላ ሻንጣዬን አስቀምጬ፣ ገላዬን ተለቃልቄ፣ ልብስ ቀይሬ ደረጃውን መውረድ እንደጀመርኩ ከሰዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠምኩ፡፡ የጭንቅላት ሰላምታ ሰጥቼ አለፍኳቸው፤ ምላሽ የለም፤ ፈገግ አልኩ፡፡ ከወዲሁ የሰሞኑ ምስራቅ ኢትዮጵያ አክራሞቴ ምን ሊመስል እንደሚችል አሰብኩና፣ በልጅነቴ ከሰፈር ማቲዎች ጋር የምንጫወተውን የአኩኩሉ ድብብቆሽ አስታውሼ፣ በድጋሚ ለራሴ ፈገግኩ፡፡
ገና ከአዲስ አበባ ስነሳ ማህበራዊ ጉዳዬን ስጨርስ የድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሶማሌ ክልልን ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ለማዳመጥ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት የሚያቆይ ፕሮግራም አስቀድሜ ይዤ ነበር፤ ከአራት ቀን ቆይታ በኋላም ቀጥታ ወደዚሁ ስራዬ ነበር የገባሁት፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት እንድሰጥ ያደረገኝ በቅርቡ ሐረር ከተማ ውስጥ በተከበረው ‹‹የዓለም የመቻቻል ቀን›› ላይ በክልሉ የተንሰራፋው መድልዎና የሐብሊ ተፅዕኖ ተደብቆ፣ ፍትሐዊ አስተዳደር የሰፈነ ለማስመሰል መሞከሩ፤ እንዲሁም ህዳር 29 ቀን በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ (ጅግጅጋ) የሚከበረውን ‹ስምንተኛው የብሔር ብሔረሰብ ቀን›ን አስመልክቶ አካባቢውን ከዋጠው ስጋት በተቃራኒው መንግስት እየነዛ ያለው የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ከተጨባጩ እውነታ ጋር ለመፈተሽ ፍላጎት አድሮብኝ ነው፡፡
ፊታችሁን ወደ ምስራቅ…
ምስራቅ ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ የ3ሺ ዓመት ታሪክ ዕኩሌታውን ሰላምና መረጋጋት የተሳነው ከመሆኑም በላይ፣ ለማዕከላዊ መንግስት የስጋት ምንጭ ሆኖ ነው ዛሬ ድረስ የቀጠለው፡፡ ከአቶማን ተርኪሽ ወታደሮች እስከ አል-ሸባብ ሰርጎ ገቦች ድረስ መተላለፊያ ‹‹ኮሪደር›› ሆኖ አገልግሏል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ሶማሊያውያን የዘር ግንድ ከጐረቤት ሀገራት ሶማሊያና ጅቡቲ ጋር የሚተሳሰር መሆኑና የሃይማኖትና የኢኮኖሚ ምንጭም ተመሳሳይነት አካባቢውን በበቂ ደረጃ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንዳደረገው የፖለቲካ ተንታኞች ያምናሉ፤ ነዋሪዎቹ በቀላሉ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው እየተዘዋወሩ የሚኖሩ መሆናቸውም ሌላው ችግር እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ ቅኝ ገዥዎቹ የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው አካባቢውን ‹ፍሬንች ሶማሌ ላንድ›፣ ‹ብሪታኒያ ሶማሌ ላንድ› እና ‹ኢታሊያ ሶማሌ ላንድ› በሚል ከፋፍለው ማስተዳደራቸው፣ ከሶማሊያ ነፃነትም በኋላ የሞቃዲሾን ቤተ-መንግስት የተቆጣጠሩ ገዢዎች ‹ታላቋን ሶማሊያ እንመሰርታለን› በሚል ቀቢፀ ተስፋ ከአንድም ሶስቴ የኢትዮጵያን ወሰን ተሻግረው የኃይል ወረራ መፈፀማቸው የአካባቢውን ውጥረት ይበልጥ አባብሶት ነበር፤ ከዚያም ባሻገር የዚያድባሬ ሶማሊያ መፈራረስም የቀጠናውን ሠላምና ፀጥታ ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታል፡፡
በዚህ ሁሉ ከባቢያዊ ውጥረት እየታመሰ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ በአንድነት በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ስር ሲተዳደር የቆየው የምስራቁ የሀገራችን ክፍል፣ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ ባነበረው ‹‹ፌደራሊዝም›› በሶስት ሊከፈል ችሏል፤ ‹‹የሶማሌ እና ሐረር ክልል›› እንዲሁም ‹‹የድሬዳዋ አስተዳደር›› በሚል፡፡ ይህ ሁኔታም ከዚህ ቀደም በውጭ ተፅዕኖ ይተራመስ የነበረውን ‹ጂኦ-ፖለቲክስ› ብሔር  ተኮር ለሆነ ተጨማሪ አዲስ ቁርቁስ አጋለጠው፡፡ በአናቱም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ኦጋዴን፣ ጎዴ፣ ደጋሀቡር፣ ቀለፎን የመሳሰሉ ከተሞች ክልሉን ‹እንገነጥላለን› የሚሉት የኦጋዴን ብሔራዊ ግንባር ታጣቂዎች መርመስመሻ መሆናቸው አካባቢውን የስጋት ቀጠና አድርጎታል፤ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ድሬዳዋ ላይ ያነጋገርኳቸውና በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአስተዳደሩ አባል የነበሩ አቶ ኡስማን (ለዚህ ፅሁፍ ስማቸው የተቀየረ) ‹‹የዚህ ሁሉ ተጠያቂ ለጣልቃ ገብነቱ ያልተመቹትን የአካባቢው ልሂቃን ‹ለወረራ የመጡ የዚያድባሬ መኮንኖች› እያለ አሸማቅቆ ከፖለቲካው ገፍቶ በማስወጣት ክልሉን ዛሬ ላለው ደካማ አስተዳደር የዳረገው ኢህአዴግ ነው›› ይላሉ፡፡ በግልባጩ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ካሳ ተክለብርሃን የተገፉት ሰዎች ኢትዮጵያዊ አለመሆናቸውን ለ‹‹ዘመን›› መፅሄት የገለፀው እንዲህ በማለት ነበር፡-
‹‹ሶማሊያ የፈራረሰበት ወቅት ስለነበር በጣም ትላልቅ የሶማሊያ ተፈናቃዮች የሰፈሩባቸው ካምፖች ነበሩ፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ አንዱ የስደተኞች ካምፕ የነበረባት አገር ነበረች፡፡ በተለይ አርትሼክ አካባቢና ሌሎች አካባቢዎችም ትልልቅ ካምፖች ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የመጡ የዚያኛው ሶማሊያ መኮንኖች፣ ሲቪል ሰራተኞች ኢንጂነሮችና ፓይለቶች ነበሩ፤ በአካል ያገኘናቸው የምናውቃቸው እነዚህ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ጋር የሚለያቸው ነገር ስላልነበረ በአብዛኛው በስደተኛነት ከመጡ በኋላ የአካባቢውን የፖለቲካ ስልጣኑንም ያደራጁት እነሱ ነበሩ፡፡ አንዱ ትዝ የሚለኝ ይሄ ነው፡፡ ይሄንን የኢህአዴግ ሰራዊትና ከላይ የሄደው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሊለየው አይችልም ብቻ ሳይሆን ያ የመጣውን እንዳለ የሚያቅፍ ሁኔታ ነው የነበረው በአካባቢው፡፡ ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ያ ኃይል ነው እንግዲህ አዲስ በተፈጠረው አጋጣሚ የታላቋ ሶማሊያን አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሶማሊያ ላይ ለመዝራት ትልቅ ጥረት ያደረገው››
ይህ ክርክር በራሱ ኢህአዴግ ‹‹ፊታችሁን ወደተረጋጋችው ምስራቅ ኢትዮጵያ (ሶማሊ ክልል) መልሱ›› ያለበት አውድ የተለመደው የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ እንጂ አካባቢው የጦርነት ወረዳን ያህል የሚያሰጋ መሆኑን ያመላክታል ፡፡ እናም ከአርቲስቶች እና ጋዜጠኞች እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፊት-አውራሪነት የተካሄደው የጉብኝት ፕሮግራም፣ መንግስት ምንም እንኳ የህዝቦችን አንድነት ‹የማጥበቅ ዕቅድ› የሚል የዳቦ ስም ቢሰጠውም፣ ‹ሶማሌ ክልል ፍፁም ሰላም ነው› የሚል የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ለመንዛት መሆኑን ለመረዳት በአካባቢው ያለውን የፀጥታ አጠባበቅ ብቻ መመልከቱ በቂ ይመስለኛል፡፡
የቦምባስ ዕገታ
ዘንድሮ ለስምንተኛ ጊዜ ‹‹ሕገ-መንግስታችን ለህዳሴያችን›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን›› በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ በመሆኑ በአካባቢው ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት ለመለካት ረቡዕ ህዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ወፍ ጭጭ ሳይል ነበር ድሬዳዋን ለቅቄ ወደ ሐረር ጉዞዬን የተያያዝኩት፡፡ ይህንን ሰዓት የመረጥኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አበባ ላይ እንኳ ጋብ እየለ የመጣውን የደህንነት ሰራተኞች ክትትል ድሬዳዋ ላይ በየደረስኩበት ሲያንዣብብብኝ፣ በማስተዋሌ፣ ምናልባት ከዕይታ ውጪ መንቀሳቀስ ብችል በሚል እሳቤ ነበር፡፡ መኪናው ከአንድ ቀን በፊት የተከራየሁትና ድሬ ውስጥ ያልተጠቀምኩበት በመሆኑ፣ በስጋት የሚንጠውን የደንገጎ አቀበትም ሆነ ጥንታዊቷን ሐረር ከተማ አቋርጠን እስክናልፍ አንዳች ችግር አላጋጠመንም፡፡ ይሁንና ከሐረር በግምት 80 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሶማሊያ ክልል የምትገኘው ቦምባስ ከተማ ደርሰን ጥቂት እንደተጓዝን፣ መኪናውን ዳር አስይዞ እንዲያቆም አንድ የትራፊክ ፖሊስ ለሹፌሩ የእጅ ምልክት አሳየው፤ ይሄኔም ነው ድሬ ላይ እንደ ተሰወርኩባቸው እርግጠኛ ሆኜ በልቤ ከሳቅኩባቸው ሁለቱ ሰላዮቼ ጋር ፊት ለፊት የተፋጠጥነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሜን ጠርተው አነጋገሩኝ፤ እኔም ከምንም ነገር በፊት መታወቂያቸውን እንዲያሳዩኝ ጠየቅኩ፤ ሳያቅማሙ አሳዩኝ፤ ወዲያውኑም የአፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ እንዳልሆነ የአነጋገር ዘዬው በግልፅ የሚያስታውቀው አንደኛው የደህንነት አባል፣ ከዚህ በላይ ጉዞውን መቀጠል እንደማልችልና በቀጥታ ወደ ድሬዳዋ መመለሱ እንደሚጠቅመኝ ሊነግረኝ ሞከረ፡፡ ከመገረሜ ብዛት ንግግሩን ለመረዳት ጥቂት ሰከንዶች ፈጅተውብኝ ነበር፡፡ መቼም ይህ ሰው ቀልደኛ መሆን አለበት! አለዛ በገዛ ሀገሬ የት ድረስ መሄድ ወይንም የት ቦታ ጉዞዬን መግታት እንዳለብኝ ሊወስንልኝ ባልደፈረ ነበር፤ ሆኖም ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ምን ማለት እንደፈለገ እንዲያስረዳኝ በትህትና ጠየኩት… ይኼኔ ጓደኛው ጣልቃ ገባና ወደ ጅግጅጋ ለመሄድ ማሰቤን እንደደረሱበትና ወደ ከተማው እንድገባ እንደማይፈቅዱልኝ ቆጣና ኮስተር ብሎ አሳወቀኝ፡፡ እኔም ፈርጠም ብዬ እዚህ ድረስ መጥቼ ጅጅጋ ሳልደርስ እንደማልመለስ ቁርጡን ነገርኳቸው፡፡ ቃለ-ምልልሱ እየከረረ ሲሄድ ማስፈራራቱን ወደ ሹፌሩ አዞሩትና በብርቱ ያዋክቡት ያዙ፤ ይህ ድርጊታቸው ያልጠበቅኩት በመሆኑና የሹፌሩንም ምላሽ አለማወቄ መጠነኛ ድንጋጤ አጫረብኝ፡፡ እንደገመትኩትም ሁኔታውን በፍርሃት ተውጦ ይከታተል የነበረው ሹፌር ትንሽ እንኳ ሳያንገራግር መኪናውን ቆስቁሶ ወደ ሐረር አዞረው፡፡
‹‹ምን ሆነሃል?›› አልኩት በንዴት ጮኽ ብዬ፡፡
‹‹ወንድሜ እኔ ቤተሰብ የማስተዳድር ሰው ነኝ፡፡››

 

(ተመስገን ደሳለኝ)

ደግሞ ካሁኑ ዱለታው 2007 ምርጫ


አዎን አውቃለሁ፣ የምን ምርጫ ነው ትሉ ይሆናል፡ ይህም የኔም ጥያቄ ነው የእናንተ ብቻ ሳይሆን። የህውሃት/ወያኔ አገዛዝ እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ዳግም ትክክለኛ የሆነ ምርጫ
normal_904604ሊደረግ እንደማይችልና እንደማይኖር ብዙዎች የተነበዩት ነው። የሕዝብን ድምፅ አክብሮ በተሸናፊነት አምኖ ወያኔ ሥልጣኑን የመልቀቁ ጉዳይ ያከተመለት ይመስላል።
ህውሃት/ወያኔ አሁንም ስለምርጫው በሰፊው በማውራት ላይ ይገኛል፡ ሕዝብን በእህልና በምግብ አቅርቦት፡ በሥራ እድልና በመሳሰሉት እንደ ቀብድ በማስያዝ፡ በፓርቲው ስር ካልታቀፉ በሐገሪቱ ውስጥ ሊያገኟቸውና ሊጠቀሙባቸው የሚገባቸውን ሰብዓዊ መብቶች በመግፈፍ በውዴታ ሳይሆን በግዴታ የፓርቲውን የአባልነት ፎርም በማስሞላት ላይ ይገኛል። በቀደመው ምርጫ ድምጻቸውን ለተቃዋሚዎች የሰጡትን ግለሰቦች ከስራቸው እንዲባረሩ ወይም ሐገር ለቀው እንዲወጡ ለመጪውም ምርጫ እንቅፋት የማይሆኑበትን መንገድ በመቀየስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡
ለማንኛውም ባለፈው የክልል ምርጫዎች እንደተደረገው አሁንም ምርጫው የሚካሄደው ወያኔ ከራሱ ከወያኔ ጋር ይሆናል እንጂ በዚህ ሁካታና የመብት መጣስ በሰፊው በተንሰራፋበት ሁኔታ ጠንካራ ተቃዋሚ ገብቶ ሥነሥርዓት ባለው ሁኔታ ምርጫ ይካሄዳል ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ለዚህም ነው 2002 ምርጫ ሲሉን የምን ምርጫ የሚለው ጥያቄ ሲያስተጋባ የምንሰማው።
እውነት ግን የምን ምርጫ ከአሁን በኋላ?

ኢትዮጵያ ”ብሔር ብሄረሰብ” እያለች እንድትዘምር ሲፈረድባት ጎረቤቶቿ ግን በብሄር ስም የፖለቲካ ድርጅት መመስረትን በሕግ ከልክለው በአንድ ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ላይ ደረሱ


ኢትዮጵያ ያረጀ ያፈጀውን የማርክሲስት አስተሳሰብ ”ብሔር ብሄረሰብ” ርዕዮት እንድትዘምር ተፈርዶበታል።ህዳር 29 ቀን ጅጅጋ ላይ የቀለጠ ድግስ ተዘጋጅቷል።የእዚህ አይነት ዝግጅት commoncurrበኢትዮጵያ ወጣቶች መካከል ለምሳሌ በትምህርት ቤቶች መካከል የሚደረግ ከፖለቲካዊ ይዘት የራቀ ግን ወጣቶች የሚቀራረቡበት መልክ ቢኖረው ብዙ ፍሬ ባፈራ ነበር።የኢህአዲግ ዝግጅት ግን ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርጋቸው እልፍ ነገሮችን ማውሳት ትቶ የሚለያዩበት ነገር እየተነቀሰ የሚነገርበት መርሃ ግበር መሆኑ ነው አሳዛኙ ነገር።
ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ይሁን እንጂ ጎረቤቶቻችን ግን በሀገራቸው በብሄር ስም የፖለቲካ ድርጅት መመስረትን በሕግ ከልክለው በአንድ ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ላይ ደረሱ ።ቅዳሜ ህዳር 21/2006 ዓም የኬንያ፣ዩጋንዳ፣ታንዛንያ፣ቡሩንዲ እና ሩዋንዳ መሪዎች በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ተገናኝተው በአስር ዓመት ውስጥ የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራቸው የፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ማለት ኢትዮጵያን የሚቀናቀን ትልቅ ገበያ እንደሚፈጥሩ ይታመናል።ኢትዮጵያ በእዚህ ጊዜ ቢያንስ በታዛቢነት አለዝያም ከደቡብ ሱዳን፣ጅቡቲ፣ሱማልያ ወዘተ ጋር የጋራ ገበያ የምትፈጥርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባት ነበር።ከእዚህ ይልቅ ”ምኑ ቀርቶብኝ በወጉ በኮነነኝ” እንደሚባለው የጎረቤት የጋራ ገበያ ቀርቶ ጠንካራ ሃገራዊ አንድነት እንዳትፈጥር በብሄር እንድታስብ ተፈርዶባታል።ህዳር 29 በቴሌቭዥን እያዘፈነች እበላ ባይ አፈጮሌ ካድሬዎቿ ስሽሞነሞኑ ማየት የሰሞኑ አሳዛኝ ድርጊት ነው። ጉዳያችን

 | 

mandag 2. desember 2013

ESAT Human Rights Ethiopian Prisoners in Yeman Sena Nov 30 2013


ESAT Daily News Amsterdam Dec 02 2013 Ethiopia


ሰበር ዜና፣ ግንቦት 7 ወያኔ ላቀረበው “እንደራደር” ጥያቄ መልስ ሰጠ

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ

ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።

ኢህአዴግ/ህወሃት ከግንቦት 7 ጋር ለመደራደር ጥያቄ አቀረበ


እንደ ኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን) ዘገባ ከሆነ “ኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ከግንቦት ሰባት ለፍትህና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ጋር ለመደራደር ጥያቄ አቀረቧል።
የኢሳት ዜና አገልግሎት በአጭር ሰበር ዜና ዘገባው እንዳለው ማምሻውን የግንቦት ሰባትን አመራሮች መልስ ይዞ ብቅ ይላል።
ይህ በዚህ እንዳለ የኢሳትን ሰበር ዜናን ተከትሎ በማህበራዊ መገናኛ መረቦች ኢትዮጵያውያን አስተያየቶችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ…
Ginbot 7 logo

søndag 1. desember 2013

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢ/ር ይልቃል በጀርመን- በስዊዘርላንድ – በሆላንድ – በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ያደርጋሉ

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢ/ር ይልቃል በጀርመን- በስዊዘርላንድ – በሆላንድ – በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ያደርጋሉ
blue-party-ethiopiaየሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል። ትላንት ኖቨምበር 29 ጀርመን ፍራንክፈርት የገቡት ኢ/ር ይልቃል በመጪዎቹ ቀናት በአውሮፓ ከተሞች ተከታታይ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስተባባሪ ኮሚቴው በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ አስታውቋል።
ለጊዜው በደረሰን የስራ ሰሌዳ መሰረት :-
– ቅዳሜ ኖቬምበር 30 በጀርመን ኑረንበርግ ከኢትዮጵያኖች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
– ሰኞ ዲሴምበር 2 በፍራንክፈርት የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።
– ዲሴምበር 5 ጄኔቭ ስዊዘርላንድ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ይሳተፋሉ።
– ቅዳሜ ዲሴምበር 7 በሆላንድ ህዝባዊ ውይይት ያደርጋሉ።
ከአውሮፓ ቆይታቸው በኋላ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ በመጓዝ በዲሴምበር 30 አርሊንግተን በተዘጋጀው ስብሰባ ከፕ/ር አል ማርያም ጋር ንግግር ያደርጋ

Saudi Arabia: Labor Crackdown Violence (Human Rights Watch)


November 30, 2013
Ethiopian Workers Allege Attacks, Poor Detention Conditions
(Beirut) –  Ethiopian migrant workers have been the victims of physical assaults, some of them fatal, inSaudi Arabia following a government crackdown on foreign workers. Many workers seeking to return home are being held in makeshift detention centers without adequate food or shelter.
Human Rights Watch spoke to five Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia. Four Ethiopians in Riyadh told Human Rights Watch that the attacks began after November 4, 2013, when authorities resumed a campaign to arrest foreign workers who they claim are violating labor laws. Security forces have arrested or deported tens of thousands of workers. Saudi officials and state-controlled media have said that migrant workers have also been responsible for violence, including attacks on Saudi citizens, in the wake of the crackdown.