mandag 1. juli 2013

“(ከኢትዮጵያ ጋር) በፕሬዚዳንት ደረጃ ግንኙነታችንን ማጉላት አንፈልግም”

“(ከኢትዮጵያ ጋር) በፕሬዚዳንት ደረጃ ግንኙነታችንን ማጉላት አንፈልግም”
ከመካከለኛው አፍሪካ የአሜሪካንን ቀልብ የሚስብ አገር የለም። የደቡብ አፍሪካ መመረጥ ካላት ኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ሚናዋ አንጻር ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ያሉት ዴቪድ ሺን ከምስራቅ አፍሪካ አስር አገሮች መካከል አራቱን በመምረጥ የግል አስተያየታቸውን አቅርበዋል። ሴኔጋል የተመረጠችው ፈረንሳይኛ ተናጋሪና የምዕራብ አፍሪካ አገር በመሆኗ ነው።
የቪኦኤው ሰለሞን አባተ ያነጋገራቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ የቀድሞ አምባሳደር ዴቪድ ሺን ስለ ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት ሲናገሩ ኬኒያን አንስተው ነበር። የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አባት ኬንያዊ ቢሆኑም ኦባማ ኬንያን የጉብኝታቸው አካል ያላደረጉት አዲሱ ፕሬዚዳንትና ምክትላቸው በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ችሎት የሚፈለጉ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቀዋል። በወንጀል የሚፈለጉ መሪዎች ባሉበት አገር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጉብኝት አያደርግም በማለት ተናግረዋል።
o in africaዩጋንዳ ፣ ኢትዮጵያና ታንዛንያን ለንጽጽር ያቀረቡት ዶ/ር ሺን ሶስቱም አገሮች አሜሪካ የምታስቀምጠውን መለኪያ አያሟሉም። በታንዛኒያ ግን የፕሬዚዳንቱ የስልጣን ጊዜ ባግባቡ ተገድቦ ተቀምጧል። የአመራር ለውጥ ያካሂዳሉ። ጎልቶ የሚወጣ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት አያያዝ ጉድለት አይታይም ብለዋል። በዚህም የተነሳ ታንዛኒያ የተሻለች አገር ተብላ መመረጧን አመልክተዋል።
ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት በዓል ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ አዲስ አበባ መሄዳቸውንና ከመንግስት ክፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ያወሱት ሺን፣ ኢትዮጵያ በኦባማ ጉብኝት እቅድ ውስጥ አለመሆኗ የማግለል ጉዳይ እንዳልሆነ አመልክተዋል። አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የመያዝ ፍላጎት  እንዳላት የጠቆሙት ሺን “ይህን ግንኙነት በፕሬዚዳንት ግንኙነት ደረጃ ማጉላት አንፈልግም” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቻይና ፕሬዚዳንት በቅርቡ ሶስት የአፍሪካ አገሮችን ሲጎበኙ ኢትዮጵያን አለመጎብኘታቸውን አንስተዋል። በምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤና ጥናት ማካሄዳቸው የሚታወቀው ሺን “አሜሪካ ግንኙነቱን በፕሬዚዳንት ደረጃ ማጉላት አትፈልግም” ያሉበትን ምክንያት አላብራሩም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar