mandag 1. juli 2013

“ለቤተሰቦቼ እቃ ለመላክ ስጠይቅ ሃላፊነት አንወስድም ተባልኩ” የፖስታ አገልግሎት ፖስታ ይጥላል፣ ያበላሻል፣ ያልተባለው ቦታ ይልካል

“ለቤተሰቦቼ እቃ ለመላክ ስጠይቅ ሃላፊነት አንወስድም ተባልኩ”
የፖስታ አገልግሎት ፖስታ ይጥላል፣ ያበላሻል፣ ያልተባለው ቦታ ይልካል
“ለወንድሜ ሞባይል ለመላክ ፖስታ ቤት ስጠይቅ የምልክበትን አገር ጠየቁኝ። ኢትዮጵያ እንደሆነ ነገርኳቸው። ኢትዮጵያ ከሆነ ለሚላከው ዕቃ ሃላፊነት አንወስድም አሉኝ” ስትል ለጎልጉል ግራ መጋባቷል በመግለጽ አውሮፓ እንደምትኖር የገለጸች ኢትዮጵያዊ ይህንን ጥያቄ የሰነዘረቸው ከወር በፊት ነበር።
በተመሳሳይ ፖስታ የሚጠቀሙ ወገኖች ችግር እንደሚገጥማቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። የላኩት ጥቅል postየጠፋባቸውና የተበላሸባቸው ያማርራሉ። ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓም ፋና ይፋ ያደረገው ዜና ይህንኑ ችግር ወለል አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት የደብዳቤና የጥቅል መልእክት አገልግሎት ደህንነትን በመጠበቅ በኩል ክፍተቶች እንዳሉበት የገለጸው ፋና ዜናውን ያገኘው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሳይንስና ቴክኖሎጂ  ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትን የአስራ አንድ ወራት እቅድ አፈፃፀምን በገመገመበት ወቅት እንደሆነ አመልክቷል።
ቋሚ ኮሚቴው እንዳለው ከሆነ በድርጅቱ የሚበላሹ፣ የሚጠፉና በተሳሳተ አድራሻ የሚላኩ መልእክቶች እየበዙ መጥተዋል፣ በዚህም ምክንያት የተገልጋዮች ቅሬታም እየጨመረ ነው። ችግሩን ያደመጠው ቋሚ ኮሚቴው ይህ እንዲስተካከልና በቀጣይ በዘርፉ የሚታየው ተገቢ ያልሆነ አሰራር እንዲሻሻልና አገልገሎቱ የደንበኞችን ፍላጎትን በሚያረካ መልኩ እንዲሰጥ ማሳሰቡን ፋና አስታውቋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar