fredag 26. juli 2013

Tourism and the abuse of Hamer women in Ethiopia

Tourism and the abuse of Hamer women in Ethiopia


The Vancouver Sun
by Daphne Bramham, Vancouver Sun columnist
Women from Ethiopia’s South Omo Valley
Women from Ethiopia’s South Omo Valley are seen here dancing. They are also severely beaten as part of a coming of age ceremony that can be witnessed and photographed by wealthy tourists.
Photograph by: Andrew Renton, Vancouver Sun
Bored with the usual round of museums, art galleries, cathedrals, temples or world heritage sites and with appetites whetted by documentaries, rich travellers are looking for authenticity.
Their desires have spawned a number of discrete and sometimes disturbing niche markets.
There are the adventurers. Images of tourists lined up to summit Everest, for example, are now almost as familiar as the images of their discarded oxygen bottles strewn at the Nepalese mountain’s base.
There’s poverty tourism (a.k.a. poor-ism or slum tourism) where seeing the living conditions of the desperately poor can be as life changing for the viewer as it is exploitative of the viewed.
There’s volun-tourism, where you pay to work for non-profit organizations such as Habitat for Humanity.
In Lac-Mégantic, Que., grieving people have come face-to-face with disaster tourists snapping photos of what and who has been left behind after the tragic and devastating train derailment and explosion.
And there’s the kind I discovered reading the weekend travel section of The Sun that’s perhaps best described as citizen-anthropologist trips. They’re cloaked as adventure tourism and wrapped in a self-congratulatory tolerance for other people’s traditions and customs.
In this case, it was the ritualized abuse of Hamer women in Ethiopia’s South Omo Valley.
Vancouver-based travel writer Andrew Renton described a three-day ceremony marking a young man’s coming of age that culminates with girls and women getting beaten and lashed so badly with sticks that they all bear the scars.
He recounts buying medication for one girl whose wounds had turned septic, “but she is still not happy” because the next day she was to be beaten again as part of her brother’s initiation ceremony.
The account is chilling.
“I find my girl and turn her around. Her eyes are glazed. Her back is running with blood. I’m told she took all the medication in preparation for today’s event.”
The italics are mine; the paternalistic possessive pronoun is Renton’s even though he viewed and recounted the beating of girls and women — black, African girls and women — with detachment.
His account and others describe the women and girls as being either drunk, drugged or in a trance during the beatings, which often go on for more than an hour.
No photos of the beatings of the scarred and bloodied backs of the girls and women were published in the paper. That would, no doubt, ruin the happy tourism buzz.
And, make no mistake, the writer wasn’t a lone, plucky adventurer who serendipitously happened upon this ritual during his nine days of playing citizen-anthropologist.
One photo shows nine other white, camera-toting tourists in the half-circle around the ceremony.
Think about it. What they witnessed would be criminal assault in Canada and most countries and probably even Ethiopia.
The story ended with this jaunty, verbal wave: “Whether you agree with the customs or not, the people and their traditions are real.”
This glib cultural relativism begs fundamental questions.
Is it morally right to do nothing when another person or even an animal is being beaten so badly that they’re left bleeding and scarred?
Are rural Ethiopian women and girls (or any others in the developing world) not entitled to the same rights and protections as Canadians?
The coming-of-age ritual may well be an ancient one. But it’s one of the many reasons that Ethiopia is one of the worst countries to be a girl or a woman, ranking 173 out of 187 countries when it comes to gender inequality.
Another old custom/tradition in Ethiopian herding societies is the most extreme form of female genital mutilation, which entails the removal of all external genitalia.
The United Nations unanimously passed a resolution last December calling for a global ban on the practice, which UNICEF says is rampant in Ethiopia’s rural areas even though it has been outlawed.
So far, there are no reports of this ritual being carried out in front of tourists.
But in a country so desperately poor, who’s to say what people may be willing to do for money?
For the writer’s brief look at real life in the South Omo Valley, he paid nearly 10 times what the average Ethiopian earns in a year. His $3,300 “covered absolutely everything for nine days except alcohol.”
It’s a fair bet that very little of what the gawking travel writer and other tourists paid to witness the abuse will trickle down to girls like the poor, wretched one described in the article.
Yet, for the Ethiopian herders living at the desperate margins even a pittance can make a difference.
The troubling question is what kind of difference?
If rich Westerners pay high prices and set aside their own cultural values to watch ritualized abuse, it’s possible that rather than being impartial observers their very presence exacerbates and may even perpetuate it

søndag 7. juli 2013

Zone9 እሁድ ጠዋትን በዝዋይ ማረሚያ ቤት — በቀለ ገርባን አገኘነው።

Zone9
እሁድ ጠዋትን በዝዋይ ማረሚያ ቤት — በቀለ ገርባን አገኘነው።

የዞን ዘጠኝ አባላትና ወዳጆቻችን ደርዘን ሆነን ዛሬ (ሰኔ 30/2013) ወደዝዋይ የተዛወሩ እስረኞችን ለመጠየቅ ሄድን።

በመጀመሪያ ያገኘነው በቀለ ገርባን ነበር። መልከ መልካሙ በቀለ አውርተው የሚጠግቡት ዓይነት ሰው እንደሆነ ለማወቅ ሄዶ ማየት ያስፈልጋል። ከእሱጋ ስናወራ ከሌሎችጋ ለመገናኘት ያቀድንበት ሰዓት እስከሚጣበብ ድረስ ዘግይተናል።

በቀለ ገርባ ስለሰላማዊ ትግል አብዝቶ ያወራል። ከ32 እስረኞችጋ አንድ ቦታ እንደታሰረ እና በተንጣለለው የዝዋይ ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ በተለይ እነሱ በአንዲት ውሱን፣ በተለምዶ ጨለማ ቤት የሚባለው ክፍል ውስጥ እንዳለ አጫውቶናል። (እዚህ ቦታ በግንቦት ሰባትነት ክስ የተፈረደባቸው ጄነራሎችና በነአንዱአለም አራጌ መዝገብ የተከሰሱት እዚሁ ይኖራሉ) ሆኖም ከቃሊቲ አንፃር ሲታይ ዝዋይ በጣም የተሻለ ምቹ እና ሠላማዊ እንደሆነ፤ ሌላው ቀርቶ ለሕክምና አዲስ አበባ መዛወር ኖሮበት ይቅርብኝ እንዳለ ጨምሮ ነግሮኛል።

በቀለ አሁን ከእስር ለመፈታት አመክሮው ተቀንሶ 2 ዓመት ከአራት ወር ከዘጠኝ ቀን ነውም ብሎናል። በእስሩ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም ድጋፍ እያደረገለት በመሆኑ እንደሚበረታና አሁንም ወደፊትም ብቸኛው የለውጥ መንገድ ሠላማዊ ትግል መሆኑን ለሕዝብ በምታስተላልፉት መልዕክት ላይ አስፍሩልኝ ብሎናል። በፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ቅጣት ማቅለያ ንግግሩን አስመልክቶ ስንጠይቀው ለማለት ብቻ ሳይሆን የማምንበት የሕይወት ፍልስፍናዬ ነው ሲል ነግሮኛል።

ከዚያ በኋላ ጋዜጠኛ ውብሸት፣ ናትናኤል፣ ዘሪሁንን እና አበበ ቀስቶን አግኝተን አነጋግረናቸው በጥንካሬያቸው ተበራትተናል።

onsdag 3. juli 2013

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ እንደማይወርዱ አስታወቁ፤ በግጭት ሕይወት ጠፋ

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ እንደማይወርዱ አስታወቁ፤ በግጭት ሕይወት ጠፋ

ፕሬዚዳንቱ ፍንክች እንደማይሉ አቋማቸውን ዛሬ – ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ምሽት ላይ ባደረጉትና በሃገሪቱ ብሔራዊ ራዲዮና በቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ንግግር ያስታወቁት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎቻቸው አደባባይ ወጥተው እንዲወርዱ እየጠየቋቸው ባሉበት ወቅት ነው፡፡
የዛሬ ዓመት አካባቢ በሃገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ ነፃ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሞርሲ ሕገመንግሥታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በመወጣት እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ ጦር እጁን ከፖለቲካው ቀውስ ውስጥ እንዲያወጣም አሣስበዋል ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፡፡
የግብፅን ባንዲራ የሚያውለበልቡ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል – ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
በሚስተር ሞርሲ እና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ያለው ልዩነት እስከነገ፤ ረቡዕ ባለው ጊዜ ካልተፈታ ለግብፅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይበጃል የሚሉትን የራሣቸውን የጎዳና ትልም እንደሚደነግጉ የጦር ኃይሎቹ መሪዎች ማስጠንቀቃቸውና ቀነ-ገደብ መቁረጣቸው ይታወሣል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን እያሰሙ በነበሩበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ተቃዋሚና ደጋፊዎቻቸው የሆኑ ሰልፈኞች የካይሮን አደባባዮችና ጎዳናዎች አጨናንቀዋል፡፡
ከመሪያቸው ጎን ቆመው እነርሱ “ማንኛውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት” ያሉትን የጦሩን እርምጃ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ እየዛቱ ያሉት የሞርሲ ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ናስር ቀበሌ የተሰባሰቡ ሲሆን ሞርሲ ሥልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚለውን ጥያቄአቸውን የሚያሰሙት ተቃዋሚዎች ደግሞ ማዕከላዊውን የካይሮ ጣሕሪር አደባባይ ሞልተውታል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሣ ግጭት ካይሮ ውስጥ ዛሬ (ማክሰኞ) የሰባት ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሕክምና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ወታደሮች ካይሮ ቤተመንግሥት አጥር ግቢ ላይ፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም ወታደሮቹ “ሕገመንግሥቱን ለማቋረጥ፣ ሕግ አውጭውን አካል ለመበተንና የሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም እየተዘጋጁ ነው” የሚል ሾልኮ የወጣና ለመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ሽው ያለ ጭምጭምታ ጠቁሟል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ አባላት “የተመረጠን ፕሬዚዳንት ለመገልበጥ የሚደረግን ሙከራ ለማቆም” ከታንኮች ፊት ቆመው መስዋዕት እንደሚከፍሉ እየዛቱ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ሞርሲ ተቃዋሚዎቹን ሰልፈኞች እያዳመጡ መሆናቸውን እንዲያሣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማክሰኞ ጠዋት ስልክ ደውለው ጠይቀው ተቃዋሚዎችም የግብፅን ዴሞክራሲያዊ ሂደት መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል፡፡
አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ለግብፃዊያኑ ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ በተካሄዱ ሰልፎችና በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ከሃያ በላይ ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል፡፡

tirsdag 2. juli 2013

አቶ ታምራት በንግድ ተሰማሩ፤ ቢተው ስልጣን ያዙ

አቶ ታምራት በንግድ ተሰማሩ፤ ቢተው ስልጣን ያዙ


ከኢየሩሳሌም አርአያ
በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ወገኖች፣ ታምራት ያንን ቢናገሩም በቃላቸው ግን እንዳልተገኙ አስረድተዋል። « የኢየሱስ አገልጋይ ሆኜ እኖራለሁ» ያሉት ታምራት አሁን ወደ ንግድ አለም መግባታቸው እንዳስገረማቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ሌላው ቢቀር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ለሰሩት ጥፋት ህዝብን ይቅርታ ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፣ በይፋ አደባባይ ወጥተው ህዝብን ይቅርታ የጠየቁት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ገብሩ ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል። አቶ ታምራትና አቶ ስዬ ግን ይህን ለማድረግ ጨርሶ እንደማይፈልጉ ከያዙት አቋም በቀላሉ መረዳት ይቻላል ብለዋል።Former Prime Minister Tamrat Layne
በሌላም በኩል የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል የነበሩትና ደቡብን በበላይነት ሲያሽከረክሩ ቆይተው በ1993ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተከሰው የታሰሩት አቶ ቢተው በላይ ለስድስት አመት ታስረው ከተፈቱ በኋላ በአቶ መለስ ዜናዊ የአፋር ክልል አማካሪ ተደርገው ተሹመው እንደነበረ ምንጮች አጋለጡ። ከአቶ አባተ ኪሾ ጋር ተከሰው የነበሩትና ከሕወሐት ተገንጥሎ ከወጣው <አንጃ> ቡድን አንዱ የነበሩት አቶ ቢተው ተመልሰው የመለስ አገልጋይ መሆናቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአፋር ክልል አማካሪ ሆነው ለሶስት አመት የሰሩት ቢተው በአሁኑ ወቅት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሎጅ ተዛውረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። የአቶ ቢተው ወንድም ኮ/ል ሲሳይ (በቅፅል ስሙ ሃመዴ) ጀግና ኢትዮጲያዊና አገሩን የሚወድ ታታሪ እንደነበርና በአሰብ ውጊያ ከነሂሊኮፕተሩ ጋይቶ ማለፉን ምንጮቹ አመልክተዋል። አንድም ቀን ስሙ በነመለስ ተነስቶ የማያውቀውና የጡረታ መብቱ እንኳ ሊከበርለት ያለቻለው ሟቹ ኮ/ል ሃመዴ ልጆቹ ያለአሳዳጊ ተበትነው መቅረታቸውን ምንጮቹ ሳይገልፁ አላለፉም።

mandag 1. juli 2013

የአስካሉካን ትሬዲንግ ባለቤት 6 አመት ከ6 ወር እስራት ተፈረደባቸው

የአስካሉካን ትሬዲንግ ባለቤት 6 አመት ከ6 ወር እስራት ተፈረደባቸው 

በደቡብ አፍሪካ ተካሂዶ በነበረው የ2010 የአለም ዋንጫ ወደ ደቡብ አፍሪካ መግባት የሚያስችል የ10ሺህ ሰዎችን ቪዛ ልሰጣችሁ እችላለሁ በሚል 1200 ከሚደርሱ ዜጉች ከ25-37ሺህ ብር በነፍስ ወከፍ በመቀበል አጭበርብረዋል ባላቸው የአስካሉካን ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ግርማዬ ገ/ሚካኤል ላይ ፍርድ ቤት የ6 አመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና የ8ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ባለፈው ማክሰኞ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

አቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ ካቀረባቸው ስምንት ክሶች መካከል ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ያላቸው በሰባት ክሶች ሲሆን ከህዳር 7 እስከ ግንቦት 2002 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ግለሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ከ25ሺህ እስከ 37ሺህ ብር ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ዜጐች እንዲጉላሉ በማድረግ እና የንግድ ፍቃዳቸው የአስመጪነትና ላኪነት ሆኖ ሳለ ባልተፈቀደላቸው የስራ መስክ ተሰማርተው ወንጀል በመፈፀም ከሀገር ለመኮብለል ሞክረዋል ሲል ክሱን አጠናክሮ አቅርቧል፡፡

አቃቤ ህግ ግለሰቡ የፈፀሙት ከባድ የማታለል ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ 11 የሰው ምስክሮችንና 20 የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት በማቅረብ አስረድቷል፡፡ ተከሳሹ አቶ ግርማይ በበኩላቸው፤ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲሉ ክደው የተከራከሩ ሲሆን በወቅቱ የደቡብ አፍሪካ ቪዛ እሰጣለሁ ያልኩት በእጄ የተገኘን መረጃ ምክንያት አድርጌ ነው ካሉ በኋላ ይህም ሆኖ ለተበዳዮቹ ሃብትና ንብረቴን ሸጬ የሚገባቸውን ካሳ ከፍያለሁ ከማለታቸውም በተጨማሪ ሰባት የመከላከያ ምስክሮችንና ሰነዶችን አቅርበው ተከራክረዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ሲያዳምጥ የቆየው ችሎቱ፤ ጉዳዩን መርምሮ ተከሳሹን ጥፋተኛ ናቸው ያለ ሲሆን እንደ ቅጣት ማቅለያ አቅርበውት የነበረውን ለተበዳዮች ካሳ ከፍያለሁ የሚለውን የመከራከሪያ ሃሳብ እሳቸው ፈቅደውና ተፀፅተው ሳይሆን የፍትሐብሄር ክስ ተመስርቶባቸው በመረታታቸው የፈፀሙት በመሆኑ እንደቅጣት ማቅለያነት አልቀበለውም ብሏል፡፡ተ ከሳሹም በሰባት ክሶች ጥፋተኛ ተብለው በድምሩ ስድስት አመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እና በስምንት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ሲል ወስኗል፡፡
አልሸባብ በሶማሊያ ተሽመደመደ፤ ሼኽ ዳሒር ሃዌስ ተይዘዋል፤
አሸባሪነትን በመዋጋት ሲሞዳሞዱ የቆዩት ኢትዮጵያና አሜሪካ ወዴት ያመሩ ይሆን?
SOMALIA MILITIA
የአልሸባብ መሪዎች በራሳቸው ተዋጊዎች መገደላቸው ተሰማ። ከተገደሉት መካከል አንደኛው ያሉበትን ለጠቆመና ላጋለጠ አምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ የታወጀባቸው ነበር። የቪኦኤ የአማርኛው ክፍል በዘገበው ዜና መሰረት አልሸባብ በሶማሊያ እየተንኮታኮተ የመክሰም ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች ይመስላል።
አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ አባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር  ሲያውል፣ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ያሉ ነበሩ ብሏል። “ሁለቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ አሻፈረን ብለው አንገራገሩ፣ በተኩስ መካከል ተገደሉ፤ አምላክ ነፍሳቸውን ይማርና በገነት ያስቀምጥ፡፡ ሃሣቡ እነርሱን ለመግደል አልነበረም፡፡ በቁጥጥር ሥር አውለን እሥልምና ችሎት ፊት ልናቀርባቸው ነበር” ሲል እስልምና ችሎት ፊት ሳይቀርቡ በተኩስ ልውውጡ ወቅት መገደላቸው እንዳሳዘነው መግለጹን የቪኦኤ ዜና ያስረዳል።
ሰዎቹ የተገደሉት ከሞቃዲሾ 350 ኪ.ሜ በስተደቡብ በምትገኝ ብራቫ የምትባል ከተማ ውስጥ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የተገደሉት ሰዎች እነማን እንደሆኑ የአል-ሻባብ ቃል አቀባይ አልተናገረም፡፡ ይሁን እንጁ የቪኦኤ ሶማሊኛ አገልግሎት የተለያዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን አነጋግሮ በተለያዩ ስም የሚጠሩት የአልሸባብ አመራር መሞታቸውን አመልክቷል። በዚሁ መሰረት ኢብራሂም ሃጂ ጃማ ፣ ኢብራሂም አል-አፍጋን ፣ በተቀጥያ መጠሪያው አቡ ባካር አል-ዛይሊዪ እና ሼኽ አብዲሃሚድ ሃሺ ኦልሃዬ ወይም በቅፅል ስም ሞዐሊም ቡርሃን የተገደሉ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
መሪዎቹ የተገደሉት የዛሬ አሥር ቀን ሰኔ 12 መሆኑንም የቪኦኤ ምንጮችን የጠቀሰው የሶማሊኛ አገልግሎት ዘገባ አመልክቷል፡፡የአል-ሻባብ ምንጮች እንደሚሉት አል-አፍጋን የተገደለው ከመስጂስ እየወጣ ሳለ በተተኮሰበት ተከታታይ ጥይት ሲሆን ሙዐሊም ቡርሃን የተገደለው ከቤቱ ተይዞ ከተወሰደ በኋላ ነው፡፡
ይህ አጋጣሚ ከተፈጠረ ከሁለት ቀናት በኋላ ለተገደሉት ሁለት ሰዎች የቅርብ ወዳጅ እንደነበረ የሚነገረው ዋነኛው የአል-ሻባብ መሪ ሼኽ ሐሰን ዳሂር አዌይስ ከአካባቢው በጀልባ በማምለጥ ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ተይዞ እጁ ለመንግሥት አስረክቧል። ከተገደሉት አንዱ ኢብራሂም አል-አፍጋን በአል-ሻባብ ውስጥ በርካታ የሥልጣን ቦታዎች የነበሩት ሲሆን የቡድኑ ምክትል መሪ፣ የገንዘብ መምሪያው ኃላፊና የኪስማዮ ገዥ ሆኖ ሠርቷል፡፡ ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ያሉበትን መረጃ ለሚሰጥ በእያንዳንዳቸው ራስ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ ማስታወቂያ ካወጣችባቸው ሰባት የአል-ሻባብ መሪዎች አል-አፍጋን አንዱ ነው፡፡
አል-አፍጋን ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቨርጂንያ ውስጥ ይኖር የነበረ ሲሆን እአአ በ1980ዎቹ ውስጥ ከሙጃሕዲን ጎን ተሰልፎ ለመዋጋት ወደ አፍጋኒስታን መሄዱንና በ1991 ዓ.ም የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ሲወድቅና ሥርዓተ-መንግሥቱ ሲፈራርስ እጅግ የከፋ ዓይነት ጂሃድ ወደ ሶማሊያ ማስገባቱና ሶማሊያ ውስጥ የመጀመሪያውን የጂሃድ ማሠልጠኛ ሠፈር ማቋቋሙን ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
አል-አፍጋን ከአል-ቃይዳው መሥራችና መሪ ኦሣማ ቢን ላደን ጋርም ብዙ ግንኙነቶች እና ንግግሮች እንደነበሩት ቢን ላደን በ2011 ዓ.ም ከተገደለ በኋላ ሲናገር ድምጹ ይሰማ እንደነበር ታውቋል፡፡ ሌላው ተገዳይ ሙአሊም ቡርሃን አል-ሻባብ ውስጥ ዋነኛ የሚባል የሃይማኖት ሊቅ እና የቡድኑ የመማክርት ምክር ቤት አባል እንደነበረ ተገልጿል፡፡
የአልሻባብ አመራር በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲዳከም፤ ባለፉት በርካታ ዓመታት ኢህአዴግ የአሜሪካ ወዳጅ ነኝ በማለት እንዲሁም አሜሪካም “ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ሸሪካችን ነች” በማለት ሲሞዳሞዱበት የነበረው አጀንዳ “በቀጣናው አሸባሪዎችን መዋጋት የሚል ነበር”፡፡ በተለይም እነ አቶ መለስ አልሻባብ የአልቃይዳ ስሪት ነው፤ አሸባሪነትን እንዋጋለን በማለት በአልሻባብ ስም የፈለጉትን የፖለቲካ ጥቅም ሲፈጽሙ ኖረዋል፡፡ ታዲያ ይህ የአልሻባብ መዳከም በዕቅድ የተከናወነ ይሆን? ወይስ የተበላበት ዕቁብ ስለሆነ ሌላ የታሰበ አዲስ ፕሮጄክት አለ? አልሻባብ ቁጥር 2 ወይም “ጸረ አሸባሪነትን መዋጋት ቁጥር 2”? ወይስ ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ ጉብኝታቸው ከምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን አለመምረጣቸው ጋር ተዳምሮ አሜሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ድራማ አዲስ የፖለቲካ ጽፈ ተውኔት አዘጋጅታ ይሆን? መቆየት ደጉ ብዙ ያሳየናል!

እንጀራ ብሔራዊ ደረጃ ወጣለት አንዳንዴ ለገበያ የሚቀርበው እንጀራ ለበሽታ የሚዳርግ ነው

እንጀራ ብሔራዊ ደረጃ ወጣለት
አንዳንዴ ለገበያ የሚቀርበው እንጀራ ለበሽታ የሚዳርግ ነው
የጤፍ እንጀራ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ብሔራዊ ደረጃ እንደወጣለት ታወቀ። ፋና ኤጀንሲውን በመጥቀስ እንዳመለከተው ጤፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ደረጃ ወጥቶለት መጽደቁን አመልክቷል። ዜናው ደረጃ የወጣለት ጤፍ ምን መስፈርቶች እንደተቀመጡለት አላብራራም። በኢትዮጵያ የጤፍ እንጀራ ወደ ውጪ በመላክ ንግድ የከበሩ ነጋዴዎች በብሔራዊ ደረጃ በጸደቀው አዲሱ የጤፍ ደረጃ መሰረት አዘጋጅተው ኤክስፖርት መላክ እንዳለባቸው የሚያስገድድ ሁኔታ ስለመቀመጡም የተገለጸ ነገር የለም።
በአውሮፓና አሜሪካ በተለያዩ ሱፐር ማርኬቶች፣ የግል የገበያ ሱቆችና የቤንዚን ማደያዎች ገበያ ላይ የሚገኘው የጤፍ እንጀራ injeraአንዳንድ ጊዜ ደረጃውን ያልጠበቀ፣ የሚኮመጥጥ፣ አይን የሌለው፣ የሚፈረካከስና ወዝ የሌለው እንጀራ የሚቀርብበት አጋጣሚ በርካታ ነው። በላስቲክ ታሽጎ ከፍሪጅ እየወጣ የሚሸጠው እንጀራ ጉዱ የሚታወቀው ቤት ከገባ በኋላ በመሆኑ በርካታ ተጠቃሚዎች እንደሚማረሩ ለማወቅ ችለናል።
አንድ እንጀራ እስከ ሰባ ብር በመግዛት የሚመገቡ የስካንዲቪያን አገራት ነዋሪዎች እንጀራ መመገብ  ቢወዱም ገበያው ላይ አንዳንዴ የሚቀርበው እንጀራ ለጨጓራ ችግር የሚዳርግ እንደሆነ ተናግረዋል። አዲስ ብሔራዊ ደረጃ ያወጣው ኤጀንሲ ህግ ማውጣቱን ብቻ ሳይሆን በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ቁጥጥር ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። እንጀራ ወደ ውጪ ለመላክ ፈቃድ ያወጡ ነጋዴዎች ህጉን አክብረው እንዲሰሩ የማስገደድ ተግባሩን እንዲገፋበትም ጠቁመዋል። ችግር ካጋጠማቸውም ማስረጃ በመያዝ ቅሬታቸውን ማሳወቅ የሚችሉበት አግባብ እንዲዘረጋላቸው ሃሳብ ያቀረቡም አሉ።

“(ከኢትዮጵያ ጋር) በፕሬዚዳንት ደረጃ ግንኙነታችንን ማጉላት አንፈልግም”

“(ከኢትዮጵያ ጋር) በፕሬዚዳንት ደረጃ ግንኙነታችንን ማጉላት አንፈልግም”
ከመካከለኛው አፍሪካ የአሜሪካንን ቀልብ የሚስብ አገር የለም። የደቡብ አፍሪካ መመረጥ ካላት ኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ሚናዋ አንጻር ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ያሉት ዴቪድ ሺን ከምስራቅ አፍሪካ አስር አገሮች መካከል አራቱን በመምረጥ የግል አስተያየታቸውን አቅርበዋል። ሴኔጋል የተመረጠችው ፈረንሳይኛ ተናጋሪና የምዕራብ አፍሪካ አገር በመሆኗ ነው።
የቪኦኤው ሰለሞን አባተ ያነጋገራቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ የቀድሞ አምባሳደር ዴቪድ ሺን ስለ ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት ሲናገሩ ኬኒያን አንስተው ነበር። የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አባት ኬንያዊ ቢሆኑም ኦባማ ኬንያን የጉብኝታቸው አካል ያላደረጉት አዲሱ ፕሬዚዳንትና ምክትላቸው በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ችሎት የሚፈለጉ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቀዋል። በወንጀል የሚፈለጉ መሪዎች ባሉበት አገር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጉብኝት አያደርግም በማለት ተናግረዋል።
o in africaዩጋንዳ ፣ ኢትዮጵያና ታንዛንያን ለንጽጽር ያቀረቡት ዶ/ር ሺን ሶስቱም አገሮች አሜሪካ የምታስቀምጠውን መለኪያ አያሟሉም። በታንዛኒያ ግን የፕሬዚዳንቱ የስልጣን ጊዜ ባግባቡ ተገድቦ ተቀምጧል። የአመራር ለውጥ ያካሂዳሉ። ጎልቶ የሚወጣ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት አያያዝ ጉድለት አይታይም ብለዋል። በዚህም የተነሳ ታንዛኒያ የተሻለች አገር ተብላ መመረጧን አመልክተዋል።
ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት በዓል ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ አዲስ አበባ መሄዳቸውንና ከመንግስት ክፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ያወሱት ሺን፣ ኢትዮጵያ በኦባማ ጉብኝት እቅድ ውስጥ አለመሆኗ የማግለል ጉዳይ እንዳልሆነ አመልክተዋል። አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የመያዝ ፍላጎት  እንዳላት የጠቆሙት ሺን “ይህን ግንኙነት በፕሬዚዳንት ግንኙነት ደረጃ ማጉላት አንፈልግም” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቻይና ፕሬዚዳንት በቅርቡ ሶስት የአፍሪካ አገሮችን ሲጎበኙ ኢትዮጵያን አለመጎብኘታቸውን አንስተዋል። በምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤና ጥናት ማካሄዳቸው የሚታወቀው ሺን “አሜሪካ ግንኙነቱን በፕሬዚዳንት ደረጃ ማጉላት አትፈልግም” ያሉበትን ምክንያት አላብራሩም።

አበባ እርሻ የሚሰሩ የኬሚካል ጉዳተኞች በርክተዋል የውጪ ምንዛሬ ገቢው 40% ቀነሰ

አበባ እርሻ የሚሰሩ የኬሚካል ጉዳተኞች በርክተዋል
የውጪ ምንዛሬ ገቢው 40% ቀነሰ
በከፍተኛ ደረጃ የእርሻ መሬቶችን ወደ አበባ እርሻ ማሳ ለሚቀይሩ ባለሃብቶች በመሸጡ ተቃውሞ የሚሰነዘርበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ የዜጎችን ህይወት እየተፈታተነ ነው። በአነስተኛ ክፍያ በአበባ እርሻዎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ወገኖች ከኬሚካል ጋር በተያያዘ እየደረሰባቸው ያለው የጤና መጓደል አስጊ እንደሆነ አሁንም ድረስ ትኩረት እንደሚፈልግ እየተነገረ ነው።
ለገቢው ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መንግስት በበጀት ዓመቱ ከዘርፉ የጠበቀውን ገቢ አለመግኘቱን ተጠቁሟል። ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን በላይ የአበባ ዘንግ፣ 114ሺ ቶን አትክልት እና 13ሺ ቶን ፍራፍሬ ባለፉት 11 ወራት ወደ ተለያዩ ሀገራት ቢላክም flower farm eesመጠኑ ከእቅድ በታች እንደሆነ ተገልጾዋል። ፋና የኢትዮጵያ  ሆርቲካልቸር ልማት ኤጄንሲን ጠቅሶ እንደዘገበው ወደ ውጪ ከተላኩት የአትክልት ምርቶች ከ212 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። ገቢው ከእቅዱ ስልሳ በመቶ ብቻ ነው። ኤጀንሲው ለገቢው መቀነስ የአለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝና በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ሁኔታ መለዋወጥ እንደ ምክንያት አቅርቧል።
ከአበባ እርሻ ጋር በተያያዘ በርካታ ዜጎች ለበሽታ መዳረጋቸውና በቂ የጤና ዋስትና እንደሌላቸው በተደጋጋሚ የሚገለጽ ችግር ነው። በአበባ ማበልጸጊያ ድንኳን ውስጥ የሚሰሩ ዜጎች ለኬሚካል ብክለት መጋለጣቸው የከፋ ችግር ከመሆኑም በላይ ከእርሻዎቹ የሚወጡ ፍሳሾች ወራጅ ውሃና ወንዝ ጋር በመቀላቀል አደጋ እያስከተለ ነው። ከዚህም በላይ የአበባ እርሻዎች ከፍተኛ ሃይል ያለው መርዝ ስለሚጠቀሙ መሬቱ ለወደፊቱ እህል እንደማያበቅል ባለሙያዎች በጥናት አረጋግጠው ያቀረቡበት የማይመከር ኢንቨስትመንት እንደሆነ መጠቆሙ አይዘነጋም።

“ለቤተሰቦቼ እቃ ለመላክ ስጠይቅ ሃላፊነት አንወስድም ተባልኩ” የፖስታ አገልግሎት ፖስታ ይጥላል፣ ያበላሻል፣ ያልተባለው ቦታ ይልካል

“ለቤተሰቦቼ እቃ ለመላክ ስጠይቅ ሃላፊነት አንወስድም ተባልኩ”
የፖስታ አገልግሎት ፖስታ ይጥላል፣ ያበላሻል፣ ያልተባለው ቦታ ይልካል
“ለወንድሜ ሞባይል ለመላክ ፖስታ ቤት ስጠይቅ የምልክበትን አገር ጠየቁኝ። ኢትዮጵያ እንደሆነ ነገርኳቸው። ኢትዮጵያ ከሆነ ለሚላከው ዕቃ ሃላፊነት አንወስድም አሉኝ” ስትል ለጎልጉል ግራ መጋባቷል በመግለጽ አውሮፓ እንደምትኖር የገለጸች ኢትዮጵያዊ ይህንን ጥያቄ የሰነዘረቸው ከወር በፊት ነበር።
በተመሳሳይ ፖስታ የሚጠቀሙ ወገኖች ችግር እንደሚገጥማቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። የላኩት ጥቅል postየጠፋባቸውና የተበላሸባቸው ያማርራሉ። ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓም ፋና ይፋ ያደረገው ዜና ይህንኑ ችግር ወለል አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት የደብዳቤና የጥቅል መልእክት አገልግሎት ደህንነትን በመጠበቅ በኩል ክፍተቶች እንዳሉበት የገለጸው ፋና ዜናውን ያገኘው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሳይንስና ቴክኖሎጂ  ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትን የአስራ አንድ ወራት እቅድ አፈፃፀምን በገመገመበት ወቅት እንደሆነ አመልክቷል።
ቋሚ ኮሚቴው እንዳለው ከሆነ በድርጅቱ የሚበላሹ፣ የሚጠፉና በተሳሳተ አድራሻ የሚላኩ መልእክቶች እየበዙ መጥተዋል፣ በዚህም ምክንያት የተገልጋዮች ቅሬታም እየጨመረ ነው። ችግሩን ያደመጠው ቋሚ ኮሚቴው ይህ እንዲስተካከልና በቀጣይ በዘርፉ የሚታየው ተገቢ ያልሆነ አሰራር እንዲሻሻልና አገልገሎቱ የደንበኞችን ፍላጎትን በሚያረካ መልኩ እንዲሰጥ ማሳሰቡን ፋና አስታውቋል።