søndag 30. juni 2013

ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል


ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል 

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። 
ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ – ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና መጠላለፍ ነው ብለዋል።  
 ጄ/ል ክንፈ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደሆነ ያስታወሱት ምንጮቹ ከስልጣን ሊያግዳቸውም ሆነ ሊያወርዳቸው የሚችለው በህግ ስልጣን የተሰጠው ጠ/ሚኒስትሩ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚሁ መሰረት ስልጣኑ በአዋጅ የተቀመጠው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪይም ቢሆንም – በግልፅ የሚታየው ግን ከህግ ውጭ የጄ/ል ሳሞራ ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ ከመሆኑ በተጨማሪ የታገደውን ጄ/ል ወደ ቦታው የሚመልሰው በተቃራኒው የቆመውና በሕወሐት ውስጥ ያለው የነስብሃት ቡድን መሆኑን ምንጮቹ ያመለክታሉ። አቶ መለስ ይዘውት የቆዩትና “በሕገ-መንግስቱ ተሰጠ” ከተባለው ስልጣን በአብዛኛው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ሊሰጥና ሊተላለፍ አልቻለም ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ ቁልፍ የሆነው የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነትን ጨምሮ በርካታዎቹ ሕገ-ወጥ በሆነ ሁኔታ በሕወሐት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አመልክተዋል።  
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን ምንጮች ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም ፥ « ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን እንዲሁም « አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ ያለውን ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በሌላም በኩል የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ብ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ በበኩላቸው፥ ከእንግሊዝ አገር ረቀቅ ያለ መሳሪያ በማስመጣት በስካይፕ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉትን ግንኙነቶች በመጥለፍና ተዛማች የስለላ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ከገለፁ በኋላ « ግንቦት ሰባት ከግብፅ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለህዝቡ ከነገርነው ከጎናችን ይቆማል፣ ግንቦት ሰባትን በማውገዝ የእንቅስቃሴው ተባባሪ አይሆንም፣ በአገር ውስጥ ያሉትም ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ህዝቡ አይቃወምም፤ እንዳውም ለመንግስት ድጋፍ ይሰጣል፤» በማለት በተሰብሳቢ መኮንኖች ጭምር ገረሜታን የፈጠረ ንግግር ማድረጋቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። በዚህም ለሕዝብ ያላቸውን ግምትና የግንዛቤ ደረጃ ያመላከተ ነው ያሉት ምንጮቹ የጄ/ል ተክለብርሃን የእውቀት ደረጃ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። የኤንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአቶ ደብረፂዮን ጭምር በበላይነት እንደሚመራና አቶ ሃ/ማሪያም የሚያውቁት እንደሌለ ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በሕገ – መንግስቱ መከላከያ ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ ቢደነግግም፣ ከወረቀት በዘለለ ተግባር ላይ ሲውል እንደማይታይና የነሳሞራና ተከታዮቻቸው ተደጋጋሚ አቋምና ተግባር በቂ ማስረጃና ማሳያ መሆኑን ምንጮቹ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል።
በመጨረሻም፥ የታገዱ ሌሎች ጄኔራሎችን ጉዳይ እንዲሁም ባለፈው ወር በሳሞራ ትእዛዝ የተባረሩ የሕወሐት ጄነራሎች ወደ ከፍተኛ ንግድ መሰማራት በተመለከተ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።

የግል ባንኮች ህልውና አደጋ ላይ ነው ተባለ


የግል ባንኮች ህልውና አደጋ ላይ ነው ተባለ

የግል ባንኮች ህልውና አደጋ ላይ ነው ተባለ
የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት የቁጠባ ፕሮግራም መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲከናወን መደረጉ በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነና በአጭር ጊዜ የግል ባንክ ዘርፉን ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥል የባንክ ባለሙያዎች ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ እስካሁን ከ750ሺህ በላይ ግለሰቦች የቤቶች ልማት ቁጠባ ሂሣብ በንግድ ባንክ እንደከፈቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የግል ባንክ ባለሙያ፤ እሣቸው በሚሠሩበት ባንክ ደንበኛ የነበሩ ግለሠቦች በቤቶች የቁጠባ ፕሮግራም ተሣታፊ ለመሆን ከባንኩ ገንዘብ በማውጣት በመንግስት ባንኮች እያስቀመጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ሣምንታትም ባንኩ በዚህ አገልግሎት ተጠምዶ መቆየቱን የተናገሩት ባለሙያው፤ “በእነዚህ ጊዜያትም የባንክ ሂሣብ ለመክፈት ወደ ባንካችን የመጣ ደንበኛ አላጋጠመኝም” ብለዋል፡፡ በባንኩ ያላቸውን ገንዘብ ለማውጣት የሚመጡ ደንበኞች መበራከታቸውንና ይህም ባንኩ ራሱን ለማቋቋም ለዓመታት የደከመበትን ልፋቱ ከንቱ እንደሚያስቀረውና ቀጣይ ህልውናውንም አደጋ ላይ እንደሚጥለው ባለሙያው ይናገራሉ፡፡ ስማቸውና የሚሠሩበት ባንክ እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሌላ ባለሙያም፤ በአሁን ሠአት ባንካቸው የውጭ ምንዛሬ እና የሃዋላ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባለፈ አዳዲስ የባንክ ሂሣብ የሚከፍቱ ደንበኞች እያስተናገደ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለም የባንኩ ህልውና አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
የኢዴፓ ሊ/መንበርና ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሼ ሠሙ በበኩላቸው፤ መንግስት መንግስታዊ በሆነው የንግድ ባንክ በኩል ብቻ ዜጐች እንዲቆጥቡ ማወጁ ከነፃ ገበያ ስርአት ጋር የሚቃረን መሆኑን ገልፀው ይህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ የህልውና አደጋ መጋረጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህ አካሄድ ከቀጠለም ያለ ጥርጥር ከሶስት እና አራት አመታት በኋላ የበርካታ የግል ባንኮች ህልውና እስከ መጨረሻው ሊያከትም ይችላል ብለዋል - አቶ ሙሼ፡፡ የቤቶች ልማት ቁጠባ ፕሮግራም ሁለት መሠረታዊ ተፅዕኖዎች አሉት የሚሉት አቶ ሙሼ፤ አንደኛው በግል ባንክ ውስጥ ከሚያስቀምጡ ደንበኞች ገንዘብ ላይ ማበደር አንዱ የባንኮች ተግባር መሆኑን ገልፀው፤ አሁን ግን ይህን ተግባር የሚያከናውኑበት ገንዘብ ወደ መንግስታዊ ባንክ እንዲሸሽ መደረጉን ይናገራሉ፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን የግል ባንኮች በብዙ ዓመታት ያፈሯቸውን ነባር ደንበኞችም እንዲያጡ ያደርጋል ብለዋል፡፡ መንግስት የቀረፀው የቤቶች ልማት ፕሮግራም የግል ባንኮች አዳዲስ ደንበኞችን እንዳያፈሩ ማድረጉ ሁለተኛው ተፅዕኖ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በተቃራኒው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አዲዲስ ደንበኞችን እንዲያገኝ ይረዳዋል ብለዋል፡፡ ነባሩም ይሁን አዲስ ደንበኛ ከግል ባንኮች ወጥቶ ወደ መንግስት ባንክ መሄዱ የነፃ ገበያ ስርአት እንዲከስም ከማድረጉ ባሻገር ባንኮችም በህብረተሠቡ ዘንድ ለዘመናት የገነቡትን ጠንካራ እምነት እንዲያጡ ያደርጋል በማለት የግል ባንኮች ላይ የተጋረጠውን አደጋ ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ መንግስት የግል ባንኮች ከሚያበድሩት ገንዘብ ላይ 27 በመቶ የህዳሴውን ግድብ ቦንድ እንዲገዙ ማዘዙን ያስታወሡት አቶ ሙሼ፤ የአሁኑ የግል ባንኮችን ያገለለው የቤቶች ቁጠባ ፕሮግራም ሲጨመርበት በባንኮቹ ላይ የሚደርሰው ጉዳት የቱን ያህል እንደሆነ መገመት አያዳግትም ብለዋል፡፡ “መንግስት የግል ባንኮችን ለማጥፋት ታጥቆ መነሣቱ የሚገርመኝ ጉዳይ ነው” ያሉት አቶ ሙሼ፤ በዚህ አካሄድ ከሦስት እና አራት አመት በኋላ የግል ባንኮች ሊጠፉ እንደሚችሉ ምንም ጥያቄ የሚያስነሣ ጉዳይ አይደለም ይላሉ፡፡
ኢህአዴግ ጉልበትና አቅም ያለው የግል ዘርፍ እንዲፈጠር አይፈልግም የሚሉት አቶ ሙሼ፤ በግል ባንኮች ላይ እየደረሠ ያለው ጫናም የዚሁ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ አባባላቸው ማስረጃ ሲያቀርቡም በቅርቡ የወጣ ጥናት ኢትዮጵያ በመንግስት ኢንቨስትመንት ከአለም 2ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ በግል ኢንቨስትመንት ግን በመጨረሻው ረድፍ ከተዘረዘሩት ሃገራት አንዷ ነች ብለዋል፡፡ አቶ ቡልቻ ደመቅሣ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊትም ከቻይና ለሚመጣ ማንኛውም እቃ በንግድ ባንክ በኩል ብቻ ግብይቱ ይፈፀም የሚል ህግ መፅደቁን አስታውሠው፣ ያሁኑ ሲጨመርበት በእርግጥም የግል ባንክ ዘርፉ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል፡፡ መንግስት በተደጋጋሚ በባንክ አሠራር ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ለዘለቄታው የማያዋጣ ተግባር መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቡልቻ፤ እንዲህ ማድረጉም አገሪቱን የዓለም ንግድ ድርጅትን ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ማህበራት አባልነት እንዳገለላት በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
Read 3011 times

lørdag 29. juni 2013

ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

“ግብረሰዶማዊነት ወደፊት!”
obama in senegal
በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሴኔጋል ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር እንደሚገባው አስታወቁ፡፡ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት ሰዶማውያንን የሚደግፍ ውሳኔ ሰሞኑን በማሳለፉ ደስታቸውን ገለጹ፡፡ የሴኔጋሉ አቻቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይወነጀሉ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናገሩ፡፡
ሰሞኑን በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝታቸውን በጀመሩባት ሴኔጋል የግብረሰዶማውያንን መብት በተመለከተ ለአፍሪካውያንና ለመሪዎቻቸው ማብራሪያና “ትምህርት” ሰጥተዋል፡፡ “መንግሥታት ዜጎቻቸውን እንዴት ሊያስተናገዷቸው ይገባል፤ ሕጉስ እንዴት ሊያያቸው ይገባል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊስተናገድ ይገባዋል” በማለት “ግብረሰዶማዊነት ወደፊት” የሚያስብል ንግግር አድርገዋል፡፡
አፍሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ኦባማ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት የግብረሰዶማውያንን መብት ሊያስከብር የሚችል ውሳኔ ማስተላለፉ እንዳስደሰታቸው በጉብኝታቸው ወቅት ጠቁመዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ውሳኔ ለጋብቻ መጠበቅ ከለላ የሚያደርገውን Defense of Marriage Act (DOMA) የተባለው ሕግ ለወንድና ሴት ተጋቢዎች ብቻ በማለት ያስቀመጠው ከለላ የግብረሰዶማውያንን መብት ይጻረራል በማለት ነበር፡፡ ስለሆነም በፍርድቤቱ ውሳኔ መሠረት  በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል የተፈጸመ “ጋብቻ” ከፌዴራል መንግሥት የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞችን ሊያስከለክል አይገባም በማለት ወንድ ሚስትም ሆነ ሴት ባል ያላቸው ሁሉ የጥቅሙ ተካፋይ እንዲሆኑ ፈቅዶላቸዋል፡፡ እንዲሁም በካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት የሰዶማውያን ጋብቻ እንዲቀጥል ፈቃድ የሚሰጥ ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድቤቱ አስተላልፏል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ግብረሰዶማዊነት በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በበኩላቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይከሰሱ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናግረዋል፡፡ “በጣም በመቻቻል” የምንኖር ነን ያሉት የሴኔጋሉ መሪ አገራት ውስብስብ የሆኑ ሕጎችን በራሳቸው ጊዜ በተግባር ላይ እንደሚያውሉ በመጥቀስ የኦባማን ሃሳብ ተግሳጽ በተሞላበት ምላሽ አስተናግደውታል፡፡
በመቀጠልም አገራቸው ሴኔጋል ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት ያቆመች መሆኗን በመናገር አሜሪካ ግን ይህንን እስካሁን ተግባራዊ አለማድረጓን በመጥቀስ ኦባማን ተሳልቀውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ወንጀለኞችን በሞት የመቅጣት ህግ ከ30 በላይ ግዛቶች ውስጥ ተግባራዊ ሲሆን በተለይም በቴክሳስ በሰፊው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት እንደገና ከተጀመረ ከ1974ዓም በኋላ የቴክሳስ ጠቅላይግዛት 500ኛዋን ወንጀለኛ ሰሞኑን በመግደል የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡

“ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

በፈረንሣይ አብዮት አካባቢ ህዝቡ መራቡን በተለይም የፈረንሣይ ጭሰኞች መቸገራቸውና በረሃብ እየተንገላቱ መሆናቸውን የተነገራት ልዕልት ማሪ አንቷኔ (“Qu’ils mangent de la brioche”) “ከራባቸው ኬክ ይብሉ” ብላ መልሳለች እየተባለ ለዘመናት ሲዘበትባት ኖሯል፡፡ ልዕልቲቱ ይህንን ለማለትዋ የተረጋገጠ ነገር ባይሆንም ነጻነት፣ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ … ለጠማው የአፍሪካ ሕዝብ ባራክ ኦባማ “የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር ይገባል” በማለት መሠረታዊውን የህዝብ ጥያቄ ችላ ማለታቸው “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” የማለት ያህል እንደሆነ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ጠቁመዋል፡፡
በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት “ለውጥ” እና “ተስፋ” ቀዳሚ ዓላማቸው አድርገው የበርካታዎችን ቀልብ የሳቡት ባራክ ኦባማ፤ ለአፍሪካ መሠረታዊ ችግር እስካሁን ጆሮ አለመስጠታቸው ብዙ የተባለበት ነው፡፡ ሰሞኑን በአሜሪካ ምክርቤት “ኢትዮጵያ፤ ድኅረ መለስ” በሚል ርዕስ በተደረገው ምክክር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የተናገሩትን በድጋሚ ያስታወሱም አሉ፡፡ በወቅቱ አቶ ኦባንግ ያሉት “ኦባማ ለምርጫ በተወዳደረ ጊዜ ጥቂት ደመወዝ የሚከፈላቸው ኢትዮጵያውያን የምርጫ ዘመቻውን ደግፈው ነበር፤ እስካሁን ከኦባማ የሰሙት ነገር የለም” በማለት ነበር፡፡
ከምዕራባውያን የሚመነጨውን ማንኛውንም ነገር – ከፖለቲካ እስከ ማኅበራዊ አመለካከት – ትክክለኛ አድርገው ለሚቀበሉ ግብረሰዶማዊነት ሥልጣኔ ይመስላቸዋል በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ የሃይማኖትና የማኅበረሰብ ሳይንስ ጉዳዮች ምሁር “ጋብቻ” የሚለውን ቃል ለሁለት ወንዶች መጠቀም እርስበራሱ የሚጋጭ ጉዳይ ነው በማለት ተመሳሳይ ጾታ ብሎ ጋብቻ ማለት የተሳከረ አነጋገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “ይህ የሰዶማውያን መብት ይከበር የሚለው ጉዳይ በሕግ እየጸደቀ ሲሄድ ድርጊቱን ከሃይማኖታቸው አኳያ የሚቃወሙ ሰባኪያን የሃይማኖት ትምህርታቸውን በሚያስተምሩበት ቤ/ክ ይሁን መስጊድ ወይም ምኩራብ ግብረሰዶማዊነትን እየተቃወሙ ሰበካ ማድረግ በህግ የሚያስጠይቃቸው ይሆናል” በማለት ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን የማኅበረሰብ ቀውስ ጠቁመዋል፡፡
bush in africaበሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው ወቅት ዳግም የመመረጥ ፈተና የሌለባቸው የአሜሪካ መሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን የአፍሪካን የዱር እንስሳት እየጎበኙ ወደፊት ለሚሠሩት ፕሬዚዳንታዊ ቤተመጻህፍት (ፋውንዴሽን) ፎቶ እንደሚሰበስቡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ የባራክ ኦባማም ጉብኝት ከዚህ የተለየ አለመሆኑ ግልጽ ሲሆን “የአፍሪካ ልጅ” እየተባሉ ሲሞካሹ የኖሩት ፕሬዚዳንት ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ሲገቡ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ገጥሟቸዋል፡፡ ቅዳሜ የክብር ዶክትሬት በሚቀበሉበት የዮሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል፡፡
ዛሬ ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ደቡብ አፍሪካውያን “ይቻላል” (Yes! We can!) ለሚለው የኦባማ የምርጫ መፈክር “አትችልም!” (“No, You Can’t Obama,”) የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ “ኦባማ የመጣው አፍሪካንና ደቡብ አፍሪካን ለመዝረፍ ነው” በማለት ጠንካራ ተቃውሞውን የገለጸው አንዱ ተሰላፊ “አፍሪካውያን በብዙ መልኩ እየተሰቃዩ እያለ እርሱ ግን የአፍሪካን ሐብት፤ ወርቅ፣ አልማዝ፣ … ለመዝረፍ ነው የመጣው” ብሏል፡፡obama s africa
የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ፣ … ዕጦት ላንገላታውና በአምባገነኖች መዳፍ ሥር ለሚሰቃየው የአፍሪካ ሕዝብ በቃላት እንኳን ድጋፋቸውን ከመስጠት እስካሁን የተቆጠቡት ኦባማ አሜሪካ በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አገሮች ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ፍላጎቱ እንደሌላት በማያወላውል መልኩ ያረጋገጠ መሆኑ የብዙዎች ግንዛቤ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ኃይል ጥያቄ ውስጥ የሚጥልም ነው፡፡
በአውሮጳ የፖለቲካ ምጣኔሃብት ተመራማሪ የሆኑ እንደሚሉት “አሜሪካኖች እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዓይነቱን አምባገነናዊ አገዛዝ እስኪያስመልሰው ድረስ በዕርዳታ ገንዘብ ካሽሞነሞኑ በኋላ“ኢህአዴግን ምን እናድርገው” በማለት “ምክር ስጡን” እያሉ በሕዝብ ሰቆቃ ላይ ያላግጣሉ፡፡ ሲሻቸውም ደግሞ አፍሪካ ድረስ በመሄድ “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” በማለት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን ችግር ያልሆነውን የግብረሰዶማውያን መብት መከበር ይሰብኩናል፡፡ ታዲያ ለዚህ ልግጫ መልሳችን መሆን የሚገባው “ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ነጻነታችንን አንለምንም፤ አሜሪካ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት እንድትሆንብን አንፈልግም” በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ምክርቤት በተካሄደው ምክክር የተናገሩትን ዓይነት ቁርጠኝነት ነው በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡
obama africa trip100ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው የኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት በአሁኑ ጊዜ በበጀት ቀውስ ምክንያት በርካታ ሠራተኞች ደመወዛቸው እየተቆረጠ ባለባት አሜሪካ አነጋጋሪ መሆኑን ዋሺንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡ የደኅንነት ሰዎችን እንዲሁም 14ሊሞዚን፣ 56 ጥይት የማይበሳቸው ድጋፍ ሰጪ  መኪናዎች፣ ሙሉ የህክምና ባለሙያዎችን የያዘና ጀቶችን የጫነ መርከብ … ለፕሬዚዳንቱና ለቤተሰባቸው ጥበቃ በማድረግ ሥራ ላይ እንደሚውሉ ጋዜጣው ያብራራል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ በደቡብ አፍሪካ የሁለት ቀን ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰኞ ወደ ታንዛኒያ ያመራሉ፡፡ የአባታቸው የትውልድ አገር ነው የሚባለውን ኬኒያ ሳይረግጡ በዚያው ወደ አገራቸው እንደሚያቀኑ የጉዞ መርሃግብራቸው ያስረዳል፡፡

torsdag 27. juni 2013

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ

944727_669620733054391_1701842863_n1.jpgታሪክ እንደሚያስረዳው የጎንደር ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት ብዙ ዋጋ የከፈለ አሁንም እየከፈለ ያለ ነው፡፡ ለሀገር አንድነትና ሉአላዊነት ደንታ የሌለው የኢህአዴግ ስርአት የጎንደርን ድንግል መሬት ለሱዳን አስረክቧል፡፡ አባቶቻችን በደም የዋጁትን የሀገራችንን መሬት ለባዕዳን ያስረከቡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለህግ እንዲቀርቡ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በተለይም የጎንደር ነዋሪ የመጠየቅ ታሪካዊ ግዴታ አለበት፡፡ ኢህአዴግ ተጨማሪ መሬቶችን ለእየቆረሰ ላለመስጠቱ ምን ማረጋገጫ አለን? ሚሊዮኖች ሆነን ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምንጠይቅበት ጊዜው አሁን ነው፡፡  
Ø  ኢትዮጵያ ዜጎች ሰርተው የሚኖሩባት፣ነግደው የሚያተርፉባት፣ልጅ ወልደው የሚያሳድጉባትና አስተምረው ለስራ ማብቃት የሚችሉባት ሀገር አልሆነችም፡፡ ስራአጥነት ተንሰራፍቶባታል፤ ዜጎች ዲግሪ ይዘው ኮብል ስቶን ፈላጭ ሆነዋል፣ በሀገራቸው ሰርተው መኖር ያልቻሉ ወጣቶች አስፈሪ የባህርላይና የበረሀ ጉዞዎችን በማድረግ ሀገር ጥለው ተሰደዋል፣በዋጋ ንረት አብዛኛው ዜጋ ያቃስታል፡፡ የነዚህ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምንጭ ኢህአዴግ የሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ነው፡፡ የስርአቱ ቁንጮዎች የተዘፈቁበት ሙስና ለችግሮቹ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በየጊዜው ከሀገራችን በህገወጥ መንገድ በኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚወጣው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብም ከደሃው ጉሮሮ የተነጠቀ እንደመሆኑ ለህዝባችን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል፡፡ ከስርአቱ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት ግለሰቦች ተንደላቀው ሲኖሩ የተቀረው ህዝብ ግን በመኖርና ባለመኖር መካከል ይንገላታል፡፡ ታዲያ እስከመቼ በዋጋ ንረት ተቆራምደን፣በስራአጥነት ተንገላተን፣በስደት ክብራችንንና ህይወታችንን አጥተን፣ የበዪ ተመልካች ሆነን እንቀጥላለን? በሀገራችን ኢኮኖሚ እኩል ተጠቃሚ የመሆን መብታችንን ለማስከበር ጊዜው አሁን መሆን አለበት፡፡
በ   ፀረ ሽብር ህጉ ሰበብ ከፌደራል መንግስት ተልከን መጥተናል የሚሉ የደህንነት ሀይሎች ጎንደር ላይ የፈለጉትን ሰው ማሰርና እንደዕቃ በአደራ ማስቀመጥን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ በርካታ ዜጎች በቤተሰቦቻቸውና በወዳጆቻቸው ሳይጎበኙ በተለያዩ እስር ቤቶችና ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች አበሳቸውን እያዩ ይገኛሉ፡፡ በአፋኙ የኢህአዴግ መንግስት የታሰሩ ወገኖቻችንን እንዲፈቱ አስቀድሞ ጥያቄ ለማቅረብ ከጎንደር ህዝብ የሚቀድም ማን ይኖራል?የፀረሽብር ህጉ እንዲሻርና በዚህ ኢህገ መንግስታዊ ህግ የታሰሩ ዜጎች በነፃ እንዲለቀቁ ለመጠየቅ የጎንደር ህዝብ በአደባባይ ድምፁን ያሰማል፡፡     
Ø  ኢህአዴግ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረውን የጎንደር ህዝብ በዘር ለመካፋፈል ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡ የስርአቱ ማለሟሎች በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ለ22 እንዳደረጉት ሁሉ በጎንደርም አንዱን ቅማንት ሌላውን አማራ በማለት በነገድ ለመለያየት የሚያደሩት የክፋት ድር መበጣጠስ ያለበት አሁን ነው፡፡ አንድነታችንን ለማጥፋት የሸረቡትን ሴራ በአደባባይ ለማጋለጥ ጊዜው አሁን ነው፡፡
አንድነት ፓርቲ በነዚህና ሌሎች ህዝባዊ ጥያቄዎች ዙሪያ የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በገዢው ፓርቲ ላይ የማያቋርጥ ጫና ለመፍጠር ሀገር አቀፍ ተግባራዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በመሆኑ የዚህ ንቅናቄ አካል በመሆን ድምፃችንን በጋራ እንድናሰማ እንጠይቃለን፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

onsdag 26. juni 2013

ሚሚ ስብሃቱና አያ ጅቦ

ሚሚ ስብሃቱና አያ ጅቦ


  • digg
  • 3
     
    Share
Mimi
እንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በቅርቡ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል አቢይ ርዕስ የህዝባዊ ንቅናቄ ጥሪ ለህዝብ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡አንድነት በዚህ ህዝባዊ ንቅናቄ የአንድ ሚልዮን ዜጎችን ፊርማ በማሰባሰብ የዜጎችን የማሰብ፣ የመናገር ፣በነጻነት የመደራጀትና ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን ጨምሮ ከህገ መንግስቱ ጋር ይጋጫል ያለውን የጸረ ሽብር ህግ እንዲሰረዝ ህጋዊ መስመርን በመከተል ጫና እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡
ይህንኑ መግለጫ ተከትሎ የዛሚዋ ሚሚ ስብሃቱ በምትመራው ‹‹የጋዜጠኞች የክብ ጠረጴዛ ››የውይይት መድረክ የአንድነትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከግብጽና ከግንቦት 7 ጋር በማቆራኘት ‹‹ፓርቲው ይህንን እንቅስቃሴ ያደረገው የህዳሴው ግድብ እንዳይሳካ ከሚፈልጉ ሀይሎች የገንዘብ ድጉማ ተደርጎላቸው ነው፡፡››በማለት የወረደና የተለመደ ፍረጃዋን አስደምጣለች፡፡ አንድነትን ለፍርፋሪ ያጩት እነ ሚሚ አልገባቸውም ወይም ሆን ብለው የሚሰማቸው ካለ ለማሳሳት አልያም አፍቅሮተ ኢህአዴግነታቸው ከኢህአዴግም በላይ ራሳቸውን እንዲያስቀምጡ አድርጓቸው ይሁን በተለየ መንተገድ የአንድነትን የሰላማዊ ትግል ጥያቄ አንድ ከረጢት ውስጥ በመክተት ፓርቲውን ለማስወንጀል ደንጊያ ለማቀበል ታትረዋል
ግን አንድነት ለምን የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ ይታገላል; ኢትዮጵያስ የሽብር ህግ አያስፈልጋትም የሚል አመለካከት አንድነት አለውን; ይህ ምላሽ ሁለት ጆሮዎቿን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የደፈነችውንና በነጻ ሚዲያ ስም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ያገኘችውን ሚሚንና ሁለቱን ደንገጡሮቿን አይመለከትም፡፡
1)አንድነት በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከኢህአዴግ ጋር በተቃራኒነት ስለተሰለፈ ብቻ ለማንም አሳልፎ አይሰጥም፣የአገሪቱን ጥቅም ከሚጎዳ የትኛውም ቡድን ጋርም የሚፈጽመው ምንም አይነት ስምምነት አይኖርም፡፡አንድነት በዚህ በኩል ጽኑ ኢትዮጵያዊ አቋም አለው፡፡እንዲህ አይነት ልምድና ታሪክ ያለው አሁን በገዢነት መንበር ላይ የተቀመጠው ኢህአዴግ እንጂ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማያወላውል አቋም ያለው አንደነት አይደለም፡፡ለገዢው ፓርቲም የሚበጀው የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ከወቅታዊ ሁነቶች ጋር በግድ በማዛመድ ትርጉም መስጠት ሳይሆን ለመነጋገርና እውነታውን ለመቀበል መዘጋጀት ብቻ ነው፡፡
2)አንድነትና ግንቦት 7 ማቆራኘት ሚሚየጀመረችው አይደለም፡፡የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማ ጭምር ፍረጃቸውን ማስደመጣቸውን በሰላማዊ ትግል ዙሪያ ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ለብዙዎች አርአያ የሆነውን አንዷለም አራጌን በሽበርተኝነት በመወንጀል እድሜ ልክ አስፈርደውበታል፡፡አንድነት በህዝብ ድምጽ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ገዢው ፓርቲ በየእለቱ የሚደቅንበትን መሰናከል እየተሻገረ የሚታገል ብረትን የሚጠላ ሰላማዊ ፓርቲ ነው፡፡እነ ሚሚ የህዝቡ መነቃቃትና የትግል መንፈስ መነሳሳት ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸው ይሉት ይጨብጡትን ስላጡ አንድነት በዚህ የተለመደ ፍረጃ በመደናገጥ አንድ ስንዝር ወደኋላ አይልም፡፡
3)አንድነት የጸረ ሽብር ህጉ ይሰረዝ ያለው ሚሚ እንደምትለው ከግብጽ ወይም ከግንቦት ሰባት ትዕዛዝ ስለ ወረደለት ሳይሆን በሽብር ህጉ ህገ ወጥነት ዙሪያ ከበቂ በላይ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በመሰብሰቡ ነው፡፡የአገሪቱ ህገ መንግስት በአንቀጽ 9 በግልጽ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጭ የትኛውም አይነት ህግ ወይም መመሪያ ተቀባይነት እንደሌለው እያወጀ የጸረ ሽብር ህጉ 15 ያህል አንቀጾች ህገ መንግስቱን እየተጣረሱ ፣የዜጎች መብት እየተደፈጠጠና ገዢው ፓርቲ ህጉን በሽፋንነት እየተጠቀመ ጋዜጠኞች፣ፖለቲከኞች፣የሃይማኖት ተደራዳሪዎችና አክቲቪስቶችን እያሰረና እያሰበረገገ ባለበት ሁኔታ አንድነትና ፊርማቸውን በተዘጋጀው ሰነድ ላይ እያኖሩ ያሉ ዜጎች ያሰሙትን ተቃውሞ ከግብጽ ፍርፋሪ ጋር ማቆራኘት ‹‹አያ ጅቦ ሳታመሃኝ ብላኝ››የምትለውን ተረት እንድናስታውስ ያደርገናል፡፡
የአውሬ-አምባው ካድሬ ዳዊት ከበዯ
ከያሬድ አይቼህ -
እስካሇፈው ሃሙስ ድረስ የአውራምባ ታይምስ ድረገጽ አዘጋጅ አቶ ዳዊት ከበዯ ጋዜጠኛ ነው ብዬ አምን
ነበር። ባሇፈው ሃሙስ በአቶ ዳዊት ድረገጽ ሊይ ስሇ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የተሇጠፈውን የድምጽ ቅጂ
አዳመጥኩኝ ፤ የተጻፈውንም አጭር ጽሁፍ አነበብኩ። አቶ ዳዊት የሚሰራው የጋዜጠኛ ስራ ሳይሆን ፡
የካድሬና ፕሮፓጋንዳ ስራ መሆኑን አምኜበታሇሁ። ሊብራራ።
የድምጽ ቅጂውን ያዳመጠ ሰው በቀሊለ እንዯሚረዳው ዶ/ር ብርሃኑ ተሰጠን ያለትን ገንዘብ ከግብጽ
ሇመሆኑ በቅጂው ሊይ ምንም መረጃ የሇም። ሇምነድን ነው ታዲያ አቶ ዳዊት በጽሁፍ “ምንጮቻችን”
ገንዘቡ ከግብጽ እንዯሆነ ነግረውናሌ ያሇው? እዚህ ሊይ አቶ ዳዊት ተራ የካድሬነት ስህተት ፈጽሟሌ።
ቅጂው በዩ-ቱዩብ ሊይ የተሇጠፈበት ጊዜ (ረቡዕ ጁን 19) የአሜሪካው ምክር ቤት የዉጭ ጉዳይ ኮሚቴ
“ድህረ መሇስ ኢትዮጵያ” በሚሌ ያዯረገውን ጉባዔ ሇማጥቃት የተዯረገ ይመስሊሌ ፤ ምክንያቱም ዶ/ር
ብርሃኑ ተጋባዥ መሆናቸው ቀድሞ ስሇታወቀ።
አቶ ዳዊት በድረ-ገጹ ሊይ የድምጽ ቅጂውን ከዩ-ቱዩብ የሇጠፈው ሃሙስ ጁን 20 ነበር። ሃሙስ ጁን 20
የአሜሪካው ምክርቤት ጉባዔ የተዯረገበት ቀን ነው። ዳዊት ምን ነካው? ከምር! ምን ነካው?
እኔ የግንቦት-7 ዯጋፊ አይዯሇሁም ፤ ግን ግንቦት-7 የእኔ ችግር አይዯሇም ፡ የኢህአዴግ እንጂ። አቶ ዳዊት
ይሄ አሌገባው ይሆን? ግንቦት-7 እንኳን 500 ሺ ዶሊር ፤ 500 ሚሉዮን ዶሊር ቢሰጠው ይገባዋሌ።
ግንቦት-7 የቆመሇት አሊማ በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ፡ ነጻነት እና ዴሞክራሲ ሇማምጣት እንጂ እንዯ
ኢህአዴግ በሙስና የነቀዘ ፡ በሰብዓዊ መብት ረገጣ የሰሇጠነ ፡ የኮሮጆ ላባ መንግስት ሇመመስረት
አይዯሇም።ታዲያ አቶ ዳዊት ዳግማዊ-አይጋ-ፎረም ሇመፍጠር ነው ሙከራቸው? ዳዊት ከአይጋው አቶ ኢሳያስ
አጽብሃ በጣም የተሻሇ ግብረግብ እና የጋዜጠኝነት መርህ ያሇው ሰው ይመስሇኝ ነበር።
ድርጊቱ ስህተት ከሆነ አቶ ዳዊት የይቅርታ ዯብዳቤ ቢጽፉ የባሇሙያ እጣፈንታቸውን ሉያድኑ ይችለ
ይሆናሌ።
ካሌሆነ ግን አውራምባ የአውሬ-አምባ ሆኖ ይቀራሌ።
- - - - - -
ጸሃፊውን ሇመጠርነፍ ፡ ሇማስፈራራት ወይም በኮንዶ ሇመዯዯሌ በዚህ ይጻፉሇት፦
yared_to_the_point@yahoo.com

Ethiopia opposition threatens protests over anti-terrorism law

(Reuters) - An Ethiopian opposition party called on Thursday for the government to scrap an anti-terrorism law it says is used to stifle dissent, threatening a repeat of protests that brought thousands onto the streets of Addis Ababa early this month.
The rally on June 2, organized by another opposition group, was the first large-scale protest in the Ethiopian capital since a disputed 2005 election ended in street violence that killed 200 people.
Opposition groups in the Horn of Africa country were vibrant until that vote but have since largely retreated from public view, the result, analysts say, of harassment by the authorities and divisions within their ranks.
They routinely accuse the government of intimidating and imprisoning their members and rigging elections against them. Ethiopia's 547-seat legislature has only one opposition member.
The anti-terrorism law ratified in 2009 makes anyone caught publishinginformation that could induce readers into acts of terrorism liable to jail terms of 10 to 20 years. Opponents say it is used indiscriminately to target anyone who opposes government policy.
"We shall demand that the anti-terror law be abolished immediately. It contradicts the constitution and violates the rights of people," Unity for Democracy and Justice (UDJ) party spokesman Daniel Tefera said at a news conference in Addis Ababa.
In a statement, UDJ said the government was doing too little to tackle unemployment and corruption and announced a campaign of nationwide debates and rallies.
"If there is no positive response from the ruling regime, we shall go to court with the millions of signatures in our hands," it said.
More than 10 journalists have been charged under the anti-terrorism law, according to the Committee to Protect Journalists, which says Ethiopia has the highest number of exiled journalists in the world.
The government dismisses the claims that it is cracking down on dissent and says the law is needed it its fight against separatist rebels and armed groups who it says are backed by arch-foe Eritrea.
Analysts say the opposition may have found renewed vigor since the death last year of Prime Minister Meles Zenawi, who was praised abroad for delivering strong economic growth but criticized for keeping a tight grip on power for 21 years.

Prime Minister Hailemariam Desalegn has for now shown no sign of a major shift in policy away from his predecessor.