የህወሓት አገዛዝ መቃወም ሀገር
መጥላት አይደለም!!
ለዚህ ፅሁፍ መነሻ ያደረኩት ነገር ቢኖር በስርዓቱ
ደጋፊዎች ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ። ከሚሰነዝሯቸው ሀሳቦች በተደጋጋሚ የምመለከትው ነገር ቢኖሮ የህወሓት አገዛዙ
መቃወም ማለት ሀገር መጥላት አድርገው ሲገነዘቡ አስተውያለው።
በመጀመሪያ ደረጃ ህወሓትና ሀገር ይለያሉ!!
ህወሓት ማለት የአንድ ብሄር ስብስብ ሲሆን፤ በትጥቅ ትግል ታግሎ ስልጣን የያዘ አንድ ቡድን ነው። ሀገር ማለት ብዙ ህዝቦችን፣
ብዙ ቋንቋዎችን፣ ብዙ ብሄሮችን፣ ብዙ ጎሳዎችን፣ ብዙ ባህሎችን፣ ብዙ እሴት. . . . . . . . . . ይዛ የምትኖር ማለት
ነው። ከልዩነታቸው ተነስተን ብዙ ነገር ልንገነዘብ እንችላለን። እርግጥ ነው ይህ ሊናገሩ የሚችሉት ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ነው። አንድ
አባባል አለ “አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል” አይደል የሚባለው። ህወሓት ተቃውሞ ሲገጥመው ጥቅማቸው የሚነካባቸው አካላት አሉ፤
ለዚህም ነው ስርዓቱን ለሚቃወሙ ሰዎች ሀገራቸውን እንደሚጠሉ ተደርጎ የሚታዩት።
የህወሓት አገዛዙን መቃወም ሀገር መጥላት ጋር
የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም። ህወሓት በሀገሪቱና በህዝቦቾ ላይ የሚፈፅመውን እኩይ ተግባር መቃወም ከሀገር መጥላት ጋር ሊያገናኙ
የማይችሉ ነገሮች ናቸው። ህወሓት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን ድረስ በዜጎች ላይ የሚደረሰው ስቃይና መከራ ቀጥሏል።
በመከራና ስቃይ ውስጥ ሆነው ሲቃወሙ እጣ ፈንታቸው ሞት ወይ እስራት በሆነበት ስርዓት ውስጥ ህወሓትም ሆን ደጋፊዎች ስርዓቱን መቃወም
ሀገር እንደመጥላት ይመለከቱታል።
ሀገር መጥላት ለሚባለው ነገር፤ ማንኛውም ሰው
ስለሀገሩ ልዩ ፍቅርና ክብር አለው። ስለሀገሩ ክብርና ፍቅርም ብዙ መሰዋዓትነት የሚከፍል፤ እየከፈለም የኖረ ህዝብ ነው። በየትኛውም
አለም ላይ ሀገሩን የሚጠላ ህብረተሰብ የለም። በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ስርዓት መወደድም ሆን መጠላትም በመንግስትና በህዝቦች መካከል
ያለው ግንኙነት ይወስነዋል። ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ እንደ መንግስት
ሆኖ ሀገሪቱን እየገዛት ያለው የአንድ አካባቢ ተዋላጆች ብቻ በመሆኑ በህዝቦች እና በገዥው ስርዓት መካከል በጣም ከፍትኛ ችግር
ይገኛል።
አሁን ላይ ህወሓትን መቃወም ማለት ከህዝብና
ከሀገር ጎን መቆም ማለት ነው። በዚህ ወቅት በመላው ሀገሪቱ የአገዛዝ ስርዓቱን በመቃወም ላይ ይገኛሉ። ይህ ተቃውሞ ስርዓቱ በፈጠረው
ተፅዕኖ የመጣ ነው። በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ተቃውሞ ይበልጥ መጠናከሩ ሁኔታ በሀገሪቱ ላይ የመሬትን ወረራን በተመለከት ተቃውሞውን
ይበልጥ አጎልቶታል። ህወሓትና ቤተሰቦቻቸው በአሁን ጊዜ በሀገሪቱ ላይ ከፈተኛ የመሬት ወረራ ላይ መጠመዳቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተገነዘበው
ጉዳይ ነው።
ስለ ህወሓት ተቃውሞ በተመለከት ገና ከጅምሩ
ሲታገል የነበረው አንድን ብሄር ነፃ ለማውጣትና የሀገሪቱን ታሪኳን ለማጥፋት ሲታገል የመጣ ቡድን ነው። ይህው በ25 አመታት ውስጥ
በኢትዮጵያዊን ዜጎች በውጭም ሆን በሀገር ውስጥ የሚደርሱ አሰቃቂ ግፎች የዚህ ስርዓት ቅጥ ያጣ ስልጣን መከት ያደረገ መሆኑ ነው።
እነዚህና ሌሎች ችግሮ በመመልከት ነው ተቃውሞ ከዕለት ወደ ዕለት ሊበረታ የቻለው።
ይህ ህዝብ ለስርዓቱን አልገዛም ማለቱ ሀገሩን
እንደሚጠላ መታሰቡ የሚገርም ነው!! በህወሓት ዘመን ዳር ድንበር የተደፈረበት፣ ዜጎች የሚገደሉበት፣ የሚታሰሩበት፣ የሚሰደዱበት፣
የሚፈናቀሉበት ዘመን. . . . . . . ከዚህ ዘመን የተረፈን መከራና ውርደት ነው። ይህን መቃወም ሀገር መጥላት ሊባል አይገባም፤
ለሀገር ተቆርቋሪነት እንጂ እንሱ ይህን እኩይ ተግባር በሀገሪቱና በህዝቡ ላይ እየፈፀሙ ሀገር ጠሉ አልተባሉም።
ይህን አስመልክቶ ለሚነሱ ተቃውሞው በተለያዩ
አጋጣሚዎች የተለያዩ ስም በካድሬዎችም ሆን በደጋፊዎቻቸው ሲሰጡ ይስተዋላል። ምንም አይነት ስም ቢሰጥም ህወሓትን ከመቃወም የሚሰንፍ
የለም።
እግዚሐብሄር ኢትዮጵያና ህዝቦቾን ይባርክ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
ቃልኪዳን ካሳሁን (ከኖርዌ)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar