torsdag 19. september 2013

አና ጎመሽ – ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉ

አና ጎመሽ – ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉ

ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡ ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡
ሽልማቱ ለሃሣብ ነፃነት ለሚታገሉና ለታገሉ የሚሰጥ የአውሮፓ ፓርላማ ዓመታዊ ክንዋኔ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያኑን ዕጩዎች ርዕዮት ዓለሙንና እስክንድር ነጋን ለሽልማት ካቀረቡት አርባ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት አንዷ የፓርላማው አባል፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው እና የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አባል የሆኑት አና ጎመሽ ይገኙበታል፡፡

​በአሁኑ ምርጫ ርዕዮት እና እስክንድር ቁጥራቸው ወደ 12 ከሚደርስ ከመላው ዓለም ከተጠቆሙ ሰዎች መካከል ወደ ሰባቱ አጭር ዝርዝር የገቡ መሆኑን ሚስ ጎመሽ ጠቁመው ፓርላማው የፊታችን ጥቅምት ውስጥ በሚያደርገው የተሟላ ስብሰባው ላይ አንዱ ለሽልማቱ በድምፅ እንደሚወጣ አመልክተዋል፡፡

እስክንድርና ርዕዮት የተመረጡት ፓርላማው ባወጣው መስፈርት መሠረት የሚያደርጉት ትግል የሃገራቸው ዴሞክራሲ፣ ነፃነትና ፍትህ የለው አስተዋዖ ተመዝኖ መሆኑንም ሚስ ጎመሽ ገልፀዋል፡፡

“እነዚህ ሰዎች እውነተኛ የሰብዓዊ መብቶች ታጋዮች ናቸው – ያሉት አና ጎመሽ ሁለቱ የኅሊና እሥረኞች ብቻ ሣይሆኑ በኢትዮጵያና በመላ አፍሪካም ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት ለሚታገሉ ሁሉም ደወል ወይም መታያ ናቸው” ብለዋል፡፡

የያዝነው የአውሮፓ ዓመት የሃሣብ ነፃነት የሳኻሮቭ ሽልማት ዕጩዎች ስሞች ለውጭ ጉዳዮች እና የልማት ኮሚቴዎቹ ጥምር ስብሰባ መቅረባቸውን የአውሮፓ ፓርላማ ያስታወቀው ከትናንት በስተያ ሰኞ ነበር፡፡

በፓርላማው መግለጫ መሠረት ፓኪስታናዊቷ ማላላ ዩሳፍዛይ፣ አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደን፣ ኢትዮጵያዊያኑ ርዕዮት ዓለሙ እና እስክንድር ነጋ፣ ቤላሩሲያዊያኑ አሌስ ቢያላትስኪ፣ ኤድዋርድ ላባዉ እና ማኮላ ስታትኬቪች በመላ የሃገሪቱ የፖለቲካ እሥረኞች ስም፣ ሩሲያዊው ሚኻይል ኾርዶቭስኪ፣ የቱርኩ “የቆመ ሰው” በሚል መጠሪያ የተጀመረው በቱርክ መንግሥቱ ላይ አፍጣጭ የታክሲም አደባባይ ተቃዋሚዎች ንቅናቄ የመጀመሪያው ተሰላፊ ኤርዶም ግዩንድዩዝ፣ የሲኤንኤን ቴሌቪዥን አውታር “ፍሪደም ፕሮጀክት (የነፃነት ፕሮጀክት)፡- ዘመነኛውን ባርነት ማብቃት” የሚባለው ፕሮግራም ናቸው፡፡

lørdag 10. august 2013

ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”
ኢህአዴግ አክራሪነትን እየጋበዘ ነው!!

”የሰላማዊ ትግል ምንነት ለማይረዱ ትልቅ ትምህርት የሰጠ፣ ኢህአዴግ ፍጹም የሆነ ልምድ ባካበተበትና ኤክስፐርት በሆነባቸው የትግል ስልቶች ብልጫ ወስዶ ለማንበርከክ እንደሚያስቸግር፣ ሰላማዊ ትግል ከራስና ከስሜት ጋር የሚደረግ ታላቅ አስተምህሮት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። የድምጻችን ይሰማ ትግል በዚህ መልኩ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆኖ ይቆያል” በግል አድራሻ ከተላከ አስተያየት የተወሰደ።

በአሃዝ፣ ጉዳቱ በሚገለጽበት መጠን፣ ጉዳቱ የሚገለጽበት ደረጃና የቋንቋው አቅም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወገኖች፣ የውጪ ታዛቢዎች፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ራሱ ኢህአዴግ፣ ህወሃትና መላው ወዳጆቹ በአንድ እውነት ይስማማሉ። እሱም ህወሃት ራሱ ባመጣው ጣጣ፣ ራሱ ትዕዛዝ ሰጪ ሆኖ ያደረሰው ሰብአዊና በቀላሉ ሊበርድ የማይችል መከራ እንደሆነ በየአቅጣጫው አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ያለ ምንም ማጋነን ኢህአዴግ ደም አፍሷል፣ ህይወት ቀጥፏል፣ አስሯል፣ ገርፏል፣ ፈንክቷል፣ ጣጣው ለሌሎች የሚተርፍ አካሄድ በመከተሉ ችግሩን አወሳስቦታል። ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ርምጃ የሚወስደው “ከብዙ ትዕግስት” በኋላ መሆኑን “በመንግሥት ወግ” ቢገልጽም “የሚያምነው ያገኘ አይመስልም” የሚል ወቀሳም ይሰነዘርበታል። እንደውም “ለየትኛዋ የሚወዳት አገር” በሚል ለፕሮፓጋንዳ አፉን በከፈተ ቁጥር ዘለፋ እየወረደበት ነው።

“ኢህአዴግ ጉልበት አልባ ተደረገ!”

ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል የሚሉ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች ገለጻቸው ለሌላው ግራ የሚያጋባ አባባል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። ግን በነሱ እምነት ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል። አቅም አልባ ያደረገው “የድምጻችን ይሰማ” የትግል ስልት ነው። ኢህአዴግ ያለውና የሚታወቅበት መለያው የታጠቀው መሳሪያ፣ ወታደሩ፣ የፌደራል ሃይሉ፣ የክልል ፖሊስ፣ ፈጥኖ ደራሹ፣ የሰላምና መረጋጋቱ ፣ የስለላ ሃይሉ፣ የአጋዚ ጦሩ፣ የአንድ ለአምስት አወቃቀሩ … ከሁሉም በላይ ደግሞ ጉልበተኛነቱን የሚቆጣጠሩለት የአንድ ብሔር “ታማኝ” ሃይሎች መሆናቸው እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ።

“ኢህአዴግ አለኝ የሚለውን ጉልበቱን መጠቀም ቢፈልግም መድረኩን ‘በተጠና’ የትግል ስልት በሚፈልገው ደረጃ ሊጠቀም አለመቻሉ በደጋፊዎቹና በራሱ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “የሙስሊሞች እንቅስቃሴ፣ የዕዝ ሰንሰለታቸውን ጠብቀው የሚያካሂዱት ትግል ኢህአዴግ ጉልበቱን እንዳይጠቀም ከልክሎታል። አሁን እየወሰደ ያለውና የወሰደው የሃይል ጥቃት ሊወስድ ከሚፈልገው ጋር ሲነጻጸር ሃይሉ ሽባ መደረጉን ያሳያል፤ ይህ ደግሞ የሰላማዊ ትግል ውበት ነው” ሲሉ ኢህአዴግ በገባው ጭንቅ መጠን ርምጃ ባለመውሰዱ እንደሚቆጭ ይናገራሉ። በሌላ አነጋገር የሽብር፣ የማሸበርና የመግደል “ጠቢብ” ለሆነው ኢህአዴግ አሁንም ችግሩ የሚፈታው በሃይል፣ በባሰ ሃይል እንደሆነ ከማመን አላፈገፈገም ሲሉ ያብራራሉ።

ኢህአዴግ ነገሮችን እያባባሰ የሰላማዊ ትግሉን ወደ አመጽ ለማስቀየር ሃሳብ ቢኖረውም “የድምጻችን ይሰማ ህብረት አስቀድሞ መረጃ የማግኘትና በሰላማዊ ትግል ተክኖ መገኘት ኢህአዴግ ያሰበውን እንዳይፈጽም አድርጎታል” በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። እነዚህ ክፍሎች ኢህአዴግ “አክራሪነትን የሚሰብኩና የሚያቀነቅኑ አሉ” በማለት ለሚለፍፈው “እስካሁን የአክራሪ ሙስሊም እንቅስቃሴ ስለመታየቱ መረጃ የለም። ከተፈጠረም አክራሪነት እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆነው ራሱ ኢህአዴግ ነው። ደም ማፍሰሱን አጠናክሮ በቀጠለና ዜጎችን ማሰሩ በገፋበት ቁጥር ለመሞት የሚዘጋጁ ዜጎች አገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል የወንድሞቻቸውን ጭፍጨፋ በመመልከት የመስዋዕትነቱ ተካፋይ ለመሆን ዓለምአቀፋዊ የሙስሊም ኅብረተሰብ ቁጣ ያስተባብርና ራሱን ችግር ላይ ይጥላል፤ ለአገርም መከራ ይሆናል፡፡”

በተቃራኒው አክራሪነት እየተስተዋለ የመጣው አሁን እንዳልሆነ የሚናገሩ ክፍሎች “በአሁኑ ሰዓት አገራችን ውስጥ ያለው የሃይማኖት ውህደት ቀደም ሲል እናቶቻችንና አባቶቻችን በየዋህነት ሲያደርጉት እንደነበር አይነት ነው ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው” በማለት ይናገራሉ። በማያያዝም እንዲህ ያለው ስጋት በሰላማዊ ትግል ጉልበት አልባ የሆነውን ኢህአዴግ ሃይል እንዲያገኝና ይህንን ሃይል እንዲተማመን አድርጎታል ሲሉ ይከራከራሉ።

“ኢህአዴግ ሰክሯል”

ኢህአዴግ መስከሩን፣ አንጎሉ መዞሩንና የሚያደርገው እንደጠፋው የሚናገሩ ክፍሎች እንደሚሉት የኢድ ቀን ኢቲቪ ያሰራጨውን ዜና ቀላል ምሳሌ አድርገው ያቀርባሉ። የድምጻችን ይሰማ መነሻ ምክንያት የሆኑትን አዲሱን የመጅሊስ መሪ በቴሌቪዥን መስኮት አቅርቦ “ሙስሊሞች ላይ የወሰዳችሁትና የምትወስዱት ርምጃ የሚደገፍ ነው፣ ትክክል ነው” በማለት ያቀረበው ቃለ ምልልስ “ከስካርም በላይ አዙሪት ነው” ሲሉ የኢህአዴግን የበሽታ መጠን ይገልጻሉ። ሙስሊሙን አንኳን አሰራችሁት፣ ደበደባችሁት፣ ገደላችሁት በሚል ደረጃ “ደግ አደረጋችሁ፣ ርምጃችሁ ትክከል ነው” በማለት ዜና ማሰራጨቱ ኢህአዴግ በራሱ ሚዲያ በችግሩ ላይ እሳት ማርከፉን የሚያመላክት ስለመሆኑ በማሳያነት ያቀርባሉ።

አንድ ጤና ያለው መንግስት የህዝብ ቁጣ ሳይለሳለስ፣ የቁጣውን መንስዔ አደባባይ በማቅረብ “ተጎዳን በሚሉ የህብረተሰብ፣ በተለይም የአንድ እምነት ተከታዮች ፊት ማዘፈን ኢህአዴግን የያዘውን የስካር የዞረ ድምር (ሃንግኦቨር) የማሽተት ያህል ነው” የሚሉት ክፍሎች ኢህአዴግ ቢያንስ ለራሱ፣ ህወሃትና ቁንጮው ላይ ሆነው ሃብት ለሰበሰቡት ሲል እርቅ ሊወርድ የሚችልበትን መንገድ እንዲያስብበት ይመክራሉ። ጉዳዩንም በጥበብ እንዲይዘው ይመክራሉ።

መተማመን ድሮ ቀረ!!

በሙስሊም ወገኖች አወሊያ የተጀመረው የድምጻችን ይሰማ ጥያቄ፣ የኢህአዴግ የጥያቄው አያያዝ ችግር ተዳምሮበት የእምነቱ ተከታዮች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተቃውሞው እየተዳረሰ ይገኛል። የአገሪቱን ሙስሊሞች ከጫፍ እስከጫፍ በሚያስገርም የግንኙነት መረብ እያስተባበረ የሚነደው ሰላማዊ ቁጣ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ድጋፍ አለማግኘቱን ለኢህአዴግ ሃይል እንደሆነው የሚናገሩ ወገኖች “ይህንን አስመልክቶ በሚቀርበው መረጃ ግራ ተጋብተናል” ይላሉ።

“እንኳን የሌላውን ሃይማኖት የራሳቸውን ሃይማኖትና ስርዓት ማስጠበቅ ያቃታቸው የክርስትናው ሃይማኖት ተከታዮች፣ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ደገፉ ተብሎ ሲዘገብ ዘገባው ሚዛን የሚደፋ አይሆንም” በማለት የሚከራከሩ ክፍሎች “የክርስትና እምነት ተከታዮች ለእምነታቸው ሊሰጡ የሚገባውን ክብር ከድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ መማር ከቻሉ ይህ ብቻ በራሱ ይበቃል” በማለት በተቃራኒ ወቀሳ ይሰነዝራሉ። እንደውም የራሳቸውን የእምነት ቤት ማጽዳት ባለመቻላቸው ሊወቀሱ እንደሚገባ መረጃ በማጣቀስ ይከራከራሉ።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ላይ ካለው የረዥም ጊዜ የተቀነባበረ ሴራና የምንገኝበት የጂኦ ፖለቲካ ካሸከመን ጣጣ ጋር በማዳመር “ሜዳዎች ሁሉ ሸራተን ሆነው አይዋቡም” የሚል አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች “መተማመን ድሮ ቀረ” ሲሉ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ዝምታ ይገልጹታል።

“ሙስሊሞች አብዛኞች በሆኑበት ቦታ ያለ ችግር ቢፈልጉ አክርረው፣ ቢፈልጉ አለዝበው እምነታቸውን ያራምዳሉ። አነስተኛ በሆኑባቸው አገራት ደግሞ ያለውን የአስተዳደር መሰረት የመጋራት ፈተና ይፈጥራሉ” የሚሉት እነዚህ ክፍሎች “እነዚህ በሌሎች አገሮች የታዩ ተሞክሮዎች ከምዕራቡ መገናኛ ውስወሳ ጋር ተዳምረው በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ያስቀመጡት ጠባሳ ቀላል አይሆንም። ኢትዮጵያ ውስጥም ይህ ችግር አለ” ባይ ናቸው። በሌላም በኩል በማህበራዊ ድረገጾች አርሲ አርባ ጉጉና ጅማ የተከናወነውን በማንሳት ሰሞኑንን ለመከራከር የሞከሩትን በመጥቀስ የፍርሃቻው ማሳይ አድርገው ያስቀምጡታል።

ፍጹም ሰላማዊ ትግል – ፍጹም የሚያስቀና ህብረት!!

መሰረታዊ የእምነትና አመራር ጥያቄ በማንሳት ትግላቸውን በተጠና መንገድ የሚያካሂዱት የ”ድምጻችን ይሰማ” የትግል መስመር አስገራሚ እየተባለ ነው። ህብረታቸውና በተዋረድ የሚያካሂዱት መናበብ አስደማሚ ሆኗል። አልፎ አልፎ ከሚሰራጩ ወፍ ዘራሽ5 መልዕክቶች በስተቀር መሪዎችን በመከተል የሚያሳዩት ትብብር የሚያስቀና እንደሆነ እየተነገረ ነው። ተመሳሳይ ዓላማ ይዘው እርስ በርስ የሚቧቀሱት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች ከድምጻችን ይሰማ “የሰላማዊ ትግል” ቀመር ሊማሩና ይሁንታ ካገኙ ስልጠናም ሊወስዱ እንደሚገባ የሚናገሩ ተበራክተዋል።

እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የሙስሊም ወገኖች ጥያቄና ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ወደኋላ እንደማይሉ በመደጋገም ይፋ እያደረጉ ነው። ኢህአዴግ ከተካነበት ድርጅቶችን የመሰንጠቅና “የእባቡን አንገት ቁረጥ” ከሚለው የአምባገነኖች መርሁ አንጻር ድምጻችን ይሰማ ውስጥ ዘልቆ መግባት አለመቻሉ አስገራሚ የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። ቅንጅት እንደ ሰደድ እሳት አገር አዳርሶ ኢህአዴግን ባስጨነቀ ማግስት “ሳሎኑ ተበርግዶ ኢህአዴግ ሲንቦጫረቅበት” የተመለከቱ፤ ዓመት ከመንፈቅ ያህል የዘለቀውንና ከዕለት ወደ ዕለት በብቃትም ሆነ የኢህአዴግን መሠሪነት በመመከት እንዲሁም የተጠና የትግል ችሎታ በማሳየት ወደር ያልተገኘለትን የድምጻችን ይሰማ ትግል ከማድነቅ ወደኋላ አይሉም። ለሌሎች ሲመክሩም የመስመርና የትግል አስተላለፍ ለውጥ ለማድረግ አሁንም ጊዜው እንዳላለፈ ሊገነዘቡት ይገባል በማለት ለሌሎች የሰላማዊ ትግል ምንነት ላልገባቸውና የገባቸው መስሏቸው ተስፋ ለቆረጡ ይመክራሉ፡፡
 (http://www.goolgule.com/) 
Photo: ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ”
ኢህአዴግ አክራሪነትን እየጋበዘ ነው!!
http://www.goolgule.com/a-non-violence-beyond-politics/

..............................................................................................
ማስታወሻ

ይህ ሪፖርታዥ የተቀናበረው የዝግጅት ክፍላችን ካነጋገራቸው ወገኖችና በኢሜል ከተላኩ መልክዕክቶችና አስተያየቶች በመመርኮዝ ነው። ለንባብ እንዲያመች የአርታኢ ስራ ከመሰራቱ ውጪ ሙሉ ሃሳቡ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ያሰፈሯቸው ነው። አሁንም በዚህ ጽሁፍ ላይ የቀረቡትን ሃሳቦች በማስፋትም ሆነ በመቃወም የሚላኩ ጽሁፎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን። (ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከቢላል Tube Photos ድረገጽ ነው)
=========================================
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ድምጻችን-ይሰማ፦ የመጀመሪያው በሳል ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ትግል

ድምጻችን-ይሰማ፦ የመጀመሪያው በሳል ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ትግል 

ከያሬድ አይቼህ

ህወሃት ደደብ ነው። ምንም የማይገባው ፡ ገደብ የማያቅ ፡ ግርድፍ ባዕዳዊ ድርጅት ነው። በአስተሳሰቡ ባዕድ ፡ በስነምግባሩ ባዕድ ፡ በግብረገቡ ባዕድ። ይሄን የህገ-አራዊት ድርጅት ፊት ለፊት የገጠመው የድምጻችን-ይሰማ ንቅናቄ ነው። የንቅናቄው ብስለት ፡ አርቆ አሳቢነት ፡ አገራዊነት እና ሰብዓዊነት ድንቅ ነው ፤ ድንቅ!
ከ18 ወራት በፊት አካባቢ የጀመረው የድምጻችን-ይሰማ ንቅናቄን በመጠኑ ግራ በመጋባት እና በተደባለቀ ስሜት ስከታተል ቆይቻለሁ። በዩናይትድ ስቴትስ የምንኖር ሰዎች የአሜሪካንን ፊሪሃ-ኢስላም (islamophobia) ፕሮፓጋንዳ ሌት ተቀን ስለምንጋተው ፡ እኔም ፈሪሃ-ኢስላም ተጠናውቶኝ ነበር። “ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም አሸባሪነትን ያስተናግዱ ይሆን?” የሚለው ጥያቄ በአይምሮዬ ጀርባ ሲያንዣብብ ቆይቷል።
ልጅ ኢያሱ መሃመድ አሊ (100 ዓመት)
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪካዊ የሆነ የመንግስታዊ ተቋም ጫና እና ጭቆና እንደ ደረሰባቸው አምናለሁ። ልጅ ኢያሱ መሃመድ አሊን እንዳይነግስ ያገደው መንግስታዊ ፈሪሃ-ኢስላም ፡ በሌሎች ታሪካዊ ክስተቶችም ጫናውን እና ጭቆናውን ማሳየቱ የሚካድ አይደለም።
ሆኖም ግን አራዊቱ ህወሃት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ፈሪሃ-ኢስላምን ተጠቅሞ መጅሊሱን (የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበርን) ለመቆጣጠር መፈለጉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አሁንም የመንግስት ተቋማዊ ጭቆና ቀንበር ፡ ከልጅ ኢያሱ መሃመድ አሊ ከስልጣን መባረር 100 ዓመት በኋላ ፡ ደግሞ መከሰቱ ሙስሊሞች መብታቸውን ካለስከበሩ ማንም እንደማያስከብርላቸው የሚያስረግጥ ሃቅ ነው።
የ18 ወራት ፈተና
ድምጻችን-ይሰማ ላለፉት 18 ወራት እንደ ወርቅ ተፈትኗል። መሪዎቹ ታስረዋል። ያልተለወጠው ነገር ቢኖር ግን የንቅናቄው ብስለት ፡ አርቆ አሳቢነት ፡ አገራዊነት እና ሰብዓዊነት ናቸው። ንቅናቄው በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ለመብታቸው ለሚታገሉ ዜጎች ፡ ቡድኖች ፡ ድርጅቶች ሁሉ ትልቅ አርአያ ነው።
የድምጻችን-ይሰማን አርአያነት በመከተል ሌሎች ንቅናቄዎች ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ፋና ወጊ ሰላማዊ ትግልን ማራመዳቸው አይቀሬ ነው። የንቅናቄው ራሱን መግዛት ፡ ለአራዊቱ ህወሃት ወጥመዶች ራሱን አሳልፎ አለመስጠት ፡ በጽናት ጥያቄዎቹን በአርብ ጸሎት ላይ ማሰማቱ እጅግ ድንቅ ነው። ፍርሃት የማይበግረው ፡ የአውሬው ወያኔ ሚዲያ የማያግደው ፡ የሰላማዊ ትግል ጀግኖች ንቅናቄ በኢትዮጵያ ባለፉት 18 ወራት ተወልዷል።
የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች
አንዳንድ መሰሪ ፡ መርዛም ግለሰቦች የድምጻችን-ይሰማን ንቅናቄ “ለምን ለሁሉም ጥያቄ አይታገሉም?” የሚል የጥገኛነት ትችት ሊያሰራጩ ሲሞክሩ ፡ በተለይ ‘ሲቪሊቲ’ በሚባለው የፓልቷክ የዉሃ ላይ ኩበቶች ስብሳቤ ክፍል አዳምጫለሁ። ለራሴ ነፃነት ሃለፊነቱ የእኔ ነው።

በዲያስፓራ ተቀምጠን ፊትለፊት ያለምንም ፍርሃት አራዊቱን ወያኔ የሚጋፈጡትን የሰላማዊ ታጋዮች መተቸት የሞራል ዝቅጠት ፡ የስነልቦናን ውርደት እና የሰብአዊነት ኪሰራን የሚያሳይ ነው። የዲያስፓራ ቱልቱላዎች እረፉ። ባታርፉም ምንም ስለማታመጡ እረፉ።
ድምጻችን-ይሰማን መቃወም አራዊቱን ወያኔን መደገፍ ነው። ፈሪሃ-ኢስላም ያላችሁ ሰዎች ፡ የድምጻችን-ይሰማን የትግል መስመር ፡ ፈተና እና ጽናት ብታጤኑ እንደ እኔ ከፍርሃታችሁ ነጻ ትወጣላችሁ።
ድምጻችን-ይሰማ ግፋ! ቀጥል! በአላማህ ጽና!
ክብር ለሰማዕታት!
ኢድ ሙባረክ።
- – -

በኢድ ተቃውሞ ከ2ሺ በላይ ሰዎች ታስረዋል

በኢድ ተቃውሞ ከ2ሺ በላይ ሰዎች ታስረዋል

በፖሊስና ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች በተፈጠረው ግጭት በርካቶች ቆስለዋል
በበርበሬ ተራ አካባቢ የነበረው ግጭት ከፍተኛ ነበር

በአወሊያ ት/ቤት በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዙሪያ፣ ከዚያም አልፎ በአክራሪነትና በሃይማኖት ነፃነት ጉዳይ፣ ሲብስም የፖለቲካ ጥያቄዎች እየተጨመሩበት ሲብላላ የቆየው አለመግባባት ወደ ግጭት የተሸጋገረው ከአመት በፊት የረመዳን የፆም ወቅት ቢሆንም፤ ባለፈው ሃሙስ እለት የኢድ በዓል ላይ የተፈጠረው ግጭት ብዙ ሰዎችን ለጉዳት የዳረገና ከሁለት ሺ በላይ ሰዎች የታሰሩበት ሆኗል፡፡ 

ሃሙስ ጠዋት በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው ባሉ ጎዳናዎች የተከበረው የኢድ በዓል ላይ የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደሚካሄድ ቀድሞም ሲጠበቅ የነበረ ነው፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው አስተባባሪዎች በበራሪ ወረቀትና በኢንተርኔት የተቃውሞ ጥሪ ሲያስተላልፉ ሰንብተዋል፡፡ በስታዲየምና በዙሪያው የኢድ በዓል ስነ ስርዓት እንደተጠናቀቀ፣ የተቃውሞ አስተባባሪዎች ድምፅ የተሰማው ስታዲየሙ ውስጥ ሲሆን፣ በየአካባቢውና በዙሪያው ባሉ ጎዳናዎች ተስፋፍቶ ተስተጋብቷል፡፡

አጀማመሩ ላይ ግጭት አልተፈጠረም፡፡ የተቃውሞ ድምፅ እያሰሙ የሚጓዙትና በየአቅጣጫው የተሰማሩ ፖሊሶች ሲገጣጠሙ ነው ግጭት የተፈጠረው፡፡ በተለይ ከስታዲየም ወደ ሲኒማ ራስና አውቶቡስ ተራ፣ ወደ ፒያሳና መርካቶ፣ ወደ ባምቢስና ፍላሚንጎ በሚወስዱ አቅጣጫዎች ከተፈጠሩት ግጭቶች ሁሉ ወደ መርካቶና አውቶቡስ ተራ በሚወስደው በርበሬ ተራ አካባቢ የነበረው ለበርካታ ሰዓታት የዘለቀና የከፋ ነው፡፡

በየቅያሱና በየሰፈሩ ጭምር ዱላ በያዙ ፖሊሶችና ድንጋይ በሚወረውሩ አካባቢው ተረብሾ የዋለ ሲሆንና በየጎዳናው ላይ የሚታየው ትዕይንት የግጭቱን ስፋት ያሳያል፡፡
የተወረወሩ ድንጋዮች መንገዱን ሸፍነውታል፡፡ በፖሊስ የተደበደቡ ወይም በድንጋይ የተፈነካከቱም ሞልተዋል፡፡

በረብሻው ወቅት ከየአቅጣጫው በፖሊስ እየተያዙ የሚመጡ ሰዎች ትንሿ ስታዲየም ውስጥና ፖስታ ቤት አካባቢ ባለው ፓርክ ውስጥ ነበር ታስረው እንዲቆዩ የተደረገው፡፡ ችግር ፈጥረዋል ተብለው በሁለት ቦታዎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች ቁጥር 3ሺ ይደርሳሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ከፊሎቹ አመሻሽ ላይ ተለቀዋል፡፡ ቀሪዎቹ ግን በየክፍለ ከተማው በእስር እንዲያድሩ ተደርጓል፡፡ ባለፉት ሳምንታት መጀመሪያ በአንዋር መስጊድ ከዚያም በቦኒ መስጊድ እና በቶፊክ መስጊድ ሦስት ተቃውሞዎች መካሄዳቸው ይታወሳል፡፡

“የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ”፣ “የደሴው ሼህ ግድያ ድራማ ነው”፣ “መጅሊሱ (ምክር ቤቱ) እኛን አይወክልም”፣ “ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም”፣ “በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም”፣ “አህበሽ የተባለው አስተሳሰብ ይቅር”፣ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይግባ”፣ “አወሊያ የሙስሊሙ ተቋም ነው” የሚሉ ጥያቄዎችና መፈክሮች ሲስተጋቡም ቆይቷል፡፡

fredag 26. juli 2013

Tourism and the abuse of Hamer women in Ethiopia

Tourism and the abuse of Hamer women in Ethiopia

The Vancouver Sun
by Daphne Bramham, Vancouver Sun columnist
Women from Ethiopia’s South Omo Valley
Women from Ethiopia’s South Omo Valley are seen here dancing. They are also severely beaten as part of a coming of age ceremony that can be witnessed and photographed by wealthy tourists.
Photograph by: Andrew Renton, Vancouver Sun
Bored with the usual round of museums, art galleries, cathedrals, temples or world heritage sites and with appetites whetted by documentaries, rich travellers are looking for authenticity.
Their desires have spawned a number of discrete and sometimes disturbing niche markets.
There are the adventurers. Images of tourists lined up to summit Everest, for example, are now almost as familiar as the images of their discarded oxygen bottles strewn at the Nepalese mountain’s base.
There’s poverty tourism (a.k.a. poor-ism or slum tourism) where seeing the living conditions of the desperately poor can be as life changing for the viewer as it is exploitative of the viewed.
There’s volun-tourism, where you pay to work for non-profit organizations such as Habitat for Humanity.
In Lac-Mégantic, Que., grieving people have come face-to-face with disaster tourists snapping photos of what and who has been left behind after the tragic and devastating train derailment and explosion.
And there’s the kind I discovered reading the weekend travel section of The Sun that’s perhaps best described as citizen-anthropologist trips. They’re cloaked as adventure tourism and wrapped in a self-congratulatory tolerance for other people’s traditions and customs.
In this case, it was the ritualized abuse of Hamer women in Ethiopia’s South Omo Valley.
Vancouver-based travel writer Andrew Renton described a three-day ceremony marking a young man’s coming of age that culminates with girls and women getting beaten and lashed so badly with sticks that they all bear the scars.
He recounts buying medication for one girl whose wounds had turned septic, “but she is still not happy” because the next day she was to be beaten again as part of her brother’s initiation ceremony.
The account is chilling.
“I find my girl and turn her around. Her eyes are glazed. Her back is running with blood. I’m told she took all the medication in preparation for today’s event.”
The italics are mine; the paternalistic possessive pronoun is Renton’s even though he viewed and recounted the beating of girls and women — black, African girls and women — with detachment.
His account and others describe the women and girls as being either drunk, drugged or in a trance during the beatings, which often go on for more than an hour.
No photos of the beatings of the scarred and bloodied backs of the girls and women were published in the paper. That would, no doubt, ruin the happy tourism buzz.
And, make no mistake, the writer wasn’t a lone, plucky adventurer who serendipitously happened upon this ritual during his nine days of playing citizen-anthropologist.
One photo shows nine other white, camera-toting tourists in the half-circle around the ceremony.
Think about it. What they witnessed would be criminal assault in Canada and most countries and probably even Ethiopia.
The story ended with this jaunty, verbal wave: “Whether you agree with the customs or not, the people and their traditions are real.”
This glib cultural relativism begs fundamental questions.
Is it morally right to do nothing when another person or even an animal is being beaten so badly that they’re left bleeding and scarred?
Are rural Ethiopian women and girls (or any others in the developing world) not entitled to the same rights and protections as Canadians?
The coming-of-age ritual may well be an ancient one. But it’s one of the many reasons that Ethiopia is one of the worst countries to be a girl or a woman, ranking 173 out of 187 countries when it comes to gender inequality.
Another old custom/tradition in Ethiopian herding societies is the most extreme form of female genital mutilation, which entails the removal of all external genitalia.
The United Nations unanimously passed a resolution last December calling for a global ban on the practice, which UNICEF says is rampant in Ethiopia’s rural areas even though it has been outlawed.
So far, there are no reports of this ritual being carried out in front of tourists.
But in a country so desperately poor, who’s to say what people may be willing to do for money?
For the writer’s brief look at real life in the South Omo Valley, he paid nearly 10 times what the average Ethiopian earns in a year. His $3,300 “covered absolutely everything for nine days except alcohol.”
It’s a fair bet that very little of what the gawking travel writer and other tourists paid to witness the abuse will trickle down to girls like the poor, wretched one described in the article.
Yet, for the Ethiopian herders living at the desperate margins even a pittance can make a difference.
The troubling question is what kind of difference?
If rich Westerners pay high prices and set aside their own cultural values to watch ritualized abuse, it’s possible that rather than being impartial observers their very presence exacerbates and may even perpetuate it

søndag 7. juli 2013

Zone9 እሁድ ጠዋትን በዝዋይ ማረሚያ ቤት — በቀለ ገርባን አገኘነው።

Zone9
እሁድ ጠዋትን በዝዋይ ማረሚያ ቤት — በቀለ ገርባን አገኘነው።

የዞን ዘጠኝ አባላትና ወዳጆቻችን ደርዘን ሆነን ዛሬ (ሰኔ 30/2013) ወደዝዋይ የተዛወሩ እስረኞችን ለመጠየቅ ሄድን።

በመጀመሪያ ያገኘነው በቀለ ገርባን ነበር። መልከ መልካሙ በቀለ አውርተው የሚጠግቡት ዓይነት ሰው እንደሆነ ለማወቅ ሄዶ ማየት ያስፈልጋል። ከእሱጋ ስናወራ ከሌሎችጋ ለመገናኘት ያቀድንበት ሰዓት እስከሚጣበብ ድረስ ዘግይተናል።

በቀለ ገርባ ስለሰላማዊ ትግል አብዝቶ ያወራል። ከ32 እስረኞችጋ አንድ ቦታ እንደታሰረ እና በተንጣለለው የዝዋይ ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ በተለይ እነሱ በአንዲት ውሱን፣ በተለምዶ ጨለማ ቤት የሚባለው ክፍል ውስጥ እንዳለ አጫውቶናል። (እዚህ ቦታ በግንቦት ሰባትነት ክስ የተፈረደባቸው ጄነራሎችና በነአንዱአለም አራጌ መዝገብ የተከሰሱት እዚሁ ይኖራሉ) ሆኖም ከቃሊቲ አንፃር ሲታይ ዝዋይ በጣም የተሻለ ምቹ እና ሠላማዊ እንደሆነ፤ ሌላው ቀርቶ ለሕክምና አዲስ አበባ መዛወር ኖሮበት ይቅርብኝ እንዳለ ጨምሮ ነግሮኛል።

በቀለ አሁን ከእስር ለመፈታት አመክሮው ተቀንሶ 2 ዓመት ከአራት ወር ከዘጠኝ ቀን ነውም ብሎናል። በእስሩ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም ድጋፍ እያደረገለት በመሆኑ እንደሚበረታና አሁንም ወደፊትም ብቸኛው የለውጥ መንገድ ሠላማዊ ትግል መሆኑን ለሕዝብ በምታስተላልፉት መልዕክት ላይ አስፍሩልኝ ብሎናል። በፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ቅጣት ማቅለያ ንግግሩን አስመልክቶ ስንጠይቀው ለማለት ብቻ ሳይሆን የማምንበት የሕይወት ፍልስፍናዬ ነው ሲል ነግሮኛል።

ከዚያ በኋላ ጋዜጠኛ ውብሸት፣ ናትናኤል፣ ዘሪሁንን እና አበበ ቀስቶን አግኝተን አነጋግረናቸው በጥንካሬያቸው ተበራትተናል።

onsdag 3. juli 2013

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ እንደማይወርዱ አስታወቁ፤ በግጭት ሕይወት ጠፋ

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ እንደማይወርዱ አስታወቁ፤ በግጭት ሕይወት ጠፋ

ፕሬዚዳንቱ ፍንክች እንደማይሉ አቋማቸውን ዛሬ – ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ምሽት ላይ ባደረጉትና በሃገሪቱ ብሔራዊ ራዲዮና በቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ንግግር ያስታወቁት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎቻቸው አደባባይ ወጥተው እንዲወርዱ እየጠየቋቸው ባሉበት ወቅት ነው፡፡
የዛሬ ዓመት አካባቢ በሃገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ ነፃ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሞርሲ ሕገመንግሥታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በመወጣት እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ ጦር እጁን ከፖለቲካው ቀውስ ውስጥ እንዲያወጣም አሣስበዋል ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፡፡
የግብፅን ባንዲራ የሚያውለበልቡ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል – ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
በሚስተር ሞርሲ እና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ያለው ልዩነት እስከነገ፤ ረቡዕ ባለው ጊዜ ካልተፈታ ለግብፅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይበጃል የሚሉትን የራሣቸውን የጎዳና ትልም እንደሚደነግጉ የጦር ኃይሎቹ መሪዎች ማስጠንቀቃቸውና ቀነ-ገደብ መቁረጣቸው ይታወሣል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን እያሰሙ በነበሩበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ተቃዋሚና ደጋፊዎቻቸው የሆኑ ሰልፈኞች የካይሮን አደባባዮችና ጎዳናዎች አጨናንቀዋል፡፡
ከመሪያቸው ጎን ቆመው እነርሱ “ማንኛውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት” ያሉትን የጦሩን እርምጃ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ እየዛቱ ያሉት የሞርሲ ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ናስር ቀበሌ የተሰባሰቡ ሲሆን ሞርሲ ሥልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚለውን ጥያቄአቸውን የሚያሰሙት ተቃዋሚዎች ደግሞ ማዕከላዊውን የካይሮ ጣሕሪር አደባባይ ሞልተውታል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሣ ግጭት ካይሮ ውስጥ ዛሬ (ማክሰኞ) የሰባት ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሕክምና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ወታደሮች ካይሮ ቤተመንግሥት አጥር ግቢ ላይ፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም ወታደሮቹ “ሕገመንግሥቱን ለማቋረጥ፣ ሕግ አውጭውን አካል ለመበተንና የሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም እየተዘጋጁ ነው” የሚል ሾልኮ የወጣና ለመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ሽው ያለ ጭምጭምታ ጠቁሟል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ አባላት “የተመረጠን ፕሬዚዳንት ለመገልበጥ የሚደረግን ሙከራ ለማቆም” ከታንኮች ፊት ቆመው መስዋዕት እንደሚከፍሉ እየዛቱ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ሞርሲ ተቃዋሚዎቹን ሰልፈኞች እያዳመጡ መሆናቸውን እንዲያሣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማክሰኞ ጠዋት ስልክ ደውለው ጠይቀው ተቃዋሚዎችም የግብፅን ዴሞክራሲያዊ ሂደት መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል፡፡
አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ለግብፃዊያኑ ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ በተካሄዱ ሰልፎችና በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ከሃያ በላይ ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል፡፡