fredag 20. mars 2015

የሀሃገሪቱን ሃብት የወያኔ ባለስልጣናት ለሊቱን የጉምሩክ መጋዘኖችን ሲዘርፉ አደሩ!

ሳተናው ዜና
0
  • 2824
    Share
10395167_10203594184165064_8271715634568534826_nበሃገሪቱ አንጡረ ሃብት ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጭቆና በማድረግ ላይ የሚገኙት የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጄኔራሎች እና በደህንነት ባለስልጣናት እየተመሩ ለሊቱት ከጉምሩክ መጋዘኖች በውርስ የገቡ እቃዎችን ሲጭኑ ያደሩ መሆኑን ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል::
ለሊቱን በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የጉምሩክ መጋዘኖች የተወረሱ የመኪና መለዋወጫዎች የኤሌክትሮኒስ እቃዎች የሞባይል ቀፎዎች ውድ ጌጣጌጦች የቤት እቃዎች የመሳሰሉት በባለተሳቢ መኪናዎች አስጭነው መውሰዳቸው ሲታውቅ እቃዎቹ በሃገሪት በተለያየ አከባቢ ተበትነው እንደሚሸጡ ምንጮቹ ገልጸው ለሊቱ የጄነራል ሳሞራ የኑስ የሜ/ጄነራል ተክለብርሃን እና የአርከበ እቁባይ መኪኖች እና ጠባቂዎቻቸው እና ተላላኪዎቻቸው በየመጋዘኖቹ ሲዘዋወሩ እንደነበር እና ለዚህ ዘረፋ ተሳታፊዎቹ እነማን እንደሆኑ በግልጽ ያሳያል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል::
የወያኔ ባለስልጣናት ሕዝብን እየጨቆኑ እየዘረፉ እስከመቼ እንደሚቀጥሉ የሚያሳስብ ጉዳይ መሆንን አውቀን ህዝብን እና ሃገርን ከዘረፋ እና ከጭቆና ለማዳን ከለውጥ ሃዮች ጎን በመቆም በሃገር ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአስተባበር እና ሕዝብን በመቀሰቀስ ከአስከፊው ስርአት ነጻ ለመውጣት በጋራ መንቀሳቀስ አለብን:: ነጻነታችንን ማራጋገጥ የምንችለው እኛው ታግለን መሆኑን ማውቅ ያለብን ወስኝ ወቅት ላይ ስለሆንን በአንድነት በመቆም ይህንን የሌቦች መንግስት ስርአተ ቀብር እናጣድፈው ዘንድ ጠንክረን መስራት አለብን::

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar