søndag 12. januar 2014

የባለሥልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አያልቅም እንዴ?

 

የሃብታቸው መጠን ይፋ የሚደረገው ከስልጣን ሲወርዱ ይሆን? (ያመለጡን አሉ!)
በሃብት ምዝገባው ላይ የትዳር አጋርም ሊካተት ይገባል (መነጣጠቅ ተጀምሯላ!)
“Grand corruption” አለ የሚባለው ገንዘብ ሚኒስቴር ሲዘረፍ ነው እንዴ?
የእነቴሌ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት “ፅድቁ ቀርቶብኝ--” ያሰኛል!
ኢትዮ- ቴሌኮም በየበዓሉ የሚልከው የ “እንኳን አደረሳችሁ” መልካም ምኞት አሁን አሁን “ሙስና” እየመሰለኝ መጥቷል፡፡(ግራንድ ኮራፕሽን ሳይሆን ሚጢጢዬ ሙስና!) ለነገሩ ቢመስለኝም እኮ አይፈረድብኝም፡፡ ለምን መሰላችሁ? ዓመቱን ሙሉ በብዙ የአገልግሎት አሰጣጦች ችግር ሲያማርረን ከርሞ --- በዓል ሲደርስ እንደ ደህና አገልጋይ “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን ሊደልለን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? (“ደለለኝ --- ደለለኝ” ነው ያለችው ድምፃዊቷ) ነፍሷን ይማረውና! እውነቴን እኮ ነው… ኔትዎርክ ሳይኖር፣ ኢንተርኔት ተቋርጦ፣ የቢሮና የቤት ስልክ ጠፍቶ… እንዴት ነው “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን? (ያውም ለእኛ አሻፈረኝ በሚለን ኔትዎርክ!) እኔ የምለው ---- እኛና ቴሌ የምንተዋወቀው በስልክ አገልግሎት አይደለም እንዴ? (ከዚያ ውጭ የት ስንተዋወቅ ነው!) ከሁሉም የሚገርመኝ ደሞ ”ከመጪው ዘመን ጋር አገናኛችኋለሁ” የሚለው ፉከራው ነው፡፡ (“ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” አሉ!) እንኳንስ ከመጪው ዘመን… ከዛሬ ጋር እንኳን መች ተገናኘን! (ማን ነበር “አቅምን አውቆ ማደር ጥሩ ነው ታላቅ ችሎታ ነው” ያለው?!) አሁንማ ከምንፈልገው ሰው ጋር መገናኘት አይደለም--- ሂሳብ ለመሙላትም ኔትዎርክ ማግኘት መከራ ሆኗል (ቴሌኮም በነፃም እንኳን ገንዘብ አልቀበልም እያለን እኮ ነው!) እስካሁን የውሃና የመብራት መ/ቤቶች ለገና በዓል “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት አለማለታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምናልባት ሳልሰማቸው ብለውን ከሆነ ግን የእነሱንም ከ“ሙስና” ለይቼ አላየውም፡፡ ለምን ብትሉ… ገንዘብ የምንከፍልበትን ዋናውን አገልግሎት በቅጡ ሳናገኝ በየበዓሉ “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት ለእኔ ተራ መደለያ ነው፡፡

(የመረረው ደንበኛ አታውቁም!?) ለነገሩ እዚህ አገር እኮ ቀድመው የሚናደዱት አገልግሎት ሰጪዎቹ እንጂ ደንበኞች አይደሉም፡፡ እኛ ደህና አገልግሎት የሚሰጠን አጣን ብለን ከመናደዳችን በፊት እነሱ ቀድመውን ይናደዱብናል (“ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ” አለች አስቱ!) እናላችሁ---የበዓላት ጊዜው ድለላ ቀርቶብን አንዴም ክፍያው ተቋርጦ የማያውቀውን የውሃና የመብራት አገልግሎት ሳይቆራረጥ፤ሳይጠፋ እናገኝ ዘንድ ለብዙ መቶኛ ጊዜ እንማጠናለን፡፡ (“Where is my beef?” አለ ፈረንጅ!) ምን እንደሚገርመኝ ታውቃላችሁ? ሦስቱም የመንግስት ተቋማት ለአገልግሎታቸው መቋረጥ የሚሰጡት ሰበብ ሁሌም ተመሳሳይ ነው - እንደሰነፍ ተማሪ እየተኮራረጁ፡፡ (አዲስ ሰበብ መፍጠር ሮኬት ሳይንስ ሆነ እንዴ?) እናላችሁ ---- ውሃም መብራትም ኔትዎርክም የሚጠፉትና የሚቆራረጡት በ“ልማቱ” የተነሳ ነው፡፡ መብራት ለምን ይቋረጣል? ግድቦች እየተሰሩ ስለሆነ! ኔትዎርክ ለምን ይጠፋል? ኔትዎርክ እየተስፋፋ በመሆኑ! ውሃ ለምን ትጠፋለች? አዲስ የውሃ መስመር እየተዘረጋ ነዋ! ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ታገደ? ልማቱን ለማፋጠን! እኔ የምለው ግን ---- ነባሩ አገልግሎት ሳይቋረጥ፣ እኛም ሳንማረር --- ልማቱን ማስፋፋት እንዴት አቀበት ይሆንብናል? ሳስበው ግን አቀበት ........

http://goo.gl/9W2eUG

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar