onsdag 12. juni 2013

በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ሊደረግ ነው


በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ሊደረግ ነው

በዘሪሁን ሙሉጌታ

በተለያዩ የውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ዜጎች በሀገሪቱ በሚካሄዱ የምርጫ ስርዓት በመሳተፍ ድምፅ እንዲሰጡ ሊደረግ ነው።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ህግና ደንብ መሰረት በአረብ አገራት ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ
 በሌሎች አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምርጫ መምረጥ የሚችሉበት ዕድል እየተመቻቸ ነው

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ተሊል ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ምርጫው
 የሚከናወነው የሀገሪቱን አቅም ባገናዘበ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው ማዕከላት ውስጥ የምርጫ ጣቢያዎችን
በማደራጀት ዜጎቹ ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል።

አዲስ የተዘጋጀው የዲያስፖራ ፖሊሲ ካካተታቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ማድረግ መሆኑን
ጠቅሰዋል። ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን 2005 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የዲያስፖራ ፖሊሲ ላይ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ፣ ቁጥራቸው ከአንድ ሺ እስከ ሁለት
 ሺ ከሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር በፖሊሲው ላይ ምክክር እንደሚካሄድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ጁን 12 ቀን 2013 ዕትም

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar