torsdag 10. oktober 2013

ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል

"ኢትዮጵያ ከሁለቱም ያተረፈችው እዳ ነው"
alamudi-
በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት “ባለሃብት” በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል።
የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር።
ሳዑዲ ስታር የስራ አቅሙ ተገምግሞ መሬት እንደሚጨመርለት ቃል ቢገባለትም የወሰደውን 10 ሺህ ሔክታር በቅጡ አልተጠቀመም በሚል የግብርና ኢንቨስትመንት ሃላፊዎች ተጨማሪ መሬት ለመስጠት ሲያቅማሙ ቆይተው ነበር። ሆኖም ግን በአቋማቸው መዝለቅ ያልቻሉት ሃላፊዎች ለሳዑዲ ስታር ተጨማሪ 120 ሺህ ሔክታር መሬት ፈቅደዋል። በቅርቡ ከወራት በፊት በተካሄደ ግምገማ አነስተኛ የስራ ትጋት ውጤት ያስመሰዘገበው ሳዑዲ ስታር አዲስ ጥያቄ ማቅረቡን በጋምቤላ የሚኖሩ የድርጅቱ ባልደረቦች ለጎልጉል ገልጸዋል። ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊም በሰራተኞቹ የተጠቆመውን ዜና አጠናክረው አምነዋል።
በዚሁ መሰረት ንግድ ባንክ 62 ሚሊዮን ብር እዳ እንዳለበት፣ እዳውም በገባው ውል መሰረት እንዳልከፈለ፣ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም አለመሰካቱን፣ በዚህም የተነሳ ንብረት ለመውረስ መመሪያ መተላለፉንና ጉዳዩ ወደ ህግ መመራቱ ይፋ የሆነበትን ካሩቱሪ በተረከበው ማሳ ላይ ያስቀመጠው ንብረት ካለበት የሊዝ ዕዳ፣ የተለያዩ ክፍያዎችና የክልሉ ዓመታዊ ክፍያዎች ጋር ተዳምሮ እዳውን ይሸፍናል ተብሎ እንደማይገመት ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።
በክልሉ ኢህአዴግ በጠመንጃ ሃይል እየተተገበረ ያለው የመሬት ንጥቂያ ጉዳዩን በውል የሚያውቁ ዜጎችን፣ እንዲሁም የክልሉን ነዋሪዎች ቁጭት ላይ የጣለ መሆኑ “ባለሀብቶች” ተብለው በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩትን በሙሉ እረፍት እንደማይሰማቸው የሚጠቁሙት የጎልጉል ምንጮች “ካራቶሪን በሳንቲም ሂሳብ ተቸብችቦለት ከባንክ ብድር ጋር የተረከበውን መሬት መልሶ ለመውሰድ ከፍተኛ ኪሳራ አለ። ኪሳራው የአገርና በተለይም ለዚህ ፋይዳ ለሌለው ኢንቨስትመንት ንብረቱንና ቀዬውን በጠመንጃ የተነጠቀው የክልሉ ሰላማዊ ህዝብ ነው” በማለት ቁጭታቸውን ይገልጻሉ።
“በአካባቢው ሕዝብ ተቀባይነት ያላገኘ ኢንቨስትመንት፣ በተለይም ሰፋፊ እርሻዎች ሁሌም አደጋ ላይ ናቸው” በማለት አሁንም ኢህአዴግና ባለህብቶች ከቀድሞው ጥፋታቸው እንዲማሩ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “ካራቱሪ ከቀረጥ ነጻ ሲነግድና የተፈጥሮ ደን ሲያወድም ቆይቶ በእዳ ፋይሉ ሲዘጋ መሬቱን ለሳዑዲ የምግብ ዋስትና እንዲውል እየተደረገ ያለው ሩጫ ዳግም ስህተት እንዳይሆን” ሲሉ ይመክራሉ።
3.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማዘጋጀት የአገሪቱን ምርት 39 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ለማሳደግ አቅዶ እንደነበር የሚገልጸው ኢህአዴግ ባለበት እየረገጠ እንደሆነ ማስረጃ በማጣቀስ የሚተቹት ብዙዎች ናቸው። በተለይ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ክልል ያለውን ድንግል መሬት ከነዋሪዎቹ ጋር በመስማማት ለአገሪቱ ሕዝብ የምግብ ዋስትና ሊያውለው እንደሚገባ የግብርና ባለሙያዎች በየጊዜው የሚወተውቱት ጉዳይ ነው።
የጎልጉል ምንጮች አጠንክረው እንደሚናገሩት ካሩቱሪ የውጪ አበዳሪዎቹና የአክሲዮን ደንበኞቹ ስለከዱት ከጋምቤላ ለቅቆ ይወጣል። ካራቱሪ ቀደም ሲል 300 ሺህ ካሬ ሄክታር መሬት የነበረውና በሂደት ተቀንሶበት 100 ሺህ ሔክታር እንደቀረው፣ ከዚሁ ላይ ማልማት የቻለው አስር በመቶ ብቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

onsdag 9. oktober 2013

የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ድምፅ ከየመን

የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ድምፅ ከየመን
በየመን እና በሳዑዲ አረቢያ ድንበር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሚገኙት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የሳዑዲ አረቢያ የወሰን አጥሮች ንድፍ /በሰሜን ኢራቅ፤ በደቡብ የመን/የሳዑዲ አረቢያ የወሰን አጥሮች ንድፍ /በሰሜን ኢራቅ፤ በደቡብ የመን/

ሳዑዲ አረቢያ ከየመን ጋር በሚያዋስናት ድንበሯ ላይ በተለይ ከአፍሪካ የሚጎርፉ ስደተኞችና ፍልሰተኞችን ያስቆምልኛል ያለችውን አጥር አቁማለች፡፡ 1800 ኪሎሜትር ከሚሆነው የጎረቤቶቿ ወሰኖች በ75 ኪሎሜትር ላይ የቆመው ባለ ሦስት ሜትር ቁመት አጥር ተጠናቅቋል፡፡

ዛሬ ወደ ሳዑደ አረቢያ መዝለቅ እንደቀድሞ ቀላል አይደለም፡፡
የሳዑዲ-የመን ድንበር አጥርየሳዑዲ-የመን ድንበር አጥር

አደገኛው አጥር ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራና ከሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች ብዙ መከራ አልፈው የየመንን ምድር ከረገጡም በኋላ የሚከተላቸው ሥቃይ ከዚህ አጥር ማዶ ያለውን ሥራ የማግኘት ተስፋና ከጀርባ የተዋቸውን የመርዳት ህልማቸውን ያጨልመዋል፡፡
አደገኛው አጥርአደገኛው አጥር

የመን ውስጥ ሃያ አምስት ሺህ ስደተኞች እንዳሉ ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም የሚናገር ሲሆን በቅርቡ አራት መቶ የሚሆኑ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
ስደተኛስደተኛ

ስደተኞቹ የሚደርሱባቸው በደሎችና ችግሮች የተደራረቡ እንደሆኑ የሚናገሩ ሲሆን በተለይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር እና ሰንዐ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለችግራቸው ካለመድረሣቸውም በላይ እንደሚያንጓጥጧቸውና ሰብዕናቸውን የሚጎዱ አድራጎቶችን እንደሚፈፅሙ በማማረር ይናገራሉ፡፡
pic voa.
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

http://amharic.voanews.com/content/ethiopian-refugees-yement-10-03-13/1762631.html

lørdag 5. oktober 2013

ከ200 በላይ ስደተኞች አሁንም አልተገኙም

ከ200 በላይ ስደተኞች አሁንም አልተገኙም
 ኢሳት ዜና :- ላምባዱሳ እየተባለ በሚጠራው የጣሊያን ደሴት አካባቢ በጀልባ መስጠም ከሞቱት መካከል የ11 ሰዎች አስከሬን ቢገኙም፣ ከ200 በላይ ሰዎች አሁንም የገቡበት አልታወቀም።

ፖፕ ፍራንሲስ በስፍራው ተገኝተው አደጋውን ከተመለከቱ በሁዋላ ሀዘናቸውን ገልጸዋል፣ ችግሩን ዝም ብለው የሚያዩትን አገራትም ወቅሰዋል።
ብዙ የጣሊያን ባለስልጣናት የህጻናቱን አስከሬን እያዩ ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው ሲያለቅሱ ታይቷል።

እስካሁን ድረስ አስከሬናቸው የተሰበሰበውና የጠፉት ሰዎች ዜግነት በውል ተለይቶ አልታወቀም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር አብዛኞቹ ኤርትራውያንና ሶማሊዎች ናቸው ብሎአል።

እንዲህ አይነት አሰቃቂ አደጋ ሲደርስ ይህ የመጀመሪያው ነውም ተብሎአል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ

ኢሳት ዜና:-የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር የብቃት መመዘኛ ፈተና ዙሪያ መግባባት ባለመቻላቸው ትምህርት ማቆማቸው ተሰማ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስተላለፈው ውሳኔ በተማሪዎቹና በዩኒቨርሲቲው መካከል አለመግባባትን በመፍጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩኒቨርሰቲውም የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ግቢ ለቀው መውጣታቸውን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ እንዲወስዱ ሲጠይቃቸው ተማሪዎቹ በቂ የዝግጅት ጊዜ ይሰጠን ብለው በመጠየቃቸው አለመግባባቱ ተከስቷል፡፡
የብቃት ማረጋገጫ ፈተናውን ለመውሰድ በቂ ጊዜ ይሰጠን ብለን ብንጠይቅም ዩኒቨርሲቲው በአጭር ቀናት ውስጥ እንድንወስድ አስገድዶናል በማለት ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ለሶስት ዓመት ያህል የተማሩትን ትምህርት በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ በሁለት ቀናት ውስጥ የብቃት መመዘኛውን ውሰዱ መባሉ አግባብነት የሌለው ነው የሚሉት ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ግን ሙሉ ለሙሉ መፈተን እምቢ እንዳልን አስመስሎ በመግለጽ ላይ ነው ሲሉ ተማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡
በተማሪዎቹና በአስተዳደሩ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ፌደራል ፓሊስ ያደረገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ተማሪዎች ግቢውን ጥለው መውጣታቸው ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በአምስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ በአክራሪነትና ፅንፈኝነት ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ ፕሮግራም ባለመግባባት መበተኑን ምንጮች ለኢሳት አስታውቀዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በአክራሪነት ዙሪያ ለመወያየት ፈቃደኝነታቸውን ማሳየት ባለመቻላቸውና ሙስሊም ተማሪዎች ለጁማ ሶላት መውጣት በመሞከራቸው በግዳጅ ወደ ስብሰባ እንዲሄዱ ተሞክሮ እንደነበር ታውቋል፡፡a

በሜዲትራንያን ውቅያኖስ 130 አፍሪካዊ ስደተኞች ሞቱ

በሜዲትራንያን ውቅያኖስ 130 አፍሪካዊ ስደተኞች ሞቱ
ከሊቢያ ወደ ጣሊያን 500 አፍሪካውያ ስደተኞችን ይዛ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የእሳት አደጋ በትንሹ 130 ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸው ተሰማ፡፡
ከአቅሟ በላይ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ጣሊያን የሚሄዱ ስደተኞችን የጫነችው ጀልባ በመጨናነቋ ከተሳፋሪዎች አንዱ እርዳታን ለማግኘት ሲል በለኮሰው እሳት ጀልባዋ መቀጣጠሏን አሶሼትድ ፕሬስ ከጣሊያን ዘግቧል፡፡
የእሳት ምልክትን ከሩቅ አይተው ሰዎች ለእርዳታ ይደርሱልናል በሚል የተለኮሰው እሳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጀልባዋን በእሳት እንድትጋይ አድርጓታል፡፡
ወደ 500 የሚጠጉትም ተሳፋሪዎች ወደ አለሟት ጣሊያን ሳይደርሱ በሜድትራኒያን ውቅያኖስ ያልታሰበውን አደጋ ለመቀበል ተገደዋል፡፡
እስከ አሁን ድረስ 130ዎቹ የሞቱ ሲሆን ከ150 በላይ የሚሆኑት የገቡበት አልታወቀም፡፡
መዋኘት የማይችሉት ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ውቅያኖሱ እየዘለሉ ቢገቡም ህይወታቸው ማትረፍ ሳይችሉ መቅረታቸውን የጣሊያን ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
አምቡላንስን ሳይሆን የአስክሬን መጠቅለያዎችን ነው የምንፈልገው በጣም አሳዛኝ አደጋ ነው የተከሰተው በማለት ስደተኞቹ ሲያቀኑበት የነበረው የላምፔዱስ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ጊዩስ ኒኮሊኒ ተናግረዋል፡፡
ወደ ከተማ ለመድረስ ሶስት ኪሎ ሜትር አካባቢ ብቻ ቀርቷቸው ከነበሩት 500 ስደተኞች መካከል 159 ብቻ መታደግ ተችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት የሟቶቹ ቁጥር ያሻቅባል ተብሎ ተፈርቷል፡፡
ጀልባዋ የኤርትራ፣ ጋና እና ሶማሊያ ዜግነት ያላቸውን ስደተኞች አሳፍራ እንደነበር ታውቋል፡፡
ስደተኞቹን በህገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ ሰዎች አደጋ ሲያጋጥማቸው የሳተላይት ስልክን እንደሚጠቀሙ ቢታወቅም ከመንገደኞች አንዱ ግን ሌሎች ጀልባዎች ለእርዳታ ይደርሱልናል በማለት እሳት ለኩሶ ለምልክትነት ለመጠቀም በመሞከሩ አሰቃቂው አደጋ ሊደርስ መቻሉን የጣሊያን ባለስልጣናት በሀዘን ገልጸዋል፡፡
ተሳፋሪዎች ከነበሩበት 100 ሴቶች ሶስቱን ብቻ ከሞት መታደግ የተቻለ ሲሆን የአውሮፖ ህብረት ባለስልጣናት የህገ ወጥ ስደተኞች ዝውውር ትኩረት እንዲደረግበት በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
ባለፈው ዓመት ብቻ 500 ስደተኞች በህገ ወጥ ዝውውር ምክንያት ወደ ጣሊያን ሲያቀኑ ሞተዋል፡፡

torsdag 3. oktober 2013

ሴፕቴምበር 28,2013 በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በኖርዌ ኦስሎከተማ የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የህዝባዊ ሃይሉ ከፍተኛ አመራር ኮማንደር አሰፋ እና የግንቦት 7የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንንና ጥሪ የተደረገላቸ እንግዶችና ከተለያየ የአውሮፓናስካንዴኔቪያን ሃገሮች መጡና በጣም በርካታ የሆኑ በኖርዌ በሚኖሩ ከተለያየ ከተማ የመጡ ሀገር ወዳድኢትዮጵያውያን በተገኙበት በታላቅ ወኔና የሃገር ፍቅር ስሜት በስኬት ተከናወኖ አመሸ።

ተስፋዬ ገብረአብ እጅ ሰጠ

ተስፋዬ ገብረአብ እጅ ሰጠ
ተስፋዬ ገብረ አብን ላጋለጠው ጀግናና ለዳኛ ወልደ ሚካኤል ያለን አድናቆታችን እጅግ ታላቅ ነው። ጎልጉል !!
ተስፋዬ ገብረአብ ከኤርትራዊያን ቤተሰቦች ቢሾፍቱ ተወልዶ ያደገ በውብ የስነጽሁፍ ችሎታው ብዙዎች የሚያደንቁት ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የ‹‹ብዙ ማንነቶች›› ባለቤት ነው፡፡ አዎ! ከሁለት ወር በላይ ባልዘለቀ የብሄራዊ ውትድርና ግዳጅ መማረኩ በፈጠረለት ምቹ አጋጣሚ ከከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንቶች ጋር ለመተዋወቅ ብሎም በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል መጀመሪያ ላይ ሆኖ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት የታጨ፤ በለጋ እድሜው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ የሆነለት የኢህአዴግ ሹመኛም ነበር፡፡ ያ ግን ትናንትና ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ በማራኪ የስነጽሁፍ ችሎታው በልዩነታችን ውስጥ ስላለው ውበት ሳይሆን በልዩነታችን ልክ እንዴት መጥፋት እንዳለብን የሚሰብክ መሰሪ ባህታዊ ነው የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ ባህሪው ብዙዎች ግራ ተጋብተዋል፡፡ በተለይ የኤርትራ ገዢዎችን ስውር ዓላማ የሆነውን በኢትዮጵያ ላይ የዘር ጥላቻ የመንዛት ሰይጣናዊ ተልእኮ በየአጋጣሚው በስነ ጽሁፎቹ ላይ የማንጸባረቅ አመሉን የተረዱ ‹‹ተስፋዬ ገብረእባብ›› የሚል ስያሜ እስከመስጠት ደርሰዋል፡፡ እሱም ለኢትዮጵያ ያለውን ‹‹ተቆርቋሪነት›› ያለመታከት ይደሰኩራል፡፡
ዛሬ ግን ይህ ሰው እጅ ሰጥቷል፡፡ ለበርካታ ዘመናት የዘለቀው የተስፋዬ ብልጣብልጥነት በአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ተጋልጧል፡፡ ለሁለት አመት ያህል ተስፋዬን በቤቱ አስጠግቶ ይህንን አስደናቂ የቤት ስራ የሰራው ወጣት አክቲቪስት አለማየሁ መሰለ ይባላል፡፡

ኢ-ፍትሀዊነትን በመቃወም፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚቃጣን አደጋ በመፋለም የሚታወቀውና፤ በእስር ብዛት አገሩን ለቆ እስኪሰደድ ድረስ ከሸዋ ሮቢት እስከ ቃሊቲ ድረስ ለአመታት በኢትዮጵያን እስር ቤቶች ያሳለፈው ይህ ደፋር ወጣት ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር በመሆን የመጀመሪያውን ክፍል መረጃውን ይፋ አድርጓል፡፡ አለማየሁ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጸው ከሆነ ተስፋዬ ከኤርትራው የደህንነት መስርያቤት ጋር በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት የተለዋወጣቸው ምስጢራዊ ሰነዶችና ኦዲዮቪዧል መረጃዎች በአለማየሁ አስደማሚ ጥበብ ኮፒ ተደርገው ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለያዩ ክፍሎችም ለህዝብ ይቀርባሉ፡፡ በአለማየሁ መረጃ አቅራቢነት በዳኛ ወልደሚካኤል ተከሽኖ የቀረበው የመጀመሪያው የጽሁፉ ክፍል ከተለያዩ መረጃዎች ጋር ሊንኩን ይክፈቱ
http://www.awrambatimes.com/wp-content/uploads/Tesfaye-Gebreab.pdf
ከአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል የተወሰደ