torsdag 18. august 2016
Democracy, Justice and Freedom for Ethiopian: በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!
Democracy, Justice and Freedom for Ethiopian: በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!: በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!! ቃልኪዳን ካሳ...
በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!
በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለበጥ ግድ ነው!!
ቃልኪዳን ካሳሁን ከኖርዌ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ከአራት ጊዜ ምርጫ ቢደረግም ያው እንደሚታወቀው ምርጫውን በማጭበርበር ስልጣኑ በሃይል ከተቆጣጠሩት ይህው ሁለት አስርት አመታትን አስቆጥሯል። ምርጫውን በሃይል ስልጣን መያዛቸውን እየታወቀ ለይመሰል የሚዘጋጁ ቅድመ ዝግጅቶችና የፓርቲዎች ተሳትፎ በጣም የሚያስገርም ነው። በአምባገነን ስርዓት የምትገዛ ሀገር የህዝቦችን ድምፅ ያከብራ ተብሎ አይገመትም። ለዚህም በህወሓት የሚመራው መንግስት ትልቁ ማሳያ ይሆናል።
ይህን ፁሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ነገር በሀገራቸን ውስጥ እየታየ ስላለው ህዝባዊ እንቢተኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ከቦታ ወደ ቦታ እንዲሁም ከከተማ ወደ ከተማ በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፋ መቷል። ይህ ህዝባዊ እንቢተኝነት በህወሓት ወገን የተለያዩ ስሞች ቢሰጠውም ህዝቡ የህወሓት አገዛዝ በቃን ብሎ የተነሳበት ወቅት ነው። ይህን ተከተሎ ባሳለፍናቸው ወራቶች ውስጥ በመላው ኦሮሚያ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እንቢተኝነት እስካአሁን ድረስ አለ። የተዳፈነ ቢመስልም ረመጡ ግን ጊዜ እየጠበቀ መቀጣጠሉ የማይቀር ነው። በተመሳሳይ በወልቃይት የአማራ ማንነት ዙሪያ ላይ ውስጥ ውስጡን ሲቀጣጠል ቆይቶ ያልታሰበ እና ያልተጠበቀ የተቃውሞ የታየበት የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ በመላው አማራ ህዝብ የተነሳበት ተቃውሞ ነበር።
በሀገራችን ህወሓት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በህዝቦቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍና መከራ ጊዜውን ጠብቆ በእራሱ ጊዜና ሰዓት ገንፍሎ ወቷል። ጭቆናና በደል አልሸከምም ያለ ህዝብ ለነፃነቱ ህይወቱ መሰዋዓት እያደረገ ያለበት ሁኔታ ላይ ነው ያለነው። ህወሓቶች በሁሉም ብሄሮች ላይ ዘግንኛ የሆን ግፍና በደል ፈፅመዋል እየፈፀሙም ነው። ይህን ስል በአማራና በኦሮሞ እንዲሁም በጋምቤላ ህዝቦች የሰሯቸው ዘግናኝ ግፍና በደሎች ከሎሎች ብሄሮች ጋር እኩል ማድረጌ እንዳልሆን ትረዱኛላቹህ ብዬ ገምታለሁ። በአማራና በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈፀመው በደል የአደባባይ ሚስጥር ነው። ህወሓቶች ሁለቱ ህዝቦች "ለስልጣኔ ያሰጉኛል" የሚል ትልቅ ስጋት አለው። ሌላኛው ሁለቱን ህዝብ በማናከስ ካልቻለ ደግሞ ከሁለት ህዝቦች የሚነሱ ጥያቄዎችን መልሳቸው ጥይት በማድረግ ተያይዞታል።
በህወሓት የሚመራው መንግስት መቶ ፐርሰንት መርጦናል ብለው ያስቡት ይሆን ባያስቡት ይሻላል። በህዝብ የተመረጠ ስርዓት ቢሆንማ ኖሮ ያ ሁሉ ህዝብ ባልተገደለ፣ ባልታሰረ፣ ባልታፈነ ነገሩ በህዝብ የተመረጡ ሳይሆን በጉልበትና በሃይል ስልጣን ላይ የተቀመጡ ስለሆን ለስልጣናችን ያሰጋናል የሚሉት ህዝብ ላይ እነሱ እንደሚሉት "የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን" እንዳሉት እያደረጉ ያለበት ሁኔታ ነው። ይህ ስርዓት የለየለት ሆኖል፤ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ህዝብ ላይ እንዲህ ያለ አረመኔያዊ ድርጊት መፈፀሙ ምን ያህል የለየለት ስርዓት እንደሆነ አጉልቶ አሳይቶናል። በህወሓት የሚምራው መንግስት በህዝቦች ላይ ሁሉንም ነገር በአፈናና በመግደል ወይም በማሰር መፍትሄ የሚሆን መስሎቸው ህዝቡን ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲቆም እያደረጉት እንደሆነ ልብ አላሉ።
በዚህ ወቅት ህዝቡና በህወሓት የሚመራው መንግስት አይጥና ድመት ሁኔታ ውስጥ ተገብቷል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ከዚህ በፊት ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲታሰብ ፍቃድ በማለት ህብረተሰቡን ማጉላላት ነበር። አሁን ግን ህብረተሰቡ ከማስፈቀድ ማሰወቅ ብቻ ይጠበቅበናል በማለት የተለያዩ ህዝባዊ ሰልፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል። መብቱና ነፃነቱ ሲነጠቅ የነበረ ህብረተሰብ ከአሁን በኋላ ወይ ነፃነት ወይ ሞት ብሎ የተነሳ ህዝብ መሆኑ በተጨባጭ አሳይቷ።
በህዝብ ያልተመረጠ በህዝብ ሊገለብጥ የግድ የሆነበት ምክንያት በህወሓት የሚመራው መንግስት በህዝቦች ላይ የሚፈፅሙት እየፈፀሙት ያለው ዘግናኝ ግፍና በደል ህዝቡን በማስቆጣት ሁሉም ለነፃነቱና ለመብቱ እንዲቆም አድርጎታል። በህዝብ ያልተመረጠ አምባገነናዊ ስርዓት ለህዝቦች ከመክራና ከስቃይ ያልዘለለ ምንም ሲያደርጉ አይስተዋሉም። ለዚህም በህወሓት የሚመራው መንግስት በኢትዮያዊያን ወገኖች ላይ የሚፈፅመውን ግድያም ሆን እስራት እንዲሁም አፈና አጥብቄ እቃወማለሁ።
ድል ጭቁን ህዝብ!!
ውርደት ለአምባገኑ ህወሓት!!
Abonner på:
Innlegg (Atom)